ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኢድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረጉን አስታውቋል ::መግለጫውን ይከታተሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለግንዛቤዎ.... ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 T
ለግንዛቤዎ.... ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ ማለዳ የከተማችን ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ለውጥ 6ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ድጋፋቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል። ለውጡ ሀገራችንን
+9
ዛሬ ማለዳ የከተማችን ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ለውጥ 6ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ድጋፋቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል። ለውጡ ሀገራችንን ከፍ ባደረጉ ታላላቅ ስራዎች እና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ከፍ ብሎ አንድነት የደመቀበት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምረን ያጠናቀቅንበት፣ የቱሪዝም መስህቦች እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ የጀመርናቸው ለሰው ልጅ ቅድሚያ በሰጠው ሰው ተኮር ስራዎቻችን የበርካቶች የኑሮ ሸክም ቀልሎ እምባቸው ታብሶ ተስፋቸው የለመለመበት ነው። በቀጣይም መዲናችንን የብልጽግና ተምሳሌት፣ እንደ ስሟ ውብ እና ለኑሮ ምቹ በማድረግ በሁሉም ዘርፍ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል የማድረግ ጥረታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል። ሁሌም ድጋፋቸው ላልተለየን የከተማችን ነዋሪዎች አክብሮታችን ከፍ ያለ ነው፤ እናመሰግናለን። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ"ለሀገራችን ብልፅግና በህብረት እንቆማለን" በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ነው።
+4
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ"ለሀገራችን ብልፅግና በህብረት እንቆማለን" በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ነው።

የሀገራዊ ለውጡ 6ኛ ዓመት የድጋፍ ሰልፍ

"ሀገራዊ ለዉጡ ኢትዮጵያን የታደገና ህልውናችንን ማስቀጠል ያስቻለ ነው"በማለት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ ለመታደም ተሳታፊዎች ከየአቅጣጫው ወደ ስፍራው
+4
"ሀገራዊ ለዉጡ ኢትዮጵያን የታደገና ህልውናችንን ማስቀጠል ያስቻለ ነው"በማለት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ ለመታደም ተሳታፊዎች ከየአቅጣጫው ወደ ስፍራው እየተመሙ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኢድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረጉን አስታወቀ። ከቀናት በኋላ የሚከበረዉ የኢድ አልፈጥር በዓል ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጋር በተያየዘ የአገልግሎት መቋረጥና የአደጋ ክስተት እንዳያጋጥም አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና የተጠሪ ተቋማቱ ስራ ኃላፊዎች ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫዉ ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንዳስታወቁት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ስነ-ስርዓት የሚከበረዉ የኢድ አልፈጥር በዓል ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አንጻር ተጠሪ ተቋማቱ ተገቢዉን አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እያስተባበረና እየመራ መሆኑን ጠቅሰዉ በዓሉ ሲከበር ከኤሌክትሪክና ከጽዳት አገልግሎት አንጻር የአገልግሎት መስተጓጎል እንዳያጋጥም ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል::ከአቅም በላይ የሆኑ የአገልግሎት መቋረጦች ቢያጋጥም ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጠይቀዋል። በሌላ በኩልም አደጋን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩልም አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉም ገልጸዋል። በተጠሪ ተቋማቱ በኩልም አቶ ፍቅሬ ግዛዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙላት ተገኝ የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አበበ በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዉቶሚሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ስራ አስኪያጅ ተቋማቶቻቸዉ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላምና በደስታ እንዲከበር አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸዉንም በመግለጫዉ ላይ አስታዉቀዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች ጋር የአፍጥር ፕሮግራም አካሄዱ። በመርሀ ግብሩ ላይ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች ኤጀንሲ ፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፣የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የክፍለከተሞች ስራአስኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮችና የተቋማቱ ሰራተኞች እንዲሁም የተለያዩ እምነት ተከታዮች ታድመዋል። በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደዉ የአፍጥር መርሀ-ግብር ላይ እንደተናገሩት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ያለዉ ታላቁ የረመዳን ወር የብዝሃነት የወንድማማችነት የአብሮነትን መስተጋብራችንን የሚያጠናክር በመሆኑ ይኸን በጎ እሴት ጠብቀን ማቆየት ይገባናል ብለዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል:: የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ጉልህ ሚና ባላቸው ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ተወያይቶ አጽድቋል:: በዚህም መሰረት:- 1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል። 2ኛ. የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ለማውጣት በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በመወያየት ፤ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት በተጨማሪም የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። 3ኛ. የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ለጎዳና ህይወት ፤ ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል::።

"በስራችን ስማችንን እናድሳለን" በሚል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ባለሙያዎች ነዋሪውን ከመቼውም በላቀ ቁርጠኝነት በትጋት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ይገልፃሉ:: ፈጣን እና ትክ
+6
"በስራችን ስማችንን እናድሳለን" በሚል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ባለሙያዎች ነዋሪውን ከመቼውም በላቀ ቁርጠኝነት በትጋት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ይገልፃሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- https://t.me/aacitymanager Twitter:- https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website https://www.aacitymanger.gov.et

ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ባለመያዝ (የፅዳት ችግር ) የሚያስከትላቸው ጉዳቶች:- ለጤና ጠንቅ ነው ለአየር ብክለት ምክንያት ነው ወንዞችን ይበክላል የከተማችንን በጎ ገፅታ ያበላሻል የቱሪዝምን ገቢ ይቀንሳል ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ያመጣል ብቁ ዜጋን እንዳናፈራ ያደርጋል የአካባቢ መራቆትን ያመጣል ውሃ በመበከል እፅዋትን በመመረዝ የአፈር ብክለትን ያስከትላል እሳት በቀላሉ ያስነሳል የዝናብ ውሃ መውረጃ ቱቦ እና ቦይ በመዝጋት የጎርፍ አደጋ እንዲከሰት እና መንገድ እንዲበላሽ ያደርጋል ቆሻሻን የማስወገድ ኃላፊነት የማን ነው ? ቆሻሻን በአግባቡ የመያዘና የማስወገድ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው:: የተማሪዎች፣የወጣቶች፣ የሴቶች፣ የአዛውንቶች፣ የባለሃብቱ፣ የመንግስት ሰራተኛው፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ሃይማኖት ፣ ብሄርና ፆታ የሙያና የትምህርት ደረጃ ሳይለይ የሁሉም ነዋሪዎችን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍኤም 96.3 ሬድዮ ጋር በመተባበር የሚያቀርበውን ሳምንታዊ ፕሮግራም ሁለተኛ ክፍል ይከታተሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- https://t.me/aacitymanager Twitter:- https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website https://www.aacitymanger.gov.et