ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም ላይ የተደራጁ ማህበራት ጉለሌ ክፍለ ከተማን ጽዱ ፣ውብና ማራኪ ከማድረግ ባሻገር ቆሻሻ ሀብት መሆኑን በተግባር እያረጋገጡ እንደሚገኙ ተመለከተ፡፡ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን በአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮ ቋሚ ኮሚቴ ዘርፍና ሌሎች የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች ጉብኝት በዛሬው እለት አካሂደዋል ፡፡ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳየዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ እንደተናገሩት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ለሌሎች አርዓያ የሚሆን የሚያበረታታ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተናግረው በዘርፉ ላይ የተደራጁ ማህበራት የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ከተማችንን አዲስ አበባ ለዜጎቿ ምቹ ለማድረግና ህብረተሰቡ ጽዳትን ባህል እንዲያደርግ ኤጀንሴው በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ያሉ ሲሆን በተለይም ቆሻሻ ሀብት መሆኑን በተግባር እያረጋገጡ የሚገኙ ደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም ላይ የተደራጁ ማህበራት ለማገዝ የግንዛቤ ስራዎችን በመስራት የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው 26 የሚሆኑ በመልሶ መጠቀም ማህበራት የሚገኙ ሲሆን 6ቱ በግል ንግደ ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩ ሲሆን ከ262 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በቋሚነት የስራ ዕድል በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በተያዘው በጀት ዓመት ሩብ አመት 26 ሚሊዮን ብር በላይ ከዘርፉ መገኘቱን ሃላፊው ገልጸዋል፡፡ በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም ከተደራጁ ማህበራት መካከል ታጠቅ ፣ራሔልና ጓደኞቻቸው ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ታጠቅ በቀለ በበኩላቸው ስራውን ሲጀምሩ በ200 ብር መነሻ የጀመሩ ሲሆን በአሁን ሰዓት 10 ሚሊዮን ብር የተጣራ ካፒታል መድረሳቸውን ገልጸው ከፕላስቲክ መሰብሰብ አንስቶ የኡደት ስራዎች በመስራት በቋሚነት 20 ሰራተኞች በጊዜያዊነት 80 የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ የጉለሌ መገለጫ ከሆኑ መካከል የሸክላ ውጤቶችን ለእንግዶቹ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ አማን አንዱዓለም ለእንግዶቹ አበርክተዋል፡፡ Gullele communication-ጉለሌ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በማሌዥያ ጉብኝታችን የኳላ ላምፑር ምክትል ከንቲባ ኢስማዲ ቢን ሳኪሪን እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውልናል። በአዲስ አበባ እና ኳላ ላምፑር መካከል ትስስርን በማጠናከር በተለይም በከተማ ፕላን፣ በአረጓዴ ልማት፣ በአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ፣ በህዝብ መናፈሻዎች፣ በኢንቨስትመንት፣ በጤና፣ በንግድ እና ቱሪዝም ዘርፎች ላይ ይበልጥ ተቀራርበን መስራት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል። በነበረን ቆይታም የስማርት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከልን እንዲሁም የፐርዲና ቦታኒካል ጋርደንን ጎብኝተን የአዲስ አበባ ከተማ የማስታወሻ ችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂደናል። የማሌዢያዋ ኳላ ላምፑር ከተማን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እና በቱሪዝም ልማት እያካሄደች ያለው የትራንስፎርሜሽን ስራዎች የምንማርበት በመሆኑ የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የእሳት አደጋ መከላከያ በህንጻዎች በከተማዋ የሚገነቡና ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ህንፃዎች አስፈላጊ የእሳት አደጋ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መሳሪያ እንዲኖራቸው ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማት እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ኮሚቴ አሳሰበ፡፡ https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም See less

በከተማዋ የሚገነቡና ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ህንፃዎች አስፈላጊ የእሳት አደጋ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መሳሪያ እንዲኖራቸው ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማት እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ኮሚቴ አሳሰበ፡፡ https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም

በከተማዋ የሚገነቡና ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ህንፃዎች አስፈላጊ የእሳት አደጋ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መሳሪያ እንዲኖራቸው ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማት እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ኮሚቴ አሳሰበ፡፡ https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ማሌዢያ ኳላላምፑር ከተማ ገብተዋል። ጉብኝቱ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ማሌዢያ ጉብኝትን ተከትሎ ከፍተኛ እና ፈጣን የልማት ለውጥ ያስመዘገበችዉ ማሌዢያ የተከተለችዉ የትራንስፎርሜሽን እስትራቴጂ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ለዉጥ ጋር ሲነፃፀር የልምድ ልውውጥ ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ነዉ። የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በትላንትናው እለት ኳላላምፑር፣ ሳይበርጃን እና ሳንዌይ ከተሞችን የጐበኙ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የገንቲንግ የቱሪስት መዳረሻን በመጐብኘት ላይ ይገኛሉ::

የግብርና ምርታማነት ማሳያ በአፋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት ለጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የግንዛቤ ሰርፀት እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ሰልጠና ተጠናቀቀ። የስልጠናው አላማ በዋነኝነት የግንዛቤ ባለሙያዎችን የመፈፀም አቅም በማሳደግ በከተማው የፅዳት ስራ ላይ ጉልህ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ ማስቻል ነው። ሰልጠናው በፅዳት የሞዴሊንግ መሰፈርት ትግበራ፣ በተግባቦት አቅም፣ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ምንነትና ባህሪያት፣ የከተሜነት እሳቤ እና በቅንጅታዊ አሰራር ሰነድ ላይ የተሰጠ ሲሆን ሰልጠናው ያስገኘውን ውጤት ለመለካት የመግቢያና የመውጫ ፈተናዎች ተሰጥቷል። በሰልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው የሰራ መመሪያ የሰጡት በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ሰራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ስልጠናው በግንዛቤ ክፍተት ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ችግር ፈች የአሰልጣኞች ሰልጠና በመሆኑ በሰራ መተርጎም የሚገባው ይሆናል ብለዋል። ወ/ሮ ቆንጅት አክለውም ፅዳት የከተማችን ባህል እንዲሆን የግንዛቤና የሰርፀት ሰራው በቅንጅትና በጠንካራ የተግባቦት አቅም መተግበር የሚገባውና ውጤት የሚያመጣ እንዲሆን ተቀናጅተን መሰራት ይገባናል ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል።የከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት መሰል የአቅም ግንባታ ሰልጠናዎችን መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የሚዲያ አካላትና የጽዳት በጎ ፈቃደኞች ለክፍለ ከተማዋ ጽዳት መጠበቅ አስተዋጽዖቸው የጎላ መሆኑን ተገለጸ። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የጽዳት በጎ ፈቃደኞች እና የሚዲያ አካላት በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ስርዓትና ስራዎች ላይ ያለቸው ሚና እና በደንብ ቁጥር 167 /2016 ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ ሰጥቷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት አስተዳደሩ ክፍለ ከተማውን ጽዱ ውብና ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እያከናወነ ይገኛል በተለይ በአሁኑ ሰዓት የተጀመረው 2ኛው ዙር የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች በመተግበር ላይ ይገኛል ክፍለ ከተማዋን ውብና ማራኪ ያደርጋል በመሆኑም ዛሬ ግንዛቤ የተፈጠረላችሁ የጽዳት በጎ ፈቃደኞችና የሚዲያ አካላት ሚናችሁን በመወጣት ሞዴል ክፍለ ከተማ እንድትሆን ልሰሩ ይገባል ብለዋል። የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን አንዱዓለም በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በባለፉት ቀናት በተከበሩ የአደባባይ በዓላት የጽዳት በጎ ፈቃደኞች በአከናወኑት ተግባር ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል በመሆኑም ይህንን በማስፋትና በጎ ፈቃደኞችንና የሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የግንዛቤ ስራዎችን በማጎልበት ለተሻለ ውብና ጽዱ ክፍለ ከተማ እንድትሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠለ ይትባረክ በበኩላቸው ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የትላልቅ አለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ ጽዳትን ባህል ያደረገ ነዋሪ ለመፍጠር መንግስት በትኩረት እየሰራ ይገኛልበመሆኑም በክፍለ ከተማውን የጽዳት በጎ ፈቃደኞችና የሚዲያ አካላት ሞዴል ክፍለ ከተማ ለመፍጠር ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚልኪያስ ቦንኬ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው የተሰማሩ የጽዳት በጎ ፈቃደኞች ለህብረተሰቡ ጽዳት ላይ ያለውን ግንዛቤ በማስፋት ክፍለ ከተማውን ውብ ጽዱ እንድትሆን የድርሻችሁን ማበርከት አለባችሁ ብለዋል። የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የ ግንዛቤ ፈጠራና የህብረተሰብ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ሄርጶ በአዲሱ ኮሪደር ልማት አዋጅ 167/2016 የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ታስበዉ በሚወጡ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ለነዋሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በደንብ 167 /2016 ከተማዋ ውስጥ የለሙ ፓርኮች፣ ኮሪደሮች፣ መንገዶችና ተጓዳኝ ልማቶች ካላቸው ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ከባቢያዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ለከተማችን ጽዳት፣ ውበትና መልካም ገጽታ የላቀ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆኑ ጽዳታቸውን፣ ውበታቸውንና መልካም ገጽታቸውን የሚያበላሹ ተግባራትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና በጎ ፈቃደኞችና የሚዲያ ሰራዊትና አንቂዎች የራሳቸውን ድርሻ እንዲያበርክቱ ማስቻል እንደሆነ በስልጠናው ላይ ተገልጿል። በግንዛቤ ፈጠራ ላይ እያከናወኑ ለሚገኙ የጽዳት በጎ ፈቃደኞችና የሚዲያ አካላት የምስክር ወረቀትና አንጸባራቂ ዩኒፎርም ተበርክቶላቸዋል ። Gullele communication-ጉለሌ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ውብ መዝሙር ተጋብዛችሁዋል። ቀልጣፋና የተሳለጠ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እንዲረጋገጥ እንተጋለን! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et