1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በተለምዶ "ፓስተር አደባባይ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የዘመሙ እና ደሳሳ የቀበሌ ቤቶችን አፍርሰን ለአካባቢው ነዋሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ህንፃ መኖሪያ ገንብተን አስተላልፈናል።
ይህ አካባቢ እጅግ በጣም የቆሸሸ፣ ቤቶቹም የወዳደቁ ሲሆኑ የዛሬ ሶስት ዓመት አካባቢውን ማልማት ስንጀምር ገብተን ለመስራት የተቸገርን ቢሆንም የዛሬውን ጨምሮ ቀድመን የገነባናቸው በጠቅላላ አምስት የመኖሪያ ህንፃዎች አካባቢውን ከመቀየር በተጨማሪ በውስጣቸው መንገድ፣ የህፃናት መጫዎቻ፣ የህፃናት ማቆያ፣ ዘመናዊ የመጸዳጃና የማብሰያ ቦታዎች፣ እንዲሁም የጋራ መገልገያ ስፍራዎች ተካትተው የተገነቡ ናቸው።
ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮችን ገንብተን ለነዋሪዎች ስናስተላልፍ አካባቢውን ንፁህ እና ምቹ ከማድረግ በተጨማሪ ነዋሪዎቻቸው ዘመናዊ አናኗር እና ጤናማ ኑሮ ለማረጋገጥ ሲሆን አካባቢውን ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ለመቀየር በያዝነው እቅድ መሠረት ዛሬም ሁለት አዳዲስ ህንፃዎችን አስጀምረናል::
የሚፈሱ እምባዎችን እያበስን፣ የዘመሙ ጎጆዎችን እያቃናን እና ቆሻሻን እያፀዳን ለነዋሪዎቻችን ምቹ አካባቢን በመፍጠር እንዲሁም በከተማችን ያሉ ትውስታዎችን እና ቅርሶቻችንን አድሰን የቱሪስት መዳረሽ በማድረግ ለከተማችን ተጨማሪ ገቢ፣ የስራ እድል እና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየሰራን ነዉ።
ስራው በመንግስት አቅም ብቻ የሚከናወን አለመሆኑን በመረዳት ጥሪያችንን ተቀብለው ከጎናችን የቆሙ ልበ ቀና ባለጸጎቻችንን በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ዛሬ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖን(ETEX 2025) በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተገኝተን ጎብኝተናል፡፡
ኤክስፖው ሀገራችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በሳይበር ደህንነት፣ በፊን-ቴክ እንዲሁም በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላትን እምቅ አቅም የሚያሳይ እና ኢትዮጵያ ለዘርፉ የሰጠችውን ትኩረት እንዲሁም የተገኙ ስኬቶችን ለዓለም በማሳየት ብቁ ተተኪዎች ያሏት መሆኑን በግልፅ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
ከተማችን አዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፍራንሶችን የማዘጋጀት ብቃቷ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ባለፉት አስር ቀናት ብቻ የአፍሪካ የፖሊስ ኮንፍራንስ፣ የሳይበር ሴክዩሪቲ ኮንፍራንስ፣ የአፍሪካ ደህንነት ኮንፍራንስ፣ የፋይናንሻል ኮንፍራንስ፣ የ AI ኮንፍራንስ በማካሄድ በነገው እለት ደግሞ የአይዲ ፎር አፍሪካ እና የILO ኮንፍራንስ የሚካሄድ ይሆናል::
ይህም የከተማችንን ገቢ ከመጨመር በተጨማሪ የኮንፍራንስ እና የቱሪዝም መዳረሻነቷን ከፍ በማድረግ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ለነዋሪዎቻችን የስራ እድል የከፈተ ሲሆን ዲጂታል ኢትዮጵያ እና ስማርት አዲስ አበባን እውን ለማድረግ የተፈጠረዉ አቅም የታየበት ስለሆነ አጠናክረን እንቀጥላለን::
Industry 5.0 goes beyond technological evolution—it’s about human collaboration, sustainability, and ethical progress. Rooted in unity, purpose and inclusion, this vision sees AI and technology serving the collective good while respecting culture. Africa is not here to catch up—we are here to lead through inclusive, value-driven models that empower communities and leave no one behind.
መዲናችን ትምህርት ቤቶች ፅዳትን ባህል ያደረገ ትውልድ ለመገንባት እየተከናወኑ ያሉ አበረታች ተግባራትን አስመልክቶ @Addis Media Network ዘገባን በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ ግብር አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን አጽንኦት ሰጠተው አንሰተዋል። ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መሆኑን አውስተዋል። እንደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዮት፣ ዲጂታል መታወቂያ ብሎም “የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ” አይነት ፕሮግራሞቿ ኢትዮጵያ ሕልሞችን ወደ ተጨባጭ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተግባራት መለወጥ ችላለች። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በ2030 ማንም ወደ ኋላ በማይቀርበት አኳኋን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት አስምረውበታል።
ሀገርና ጥበብ ፤ ጥበብ ለኢትዮጲያ ማንሰራራት " በሚል መሪ ቃል በ11ዱም ክፍለ-ከተሞች አንጋፋ እና አማተር የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች የከተማዋን የልማት ስራዎች ጎበኙ
የጉብኝቱ ዋና ዓላማም በከተማዋ ባሉ ክፍለ ከተሞች ለኪነ-ጥበብ አፍቃሪዎችና ባለሙያዎች ስለ ተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች እንዲሁም ስለ ተሰሩ እና እየተሠሩ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑ እና በሀገር እድገት እና ብልፅግና ዉስጥ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የራሳቸዉ ሚና እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑ ተመላክቷል።
ጎብኚዎቹ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ በርካታና የተለያዩ የህዝብ መዝናኛ አገልግሎቶች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ተርሚናሎች ፣ፖርኮች ፣ የተለያዩ የንግድ ዘርፎችን ያቀፉ ተቋማት ፣ታሪካዊ ቅርሶች፣ የመኪና፣ የእግረኛ እና የሳይክል መተላለፊያ መንገዶች ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እና ሠዉ ተኮር ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት የተገነቡበትና የታደሱበት እንዲሁም ሰፊ የስራ እድል የተፈጠረባቸዉን ዘርፈ ብዙ መሠረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸዉም ወቅት እንደገለፁት በአዲስ አበባ ላይ የተሰሩና እየተሠሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ህብረተሰቡን ያማከሉና የከተማዋን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን የበለጠ የሚያነሳሱ ሆነዉ አግኝተናቸዋል ሲሉ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎቹ ገልፀዋል።
አክለዉም የመዲናዋ የልማት ስራዎች ለኪነ ጥበብ ዘርፉ ምቹ ሁኔታ የፈጠሩ መሆናቸውን እና በተሠራዉ ስራ መደሠታቸዉን ገልፀዉ ሀገርንና ትዉልድን በመገባት ሒደት ዉስጥ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ድርሻቸዉ የጎላ በመሆኑ ከልማቱ ጎን በመቆም የበኩላቸዉን ሚና የሚወጡ መሆኑን አሳስበዋል።
የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሀ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም!" በሚል መሪ ሃሳብ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄዷል፡
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ "የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሀ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም!" በሚል መሪ ሃሳብ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል፡፡
ንቅናቄው ከግንቦት 1 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ተከታታይ ለ5 ወራት የሚቆይ መሆኑን የጠቀሱት የክፍለ ከተማው ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ድሪባ ጉለማ ቦዮችን /ትቦዎች የማጽዳት ንቅናቄ በማፅዳት የጎርፍ ተገላጭነትን መቀነስና ከቆሻሻ የፀዳ ብሎክን አላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ በበኩላቸው የጽዳት አምባሳደሮች፣ የፖሊስ አባላት፣ የደንብ ማስከበር አባላት፣ የሴፍትኔት የጽዳት ማህበራት የሲርክ ማህበራትና ባለሙያዎች ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በንቅናቄው ላይ መሳተፋቸውን ገልፀው ንቅናቄው በ12ቱም ወረዳዎች መካሄዱን አስታውቀዋል፡፡
ግንቦት 9-2017ዓም
የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን መሠረት ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ወርሃ ክረምቱንምክንያት በማድረግ "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም!" በሚል መሪቃል የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን ፣ ቱቦዎችን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን እና ማንሆሎችን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች የተካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ደንበል አካባቢ በድምቀት ተካሂዷል።
በመርሀግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ ከከተማዋ ዕድገት ጋር ተያይዞ የሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ በአይነትም ሆነ በመጠን እየጨመረ መሆኑን ገልፀው ይህን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ እና የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓቱን ለማዘመን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሠራታቸውን ገልፀዋል።
ከክረምቱ ጋር ተያይዞ የተጀመረው የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር ለ5 ተከታታይ ወራት እንደሚቆይ ጠቁመው ደረቅ ቆሻሻ የገቢ ምንጭ እየሆነ በመጣበት በዚህ ሰዓት ቆሻሻ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም ሲሉ አብራርተዋል።
የቂርቆስ ክ/ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍታለው ከፊያለሁ በበኩላቸው የፅዳት ስራ የዘውትር ተግባራችን መሆን እንዳለበት ገልፀው ፅዱ፣ ውብ እና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማን ለትውለድ ለማስተላለፍ የሁሉም ህብረተሰብ ቅንጅታዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ግንቦት 9 / 2017 ዓ.ም
"ውብ፣ ፅዱና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ የሆነች አዲስ አበባን እናስቀጥላለን!!"-አቶ ጌታሁን አበራ የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ
የአራዳ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ፕሮግራም ከአራት ኪሎ እስከ ስድስት ኪሎ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ያካሄደ ሲሆን የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣የፅዳት አምባሳደሮችና ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ የፅዳት መርሐ ግብሩን ሲያስጀምሩ እንዳሉት "ውብ፣ ፅዱና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ የሆነች አዲስ አበባን እናስቀጥላለን፤ ልማቷንም እናረጋግጣለን ብለው አሁን ላይ እየተሰራ ያለውን የመንገድ ኮሪደር ልማት ስራ ፅዳቱንና ደህንነቱን በማስጠበቅ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ፅዳት የስልጣኔ ምልክት ነው ያሉት የክ/ከተማው ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንየው ዘላለም አካባቢን ማፅዳትና ለነዋሪ ምቹና ተስማሚ የማድረግ ስራ የዘወትር ተግባር መሆኑን ገልፀው ነዋሪው በተለይም የመንገድ ኮሪደር ልማት ስራ ንፅህናው እንዲጠበቅና ቆሻሻን ባለመጣል የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በአራዳ ክ/ከተማ የመንገድ ኮሪደር የልማት ስራ በ7/24 በፍጥነትና በጥራት እየተሰራ ሲሆን አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ፅዱና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ የማድረግ ስራ በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።
ግንቦቶ 9/ 2017
