ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በአዲስ አበባ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ስፋት እና ይዘቱ አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ሲሆን በውስጡ:-

በአዲስ አበባ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ስፋት እና ይዘቱ አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ሲሆን በውስጡ:-
+3
በአዲስ አበባ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ስፋት እና ይዘቱ አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ሲሆን በውስጡ:-

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተጠሪ ተቋማት የ2016 በጀት አመት የቴክኖሎጂ ትግበራ እቅድ አፈፃፀምና የአዲሱ በጀት ዓመት መነሻ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የከተማው ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በመሩት በዚህ መድረክ ላይ የ3ቱም ተጠሪ ተቋማት ማለትም የጽዳት አስተዳደር፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ እና የእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የበጀት አመቱ የቴክኖሎጅ ትግበራ አፈፃፀም ከከተማው ኢኖቬሽን ቴክኖሎጅ ቢሮ ጋር ዉይይት ተካሂዶበታል። በውይይቱ ላይ በበጀት አመቱ በ3ቱም የስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት ተጠሪ በሆኑት ተቋማት በቴክኖሎጅ ትግበራ ረገድ የከተማው ኢኖቬሽንና የቴክኖሎጅ ቢሮ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በታከለበት መልኩ ተናባቢና ቅንጅታዊ አሰራሩን ባጠናከረ መንገድ ውጤታማ ስራዎች መፈፀማቸው ተመላክቷል። እየተጠናቀቀ ባለው የ2016 በጀት አመት በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር በኩል 4 ቴክኖሎጅ፣ በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ 2 ፣ በፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በኩል ደግሞ 1 በድምሩ 7 ቴክኖሎጅዎች ለምተው ስራ ላይ መዋላቸው ተገልጿል። በመድረኩ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ አመራሮች በተገኙበት የ2017 በጀት አመት የመነሻ እቅድ ላይም ውይይት ተካሂዶበታል ።

በአዲስ አበባ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች ላይ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን መገምገም ዓለማዉ ያደረገ የመስክ ምልከታ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሄደ። ጉብኝቱ ከተካሄደባቸዉ ተጋላጭ ቦታዎች መካከል አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሶስት ቀጠና 5/2 ፣ በተለምዶ ድምድም ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ፣ ገላን ኮንዲሚኒየም ፣ አጂፕ ሰፈር፣ አቃቂ ወንዝ ፣ ለሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 13 ካራሎ ኮንደሚኒየም እንዲሁም ንፋስ -ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድ ቦርጋ ሰፈር ይገኙበታል። በመስክ ጉብኝቱ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉና ም/ኮሚሽነር ይክፈለዉ ወ/መስቀል እንዲሁም የክፍለ-ከተማ ፣የወረዳ አመራሮችና ባለሞያዎች ተገኝተዋል። በከተማዉ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ ክፍለ -ከተሞች አንዱ በሆነዉ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ የአደጋ ስጋቱን ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በክፍለ-ከተማ ስራ አስኪያጅ በአቶ ማናዬ ጫኔ ገለጻ ተደርጓል። እንደ አቶ ማናዬ ገለጻ በክፍለ-ከተማዉ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ 38 ቦታዎች መለየታቸዉን ገልጸዉ በተለይም በሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ ለመከላከል ለተጋላጭ ነዋሪዎች ምትክ ቤትና ቦታ የመስጠት ስራ መሰራቱንና ችግሩ እስኪቃለል ድረስ የመኖሪያ ቤት ኪራይ እየተመቻቸላቸዉ እንደሆነ በመጥቀስ ለአደጋ ስጋቱ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የበጀት እጥረት እንዳገጠማቸዉ አብራርተዋል። በመስክ ምልከታዉ ከታዩት ተጋላጭ ቦታዎች አንዱ የሆነዉ በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 13 ካራ ኮንዲሚነየምና በአካባባቢዉ ያለዉ የጎርፍ ተጋላጭነት ስጋት ያልተፈታ በመሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤትና የአካባቢዉ ነዋሪዎች ስጋቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረገዉን ጥረት እንዲያግዙ የተጠየቁ ሲሆን ነዋሪዎቹም የመፍትሄዉ አካል ለመሆን የሚያሰችላቸዉን ዝግጅት ስለማድረጋቸዉም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች በሰዉና በንብረት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከልና መፍትሄ ለመስጠት በከተማ ደረጃ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ይደዉሉ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

አዲስ አበባ የመጀመርያዎቹን ሙሽሮች ጋብቻ በክብር መዝገብ ላይ ባፈራረመችበት ዕለት ሰኔ 25 በወረቀት ስትሰጥ የነበረው የከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ማብቃቱን ይፋ አደረገች የከተማ የነዋሪነት መታወቂያን በተደራጀ መልኩ በመስጠት ከ75 ዓመት በላይ እድሜን ያስቆጠረችው አዲስ አበባ የወረቀት መታወቂያን ለመጨረሻ ግዜ ተሰናብታ ቀሪ 14 ወረዳዎችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል መሻገሯን ዛሬ ከተማዋ የመጀመርያዎቹን ሙሽሮች በ1935 ሰኔ 25 ባፈራረመችበት በ81ኛው ዓመት ቀን ይፋ አደርጋለች። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የተጀመረው የከተማው መታወቂያን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 12 የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፣ በቢሮ ሃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተፈራ ሞላ እና ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንዲሁም የአቃቂ ቃሊቲ ዋና ስራ-አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በተገኙበት የማብሰርያ ስነ-ስርዓቱ ተከናውኗል። አቶ ዮናስ በንግግራቸው እንደገለፁት ከተማውን ስማርት ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ኤጀንሲው በቀጣይም ትልልቅ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን በመስራት የድርሻውን እንድሚወጣ የገለፁ ሲሆን ይህ ታሪካዊ ቀን የተቋሙን የዲጂታል ሽግግር ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገር መሆኑን ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በቀጣይ በከተማው ከዚህ ቀደም የተሰጡ የአገልግሎት ግዚያቸው ያላበቃ የወረቀት መታወቂያዎችን የመቀየር ፣ ከተቋማት ጋር የማስተሳሰር እና ስማርት መታወቂያን /Smart Card/ በከተማዋ ለማስተዋወቅ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በንግግራቸው አመላክተዋል። ኤጀንሲው የዲጂታል ምዝገባ ስርዓቱን በአስገዳጅ አሰራር ከከተማው የመሬት አስተዳደር ስርዓት ጋር ማስተሳሰሩ ይታወሳል። ሰኔ 25/ 2016 አ.ም ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት አመት አመታዊ የስራ እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ። የከተማው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ፣ የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ማሾ ኦላና በተገኙበት ም/ ቤቱ ክትትልና ቁጥጥር በሚያደርግባቸው ተቋማት በበጀት አመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና እቅዶችና ግቦች አፈፃፀምን መሠረት በማድረግ የተገኙ ተጨባጭ ውጤቶችን በዛሬው እለት ሰኔ 24/ 2016 አ.ም ሲገመግም ውሏል። በዚህ መሠረት ምክር ቤቱ የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የ2016 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀምን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ሂክማ ከይረዲን፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና የጽ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ገምግሟል። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ2016 የበጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የከተማው ም/ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርትም ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት ተካሂዶበታል። በዉይይቱም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፉ በበጀት አመቱ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ መሻሻል የታየባቸውን ተቋማት የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ፣ ስራዎች በቴክኖሎጂ የታገዙ፣ ፍትሃዊና ቀልጣፋ እንዲሁም ብልሹ አሰራርን የቀነሱ ከማድረግ አንፃር ሰፊ ስራዎች መሰራቱንና የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል። ይህንንም ውጤት በቀጣይ በጀት አመት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል:: ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች አጠቃላይ እይታ:- 👉 የ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች በ7/24 መርህና አመራር በመንቀሳቀስ ለህብረተሰቡ ገለልተኛ በሆነ አቋም ሰብአዊ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ናቸ
+2
የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች አጠቃላይ እይታ:- 👉 የ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች በ7/24 መርህና አመራር በመንቀሳቀስ ለህብረተሰቡ ገለልተኛ በሆነ አቋም ሰብአዊ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ናቸው። ይህም ማለት ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት በማንኛውም ጊዜ ቀንም ሆነ ማታ ዝግጁ ናቸው። 💥 የ7/24 የአደጋ ጊዜ አገልግሎት አስፈላጊነት:- 👉 የ 7/24 መርህ በድንገተኛ አገልግሎቶች ውስጥ ወሳኝ ነው። ምክንያቱም በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ሁኔታ ምንም ይሁን ምን እርዳታ ሁል ጊዜ መገኘቱን ያረጋግጣል። ይህ በተለይ በየደቂቃው በሚቆጠርበት ድንገተኛ ሁኔታዎች ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው፣ ወቅታዊ ምላሽ ህይወትን እና ንብረትን በማዳን ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። 💥የአደጋ ጊዜ አገልግሎት አመራር:- 👉 ለድንገተኛ አደጋዎች በብቃት ምላሽ ለመስጠት ሰራተኞች በሚገባ የተቀናጁ፣ የታጠቁና የሰለጠኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በድንገተኛ አገልግሎቶች ውስጥ ውጤታማ አመራር አስፈላጊ ነው። በድንገተኛ አገልግሎት ውስጥ ያሉ መሪዎች ቡድኖቻቸውን ከፍተኛ ጫና በሚፈጥርባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ለመምራት ጠንካራ የመግባቢያ፣ የውሳኔ አሰጣጥና ችግር ፈቺ ክህሎቶች ሊኖራቸው ይገባል። 💥 የማህበረሰብ አገልግሎት እና ነፃነት:- 👉 የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ለህብረተሰቡ ገለልተኛ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው ቁርጠኝነት ህዝብን ጥቅም መማረጋገጥ ያላቸውን የሙያ ስነምግባር ያሳያል። ራሳቸውን ችለው በመስራት በውጫዊ ተጽእኖ ሳይደናቀፉ ለድንገተኛ ጊዜ ፈጣንና ውጤታማ ምላሽ ይሰጣሉ። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ይደዉሉ !

ዛሬ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ የዘንድሮን የአረንጓዴ አሻራ አስጀምረናል። እኛ ስንተክል ሀገርን አረንጓዴ እያለበስን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ጉልበት እየጨመርን ነው።
+6
ዛሬ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ የዘንድሮን የአረንጓዴ አሻራ አስጀምረናል። እኛ ስንተክል ሀገርን አረንጓዴ እያለበስን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ጉልበት እየጨመርን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ዛሬ የምናስመርቃቸው ሞዴል ብሎኮች ነዋሪዎች በባለቤትነት ካልተረከቧቸው መልሰው መበላሸታቸው አይቀርም" #አቶ_አደፍርስ_ኮራ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ በቂርቆስ ወረዳ 02 በተምሳሌት ብሎክነት የተለዩ ቦታዎችን ለነዋሪዎች አስረከቡ ዛሬ ለነዋሪዎች የምናስረክባቸው ሞዴል ብሎኮች ቂርቆስን የአዲስ ፈርጥ የማድረግ መርሐ ግብር አካል ናቸው ብለዋል ብሎኮቹን መርቀው ለነዋሪው ያስረከቡት የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ዛሬ የምናስመርቃቸው ሞዴል ብሎኮች ነዋሪዎች በባለቤትነት ካልተረከቧቸው መልሰው መበላሸታቸው አይቀርምና ነዋሪዎች ይህንን ተረክበው በተገቢው ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ። በቀጣይም ተጨማሪ ሞዴል ብሎኮች መፍጠርና ማስፋት እንዲሁም ለፅዳት ስራው የማይተባበርን አካል ተጠያቂ ማድረግ ከነዋሪው ይጠበቃልም ብለዋል አቶ አደፍርስ በመልዕክታቸው። ሞዴል ብሎኮች ከፅዳቱ ባሻገር ሰላምን ይፈልጋሉ ያሉት አቶ አደፍርስ አካባቢን ለማፅዳት ሀብታም ደሃ መሆንን አይፈልግምና ቆሻሻ ስለማይመጥነን ፅዳታችንን ልንጠብቅ ይገባልም ብለዋል ወረዳው 10 ሞዴል ብሎክን ፈጥሮ አሳይቶናል ይህንን ተረክቦ የማስቀጠል ኃላፊነት የነዋሪው ነውና ይህንን በተገቢው መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አስቴር ደሳለኝ። የክፍለ ከተማው አስተዳደር ወረዳ 02 ጨምሮ በሁሉም ወረዳ 156 የፅዳት ተምሳሌት ብሎክና ተቋማትን በዛሬው እለት እንደሚያስመርቅ የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ዘለቀ ገልፀዋል። Kirkos Communication-ቂርቆስ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ የከተማችን ልሳን የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በአዲስ መልክ እራሱን በማደራጀት ያስጀመረው የአዲስ ቻናል ፣ የብራንዲንግ ስራ እና የታለንት ሾው ይፋ አድርገናል:: አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የከተማ
+6
ዛሬ የከተማችን ልሳን የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በአዲስ መልክ እራሱን በማደራጀት ያስጀመረው የአዲስ ቻናል ፣ የብራንዲንግ ስራ እና የታለንት ሾው ይፋ አድርገናል:: አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የከተማችን ነዋሪዎች አይንና ጆሮ በመሆን ለውጥ በማምጣት ፣ መረጃን በመስጠት፣ በማስተማር እና በማዝናናት ሂደት ውስጥ የራሱን አውንታዊ ሚና እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን የብዝሃነትና የትውልድ ድምፅ መሆኑን በተግባር አሳይቷል:: የከተማችን ነዋሪዎች ሚዲያው የእናንተ መሆኑን በመገንዝብ የትውልድና የብዝሃነት ድምፅ በሆነው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ድምፃችሁን የምታሰሙበት ፣ ትክክለኛ የመረጃ ምንጫችሁ አድርጋችሁ የምትገለገሉበት ፣ ኢፍትሃዊነትን የምትታገሉበት እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም ከተማችሁን የምታስተዋውቁበት እንዲሆን ጥሪየን አቀርባለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ውብ አዲስ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 15ኛ መደበኛ ስብሰባው የከተማ አስተዳደሩ እየተገበረ ያለውን የተቋማት ሪፎርም ተከትሎ ለከተማው ነዋሪ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የተለያዩ አዳዲስ እና ነባ
+8
የአዲስ አበባ ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 15ኛ መደበኛ ስብሰባው የከተማ አስተዳደሩ እየተገበረ ያለውን የተቋማት ሪፎርም ተከትሎ ለከተማው ነዋሪ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የተለያዩ አዳዲስ እና ነባር ደንቦችን ለማሻሻል የቀረቡ ረቂቆችን መርምሮ አፅድቋል:: በዚህም መሰረት:- 1. የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር መመሪያ 2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሠራተኛ የስራ ልብስ አለባበስና እና ጌጣጌጥ አጠቃቀም የአፈጻጸም ደንብ ፣ 3. የመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ደንብ 4. የህብረት ስራ ማህበራ አደረጃጀትና አሰራር ደንብ 5. የህብረት ስራ ማህበራት የፋይናንስ ፣ ግዥና የንብረት አስተዳደር ደንብ 6. የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ 7. የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት እንደገና ለማቋቋም በተዘጋጀ ደንብ 8. የኤግዚብሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ 9. የከነማ መድኃኒትና የህክምና መሳሪያ አቅራቢ ድርጅት እንደገና መቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል::