1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።
ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል። ዛሬ ለአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን ጥበቃ ቆመን ውለናል። የአፈር መራቆትን ለመመከት ተሰልፈን ውለናል። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ስንደክም ውለናል። ምድራችንን አረንጓዴ ለማልበስ ልምላሜን ለመመለስ ሳንበገር ሰርተናል። ፈጣሪም ረድቶን ለዛሬዋ ጀምበር ያሰብነውን አሳክተናል።
ዛሬ 29.1 ሚሊዮን ዜጎች በ318.4 ሄክታር በጂኦስፓሻል መረጃ በተገኘባቸው ስፍራዎች ላይ ችግኞችን ተክለዋል። እስካሁን በመረጃ ቋት ከተመዘገበው ውጭ የተተከሉ ችግኞች መረጃ በተከታታይ የሚገለፅ ይሆናል።
ለአስደማሚው የኢትዮጵያውያን ኅበረት እና ጽናት እነሆ ምስጋና። ለስኬታችን የእቅድ፣ የክትትል እና የመረጃ አውታር በመሆን በትጋት የሰራችሁ አመራሮች ባለሞያዎች እና የሚዲያ ተቋማት ምስጋና ይገባችኋል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው። ይኽንኑ እንቀጥላለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!
እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮጵያውያን የዛሬ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የቻልን ሲሆን ከዚህም ውስጥ እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል::
የከተማችን ነዋሪ የመሪችንን ጥሪ ተቀብሎ ማልዶ በመነሳት በአስደናቂ አፈፃፀም ከእቅድ በላይ ችግኞችን በመትከል ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ገድል በመፈጸሙ ታላቅ አክብሮት ከምስጋና ጋር የሚገባው ሲሆን በተጨማሪም ይህ እንዲሳካ ያስተባበራችሁ እና የደከማችሁ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞቻችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ይህ ዛሬ ያሳየነውን የተባበረ ክንድ የሚያመጣውን ለውጥ በሌሎች የልማት ስራዎቻችን ላይ በመድገም የሃገራችንን ብልፅግና እውን እንድናደርግ ጥሪዬን አቀርባለሁ::
የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
+1
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።
ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል። ዛሬ ለአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን ጥበቃ ቆመን ውለናል። የአፈር መራቆትን ለመመከት ተሰልፈን ውለናል። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ስንደክም ውለናል። ምድራችንን አረንጓዴ ለማልበስ ልምላሜን ለመመለስ ሳንበገር ሰርተናል። ፈጣሪም ረድቶን ለዛሬዋ ጀምበር ያሰብነውን አሳክተናል።
ዛሬ 29.1 ሚሊዮን ዜጎች በ318.4 ሄክታር በጂኦስፓሻል መረጃ በተገኘባቸው ስፍራዎች ላይ ችግኞችን ተክለዋል። እስካሁን በመረጃ ቋት ከተመዘገበው ውጭ የተተከሉ ችግኞች መረጃ በተከታታይ የሚገለፅ ይሆናል።
ለአስደማሚው የኢትዮጵያውያን ኅበረት እና ጽናት እነሆ ምስጋና። ለስኬታችን የእቅድ፣ የክትትል እና የመረጃ አውታር በመሆን በትጋት የሰራችሁ አመራሮች ባለሞያዎች እና የሚዲያ ተቋማት ምስጋና ይገባችኋል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው። ይኽንኑ እንቀጥላለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
234 ሚሊየን
"የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ" የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስከ ረፋዱ 5 ሰአት 30 ድረስ 234 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል፡፡
ሰላማዊት ካሳ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ
ሚኒስትር ዴኤታዋ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን የችግኝ ተከላ በመላ ሃገሪቱ በከፍተኛ የዜጎች ተሳትፎ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ችግኝ ተከላ እስከ ረፋዱ 5 ሰአት ከ30 ድረስ 11 ሚሊየን ዜጎች በተከላው ተሳትፈዋል፣ 93 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለኢትዮጵያዊያንና ለመላው ዓለም ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ከ 2 ሺህ በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በመላው ኢትዮጵያ መሰማራታቸውንም ተናግረዋል፡፡
ይህንን ሃገራዊ ሁነት በቀጥታ ስርጭት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም ከ50 በላይ የቀጥታ ስርጭት መሳሪያዎች አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
+8
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የአቃቂ የፍሳሽ ማጣሪያ ግቢ ውስጥ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በጋራ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐግብር ላይ አሻራቸውን አኑረዋል።
በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ በፎቶ
#አረንጓዴዓሻራ
ለታሪካዊው የችግኝ ተከላ በዛሬዋ ታሪካዊት ቀን በተፈጥሮ ስጦታ፣ በማዕድን ሃብት እና ለም ምድር በሚታወቀው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ተገኝተናል። በዛሬው ሁነት መጨረሻ በመላው ሀገራችን ባለፉት አምስት አመታት የተተከልናቸው ችግኞች ወደ 40 ቢሊዮን ይደርሳሉ።
ባለፈው አመት ከተተከሉት ችግኞች 50 ከመቶው በምግብ ዋስትና፣ አፈር ጥበቃ እና የመሬት መራቆት ላይ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ የተተከሉ ነበሩ። በቀጣይም እንደ አባይ ተፋሰስ ባሉ አካባቢዋች ችግኞችን በመትከል የውሃ ጥበቃ ሥራን ልንደግፍ ይገባል"።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ
ዛሬ ማለዳ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብራችንን በ168 የመትከያ ቦታዎች በ250 ሄክታር መሬት ላይ ጀምረናል።
የከተማችን ህዝብ ያደረግነውን ጥሪ ተቀብሎ በማለዳ በነቂስ ወጥቶ በተከላው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ‘የጀመርነውን ሳንጨርስ አንገባም’ በሚል በችግኝ ተከላው ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ከስድስት መቶ ሚሊዮን ውስጥ ስድስት ሚሊዮኑን ችግኞች የምትተክለው አዲስ አበባ!
የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ!
እንበርታ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿ ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዉድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ 6 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል ተደማሪና ተጨማሪ ድል በጋራ እናስመዝግብ !
በነቂስ ወጥተን እንትከል !
ለመጪው ትዉልድ አሻራ እናስቀምጥ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
See less
+8
ዛሬ በስድስት የከተማችን ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች በ22 የስልጠና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 5180 ሰልጣኞችን አስመርቀናል::
ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው 30 በመቶ የንድፈ-ሀሳብ ፣ 70 በመቶውን ደግሞ የተግባር ስልጠና ከተከታተሉ በኋላ በኮሌጅ ደረጃ የብቃት ምዘና ተመዝነው ያለፉ ናቸው፡፡
ተመራቂ ተማሪዎች በስልጠና ቆይታችሁ የጨበጣችሁትን ሙያ በራሳችሁ ጥረት በማዳበር ከሀገራችሁ አልፋችሁ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ መሆን የምትችሉ እንድትሆኑ እንዲሁም የስራ ክቡርነትን ተረድታችሁ እራሳችሁን ፣ ከተማችሁን እና ሃገራችሁን የምትለውጡ እንድትሆኑ ጥሪ አስተላልፋለሁ።
ትጉሀን እጆችን ከስራ ማገናኘት የሚያስችሉ በገበያው የሚፈለጉ የሞያ መስኮችን እየለየን በማሰልጠንና በመደገፍ የአምራቾችን ቁጥር እየጨመርን ከተማችንን የምትሸምት ብቻ ሳትሆን የምታመርትም ለማድረግ በትጋት መስራታችንን ቀጥለናል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿ ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ነሃሴ 17:2016 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዐሻራችንን እናኑር::
#አንድ ቀን ቀረው
