ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ከኤሌክትሪክ አደጋ ራስዎን ለመከላከል የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎች ********************** • ያልተሸፈነ የኤሌክትሪክ ገመድ ወይንም ሽቦ ከመንካት መቆጠብ፣ • የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ከቆሮቆሮ አጥር፤ ከልብስ ማስጫ ሽቦዎች ጋር እንዳይገናኙ ማድረግ፣ • ተበጥሶ መሬት ላይ የወደቀን ወይንም የተንጠለጠለን ኤሌክትሪክ ሽቦ ከመንካት መቆጠብና ሪፖርት ማድረግ፣ • በኤሌክትሪ የተያዘን ሰው ህይወት ከአደጋ ለማዳን የኤሌክትሪክ መስመሩን ከመቆጣጠሪያው ማጥፋት፣ • ውሀ ውስጥ፣ እርጥብ መሬትና ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ነገር ላይ ቆሞ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎቹን ከመንካት መቆጠብ፣ • የኢንዱስትሪ ወይንም የቤት የኤሌክትሪክ መስመር አዘረጋግ ትክክነኛነት በባለሙያዎች ሳይረጋገጥ አለመጠቀም፣ • ማንኛውም በኤሌክትሪክ የሚሰራ መሳሪያን ለማጽዳትና ለመጠገን ሲያስፈልግ ከኤሌክትሪክ መስመር ማላቀቅ፣ • የኤሌክትሪ አደጋን ለመከላከል ማንኛውንም የኤሌክትርክ ማሽን አካል ከመሬት ጋር ማገናኘት (ground) ማድረግ፣ • በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መሳሪያዎች ላይ ቃጠሎ ከተነሳ በውሀ ለማጥፋት አለመሞከር፣ • ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከአንድ ቤት ወደ ሌላ ቤት የሚዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመር አደጋ ስለሚያስከትል ከዚህ ድርጊት መቆጠብ፣ • በማንኛውም ቦታና ጊዜ የኤሌክትሪክ አደጋ የሚያስከትል ምልክት ከታዩ ወዲያውኑ በቅርብ ለሚገኝ ጽ/ቤት ማሳወቅ፣ • የኤሌክትሪክ መስመሮች በሚያልፉባቸው አካባቢዎች ዛፎች ሲቆረጡ መስመር ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ማድረግ፣ • በኤሌክትሪክ ስራ ላይ ሲሰማሩ ተገቢ ያልሆኑ ልብሶችን ከመጠቀም መቆጠብ፣ • አሽከከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመግጨት በንብረትና በሰው ህይወት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ተገቢውን የአሽከርካሪነት ጥንቃቄ ማድረግ፣ • የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እንዲወድቁ ማድረግ በሀገር ኢኮኖሚ እና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ማድረስ በመሆኑ ድርጊቱን በጋራ መከላከል፣ • የኤሌክትሪክ ስራ ሙያን የሚጠይቅ በመሆኑ በቸልተኝነት የሚሠራ ስራ ለህይወትም ሆነ ለንብረት መጥፋት መንስኤ ስለሚሆን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው:: Source- EEU

ከተለያዩ የሃገራችን ከተሞች የተውጣጡ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል:: አዲስ አበባ ፕሮጀክት ጀምሮ በማጠናቀቅ ፣በአመራር ቁርጠኝነት እና ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ እየተመካከሩ ስራዎችን በመስራት ትልቅ ልምድ የሚቀሰምባት መሆንዋን ገልፀው የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ የከተማዋን ገፅታ የሚቀይሩ እና የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ትላልቅ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን በጉብኝቱ ወቅት መታዘባቸውን ከንቲባዎቹ ገልፀዋል:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ ላይ ለውጥ ለማምጣት የቻልነው ዋናው የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረጋችን ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከተሞች ከፕላን ውጪ ሲገነቡ ችላ በመባሉ ዛሬ በከተማ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት የልማት ስራዎችን ለመተግበር መሰናክል ስለሆነብን እኛም ዛሬ ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈጠር ከተማችንን እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ ለማድረግ በከተማዋ ስታንዳርድ ልክ በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል:: የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ በበኩላቸው ስራው እንደ ሃገር መስፋት ስላለበት እይታችንን በማስፋት ከተሞችን ውብ ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ማድረግ አለብን ያሉ ሲሆን አንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማ ልክ የሆኑ ተጨማሪ ከተሞችን መገንባት ይጠበቅብናልም ብለዋል:: የከተማ አመራሮችና ከንቲባዎች መሰጠትን ፣ ቆራጥነትን እና የምንናገረውን በተግባር መለወጥን ከአዲስ አበባ ተሞክሮ በመውሰድ ለህዝብ የገባነውን ቃል በመተግበር የህዝቡን ችግር የሚቀርፉ ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚጠበቅባቸው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል::

ይህን ያውቁ ኖሯል... በአዲስ አበባ በሚያጋጥም የኮንስትራሽን የስራ ላይ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል ፡፡በዚህ ረገድ አደጋውን ለመቀነስና ለመከላከል የሀገራችን የኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ ምን ይላል! በህንፃ ግንባታ ስራ ላይ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን ለመከላከልና ስጋቶችን ለመቀነስ እንዲሁም ከህንፃ ግንባታ ጋር የተያያዙ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ የህንፃ ህግ በሀገራችን ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ደንብ ቁጥር 243/2003 ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በህንፃ ግንባታ የሚሳተፉ አካላት የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቀው ባለመስራታቸውና ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው በአዋጅ ቁጥር 624/2001 መሰረት ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ በዚህ መሰረት:- ፨ለሚያከናውነው ግንባታ የሚያስፈልግን የዲዛይን ስራ፣ ወይም የተሰራውን ዲዛይን መሰረት የሚከናወነውን ግንባታ የሙያ ደረጃው በማይፈቅድለት ባለሞያ ያሰራ እንደሆነ፣ ወይም ፨ለሚያከናውነው ግንባታ ደረጃ ከሚጠይቀው የግንባታ ቁሳቁስ ያነሰ የጥራት ደረጃ ያላቸው ቁሳቁሶች በጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገ እንደሆነ፣ ወይም ፨ግንባታውን አግባብ ካለው አካል የመጠቀሚያ ፍቃድ ሳያገኝ ወይም ከተፈቀደው ውጪ ለሌላ አገልግሎት አውሎ የተገኘ እንደሆነ፣ ወይም ፨ በማንኛውም ሌሎች ሁኔታዎች ግንባታው የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ እንደሆነ፣ከአምስት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር ሃያ ሺህ እስከ ብር ሃምሳ ሺህ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል። ፨ማንኛውም የተመዘገበ ባለሞያ ወይም የስራ ተቋራጭ፣ በዋና ወይም በንዑስ ስራ ተቋራጭነት ወይም ከፊል ውለታ በመውሰድ ያከናወነው ህንፃ ዲዛይን ወይም የግንባታ ስራ ለሚያስከትለው ጉዳት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው አሰሪው ለሆነው ሰው አግባብነት ባላቸው የፍትሐብሄር ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ የስራ ተቋራጩ ሆን ብሎም ይሁን በቸልተኝነት በሚገነባው ህንፃ በሰው ላይ ለሚደረሰው ወይም በህንጻው አካል ላይ ለሚደርሰው የስራ ጥራት ጉድለት ተጠያቂነቱ ሳይቀር ጉድለቱን የማስተካከል ግዴታ አለበት፡፡ ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ወይም በ011-1-55-53-00 ፈጥነዉ ያሳዉቁ

ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ላይ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ፉክልቲ በተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር
+1
ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ላይ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ፉክልቲ በተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ዉሏል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንስ ከ32 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ እሳቱን በፍጥነት መቆጣጠር ተችሏል። በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም።

አዲስ አበባን ውብ እና ፅዱ በማድረግ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ፅዳትን ባህል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ። ትክክለኛውንየአዲስሚዲያኔትዎርክዲጂታልሚዲያየትስስርአውታሮችንበመቀላቀልቤተሰብይሁኑን! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - የካቲት 30/2016 ዓ.ም

አመራሩ የሚያካሂደዉ የፅዳት ዘመቻ ኅብረተሰቡን ዝቅ ብሎ ማገልገሉን የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ። https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - የካቲት 30/2016 ዓ.ም

አዲስ አበባን ውብና ፅዱ የማድረግ ስራው ውጤታማ እንዲሆን የአመራሩ ሚና የላቀ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን ተናገሩ። https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - የካቲት 30/2016 ዓ.ም

የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ፅዱና ውብ በማድረግ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይችሉ ዘንድ አመራሩ የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳሰቡ።

አዲስ አበባን ውብና ፅዱ የማድረግ ስራው ውጤታማ እንዲሆን የአመራሩ ሚና የላቀ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን ተናገሩ። https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - የካቲት 30/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ሶስት ትልልቅ የከተማዋ ደንቦች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። በዚሁ መሠረት ካቢኔው ተወያይቶ ያፀደቃቸው ደንቦችም የሚከተሉት ናቸው
+3
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ሶስት ትልልቅ የከተማዋ ደንቦች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። በዚሁ መሠረት ካቢኔው ተወያይቶ ያፀደቃቸው ደንቦችም የሚከተሉት ናቸው፦ 1ኛ ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አስተዋፅኦን ፣ አገልግሎት እና ማህበራዊ ኃላፊነት አሰራር ለመደንገግ ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ ደንብ፤ 2ኛ ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚመሩበትን ሥርዓት እንደገና ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ እና 3ኛ. የዓድዋ ድል መታሰቢያን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ መርምሮ ከተወያየ በኋላ ለተሻለ የአሰራር ሥርዓት እንዲያመቹ ለማድረግ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

"የከተማዬን ፅዳት እጠብቃለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ!" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት የካቲት 30/ 2016 አ.ም የተካሄደው የአመራሮች የፅዳት ንቅናቄ መርሐግብር ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍ
+9
"የከተማዬን ፅዳት እጠብቃለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ!" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት የካቲት 30/ 2016 አ.ም የተካሄደው የአመራሮች የፅዳት ንቅናቄ መርሐግብር ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፅዳትን ባህል በማድረግና በዘላቂነት የማስቀጠል ጉዳይ ላይ አፅንኦት ሰጥተው ቁልፍ መልእክቶች ያስተላለፉበት መድረክ ነበር::

የከተማዬን ፅዳት እጠብቃለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ!" የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር "የከተማዬን ፅዳት እጠብቃለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ቃል በወረዳ 03 ፌደራል ማረ
+8
የከተማዬን ፅዳት እጠብቃለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ!" የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር "የከተማዬን ፅዳት እጠብቃለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ" በሚል መሪ ቃል በወረዳ 03 ፌደራል ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት የፅዳት ዘመቻ እና የችግኝ መንከባከብ መርሀ-ግብር አካሄዷል። በፅዳት ዘመቻው ደጋፊ የከተማ አመራሮች ፣ አጠቃላይ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች የሀይማኖት አባቶችና ሀደ ሲንቄዎች ተሳትፈውበታል። የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ የፅዳት ዘመቻው የዛሬውን የፅዳት ንቅናቄ ልዩ የሚያደርገው አጠቃላይ አመራሩ ብቻ በንቅናቄ ወጥቶ አካባቢውን ያፀዳና ችግኞችን የተንከባከበ መሆኑንና ዋና አላማውም አመራሩ ግንባር ቀደም ሆኖ አርአያ ለመሆን መሆኑን ገልፀዋል ። የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሀላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ፅዳት ማለት እያቆሸሹ ማፅደት ሳይሆን አለማቆሸሽ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ከቢሮው ከቤቱ ከአካባቢው ጀምሮ ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ አካባቢውን ውብና ፅዱ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መዝገቡ ይስማው የፅዳት ዘመቻው አመራርነት ዘርፈብዙ መሆኑን በአርአያነትና ተምሳሌትነትና አመራሩ ዝቅ ብሎ አገልግሎት እንደሚሰጥ የታየበት መሆኑን ተናግረዋል።

"አመራሩ ለጽዳት አርአያ ሊሆን ይገባል" የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳዎች አመራሮች የጽዳት ንቅናቄ አካሄዱ። በወረዳ 13 በተካሄደው የጽዳት ንቅናቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራ
+7
"አመራሩ ለጽዳት አርአያ ሊሆን ይገባል" የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳዎች አመራሮች የጽዳት ንቅናቄ አካሄዱ። በወረዳ 13 በተካሄደው የጽዳት ንቅናቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ጨምሮ የክፍለ ከተማውና የየወረዳዎቹ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ በመርሐ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ባደረጉት ንግግር በከተማዋ የጽዳት ንቅናቄ ከተጀመሩ ወዲህ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አመልክተዋል። ለተገኘው ውጤት አመራሩ የማንቃትና የማስተባበር ሚናው ከፍተኛ እንደነበር ያወሱት ወ/ሮ ቆንጂት፣ " የዛሬው የንቅናቄ መርሐ ግብር አመራሩ አርአያ በመሆን ጽዳት የኅብረተሰቡ ባሕል እንዲሆን ድርሻውን በበለጠ ትጋት መወጣት እንዳለበት ለማረጋገጥ የተካሄደ ነው" ብለዋል። የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ በበኩላቸው ሕዝብ የጽዳት ሥራ ባለቤት እንዲሆን አመራሩ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ "ማጽዳት መቀደስ ነው" በሚል መርህ የክፍለ ከተማውና የወረዳ አመራሮች በግንባር ቀደምትነት የጽዳት ሥራ ማከናወናቸው ለኅብረተሰቡ ምሳሌ የሚሆን ተግባር እንደሆነ አስገንዝበዋል።

አዲስ አበባ ጽዱና ውብ እንድትሆን አመራሩ ከፍተኛ ሚና አለው” -ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ “ከተማዬን አፀዳለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ” በሚል መሪ-ቃል
+8
አዲስ አበባ ጽዱና ውብ እንድትሆን አመራሩ ከፍተኛ ሚና አለው” -ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ “ከተማዬን አፀዳለሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ” በሚል መሪ-ቃል የተካሄደው አመራሩ ተምሳሌትነቱን የሚወጣበት ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ በአራዳ ክ/ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በመርሀ- ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድርን ጨምሮ ከከተማ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር በመክፈቻ ንግግራቸው አመራሩ ግንባር ቀደም ሆኖ በአርዓያነት የድርሻውን ሲወጣ ስኬታማነት እንደሚረጋገጥ ገልፀዋል፡፡ዛሬ የሚካሄደው የጽዳት ንቅናቄ መነሻ በማህበረሰቡ ቀጣይነት እንዲኖረው በማስተባበር ግንባር ቀደም ሆኖ አዲስ አበባን ጽዱና ውብ በማድረግ ረገድ አመራሩ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡ ፡አመራሩ ከዚህ ቀደም መላው ከተማውን ጽዱና ሳቢ ለማድረግ በርካታ ውጤታማ ስራዎች እንደተሰራ አስታውሰው በተለይም አራዳ ክ/ከተማ የቱሪስት መስህቦች መዳረሻ እየሆነች በመሆኗ በጽዳት አለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች እንድትሆን በሚደረገው ርብርብ ድርሻቸውን እንዲወጡ ለአመራሩ አደራ ብለዋል፡፡ የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘሁ በጽዳት የበኩላችንን በመወጣት ለህብረተሰቡ ተምሳሌት በመሆን የአመራርነት ሚናን መወጣት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡የንቅናቄው ተሳታፊዎች አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ጥበብ እድገት ት/ቤት አካባቢን ጨምሮ የተለያዩ 3 ቦታዎች ላይ የማጽዳት ንቅናቄውን ሲያካሂድ ጎንለጎንም ችግኞችን ተንከባክበዋል፤ ይህም ተግባር በየሳምንቱ በሁሉም አካባቢዎች ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ አመራሩ በማስተባበር እንደሚያስቀጥል ተነግሯል፡፡

አመራሩ የክፍለ ከተማውን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት ተገለጸ። በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 3 እና 2 "ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ!" በሚል
+6
አመራሩ የክፍለ ከተማውን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት ተገለጸ። በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 3 እና 2 "ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ!" በሚል ከተማ አቀፍ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄደ፡፡ በጽዳት ንቅናቄው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ከተማችን አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ በማድረግ ከሌሎች የአለም ከተሞች ተወዳዳሪ በማድረግ ነዋሪዎቿ አካባቢያቸውንና ጤንነታቸው የተጠበቀ በአስተሳሰብ የበለፀጉ፣ በኢኮኖሚ ያደጉ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፤ ቆሻሻን ስናፀዳ ለሃገራችን ፀር የሆኑ ሃሳቦችን አብረን ማስወገድ እንደሚገባ በመጠቆም የኢትዮጵያ መፃኢ እድል የሚረጋገጠው አንድነታችንን አጠናክረን ወደ እድገት በምናደርገው ጉዞ ነው ብለዋል፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው ክፍለ ከተማውን ንፁህና ውብ እንዲሆኑ የማድረጉ ስራ በየእለቱ እየተጠናከረና እያደገ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው ጽዳት የአንድ ወቅት ስራ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባራችን በማድረግና አካባቢያችንን በንፅህና በመያዝ ስፍራዎች ፅዱና ማራኪ በማድረግ ኃላፊነታችንን እንወጣ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በጽዳት ዘመቻው ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች አጠቃላይ አመራሮች ተሳትፈውበታል።

ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ! በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጀሞ ወረዳ ዛሬ በማለዳ የፅዳት: ችግኝ ተከላና እንክብካቤ መርሀ ግብር ተካሂዷል:: በፅዳት መርሃ ግብሩ ላይ የአዲ
+6
ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናዬን እወጣለሁ! በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጀሞ ወረዳ ዛሬ በማለዳ የፅዳት: ችግኝ ተከላና እንክብካቤ መርሀ ግብር ተካሂዷል:: በፅዳት መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ ጨምሮ የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ዶክተር ዮሃንስ ጫላ በመርሀ ግብሩ ላይ እንደተናግሩት ከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ፅዱና ውብ በማድረግ ረገድ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመላክተው በተሰራው ስራና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ እውቅና ተገኝቷል:: ይህ ተግባር ከተማዋ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግና ጤናማ አምራች ማህበረስብ እንዲኖር ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ዶክተር ዮሐንስ አክለውም አዲስ አበባን የአፍሪካ ከተሞች ብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ከሚሰሩ ስራዎች መካከልም ፅዳትና ውበት ቀዳሚዎቹ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ በበኩላቸው ስራው በአመራሩ ብቻ የሚፈፀም ተግባር ባለመሆኑ ህዝቡ የራሱ ስራና የኑሮ ዘይቤው አካል እንዲያደርግ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል:: በከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየተሰራበት ያለው የፅዳትና ውበት ተግባር የወረት ሳይሆን ቀጣይነት ባለው ሂደት የነዋሪዎች ባህል ሆኖ በየዕለቱ የማፈፀም ክንውን መሆን አለበት ብለዋል።

በሁለቱ ታላላቅ አፅዋማት ቆሻሻን ከቦታው የቆሸሹ አመለካከቶችን ከአዕምሯችን ማፅዳት ሀይማኖታዊም፣ ሰዋዊም ግዴታችን ነው"#አቶ_ሙባረክ_ከማል ******************************* በክርስ
+8
በሁለቱ ታላላቅ አፅዋማት ቆሻሻን ከቦታው የቆሸሹ አመለካከቶችን ከአዕምሯችን ማፅዳት ሀይማኖታዊም፣ ሰዋዊም ግዴታችን ነው"#አቶ_ሙባረክ_ከማል ******************************* በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የዐቢይ ፆም እንዲሁም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ ከተማ ዓቀፍ የፅዳትና አካባቢ የማስዋብ ንቅናቄ በቂርቆስ ወረዳ 04 ተካሄደ። የዛሬው የፅዳትና አካባቢ የማስዋብ ንቅናቄ በኮር አመራሮች ብቻ የተካሄደ ሲሆን ዋና ዓላማውም አመራሩ መሪነቱን በተግባር እንዲያሳይ ነው ብለዋል በብልፅግና ፓርቲ አዲዲስ አበባ ቅርንጫፍ የልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳርዳር ብርሀኑ በሁለቱ ታላላቅ አፅዋማት ቆሻሻን ከቦታው የቆሸሹ አመለካከቶችን ከአዕምሯችን ማፅዳት ሀይማኖታዊም፣ ሰዋዊም ግዴታችን ነው ያሉት ደግሞ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፂ አቶ ሙባረክ ከማል ናቸው። አቶ ሙባረክ አክለውም የዛሬው የፅዳት ዓላማ ለነዚህን ታላላቅ አፅዋማት ያለንን አብሮነትና ክብር ለመግለጽ መሆኑን ገልፀው ፃሙ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የበረከትና ከፈጣሪ ምህረት የሚገኝበት እንዲሆን ተመኝተዋል። በፅዳት ንቅናቄው ላይ የከተማው ከፍተኛ አመራሮችም የተገኙ ሲሆን ከፅዳቱ በተጨማሪ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

“ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናየን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ በየካ ክፍለ ከተማ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሂደ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ
+3
“ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናየን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ በየካ ክፍለ ከተማ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሂደ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በየካ ወረዳ 01 ጨፌ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተገኝተው ፅዳቱን አስጀምረዋል። በመርሃግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት፣ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የ12 ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። የፅዳት ንቅናቄ መርሀ ግብሩ "ከተማዬን እያፀዳሁ የአመራርነት ሚናየን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ በየካ ወረዳ 01 ጨፌ ሜዳ ተከናውኖል። የከተማዋ ነዋሪ አካባቢውን ፅዱና ውብ በማድረግ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይችል ዘንድ አመራሩ የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል። አቶ ጃንጥራር አክለውም ፅዳትን ዘመቻ ሳይሆን ባህል በማድረግ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹና ማራኪ የማድረግ ስራው በጋራ መስራት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተወዳዳሪ እንድትሆን በትኩረት እየተሰራ ነው። ሁሉም ነዋሪ ከብሎክ ጀምሮ አካባቢውን በማፅዳት አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ማራኪ በማድረግ የጋራ ሀላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ሲሉ አቶ ብርሃኑ ረታ አሳስበዋል።