1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከ5 በላይ ታቦታት የሚያርፉበት የአበበ ቢቂላ ስታዲየምን የማፅዳት መርሃ-ግብር ተከናወነ፡፡
*************************
ጥር 9-2017ዓም
ለከተራና ለጥምቀት በዓልን ምክኒያት በማድረግ በርካታ ታቦታት ለጥምቀተ ባህሩ የሚያርፉበት የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ ተከናውኗል፡፡
በፅዳት ዘመቻው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ቱኩ የተለያዩ የሐይማኖት ተከታዮች የጥምቀት በዓል የተሳካ እንዲሆን የታቦታት ማደሪያዎችንና አካባቢውን የማፅዳት ስራ ማከናወናቸው አብሮነታችንንና አንድነታችንን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ሙስጠፋ አክለውም በአለም ቅርስነት በዩኒስኮ የተመዘገበው ጥምቀትን በጋራ ቆመን በወንድማማችነት ልናሳልፈው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በጽዳት ዘመቻው የፀጥታ አካላት፣ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በክፍለ ከተማው በሚገኙ በሁሉም አብያተ ክርስቲያነት ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተከናውኗል፡፡
Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በልደታ ክ/ከተማ የጥምቀት በዓል በሚከበርባቸው ቦታዎች የፅዳት ዘመቻ ተከናወነ።
በመቻሬ ሜዳ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻው የተገኙት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እንደተናገሩት በዛሬውን የፅዳት ዘመቻ የሁሉም እምነት ተከታዮች መሳተፋቸውን ገልፀው ይህ ደግሞ የእኛ ኢትዮጲያን መለያ እሴት ነው ብለዋል።
ወ/ሮ አበባ አክለውም ኢትዮጲያ ሁሉም እምነቶች ተቻችለው፣ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባት ሀገር ናት ያሉ ሲሆን ይህንን አንድትና ህብረታችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።
የጥምቀት በዓል ኢትዮጲያ ካሏት የአደባባይ በዓላት አንዱ ነው ብለው በዓሉ ከእኛ ኢትዮጲያዊያን አልፎ አለም አቀፍ በዓል በመሆኑ ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁላችንም የየድርሻችንን እንወጣ ሲሉ ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ የተለያዩ እምነት አባቶች፣ አመራሮችና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
Lideta sub-city communication office
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
መጭውን የከተራ እና ጥምቀት በዓልን አስመልክቶ በጃንሜዳ የፅዳት ንቅናቄ መርሀ-ግብር ተካሄደ።
ጥር 9 / 2017 ዓ.ም
*****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‟የጥምቀት በዓልን በፅዱ አዲስ አበባ” በሚል ሀሳብ ከነገ ጀምሮ የሚከበረው የከተራ እና ጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ታቦተ-ህጉ የሚያድርበትን ስፍራ በሁሉም ክ/ከተሞች የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር የተካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በአራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ በድምቀት ተካሂዷል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማዋ ካቢኔ አባላት፣ የከተማ እና የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የሐይማኖቶች መሪዎችና ተከታዮች እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ባደረጉት ንግግር በዓሉ የሁሉም መሆኑን ለማሳየት ቦታውን ለማፅዳት የመጡ የተለያዩ እምነት ተከታዮችና የማህበረሰብ ክፍሎችን አመስግነዋል።
ከተማዋ ሰፋፊ የልማት ስራዎች ላይ መሆኗን ገልፀው ለበዓሉ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ጨምሮ ሁሉም አገልግሎቶች በተሟሉበትና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን ጠቁመዋል።
የአብሮነት እሴት የሚጠናከርበት በዓል እንዲሆን በመመኘት የመልካም በዓል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባ ወልደ ጊዮርጊስ ባደረጉት ንግግር ሀገራችን የምትታወቅበት ፍቅር አብሮነት፣ አንድነት ወንድማማችነት መቻቻል ለመግለፅ በፅዳት ዘመቻው የተገኙ የተለያዩ እምነት ተከታዮችንና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በቤተክርስቲያኗ ስም አመስግነዋል።
ዛሬ ማለዳ የተለያዩ የእምነት ተከታዮች አብሮነት ለማሳየት ያደረጉት በሁሉም ሁኔታዎች በማጠናከር አብሮነትና ወንድማማችነት እንዲጎለብት ሁሉም የበኩሉን አሰተዋጽኦ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የተለያዩ የእምነት መሪዎች በትንንሽ ነገር ከመራራቅ በአንድነትና በአብሮነት በወንድማማችነት በመቆም አቅም ፈጥረን የነበረው እሴታችንን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
የጥምቀት በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ (በዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ቅርሶች ተብለው ከተመዘገቡ በዓላት መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
በፅዳት ንቅናቄው ላይም ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የሀይማኖት አባቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ የፅዳት አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ማምሻውን የጥምቀት በዓልን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ጋር ተወያይተናል::
የጥምቀት በዓል የተለመደውን ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ ከሃይማኖቱ አባቶች ጋር የተወያየን ሲሆን ሁላችንም በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን እና የቱሪስት መስህብነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ተባብረን በጋራ እንስራ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
"ከቃል እስከ ባህል!" በሚል መሪ ቃል በከተማችን ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መድረክ ዛሬ አከናውነናል::
የብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የማበልጸግ ራዕይ ሰንቆ ከየትኛዉም ዋልታ ረገጥ እሳቤ ርቆ ሚዛናዊ የመሃል ፓለቲካ እሳቤን በመከተል ተግባቦት ላይ የተመሰረተ የዳበረ የዴሞክራሲ ባህልን መገንባት፣ አካታች እና ሰው ተኮር ስራዎችን በመተግበር የኑሮ ጫና የሚያቀሉ እና ሀገር የሚያበለፅጉ ስራዎችን በመስራት ቃልን በተግባር እየፈፀመ ያለ ግዙፍ ፓርቲ ነዉ።
በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፎ እስከዛሬ ድረስ በሀገር ዉስጥና በዉጪ የተመዘገቡ ድሎችን የተጎናፀፈዉ በፅናት እየተራመደ ከህዝባችን ጋር በትብብር በሰራዉ ስራ ነዉ።
በቃላችን መሰረት አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ ለማድረግ 24/7 በመስራት የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጓት አስደናቂ ስራዎች ተከናዉነዋል።
የምንሰራው ስራ የሀገራችንን ዘላቂ ልማት እና ሰላም የሚያረጋግጥ በመሆኑ በቀጣይም ከህዝባችን ጋር በመሆን የኢትዮዽያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ተግተን መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በኤጀንሲው የመጀመሪያ 6 ወር የስራ አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2017 በጀት አመት የ6 ወር የእቅድ አፈፃፀምን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንዲሁም የተቋሙ አመራሮች በተገኙበት በጋራ ግምገማ አካሄደዋል።
በዚሁ ወቅት በበጀት አመቱ በ6 ወራት በተቋሙ የተከናወኑ ስራዎች ማለትም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣የክትትልና ድጋፍ፣በየጊዜዉ ስራዎችን ከመገምገም፣ከፍርድ ቤት የምዝገባ አገልግሎት፣የጤና ተቋማት ላይ የምዝገባ አገልግሎትእና ከነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት አሰጣጥ አንጻር በሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በተጨማሪም የሪፎርም ስራዎችን በተመለከተ፣የሰዉ ሀብት አጠቃቀም፣በቴክኖሎጂ ስራዎችን ከመከወን፣ ለባለሙያዎች ስልጠና ከመስጠት፣ከመልካም አስተዳደር ፣ምቹ የስራ ቦታ ከመፍጠር፣ከፋይዳ ምዝገባ አንፃር እና ሌሎች ስራዎችን የሚያሳይ ሪፖርት በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በአቶ ዮናስ አለማየሁ ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል።
በዚሁ መድረክ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በተቋሙ የተቋም ግንባታና የስራ አፈፃፁምን፣ የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጥ የላቀ በማድረግ፣ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ማሻሻያ ስራዎችን እንዲሁም እየተሰጡ ያሉ አገልግሎት በአዲስ የቴክኖሎጂ መር ስርዓት በመተካት አገልግሎቱን ከማሳደግ፣ የተገልጋይ እርካታን ከማሻሻል፣ እና ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር ረገድ፣መልካም አስተዳደር ከማስፈን በመጀመሪያዉ ስድስት ወር የተከናወኑ ተግባራት አመርቂ እንደሆነ ገልፀዋል።
አክለዉም በተቋሙ በመጀመሪያዉ 6 ወር የመጡት ዉጤቶችን በማስቀጠል የተሰጡ አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመውሰድ ለቀሪዉ የበጀት አመት ወር ክፍቶችን በማስተካከል የተሻለ ክንዉን ለማድረግ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዉ መሠረታዊ የሆኑ ግብዓቶችን ከማሟላትና የአገልግሎት ተደራሽነትን ከማስፋት አንፃር ከዚህ የተሻለ አፈፃፀም በቀጣይ መፈጠር እንዳለበት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ባለፉት ስድስት ወራት ከደረሱ አደጋዎች 7.8 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከዉድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ።
ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባና አካባቢዉ 244 የአጋጥሙ ሲሆን ከደረሱት አደጋዎች 144 የእሳት አደጋዎች ሲሆኑ ቀሪ 100 ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ናቸዉ።
የደረሱትን አደጋዎች ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ በአደጋ ዉስጥ የነበሩ 19 ሰዎችን ህይወት የታደጉ ሲሆን ከደረሱት አደጋዎችም 7.8 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከዉድመት ማዳን ተችሏል ።
በሌላ በኩል በደረሱት ምክንያት 81 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን ከ 370 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሲወድም በልዩ ልዩ አደጋዎችና ምክንያታቸዉ ባልታወቁ አደጋዎች 46 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፎ የተገኘ ሲሆን የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሟቾችን አስከሬን አንስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
በመዲናዋና አካባቢዉ የሚያጋጥሙ አደጋዎች አብዛኛዎቹ በጥንቃቄ ጉድለት የሚደርሱ በመሆናቸዉ ህብረተሰቡ በተለያዩ አማራጮች ከኮሚሽን መ/ቤቱ የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ አደጋን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የታህሳስ ወር የስራ እንቅስቃሴን የሚያስቃኝ ዜና መጽሄት ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንዲያነቡ ተጋብዘዋል።
https://t.me/aacitymanager/16256
ዛሬ ባለ 13 ወለል የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ግንባታን አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
ዘመኑን የሚመጥን የስራ አካባቢ ለመፍጠር በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነዉ ሲሰጡ የነበሩትን አገልግሎቶች ን ወደ አንድ ማእከል በማሰባሰብ አገልግሎት የሚሳልጥ ፣ ለአካል ጉዳተኞችም ምቹ፣የአገልጋይ እና የተገልጋይ እንግልት የሚቀንስ፣ ስማርት ሲቲን የመፍጠር ግባችንን ለማሳካት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተካትተውበት የተገነባ ሲሆን በውስጡ 120 ቢሮዎችን ጨምሮ እያንዳንዳቸው 1500 እና 500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ በቂ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ጂምናዚየም፣ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ ቦታ እና መሰል መገልገያዎች ተሟልተዉለታል።።
በተጨማሪ ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት በጥራት ገንብተን ያጠናቀቅነው ይህ ህንፃ ዉጪን በመቆጠብ ከዚህ በፊት ለቢሮ ኪራይ የምናውለውን ሀብት በማስቀረት ለልማት እንድናውል ያስችለናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
