1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት እንደ ከተማ አስተዳደደር የምንተማመንበት ሞዴል ተቋ… See more
ባለፉት የለውጥ አመታት በአዲስ አበባ ማዛጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የተገኙ ስኬታማ ውጤቶችን በተመለከተ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ከአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያ ኢንጀነር ወንደሙ ሴታ ጋር የተደረገ ቆይታ
See less
ዩኤን ሃቢታት "የከተማ ልማትና አስተዳደር ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቸቸው "በሚል ርእስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለተለያዩ አገራት የከተማ አመራሮች ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሲንጋፖር የተሰጠውን ስልጠናና የልምድ ልውውጥ ላይ የተካፈሉት በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለጹት ስልጠናው ከተለያዩ የአለም አገራት እና ከሲንጋፖር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን መቅሰም የተቻለበት ነው ሲሉ አስረድተዋል።
አያይዘውም ለስልጠናው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በሁሉም ዘርፍ የተመዘገበውን አስደናቂ እምርታዊ ለውጥ እና በኮርደር ልማት የተመዘገቡ ስኬቶችና ምርጥ ተሞክሮዎች ማቅረብ የተቻለበት እንደሆነም አመልክተዋል።
አክለውም በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከሲንጋፖር የተቀሰመውን ተሞክሮ እና ልምድ በሚገባ በመቀመር ለመዲናችን አዲስ አበባ ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ አጋዥ በሚሆን መልኩ ተግባራዊ የምናደርገው ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
መጋቢት 20/7/2017
የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በመንግሥት የግዢ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬትና የግዢና ንብረት አሰተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የመንግስት የግዢ አፈፃፀም ዙሪያ ላይ ያለመ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለፅ/ቤቱ ባለሙያዎች በዛሬዉ እለት ሰጥቷል።
በስልጠናዉም ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መሳይ መርሻ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የስልጠናው መድረኩን አስጀምረዋል።
የስልጠናው ዋና አላማ የመንግሥት ግዢ ምንነት ፣የህግ ማዕቀፍ፣የመንግስት ግዢን በህግ ከመምራት፣የመንግስት ግዢ መርሆች፣የግዢ ዑደት ምንነት፣የግዢ እቅድ አስፈላጊነት፣የግዢ ዝግጅት፣የግልፅ ጨረታ ምንነት እንዲሁም ከፍላጎት መግለጫ አንፃር በእነዚህ እና በሌሎች ርዕሶች ላይ ለሰልጣኞች ግንዛቤ ለማስጨበጥ የታለመ መሆኑን የፋይናንስ ቢሮ የስልጠና ባለሙያ የሆኑት አቶ ደሴ አዳም ተናግረዋል።
ስልጠናዉ ሰራተኞች አቅምን የሚፈጥርና የስራ ባህልን በይበልጥ ለማጎልበት እንዲሁም በመንግስት የግዢ ምንነት ላይ በይበልጥ ግንዛቤን የሚፈጥርና የሚረዳ እንደሆነ በስልጠናው ወቅት ተመላክቷል።
ስልጠናዉ በሰራተኛዉ ዘንድ ያለዉን የግዢ ሂደቶችን በይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እንዲሁም ስራዎችን ለማጠናከር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች የተሻለ ክህሎትን ለማሳደግ የሚረዳ አቅም መፍጠር ያስችላል ሲሉ የፅ/ቤቱ የግዢና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዋቅቶላ ጋሪ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ከሰልጣኞች ጋር በቀረበው የስልጠና ሰነድ ላይ በመወያየት እንዲሁም ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል።
የኢድ አልፈጥር በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም እንዲከበር አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ ተገለጸ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በቀጣይ ቀናት በድምቀት የሚከበረዉን የኢድ አልፈጥር በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም አንዲጠናቀቅ አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ የኮሚሽኑ አመራሮች ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በአደረጉት ዉይይት አስታዉቀዋል።
በበዓሉ አካባባበር ጊዜ እሳትና የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮች ያለበቂ ጥንቃቄ ጥቅም ላይ የሚዉሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አየተሰሩ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ ማናቸዉም አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገም ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የኮሚሽኑ አመራሮች በአደረጉት ዉይይት አስታዉቀዋል።
ህብረተሰቡ ከኮሚሽን መ/ቤቱ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንዲተገብርና ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች በነጻ የስልክ 939 ላይ በመደወል ፈጥነዉ አንዲያሳዉቁም ጥሪ ቀርቧል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አግልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ ማለዳ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ 100 ሺሕ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች እና በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎቻችን ማዕድ አጋርተናል።
የማዕድ ማጋራቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች፣ ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የዕዝነትና የመረዳዳት ወር በሆነው የረመዳን ጾም ወቅት ጠያቂ ያጡ አስታዋሽ አግኝተው በቸርነት ተጎብኝተዋል፣ ደጋፊ ያልነበራቸው በልበ ቀናዎች እጅ ተዳብሰዋል።
ሰርተው ካገኙት መስጠትና ማካፈልን ባህል በማድረግ እንደ ወትሮው ሁሉ ዘንድሮም ከጎናችን የቆሙትን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና በሁሉም ክፍለከተሞች አስተዋፅዖ ያደረጉ አካላትን በነዋሪዎቻችን እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
"Ayidde Cambalaalla!
እንኳን ለፊቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የሲዳማ ውብ ባህል መገለጫ የሆነው የፊቼ ጫምባላላ በዓል ፍቅር፣ እርቅ፣ ሰላም፣ ምስጋና እንዲሁም ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት የዘመን መለወጫ በዓል እንደመሆኑ አሁንም ይበልጥ አንድነት የሚጠናከርበት፣ እርቅ፣ ሰላም፣ አብሮነት እና ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት እንዲሆን እመኛለሁ::
በድጋሚ እንኳን ለፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
"Ayidde Cambalaalla!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
"ትናንት፣ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልእልና" በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ
የለውጡ መንግሥት ኃላፊነት የተረከበበትን 7ኛ ዓመት አስመልክቶ ”ትናንት፣ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልእልና" በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በዛሬው እለት መጋቢት 18/ 2017 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡
የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ እና የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ መኮንን ናቸው።
በመድረኩ ላይ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር እሸቱ ለማ የለውጡ ብስራት የተበሰረበት የመጋቢት ወር በኢትዮጵያውያን ዘንድ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው የአዲስ ምእራፍ ጅማሮ መሆኑን አውስተዋል።
አክለውም የመጋቢት ወር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ያደረገ ታላላቅ እና ግዙፍ ስራዎች የተከናወኑበት፣ ወንድማማችነትና ህብረብሔራዊ አንድነት እየጎለበተ የመጣበት፣የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ከፍታ እያረጋገጡ ያሉ እና ብሔራዊ ጥቅሟን እያስጠበቁ ያሉ ስራዎችን መከወን ያስቻለ ራእይና ህልምን ወደተግባር መተርጎም የተቻለበት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የጽ/ ቤት ሃላፊ እና የልዩ ወረዳው የአደረጃጀት ዘርፍ ሰብሳቢ አቶ ግርማ መኮንን ለውይይት መነሻ የሆነው ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት 7 የለውጥ ዓመታት በአገራችን እና በመዲናችን የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስራዎች እና የተገኙ ስኬቶችን በዝርዝር አመላክተዋል። ይህንኑ መሠረት በማድረግ በልዩ ወረዳው አመራር እና አባላት ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ስለ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምን ያህል ያውቃሉ ?
የፋይዳ ቁጥር በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ ነዋሪዎች የሚሰጥ ባለ 12 አሀዝ ልዩ መለያ ቁጥር ነው፡፡ የፋይዳ ቁጥር ዲጂታል መታወቂያ የያዙ ነዋሪዎች በሀገሪቱ ውስጥ ማንነትን በማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላል፡፡
ጠቀሜታው ምንድን ነው ?
• መሰረታዊ የመታወቅ መብት የሚሰጥ ትክክለኛ እና ሕጋዊ ማንነትን ለማረጋገጥ
• የባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት እና በመደበኛ ኢኮኖሚ ውስጥ ለመሳተፍ አፋጣኝ እና ትክክለኛ የህክምና ክትትል ለማድረግ ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት ጠቃሚ መረጃ መስጠትና የታካሚውን ደህንነት ማሻሻል፣
• ተማሪዎች እንደ ቤት መፅሀፍት አገልግሎት ያሉ የትምህርት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ፣
• የታክስ የፍይዳ መለያ ቁጥር /TIN/ ቁጥር ለማግኘት እንደ ቅድመ ሁኔታ በመሆን በተጨማሪ የማንነት ማጭበርበርን በመከላከል ዲጂታላይዝድ አገልግሎቶች እንዲቀላጠፉ ያደርጋል፡፡
• በሰነድ ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አማካኝነት በተለይም ሰነዶችን ለማረጋገጥ፣ስምምነቶችን ለመፈረም፣ ውክልና ለመስጠት መመስረቻ ሰነድ ለመፈረም ያገለግላል፡፡
የፋይዳ መታወቂያ የትመመዝገብ እንዳለብዎ ያውቃሉ ?
• በ11ዱም ክፍለ ከተሞች እና በአቅራቢያዎ በሚገኘው የወረዳ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ፅ/ቤት በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ለመመዝገብ ሲመጡ የሚያስፈልግ ቅድመ ሁኔታ
• ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ ሲመጡ ነዋሪውን /ተመዝጋቢውን/ ሊገልጽ የሚችል የግለሰቡን ፎቶ የያዘ የማስረጃ ሰነድ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
• ከላይ የተገለፁትን ሰነዶች ማቅረብ የማይችል ነዋሪ በፋዳ ስርዓት ውስጥ የተመዘገበን ነዋሪ እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ለተጨማሪ መረጃዎች እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል:: በዚህም መሰረት:-
1. ወ/ሮ አይሻ መሀመድ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
2. አቶ አዋሌ መሐመድ - የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ - የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ሰይፈ ደምሴ- የከነማ ፋርማሲ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ
5. አቶ ነብዩ ፍቃዱ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ዳኛቸው ፈለቀ - የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽን እና አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
7. አቶ መለሰ አንሼቦ - የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን የግብርና ኤክስቴንሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር
በመሆን ተሹመዋል::
መልካም የስራ ዘመን!
