1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ከቻይናዋ ጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ሹ ኩንሊን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
ሚስተር ሹ ኩንሊን በህዳር ወር በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የጂያንግሱ ግዛትን እንድንጎበኝ ባቀረቡልን ግብዣ መሰረት በግዛቱ ጉብኝት በማድረግ ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ በጉብኝታችን ወቅት ከጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ እና አመራሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በመወያየት በቀጣይ በጥቅሉ በኢንቨስትመንት ፣ በንግድ ፣ በቱሪዝም ፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፎች ላይ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በቀጣይም በትብብር ለመስራት ተግባብተናል።
ሚስተር ሹ ኩንሊን በጂያንግሱ ግዛት በነበረን ጉብኝት ላደረጉልን መስተንግዶ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በጽ/ቤቱ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች የተመሩበት አግባብ መልካም ነው-የመንግስትና የፓርቲ የስራ አፈፃፀም የሱፐርቪዥን ቡድን
የከተማ አስተዳደር የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በመገኘት የተቋሙን የመጀመሪያ 6 ወር የስራ አፈፃፀም ላይ በዛሬው እለት የሱፐርቪዥን ስራ አካሂዷል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተቋሙ ዉስጥ የ6 ወራት የስራ ክንውንን ሪፖርት በሰነድ የማመሳከር ስራም አከናውኗል።
በሱፐርቪዥኑ ወቅት ፅ/ቤቱ እያከወነ ያለውን የተቋም ግንባታና የ6 ወራት የስራ ክንዉን አስመልክቶ ለሱፐርቪዥን ቡድኑ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በተቋሙ የተቋም ግንባታና የስራ አፈፃፁምን የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጥ የላቀ በማድረግ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ማሻሻያ ስራዎችን እንዲሁም በተጠሪ ተቋማት እየተሰጡ ያሉ አገልግሎት በአዲስ የቴክኖሎጂ መር ስርዓት ተክቶ አገልግሎቱን ከማሳደግና የተገልጋይ እርካታን ከማሻሻል እና ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር ረገድ የተከናወኑ ተግባራትን ገልፀዋል።
የከተማ አስተዳደር የሱፐርቪዥን ቡድኑ በሰጠዉ ግብረ መልስ በፅ/ቤቱ በ6 ወር ውስጥ የተሰሩ ስራዎች የተመሩበት መንገድ መልካም የሚባል እንደሆነ ገልፀው በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ በተለይም ስራዎችን በስታንዳርድ ከመስራት አንፃር፣የተገልጋይ እርካታ ከማሳደግና ለዉጥ ከማምጣት ፣የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግ አንፃር የተሰሩት ስራዎች አበረታች እንደሆነ ተናግረዋል።
የፓርቲ ስራን በተመለከተ መሠረታዊ ድረጅት ላይ የታዩት ስራዎች በተለይም የአባላት መረጃ ቋት ከመፍጠር አንፃር፣በቴክኖሎጂ በመታገዝ ስራዎች መሠራታቸወ፣ከእቅድና መረጃ አያያዝ፣ ተተኪ አባል ከመፍጠር አንፃር፣ ለተቋማት ብሎም ለከተማዉ ጭምር አብነት መሆን እንደሚችል ተገልፆ ከፍተኛ አቅም የሚሆን ስራ መሠረቱን እና ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የቡድኑ አመራሮች አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የመጡት ዉጤቶችን በማስቀጠል የተሰጡ አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመውሰድ ለቀጣይ 6 ወር ክፍቶችን በመሙላት የተሻለ ክንዉን ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገንዝበዋል።
በተያያዘም የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ጋር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የ6ወር የእቅድ አፈፃፀም ላይ የሱፐርቪዥን ስራ አካሂዷል።
ታህሳስ 24/ 2017
በከተማችን አዲስ አበባ የምትኖሩ የአውሮፓውያኑን 2025 አዲስ ዓመት የምታከበሩ ሁሉ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ ፤ዓመቱ የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት
Wishing you all a very Happy New Year 2025! 🥳🎉🎇🎆🍾🥂✨
ከንቲባ… See more
ከሳር ቤት- ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ እንዲሁም ሃና ፉሪን መዳረሻው ያደረገው የኮሪደር ልማት ስራ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡
AMN - ታኀሣሥ 22/2017 ዓ.ም
በከተማው ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉ የፋይዳ ምዝገባ እንደ ልደት ምዝገባ አስገዳጅ እንደሚሆን ተገለፀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከከተማው ትምህርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በከተማው ካሉ የግል ትምህርት ቤት ማህብረሰብ ጋር የፋይዳ እና የልደት ምዝገባን በተመለከተ ውይይት አከናውነዋል።
በዕለቱ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የተገኙ ሲሆን ለውይይት የሚያግዝ መነሻ ገለፃ ቀርቧል።
በቀጣይ ግዚያት የፋይዳ ዘመቻ ምዝገባ ስራ በይፋ በግል ትምህርት ቤቶቹ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስተባባሪነት የሚከናወን ሲሆን የፋይዳ ምዝገባ እንደ ልደት ምዝገባ ለ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላ የምዘገባ ቅድሙ ሁኔታ እንደሚሆን ተነግሯል።
ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር በ7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ እርምጃዎች
👉 ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
👉በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
👉 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ- ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
👉መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ- የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም ሊወሰዱ ከሚገባቸው ከጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በፅዱ አዲስ አበባ ይከሄድ ዘንድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
****************
አስተዳደሩ በሰጣቸው ስምሪት መሰረት ተግባሩን በበላይነት የሚከውኑት የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ፣ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት እንዲሁም ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤቶች ሲሆኑ ክፍለ ከተማዋን ፅዱ ለማድረግ በ7/24 መርህ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በዛሬው እለትም አጠቃላይ ከዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ከባለድርሻ አካላና ከአጋር ተቋማት ጋር ተግባሩ የደረስሰበትን ደረጃ በመገምገም ተጨማሪ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።
Kirkos Communication-ቂርቆስ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የመሬት መንቀጥቀጥ ለምን ተደጋገመ?
*************
በምዕራባዊው እና በምስራቃዊው የኢትዮጵያ ደጋማ ክፍል መሃል የሚገኘው የአፋር ስምጥ ሸለቆ በየጊዜው የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ያስተናግዳል፡፡
ሰሞኑን በፈንታሌ ተራራ አካባቢ በሬክተር ስኬል እስከ 5 የተመዘገበ እና ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂዮ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ተማራማሪ እና መምህር አታላይ አየለ (ፕ/ሮ) ተናግረዋል።
በፈንታሌ ተራራ አካባቢ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ለአንድ ወር ያህል መጠኑ ቀንሶ መቆየቱን ተመራማሪው በተለይ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም ገልጸዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከቅልጥ አለት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ከባድ አደጋ ያደርሳል ተብሎ እንደማይጠበቅም ነው የተናገሩት።
ሆኖም ግን በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን ከባድ ጉደት ባያስተናግድም ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
በሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በመተሃራ አካባቢ እና በሳቡሬ ከተማ አንዳንድ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች የመሰንጠቅ አደጋ እንዳጋጠማቸው ከየአካባቢው ነዋሪዎች አረጋገጥናል ብለዋል ተመራማሪው ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ እስካሁን ጉዳት ስለ ማድረሱ የተደረገ ሪፖርት አለመኖሩንም አያይዘው ተናግረዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ በተለያዩ አካባቢዎች ያደረሰው ጉዳት ወደፊት የሚጣራ ስለመሆኑም አክለዋል።
በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ መቼ እና የት እንደሚደርስ ማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን የተናገሩት አታላይ አየለ (ፕ/ሮ)፤ አሁን የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ የሚገኘው አከባቢ በ1973 ዓ.ም እስከ 3 ወራት የዘለቀ የመሬት መንቀጥቀጥ አስተናግዶ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ ከጀመረ ከሳምንታት እስከ 6 ወራት ሊቆይም እንደሚችል ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ ያለው ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የመሬት መንቀጥቀጡን አስመልክቶ ሀሰተኛ መረጃ ሲሰራጩ እነደነበር ያስታወሱት ተመራማሪው፤ህብረተሰቡ ይህንን በተመለከተ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂዮ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሚሰጣቸውን ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ እንዲከታለተል አሳስበዋል፡፡
Ethiopian Broadcasting Corporation
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ብሔራዊ ቤተመንግሥት የኢትዮጵያ ታሪክ የሚገለጥበት ትልቅ የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ ለከተማችን ተጨማሪ ዉበት ሆኗታል !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
