1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
Welcome to Addis Ababa! Let’s make history!
Join us in Africa's capital, Addis Ababa, as we lead Africa toward a #greener, cleaner, and more #resilient future. This is … See more
የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ 25 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀዉን 2ኛዉን የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን አዲስ አበባ እንግዶቿን እያስተናገደችም ትገኛለች::
የእመርታ ቀን
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ
"የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ ሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምእራፍ አንደርስም፡፡ ያለን አማራጭ አንዳንድ እርከኖችን መዝለል ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ ፈጠራና ፍጥነት ወሳኞች ናቸው፡፡ ከተለመደው መንገድ ወጣ ማለት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ መሥራት፣ ከተለመደው ዋጋ በላይ መክፈል ያስፈልገናል፡፡ ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር አይደለም፡፡ ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው"፡፡
ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር)
ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ቃል የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሄደ።
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር "ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 2 የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በፕሮግራሙ ላይ ባሰሙት ንግግር ጳጉሜ የኢትዮጵያዊያን እና የተለየች ወር እንደመሆኗ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን በምናስመርቅበት ዋዜማ ላይ በመሆናችን በዚህ አመት ለየት ያደርጋታል ብለዋል።
ኢንጂነር ወንድሙ አክለው የከተማው አስተዳደር ከለውጡ በኋላ የኢትዮጲያውያን መገለጫ የሆነው መረረዳትና መተባበር ለማጠናከር የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ተቋም በማቋቋም አቅመ ደካሞችን በየጊዜው እየደገፈ ይገኛል በማለት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የአብሮነት ኢኒሼቲቭ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።
በዘላቂነት ከድህነት ለመውጣት እጅ ለእጅ በመያያዝ በአመራሩ ፊት አውራሪነት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ተባብረን ለማጠናቀቅ እንደበቃነው ድህነትንም የምናከስምበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ጠቁመዋል።
ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው እንዳሉት የብልፅግና እሳቤዎችን የምናሰርፅበት የጳጉሜ ወር የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት ከለውጡ ወዲህ ያከናወንባት ወር ናት ብለዋል።
ይህን ፕሮግራም ስናካሂድ ተረጂነትን ለማስፋፋት ሳይሆን በተለያየ መንገድ ሀገራቸውን ያገለገሉ እና በጊዜ ሂደት አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖቻችን በዓልን ያለጭንቀት እንዲያሳልፉ በማሰብ እንደሆነ ወ/ሮ ልዕልቲ ገልፀዋል።
የልደታ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ እንደገለፁት በዚህ ሰው ተኮር ስራ በዛሬው እለት ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ከ40, 000 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህ ክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ለ395 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ግንባታ፣ ከ3,500 በላይ የደም ልገሳ በማድረግ በዚህም ከ10,500 በላይ የክረምት በጎ ፈቃድ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን አቶ እንግዳው አያይዘው ገልፀዋል።
Lideta sub-city communication office
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመዲናችን አዲስ አበባ ከለውጡ ወዲህ በቋሚነትና በዘላቂነት ተቋማዊ መሠረት ኖሮት እየተሰራ ያለው የበጎ አድራጎት ስራ በህዝባችን መካከል መደጋገፍና መተጋገዝ ባህል እንዲሆን እያደረገ ያለ ስኬታማ ስራ ነው ሲሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት "ብዝሃነት የኢትዮጵያዊነት ጌጥ" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት እየተከበረ ያለውን የጳጉሜ 2 የህብር ቀን ምክንያት በማድረግ በተካሄደ የቤት ርክክብና የማእድ ማጋራት ስነስርአት ላይ ነው።
ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም የዛሬው የህብር ቀን ሰብአዊነታችንን፣ደግነታችን የምናሳይበት ህብረታችንን የምናጠናክርበት በዚህም በበጎ ፈቃድ የተገነቡ ቤቶችን የምናስረክብበትና የማእድ ማጋራት ተግባር በማከናወን ኢትዮጵያዊ እሴታችን እና አንድነታችን የበለጠ የምናጠናክርበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
መጪው ጊዜ ተከታታይ በአላት የሚከበሩበት እንደመሆኑ አቅመ ደካሞች በአላትን ደስ ተሰኝተው እንዲያሳልፉ የጎደለባቸውን መሙላት የምንችልበትን ሃብት ስናሰባስብ ነው የቆየነው ሲሉ ገልፀው በዚህም የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ለ35 ነዋሪዎች የሚሆን የቤት ግንባታ እያጠናቀቀ እንደሆነና ለተቋሙ ተጠሪ በሆኑት 4 ተቋማትም በተመሳሳይ እየተከናወኑ ያሉ የቤት ግንባታና መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች እየተገባደዱ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በዛሬው እለትም እንደ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጎ ፈቃደኛን በማስተባበር የተካሄደ የቤት ግንባታ ርክክብ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ለ191 ያህል የተቋሙ ባለሙያዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የማእድ ማጋራት መርሐግብርም ተካሂዷል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሐመድ በበኩላቸው የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በቅድመ አደጋ መከላከል ተግባር የከተማችንን ነዋሪዎች ህይወትና ንብረት የመጠበቅ ታላቅ ተግባር ከማከናወን ጎን ለጎን ለማህብረሰቡ ሰብአዊነት ያለውን ተግባር የመፈፀምና አቅመደካሞችን የመደገፍ ተልእኮ በተጠናከረ መንገድ እየተወጡ እንደሚገኙም አመልክተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግም፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።… See more
