1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
"እኔም የአካባቢዬ ፅዳት ባለቤት ነኝ!"
ብሎክን መሰረት ያደረገ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
በዚሁ የጽዳት ንቅናቄ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሰ፣ የክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አመራሮች እና የወረዳ አመራሮች፣ የከተማ የጽዳት አምባሳደር አርቲስቶች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች፣ የጸጥታ አካላት እና የወረዳው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
መርሃ-ግብሩ በኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀረ ሲሆን በታዋቂ አርቲስቶች በኪነ ጥበብ የተደገፈ በጽዳት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በመሪዎቻችን ትጋትና ብርታት አዲስ አበባን በውበት እና በብልጽግና የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት ለሊት እና ቀን እየተሰራ እንደሆነና በክፍለ በከተማችን በሁሉም ዘርፍ ውጤት እየተመዘገበ ነው በማለት ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽዳት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር እሸቱ ለማ እንደተናገሩት የአንድ ከተማ ማደግና መበልጸግ የሚመዘነው ጽዱና ውብ ስትሆን ነው። በዚህም ሁሉም ነዋሪ የፅዳት አምባሳደር መሆን ይገባል በማለት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ በሁሉም ዘርፍ ለውጥና ውጤት እያስመዘገበ ነው ብለዋል።
የጽዳትን ስራ ለአንድ ወገን ብቻ ባለመተው ሁሉም በመረባረብ ሞዴል መንደር እና ብሎኮችን መፍጠር እንደሚገባና የኃይማኖት ተቋማት፣ ዕድሮች እና የትምህርት ተቋማት ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግና ነዋሪው የሚሰጠውን ግንዛቤ በተግባር ላይ በማዋል ቆሻሻን ለይቶ መያዝና ማስወገድ እንዲሁም መልሶ መጠቀም እንደሚገባና ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸው በህገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ የሚጥሉ ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ በበኩላቸዉ በጽዳት ዙሪያ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ እየተፈጠረ እንደሆነ እና ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ሀብት የመፍጠር ደረጃ ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለስራ ኃላፊዎች የምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃ ግብር ተካሄዷል።
ሚያዚያ 25 / 2017 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዉጤታማ የስራ አፈፃፀማችንን በማጠናከር ክፍተቶችን እየዘጋን የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከለውጡ በፊት የከተማዋ ነዋሪዎች ፅዱና ልምላሜን አካባቢ ለማዬት ሲፈልጉ ለጉብኝት ከከተማዋ ራቅ ብለው ወደሚገኙ አካባቢዎች ነበር የሚወጡት። ዛሬ እናንተ ወጣቶች ታድላችሁዋል።ፅዱና ልምላሜ ቦታዎች በመዲናችን ተፈጥሮላችሁዋል።"
ሃጂ ሸምሱ አባስ
የመዲናችን የፅዳት አምባሳደር
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
መንግስት የአዲስ አበባ ከተማን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ እያደረገ ያለውን ተግባር ለማገዝ ነዋሪው ፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ እንዳለበት ተገለፀ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መድረክ በማዘጋጀት፣ በቤት ለቤት፣ በሻይ ቡና ፕሮግራም፣ በንቅናቄ እና በተለያዩ ስልቶች ግንዛቤ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አሳዉቋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት፣መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳትና የጎርፍ መከላከል ንቅናቄ ዕቅድ ዙሪያ ለብሎክ ካውንስል አመራሮች፤ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣አስተባባሪና ቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናየ ጫኔ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት የሚሰጠውን ግናዛቤ ወደ ተግባር ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግና በጽዳት ስራው የኃይማኖት ተቋማት፣ዕድሮች፣ድርጅቶችና ተቋማት በንቃት ልትሳተፉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ እንደተናገሩት ቀደም ሲል በመኖሪያ አከባቢ በተቋማትና በብሎክ የጽዳት ንቅናቄ ስናካሄድ የቆየን ሲሆን መጪው ክረምት በመሆኑ የፍሳሽ መውረጃዎችን ማጽዳት ይገባል ብለዋል።
በጽ/ቤቱ የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን መሪ ወ/ሮ እቴነሽ አበራ እና አቶ ጌቱ ኩምሳ የክፍለ ከተማው ጽዳት ስራዎች አስተባባሪ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።
በክፍለ ከተማው በሚፈጠር ግንዛቤ የህብረተሰቡ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደመጣና ቆሻሻን የመለየትና መልሶ መጠቀም እየተለመደ መምጣቱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ አያይዘውም መንግስት የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ውብና ማራኪ እየደረገ ያለውን ተግባር ነዋሪውም በየአከባቢው የፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም ጨለማን ተገን በማድረግ ቆሻሻ በመነገድ ላይ የሚጥሉና የሚያዝረከርኩ ህገ ወጦችን መከታተልና የወጡ ህግና ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ በቅጣት ማስተማር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሚያዝያ 24/ 2017
Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የመዲናችን የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር በይበልጥ ለማዘመን የሚያስችሉ አዳዲስ የአሰራር ስርአቶችና ስልቶችን በሳይንሳዊ ጥናት በማስደገፍ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት ከስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የተውጣጡ አመራሮች በቅርቡ በጋና አክራ ተገኝተው በጽዳት ዘርፍ ባካሄዱት የልምድ ልውውጥ ያገኙትን ተሞክሮ ባቀረቡበት ወቅት ነው።
የአመራር ቡድኑ መዲናችን አዲስ አበባ በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና ማጓጓዝ፣ በአካባቢና በከተማ ፅዳት፣ እንዲሁም ዜጎችን በፅዳት ስራ ለማሳተፍ የሚካሄዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ያላትን ምርጥ ተሞክሮ ትምህርት እንዲቀሰምበት ለጋና አክራ የዘርፉ አመራሮች አቅርበዋል።
በጋና አክራ በኩል ደግሞ " ፅዱ ጋና" Clean Ghana initiative በመተግበር በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ዘርፍ የግሉን ሴክተር ተሳትፎ ማሳደግን፣ በቴክኖሎጅ የታገዘ የቆሻሻ ልዬታ እና ወደ ሃብት የመቀየር ስራዎችን የመልሶ መጠቀምና የኮምፖስት ስራዎች ላይ በተግባር የተደገፈ ልምዳቸውን ማጋራተቸውን የአመራር ቡድኑ በሰነድ አስደግፎ አቅርቧል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት በከተማችን አዲስ አበባ በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ላይ ያስመዘገብነውን ከፍተኛ ስኬት ቆሻሻን ወደ ሃብት በመቀየርና የቆሻሻ አወጋገድ ላይ የአፈፃፀም ውጤታማነትን በእጅጉ ለማሳደግ ይህን መሰል የልምድ ልውውጦች እገዛቸው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ሚያዚያ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
44ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ከጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት እና ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተፈረሙ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ ከጣሊያን ሪፐብሊክ መንግስት የተገኘው የ11,500,000 ዩሮ ለአካባቢያዊና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የበጀት ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል ሲሆን የ16 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ30 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር የተገኘው 38,100,000 ኤስ.ዲ.አር ለመማር ማስተማር ማጎልበቻ የትምህርት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል ሲሆን 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበት ሆኖ 6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ምክር ቤቱም ብድሮቹ ምንም አይነት ወለድ የማይታሰብባቸው እና ከአገራችን የብድር አስተዳደር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን መቋቋሚያ ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ ትኩረቱን በመሠረተ ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማት ላይ በማድረግ ለግል አልሚዎችና ለመንግሥት አካላት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ ነው፡፡ ሀገራችን በአባልነት መቀላቀሏ ለግሉ ዘርፍ ተጨማሪ የፋይናንስ ሀብት በማቅረብና የግል ዘርፉን የማይተካ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት ሚና በማሳደግ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠንና ድህነትን ለመቀነስ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. ሌላው ምክር ቤቱ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት የዕቃዎች ቀረጥ ምጣኔ ቅነሳን ለማስፈፀም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል። ስምምነቱ በአባል ሀገራት መካከል ንግድ እንዲስፋፋ፣ የገበያ ትስስሩ እንዲጠናከር፣ የእሴት ሠንሰለቱ እንዲጎለብት እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማበረታታት የሚያስችል ነው፡፡ በአባል ሀገሮች መካከል የሚደረጉ ግብይቶች በታሪፍ ምክንያት ሳይደናቀፉ የእቃዎች ፍሰት የተሳለጠ እንዲሆን ከአባል አገራት በሚመጡ እቃዎች ላይ የጉምሩክ ታሪፍ ምጣኔ ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን በመወያዬት ምክር ቤቱ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለሚሰጡ አገልግሎቶች እና በኢ.ፌዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ለሚሰጡ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን በቀረቡ ሁለት ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ ተቋማቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያወጡትን ወጪ በመሸፈን፣ ገቢያቸውን አሳድገው ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ የሚያስችል የደንበኞችን አቅም ባገናዘበ መልኩ የአገልግሎት ክፍያ መወሰን አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
5. የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ነው፡፡ የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ ለውጭ ዜጎች ህጋዊ አሠራር መዘርጋቱ የውጭ ካፒታል በሀገራችን ሥራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት፣ የቤት ልማት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማነቃቃት፣ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ሚዛን ለማስጠበቅ እና ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ የሚኖራቸው በመሆኑ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
6. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው ከኦስትሪያ መንግስት ጋር የተፈረመውን የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ለማፅደቅ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የስምምነቱ መጽደቅ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ ለአየር መንገዳችን ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም ሌላ የሀገራችንን ንግድና ኢንቨስትመንት በማበረታታት፣ የውጪ ንግዱን በመደገፍ፣ ቱሪዝምን በማስፋፋት፣ የስራ ዕድል በመፍጠርና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ረገድ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
//
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
ዛሬ ጠዋት ከፕሬዝደንት ጁአዎ ማኑኤል ጎንካሌቭ ሎሬንቾ በልዩ መልዕክተኝነት መልዕክት ይዘው የመጡትን የአንጎላ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴቴ አንቶኒዮን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የሠጡት ምላሽና ማብራሪያ
ህዝብን በማዳመጥ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች እና ዝርዝር መረጃዎችን መስጠት የተጠያቂነት ስረአት ግንባታ አካል ነዉ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
See less
መዲናችን አዲስ አበባ ለአብዛኞች የአፍሪካ አገራት ከተሞች የጽዳት ተምሳሌት እየሆነች ትገኛለች"
"በየቤታችን እኛ አንፈልገውም ብለን የምንጥለው ቆሻሻ 50 በመቶ የሚሆነው ለመልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችልና ለዜጎቻችን የስራ እድል የሚፈጥር ነው።"
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ ከከተማችን ነዋሪዎች የተነሱ ጥያቄዎች በምክር ቤት አባላት አማካኝነት ቀርበው ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተናል።
ህዝባችንን ማዳመጥ እና ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን እና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት የአመራራችን መገለጫ፣ የአገልግሎታችን አንዱ እና ትልቁ አካል በመሆኑ ከነዋሪዎቻችን ለተነሱ ጥያቄዎች እንዲሁም ሃሳቦች በሙሉ ምላሽ እና ማብራሪያዎችን ሰጥተናል።
ለተነሱልን ጥያቄዎች የተሰጡ ማብራሪያዎችን እና ዝርዝር መረጃዎችን በተለያዩ ሚዲያዎች እንዲሁም በዚህ ገፅ የምንለቅ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
