1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለባለሙያዎች የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ፣ልየታ እና የማስፋት ስትራቴጂ ዙሪያ ላይ ያለመ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለሁለት ቀናት ሰጥቷል።
ስልጠናዉን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ ም/ዋና ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ስልጠናው በተቋሙ ያለዉን ባለሙያ ብቁ ፈፃሚ ለማድረግና የሚሰጠዉን አገልግሎት በእውቀት የተመራ ለማድረግ አቅም የሚፈጥር ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።
በስልጠናው ላይ ከእቅድ ዝግጅት እና ትግበራ፣ከእቅድ ግምገማ ፣በተቋም ዉስጥ የዉጤት ስርዐት ከመተግበር እና ስትራቴጂን ለፈፃሚ የማውረጃ ዘዴዎች፣ የምዝገባና የንፅፅር ሂደት ምንነት፣ ተሞክሮዎችን መለያ መስፈርቶች፣የተሞክሮ አዘገጃጀት፣በእነዚህ እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
ስልጠናውን በመስጠት ሂደት የተሳተፉት ከፐብሊክ ሰርቪስ የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ቡድን መሪ አቶ እንዳልካቸው እንዳይላሉ ስልጠናዉ በሰራተኛዉ ዘንድ ያለዉን የአገልግሎት አሰጣጥና የስትራቴጂ ቅመራ ላይ ግልፅነትን የሚፈጥር እንደሆነ አስገንዝበዋል።
የፅ/ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ዳይሬክተር ወ/ሮ እስከዳር መላኩ በበኩላቸው ስልጠናው ተቋሙ ራእይና ተልእኮውን ለማሳካት በሚያደርገው ጥረት የባለሙያውን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ እና የተሻለ ክህሎትን ለማጎልበት የሚያግዝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ ፤ አደረሰን!
እናትነት የድንቅ ፀጋ ፣ ታላቅ በረከት ፣ የሚያገርም ጥንካሬ፣ ከራስ በላይ የመኖር ችሎታ፣ የርህራሄ እና የፍቅር መገለጫ ነዉ።
ክብር ለእናቶች!!
መልካም የእናቶች ቀን!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የፋይዳ ሩጫ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል!
በዕለቱ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አትሌቶች እና የተለያዩ የህበረተሰብ ክፍል ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ፋይዳ ለኢትዮጵያ የጎዳና ሩጫ በአትሌቶች መካከል የተደረገው ውድድር ተጠናቀቀ
ፋይዳ ለኢትዮጵያ የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በአትሌቶች መካከል የተደረገው ውድድር ተጠናቋል።
በሴቶች ዮርዳኖስ ፅጋብ ስታሸንፍ ፤ ንግስቲ ሞላ እና ይርጋለም ኪዳነ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች በተደረገ ፉክክር ይስማው ድሉ ቀዳሚ ሆኗል።ይበልጣል ጋሻሁን 2ኛ ንብረት ክንዴ ደግሞ ሦስተኛ ወጥቷል።
ትልቅ አላማ ሰንቆ በተከናወነው የአትሌቲክስ ውድድር ላይ በሁለቱም ፆታ 486 አትሌቶች ተሳትፈዋል።
AMN-Addis Media Network
ፋይዳ ለኢትዮጵያ የጎዳና ሩጫ በአትሌቶች መካከል የተደረገው ውድድር ተጠናቀቀ
ፋይዳ ለኢትዮጵያ የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ በአትሌቶች መካከል የተደረገው ውድድር ተጠናቋል።
በሴቶች ዮርዳኖስ ፅጋብ ስታሸንፍ ፤ ንግስቲ ሞላ እና ይርጋለም ኪዳነ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች በተደረገ ፉክክር ይስማው ድሉ ቀዳሚ ሆኗል።ይበልጣል ጋሻሁን 2ኛ ንብረት ክንዴ ደግሞ ሦስተኛ ወጥቷል።
ትልቅ አላማ ሰንቆ በተከናወነው የአትሌቲክስ ውድድር ላይ በሁለቱም ፆታ 486 አትሌቶች ተሳትፈዋል።
AMN-Addis Media Network
የፋይዳ ለኢትዮጵያ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ነው
የፋይዳ ለኢትዮጵያ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በውድድሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች እንዲሁም ከተለያዩ ክለቦች የተወጣጡ አትሌቶች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡
በዝግጅቱ ላይ የወጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ፣ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል፡፡
የፋይዳ ለኢትዮጵያ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጓል።
AMN-Addis Media Network
አንድ ሰው አንድ ነው!
ነገ እሁድ ግንቦት 3/ 2017 በመስቀል አደባባይ እንገናኝ !
ፋይዳ ለኢትዮጵያ !
የአካባቢን ንፅህና በመጠበቅ ከኮሪደር ልማት ስራው ጋር የሚተሳሰር ብሎክ መፍጠር ይገባል" ወይዘሮ ካባ መብራቱ
የአካባቢን ንፅህና በመጠበቅ ከኮሪደር ልማት ስራው ጋር የሚተሳሰር ብሎክ መፍጠር ይገባል ሲሉ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ገለፁ።
በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ ለቡ የ2017 ዓ.ም የወርሃ ክረምት የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በዕለቱም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ መጪው ክረምት በመሆኑ የጎርፍ መውረጃ ቱቦዎች በቆሻሻ እንዳይደፈኑና አደጋ እንዳይፈጥሩ ህብረተሰቡ በተለያዩ የፅዳት የንቅናቄ ስራዎች ላይ ከሚያደርገው ዘመቻ ባሻገር የዕለትተለት ተግባሩ ማድረግ አለበት ብለዋል።
የፅዳት ስራ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ኃላፊነት መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ ካባ የአካባቢን ንፅህና በመጠበቅ ከኮሪደር ልማት ስራው ጋር ማስተሳሰርና ከተማዋን ውብ፣ ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን በሁሉም ብሎኮች ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የከተማዋን ውበት ለማስቀጠል ሁሉም ነዋሪ በአካባቢ ጽዳት ስራ ላይ ሊሳተፍ ይገባል ተባለ።
የአራዳ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በየሳምንቱ የሚያከናውነውን የጽዳት ንቅናቄ መርሀ ግብር በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 "የጽዳት ስራ የሁሉም ማህበረሰብ የዕለት ተዕለት መሆን አለበት" በሚል መሪ ቃል የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለዩ አደረጃጀቶች በተገኙበት በዛሬው እለት አካሄደ፡፡
በጽዳት ስራው ላይ የተሳተፉት የአራዳ ክ/ከተማ ዋና አፈጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘሁ ባደረጉት ንግግር ጽዳት የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን ገልጸው በተለይም ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የክልልና የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ተሞክሮውን ለማስፋት እየጎበኟት የምትገኘውን አዲስ አበባን ውበቷን እንደያዘች ማስቀጠል የሚቻለውና በየእለቱ ሁሉም ነዋሪ አካባቢውን ማጽዳት ሲችል ብለዋል፡፡
ጤናማ ህይወት ለመምራትና ምቹ መኖሪያን ለመፍጠር ቀዳሚ ተግባር መሆን ያለበት የጽዳት ስራ መሆን እንደሚገባው ያስረዱት አቶ ደሳለኝ የከተማ አስተዳደሩ ከሚያከናውነው የኮሪደር ልማት በተጨማሪ በራስ አቅም እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት አካል ተደርጎ የሚወሰድ ተግባር በመሆኑ ነዋሪውንና አደረጃጀቶችን እንዲሁም የግልና የመንግስት ተቋማትን በማቀናጀት ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ ስራውን የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ አቶ እንየው ዘላለም አካባቢያችንን በማጽዳት ወረዳችን ለነዋሪዎቹ ውብና ምቹ እንድትሆን ሁላችን ባህል አድርገን መስራት አለብን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መዉረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም" በሚል መሪ ሃሳብ ሁሉን አቀፍ የክረምት የጽዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር "የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የዉሃ መዉረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም" በሚል መሪ ሃሳብ ሁሉን አቀፍ የክረምት የጽዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዶል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይረክተር ዶ/ር እሼቱ መለስ፣ የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታን ጨምሮ የከተማ፣ የክ/ከተማና ወረዳ አመራሮች፣ አርትስቶች፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም የፅዳት አምባሳደሮች ተሳትፈዋል።
የጽዳት ንቅናቄውን መርኃ-ግብር በይፋ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይረክተር ዶ/ር እሼቱ መለስ ባስተላለፉት መልዕክት አንድ ከተማ ሰልጥናለች ወይም ተወዳደሪ ሆናለች የሚባለዉ ፅዳቷና ውበቷ ስትጠብቅ ነዉ፤ ከተማዋ ሁሉም መሠረተ ልማት ተሟልቶላት ፅዳት ከሌለ ዋጋ የለዉምና ሁላችንም በየአከባቢያችን የፅዳት አምባሰደር መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል።
እንደ ከተማ አስተዳደርም ሆነ እንደ የካ ክፍለ ከተማ በርካታ መሠረተ ልማት ስራዎች ብንሰራም ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ ባለማስወገዳችን ምክንያት የጎርፍ አደጋን ማስወገድ አልቻልንም፣ ይሄንኑ ምክንያት በማድረግ ቀጣይ አምስት ወራት ብሎክን መሠረት ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ የሚካሂድ መሆኑን ዶ/ር እሼቱ አክለዋል።
የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸዉ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት አዲስ አበባ ለሁላችንም የሚትመች ከተማ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል፤ ከነዚህ መካከል ፅዳትና ውበትን ታሳቢ ያደረጉ አንደ ክፍለ ከተማ "የየካን ከፍታ እናረጋግጥ አሻራ እናኑር" በማለት ብሎክን መሠረት ያደረጉ ስራዎች ተሠርተዋል ብለዋል።
በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ በሁሉም ብሎኮች ፅዳት የንቅናቄ ስራ ብቻ ሳይሆን አካባቢን ማፅዳት ባህል እንዲሆን የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎች መሠራቱም አቶ ብርሃኑ አስምረውበታል።
" የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም!! " በሚል መሪ ቃል የክረምት የጽዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደገለጹት ከተማዋ ለሌሎች የሃገሪቱ ከተሞች ምሳሌ እና ውብ የሆነች ከተማ ለማድረግ ሁሉም ነዋሪ በየአካባቢው የፅዳት አምባሳደር በመሆንና በባለቤትነት በመያዝ ተሳትፎውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ነጋሽ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ጽዳትን ዋነኛ ግቡ በማድረግ ከተማዋን ጽዱና ውብ በማድረግ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆንና ቆሻሻን የሚጸየፍ ትውልድ እንዲፈጠር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው 4ኛ ዙር የጽዳት ንቅናቄ ቢጠናቀቅ ክረምቱን ምክንያት በማድረግ ቆሻሻ የሚጥሉ እጆች ሳይሆን ቆሻሻ የሚያነሱ እጆች እስኪፈጠሩ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በበኩላቸዉ በጽዳት ስራ ላይ ለማህበረሰቡ የሚፈጠሩ ግንዛቤዎችን ከሃላፊነት ጋር አጠምሮ መስጠት እንደሚያስፈልግ ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍሻሽ ጋር የተያያዙ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ ብርቱ ጥሪት እንደሚያስፈልግ እና ጽዳት የሁሉም ማህበረሰብ ክፍል ሃላፊነት መሆኑን በዚህ ዙሪያም የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ በአጽኖት ተናግረዋል።
በጽዳት ንቅናቄ ላይ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣የከተማው ፖሊስ ፣የጽዳት አምባሳደሮች ፣የጽዳት ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል ።
ማህበረሰቡ ፅዳት ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ተገንዝቦ አካባቢውን በማፅዳት በመጪው የክረምት ወቅት በቆሻሻ ምክንያት ሊመጣ ከሚችል በሽታ ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ ተገለፀ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የበጋ ወራት የፅዳት ንቅናቄ ማጠቃለያ እንዲሁም የክረምት ወራት የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ ደማቅ ፕሮግራም በወረዳ 09 ልዩ ቦታው መስቀለኛ አካባቢ አካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፃዲቅ ሽኩር፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ፣የወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ከነዓን ገዛኸኝ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ፤ የክፍለ ከተማዉ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ፣የወረዳዉ አመራሮች ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ የሽርክና ማህበራት ፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፃዲቅ ሽኩር በበከሉላቸው ክ/ከተማው ባለው የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ምክንያት ለጎርፍ ተጋላጭ መሆኑንና ይህንንም ለመከላከል ኤጀንሲው ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን በማንሳት ፅዳት በየሳምንቱ በሚደረግ ንቅናቄ ብቻ የሚረጋገጥ ሳይሆን በዕለተ ዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ሊተገበር እንደሚገባና ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚመነጩ ቆሻሻዎችን በአግባቡ ማስወገድና ማስተዳደር እንደሚገባ እንዲሁም የተጀመረውን የፅዳት እንቅስቃሴ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
የመድረኩ ዋና ዓላማ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቅሰው ማህበረሰቡም ሆነ ተቋማት አካባቢያቸውን በአግባቡ በማፅዳትና ቆሻሻን ለይቶ በማስወገድ በክረምት ወቅት ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ከወዲሁ ሊከላከሉ እንደሚገባ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማዉ የወረዳ 09 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ከነዓን ገዛኸኝ በበጋው የፅዳት ንቅናቄ ከማህበረሰቡን በመቀናጀት በርካታ ስራዎችን በመስራት የማህበረሰቡ የፅዳት ባህል ማሳደግ መቻሉን በዚህም በወረዳው የሚገኙ አብዛኛው ብሎኮችን ሞዴልና ፅዱ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው መጪው ጊዜ የክረምት ወቅት እንደመሆኑ የተደፈኑ ትቦዎችን መጥረግ እንዲሁም ለጎርፍና ለመሰል አደጋዎች ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮችን ማፅዳት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ፅዳት ከራስ የሚጀምርና በድምር ሀገር ድረስ የሚሰፋ መሆኑን አንስተው ከተማዋ መንግስት በሰጠው ትኩረት የፅዳት ተምሳሌት እየሆነች እንደምትገኝና ይህንንም ለማስቀጠል ማህበረሰቡ ፅዳት በአንድ አካል ብቻ የሚፈፀም ሳይሆን የሁሉንም እርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት በመጪው የክረምት ወቅት የአካባቢን ፅዳት በመጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የጥንቃቄ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን በተጨማሪም በመልሶ መጠቀም የተሰሩ ቁሳቁሶች ለዕይታ ቀርበዋል።
