ch
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከዚህ በፊት ካዛንችስ ይኖሩ የነበሩ ጎረቤቶቻቸውን በገላን ጉራ በመገኘት ጎብኝተው እንኳን ለትንሳኤ በአል አደረሳችሁ ብለዉ ማእድ አጋርተዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ላደረጉት ጉብኝት እና ማእድ በማጋራታ ለነዋሪዎቻችን ላስተላለፉት የበዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በራሴና በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ:: መልካም በዓል! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የትንሳኤ በዓልን በገላን ጉራ ከሚገኙ የካሳንቺስ ልማት ተነሺዎች ጋር አሳልፈናል። ጎስቋላ የነበረውን ከተማ እንቀይረው ያልነው ለጋራ ጥቅም፣ ለልጆቻችን ደስታ እና መጻኢውን ዘመን ለማሳመር ብቻ ነው። የተለወጠችና ከልመና የወጣች ሃገር እውን ከማድረግ ውጪ ሌላ ሃሳብ የለንም። ይህ አዲሱ ሰፈራችሁ የምትኖሩበት ነው። ቀድሞ የኖራችሁበት ሰፈራችሁን ሄዳችሁ እንድታዩት እጋብዛለሁ። ቃል በገባነው መሰረት ካሳንቺስ እጅግ ውብ ሆኗል። ልጆቻችን ተስፋ አላቸው ፣ ከእኛ የተሻለ ህይወት መኖር ይችላሉ። የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ ነው። እኛም እናያለን፣ ልጆቻችንም ይወርሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ዛሬ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ 25ኛውን እና 26ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከፍተን አገልግሎት አስጀምረናል። ከ2014 ጀምረን በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ለማግኘት ለሚቸገሩ ወገኖቻችን 24 የምገባ ማዕከላትን ከፍተን ንፁህ፣ ጤናማ እና ትኩስ ምግብ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ ወገኖቻችን እየመገብን መሆናችን ይታወቃል። የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለከተማ ጉራራ አካባቢ 25 ኛውን እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ደግሞ 26 ኛውን የምገባ ማዕከል ከፍተን አገልግሎት አስጀምረናል። ዛሬ ያስጀመርናቸዉ እነዚህ የምገባ ማእከላት በተለያዩ የከተማችን አካባቢዎች በመጠለያ ይኖሩ የነበሩ እና ምንም ገቢ የሌላቸዉ አቅመ ደካሞች እና ለተለያዩ ለማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖቻችን ያሉበት አካባቢ በመሆኑ እነሱን ታሳቢ በማድረግ ነዉ ። 25ኛውን የምገባ ማዕከል የገነቡልን እንዲሁም የምገባውን ወጪ የሚሸፍኑልን የአያት አክሲዮን ማህበርን እና የኢፌዴሪ የጉምሩክ ኮሚሽንን በራሴ እና በተጠቃሚዎቹ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ:: ጊዜያዊ ችግሮቻችንን በመረዳዳት እየተሻገርን ለዘላቂ ልማታችን ደግሞ 24/7 በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን። መልካም የትንሳኤ በዓል ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በጾም በጸሎት ያሳለፉ አቅመ ደካሞችን ፣ አካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን በአብሮሆት ቤተመፃፍት አስፈስከናል:: በባህላችን መሰረት ሌሎች በየቤታቸዉ በለሊት ፆም ሲፈቱ እና በዓሉን በድምቀት ሲያከብሩ ጠያቂ የሌላቸው አረጋውያን ፣ የሀገር ባለዉለታዎች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የጾሙን ወቅት በጾም እና በጸሎት አሳልፈው በፍቺው ጊዜ ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ሁሌም የከተማችን አስተዳደር እንደማይዘነጋቸዉ ገልጸን ፆም አስፈትተናል:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ! የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ መላው መዋቅራችን በማስተባበር የትንሳኤን በዓል የከተማችን ነዋሪዎች በደስታና ባማረ ሁኔታ በአብሮነት ያከብሩ ዘንድ ወሳኝ አገልግሎቶችን በአገልጋይነት መንፈስ ለማሟላት የሚያስችሉ ተግባራቶች ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም በቅድመ አደጋ መከላከል፣ በከተማ ጽዳት፣ውበት እና መሰል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎቻችን በትንሳኤ ዋዜማም ሆነ የበአሉ እለት ጭምር በስራ ስምሪት እንደሚያሳልፉ እየገለፅኩ በድጋሚ በዓሉ፣ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን በድጋሚ ለመግለፅ እወዳለሁ! ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!! የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከሃጢያት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል ነው። እኛም እየሱስ ክርስቶስን በተምሳሌትነት በመከተል እርስ በርስ በመፋቀር፣ በመተሳሰብ፣ በይቅርታና ምህረት በማድረግ ከሰዉ ልጆች ጋር ሁሉ በሰላም እንድንኖር እሱ ይርዳን። በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመተሳሰብ፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን። በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፤ ትንሣኤ የመሥዋዕትነት፣ የጽናት እና የተስፋ በዓል ነው። የበደለው ዓለም ነው። የተሠዋው ግን ክርስቶስ ነው። ያጠፋው የሰው ልጅ ነው፣ የካሠው ግን ክርስቶስ ነው። ባለ ዕዳው ሰው ነው። ከፋዩ ግን ክርስቶስ ነው። የክርስቶስ ሞት አንድም ለማዳን ነው፤ አንድም ለትምህርት ነው። ስለ ብዙዎች ሲባል መሥዋዕትነት ካልተከፈለ ብዙዎችን ማዳን አይቻልም። ሀገርን፣ ሕዝብን፣ ወገንን ማዳን ከተፈለገ መሥዋዕትነት መክፈል ይገባል። ቃል ክርስቶስ በቃሉ ብቻ አልተናገረም። በመስቀል ላይ ውሎ ፍቅሩን በተግባር ገለጠው እንጂ። ራሱ አስታራቂ፣ ራሱ ታራቂ፣ ራሱም መሥዋዕት ሆነ። ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ መሥዋዕት ለመሆን የተዘጋጀ መሆን አለበት። በሌሎች መሥዋዕትነት መጓዝ የኦሪት ሰዎችም አድርገውታል። ሺ በጎችንና ሺ ፍየሎችን ሠውተው ነበረ። አልሆነም እንጂ። ሀገርን ማዳን የሚቻለው ሌሎችን በመሠዋት አይደለም። ራስን በመሠዋት እንጂ። የራስን ጉልበት፣ ጊዜ እና ዕውቀት በመሠዋት እንጂ። የራስን ክብርና ኢጎ በመሠዋት እንጂ። ሀገርን ለማዳን ወደ ትኅትና፣ ወደ ዕርቅ እና ወደ ምክክር መስቀል አውርዶ ራስን መሠዋት ያስፈልጋል። መስቀል መከራ ነው፤ ስድብ ነው፤ ግርፋት ነው፤ ውርደት ነው። ራሳችንን ለሰላምና ለዕርቅ መንገድ ስናዘጋጅ ከብዙዎች ዘንድ ስድብ፣ ርግማን፣ መከራ፣ ይጠብቀናል። የሚያዋጣን ግን ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የኢትዮጵያን መስቀል መሸከም ነው። ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ስንል መስቀሏን መሸከም። ትንሣኤ ከጽናት በኋላ የሚገኝ ድል ነው። ከፊቱ የጅምላ ፍርድ አለው፤ ከፊቱ ውግዘት አለው፤ ከፊቱ ግርፋት አለው፤ ከፊቱ መራቆት አለው፤ ከፊቱ መከዳት አለው፤ ከፊቱ የፀሐይ መጨለም፣ የጨረቃ ደም መልበስ፣ የከዋክብትም መርገፍ አለው። በዚህ ሁሉ ግን በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ክርስቶስ በጽናት ቆመ። ስለ ዓላማ ሲባል መከራን ታገሠ። ስለ ሰው ልጅ ሲባል ሁሉን እየቻለ በጽናት ተጓዘ። ሀገር ጽናት ትፈልጋለች። በመከራዎች እና በውግዘቶች ፊት በጽናት መቆም። በስድብና በንቀት ፊት በጽናት መቆም። እንደ ፀሐይ የሚታዩት ልሂቃን ሲጠፉ፣ እንደ ከዋክብት የሚታዩት ክቡራን ሲረግፉ በጽናት መቆም። አብረው የነበሩ ፈርተውና ተሽጠው ሲከዱ በጽናት መቆም - ሀገር ትፈልጋለች። በሚጸኑት ዘንድ የኢትዮጵያ ትንሣኤ እጅግ ቅርብ ብቻ አይደለም። የሚታይም ነው። ትንሣኤ ተስፋ ነው። ፈተናው እንደሚያልፍ ተስፋ ይሰጣል። ዓርብን ላየ እሑድ የሚመጣ አይመስልም ነበር። የመቃብሩን ድንጋይ ላየ የሚነሣ አይመስልም ነበር። ማኅተሙን ላየ የሚፈታ አይመስልም ነበር። ጨለማውን ላየ ብርሃን ሩቅ ይመስል ነበር። ሁሉም ግን ተገለበጠ። ታሪክን የታሪኩ ጌታ ለወጠው። ተስፋችን በደጅ ነው። ዓርብ ላይ እሑድን እናየዋለን። ከሞት ባሻገር ሕይወትን፣ ከመቃብር አልፈንም ትንሣኤን የምንመለከት ነን። የሚጨበጥ ሕልም የጠራ ምናብ አለን። ስለዚህም ወጀብና አውሎ ነፋስ አያስደንቀንም። ዛሬ ለነገ፣ ሞት ለትንሣኤ ቦታ እንደሚለቁ የምናውቅም፣ የምናምንም ነን። ለኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚተጉ ብዙዎች ናቸው። የሕማማቱ ጊዜ እያለፈ ነው። አሁን ዓርብ ወደ ማታ ላይ ነን። ከጸጥታው ቀን በኋላ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይመጣል። ከሄዱት ብዙዎች ይመለሳሉ። ከተሳሳቱት ብዙዎች ያስተውላሉ። ዓርብ ዕለት በከንቱ የጮኹት ብዙዎች ያፍራሉ። ፈራጆች ይፀፀታሉ። ተገዳዳሪዎች ይበታተናሉ። የመቃብር ጠባቂዎች ይደነግጣሉ። ኢትዮጵያ ግን አይቀሬ በሆነው ትንሣኤ ትነሣለች። ትንሣኤው ከእሥራኤል ለዓለም እንደተገለጠው ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ለዓለም ትገለጣለች። የትንሣኤ በዓል የሚያስተምረንም ይሄንኑ ነው። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

በበአላት ወቅት ጥንቃቄ አይለየን! በመዲናችን አዲስ አበባ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከትንሳኤ በአል አከባበር ጋር ተያይዞ አደጋን ለመከላከል የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎቻችን ሙሉ ዝግጁነትን ተላብሰው በየቅርንጫፍ ጣቢያዎቻችን 24/ 7 የአገልጋይነት ዲስፕሊን ተላብሰው በበአል ዋዜማውም ሆነ የበአሉ ቀን በተጠንቀቅ(Standby) የሚያገለግሉ ይሆናል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በመዲናችን ለእሳት አደጋን ለመከላከል የተደረገውን ዝግጁነት በስፍራው ተገኝቶ ያዘጋጀውን ዘገባ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግም፣ ዛሬ ጠዋት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው አሳዳጊ የሌላቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።