1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የምሽት አይናችን በርቷል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
ከኢየሱስ 41- ሚካኤል ማዞሪያ - ኳስ ሜዳ ያለውን የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራት ተጠግኖ ለአገልግሎት በማብቃቱ ጥያቄያችን ምላሽ አግኝቷል፤ የምሽት አይናችን በርቷል ሲሊ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን መ/ቤት መንገዱ ጨለማ በመሆኑ ነዋሪዎች ለአውሬ ጥቃት፣ ለወንጀል ድርጊትና በሰላም ወጥቶ ለመግባት የነበረውን ችግር ለመፍታት ነባሩን መብራት በመጠገን፣ አዲስ ቆጣሪ በማስገባትና ኤል.ኢ.ዲ አምፖሎችን በመግጠም አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል፡፡
ስራውን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው አቶ ረዳኢ መሀሪ ነዋሪና የወረዳው ምክር ቤት አባል መሆናቸውን ነግረውን ቀደም ብሎ መንገዶቹ ላይ ብርሀን ባለመኖሩ በሰላም ወጥቶ መግባት ከባድ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ መብራቱ በመጠገኑ አካባቢው በብርሀን ተሞልቷል፤ ያለምንም ስጋትና ፍርሀት በፈለግነው ሰዓት በሰላም ወጥተን መግባት ችለናል ብለዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የሚፈፀም ወንጀልን ቀድመን ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ መከላከል አስችሎናል ብለዋል፡፡
ሌላኛው ያነጋገርናቸው አቶ ሰለሞን ከምሲ ሴቶች ሲመሽ ወደ ቤታቸው ለመመለስ አዋቂ ወንዶች ከመንገድ ወጥተው ካልተቀበሏቸው በሰላም ወጥተው መግባት አይችሉም ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ወንጀልን ለመከላከል ቀደም ብሎ የተተከለው የሲሲቲቪ ካሜራ በመንገዱ ላይ ብርሀን ባለመኖሩ ምክንያት አገልግሎት ለመስጠት ተቸግረው እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ አካባቢው በብርሀን በመሞላቱ ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከልና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥበቃ ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ተናግረዋል፡፡
ሌላኛው በኳስ ሜዳ የፓርኪንግ ስራ ላይ ያገኘናቸው አቶ ታሪኩ በቀለ የመንገድ መብራቱ ባለመኖሩ እስከ መኪና መሰረቅ ወንጀል የተፈፀመበት፤ ለአውሬ የመበላትና በሰላም ወጥቶ ለመግባት ከፍተኛ ችግር አጋጥሞ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ የምሽት አይናችን በርቷል፤ የነበረው ችግር በመቀረፉ በፈለግነው ሰዓት በሰላም ወጥተን መግባት ብሎም አዳር የመኪና ጥበቃ ስራን ያለ ምንም ችግር እንድናከናውን ረድቶናል ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የጎርፍ አደጋን መከላከል ታሳቢ ያደረገ ግንባታን እንዴት እንገነባለን? በሚል ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን "ዉሀ ልክ " በተሰኘው ኘሮግራሙ በእይታ መሰናዶ ላይ በምክ…
See more
በተለወጠ አስተሳሰብ እና የስራ ባህል የማያቋርጥ ለዉጥና ስኬት ቀጥሏል
Ilaalchaa fi aadaa hojii jijjiirameen jijjiiramaa fi milkaa'inni adda hin cinne itti fufeera.
See less
የፋይዳ ለኢትዮጵያ 2ኛው CRRSA CUP የእግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ
ፋይዳ ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የነበረው 2ኛው CRRSA CUP የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሲያካሂደው የነበረው የእግር ኳስ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከልደት እስከ ሞት የሚከሰቱ ኩነቶችን በመመዝገብ ከፍተኛ ስራ እያከናወነ ነው ያሉ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘውን የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ በከተማ ደረጃ ያልተመዘገበ እና የማይታወቅ ዜጋ እንዳይኖር ኤጀንሲው በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ኤጀንሲው ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ከግንቦት 2017 ጀምሮ በ12 ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የነበረው የእግር ኳስ ውድድር በበኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
ካዛንችስ በሚገኘው እና የስፖርት ማዘውተሪያ በሆነው 28 ሜዳ በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ በበኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አራዳ ክፍለ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል፡፡
በፋይዳ ለኢትዮጵያ 2ኛው የCRRSA CUP እግር ኳስ የፍፃሜ ውድድር ላይ የቀድሞው የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፣ የብሔራዊ መታወቂያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች፣የክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የጨዋታው ኮኮብ ግብ አግቢ፣ኮኮብ ግብ ጠባቂ እና ምርጥ ተጫዋቾች በመርሃ ግብሩ ከተገኙትት የክብር እንግዶች እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !
ዛሬም ሌላኛው ብስራታችን የሆነውን ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን-ጎሮ-ቦሌ አየር መንገድ ቪአይፒ ተርሚናል ኮሪደር አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
የሁል ጊዜ ህልማችን እውን የሚሆነው በየእለቱ፣ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው ያለዕረፍት በመስራታችን እና በፈጣሪ እርዳታ ነው።
በ2ኛ ዙር ከጀመርናቸዉ ስምንቱ ኮሪደሮች አንዱ እና ከተጠናቁት ደግሞ 4ኛዉ ሲሆን አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማእከልን ከቦሌ ኤርፖርት ቪአይፒ ተርሚናል የሚያገናኝ፣ ከአንበሳ ጋራዥ - ጃክሮስ ጐሮ እና በኮሪደር አንድ ከተሰራው ቦሌ ኤርፖርት መገናኛ ሲኤምሲ ጋር የሚገጥም ነው።
የኮሪደሩ አጠቃላይ ስፋት ከ290 ሄክታር በላይ ሲሆን 12.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዲሁም 29.446 ኪሜ የሚረዝም የእግረኛ መንገድ ያለው ነው።
በተጨማሪም 15.27 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤ ከ550 በላይ ታክሲና ባሶችን የመያዝ አቅም ያላቸው 5 የባስና የታክሲ ተርሚናሎች፤ ከ800 በላይ መኪኖችን የመያዝ አቅም ያላቸው 4 ፓርኪንግን ጨምሮ ታክሲና ባስ መጫኛና ማውረጃ 17 ቤይ ተሰርቶለታል።
ዛሬ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ያደረግነው ይህ ኮሪደር 5 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት እና 2 ድልድዮች እንዲሁም 12 ኪ.ሜ የጎርፍ መውረጃ ቱቦ ዝርጋታን ጨምሮ 3.6 ኪ.ሜ የመጠጥ ውሃ ዝርጋታ እና 669 የመንገድ ዳር መብራቶች ተሰርቶለታል።
ትላልቅና መካከለኛ ካፌዎች ፤ 41 መጸዳጃ ቤቶች ፤ 9 የህጻናት መጫወቻ ቦታዎች እና 7 የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎችን ጭምሮ 4 ፕላዛዎች እና 130 ሄክታር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማትንም አካቷል።
ይህ የኮሪደር ልማት እንደ ሌሎቹ ኮሪደሮች ሁሉ ለነዋሪዎቻችን ሰፊ የስራ እድል የፈጠረ፣ ፅዱ፣ አረንጓዴ እና ምቹ የመኖሪያ አካባቢ የፈጠረ፣ አካታች እና ሁሉንም ሰዉ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ከ320 በላይ ህንፃዎች እድሳት በማድረግ እና ከ350 በላይ የንግድ ሱቆች በመክፈት የንግድ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ያደረገ፣ የመንገድ መጨናነቅን ችግር በመፍታት የትራንስፓርት ፍሰቱን የሚያቀላጥፍ እና የተለያዩ የአገለግሎት መስጫዎችን ያሻሻለ ውጤታማ ስራ ነው።
ይህ ኮሪደር በታለመለት ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቅ ደከመን ሰለቸን ሳትሉ ለተሳተፋችሁ ባለሞያዎች፤ አመራሮች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አጠቃላዩ የኮሪደር ልማት አሠራር ለመጪው ጊዜ ታላቅ ተስፋ የሚሰጠን ነው። በመጀመሪያው ምዕራፍ በአራት ኮሪደሮች ጀምረን በሁለተኛው ምዕራፍ በስምንት ኮሪደሮች ቀጥለናል። የተጠናቀቀውን እና 12.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ከአዲስ ኮንቬንሽን መዐከል-ጎሮ-ቪአይፒ ኤርፖርት ኮሪደር ዛሬ ተመልክተናል። በኮሪደሩ 29 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ እና 15.27 ኪሎሜትር የብስክሌት መጋለቢያ ተሰርቷል።
ይኽ የኮሪደር ሥራ ሰፋፊ የተሽከርካሪ መንገዶችን፣ ከጎሮ እስከ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ መንገድ እንዲሁም በአካባቢው ሰፊ የወንዝ ልማትን ያካተተ ነው። ሰባት የስፖርት ማዕከላት፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና አውቶቡስ መናኸሪያዎች፣ ካፌዎች፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች የተካተቱበት ነው። እነኚህ ግንባታዎች ሥራ ፈጥረዋል፣ መገናኛ እና መዳረሻዎችን አስፋፍተዋል፣ የከተማዋን መሠረተ ልማት አጠናክረዋል።
በሁሉም መስክ ኢትዮጵያ መበርታቷን ቀጥላለች። ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ አይደናቀፍም። አይቆምም። የእነኚህ ሥራዎች ስኬት ይኽንን ያስቻለውን የተለወጠ ርዕይ እና የሥራ ባሕል ያንፀባርቃል። እስከአሁን የከተማዋ ግማሽ ያህል የተለወጠ ሲሆን የበለጠ ለማሻሻል የምንተጋባቸው ከባቢዎች አሁንም ይቀራሉ።
ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ ር አቢይ አህመድ
በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ የሪፎርም ተግባር በአራቱ የከተማዋ ሪጅን ቢሮዎች ያመጣው ለውጥና ያስገኘው ውጤት የመስክ ምልከታን AMN-Addis Media Network ይከታተሉ
የኮሪደር ልማት በመዲናዋ የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስና የተሳለጠ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 24/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በተለያየ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስና የተሳለጠ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ለመስጠት ማስቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡
በመዲናዋ በሁለት ዙር የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች የእሳት፣ የትራፊክ፣ የጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተትና መሰል አደጋዎች እንዲቀንሱ አስችሏል፡፡
ለሰው ህይወት መጥፋት እና ለንብረት ውድመት መንስዔ የነበሩት እነዚህ አደጋዎች አሁን ላይ በከፍተኛ መጠን ቀንሰዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማቶቹ አዲስ አበባን ጽዱና ማራኪ ከማድረግ ባሻገር ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በእጅጉ እንዲቀንሱ አስችለዋል፡፡
የብስክሌት፣ የሰው እና የመኪና መንገዶች ተለይተው በመሰራታቸው በሰው እና በንብረት ላይ ይከሰት የነበረውን የትራፊክ አደጋ በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ ማስቻላቸውንም አመላክተዋል፡፡
አዳዲስ መንገዶቹ የእሳት አደጋ ቢፈጠር በፍጥነት በመድረስ አደጋውን ለመቆጣጠር እያስቻሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በመብራት መሰረተ ልማቶች የተከናወኑ የማሻሻያና አዳዲስ ስራዎች ከዚህ በፊት ይገጥም የነበረውን የሃይል መቆራረጥ በእጅጉ ለመቀነስ አግዘዋል፡፡
በወንዝ ዳርቻ ልማት ለመኖር ይቅርና ለማለፍ እጅግ አስቸጋሪ የነበሩ አካባቢዎች አሁን ላይ ወደ መዝናኛነት መቀየራቸውን አመላክተዋል፡፡
ልማቱ በወንዞች አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ ወገኖችን ህይወት ከአደጋ ከመታደጉ ባሻገር በተሰሩ የልማት ስራዎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በመሆን ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ማስቻሉን አስረድተዋል፡፡
የፍሳሽ ማስወገጃ ባልነበራቸው አካባቢዎች ላይ መሰረተ ልማቶች በአዲስ መልክ እንዲሰሩ ማድረግ መቻሉ ሌላኛው የኮሪደር ልማቱ ትሩፋት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በመዲናዋ የተከናወኑ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች ከዚህ በፊት በመዲናዋ ይከሰቱ የነበሩ ልዩ ልዩ አደጋዎችን ለመቀነስና የተሳለጠ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለመስጠት ማስቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ስራ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
#Ethiopia
#ኢትዮጵያ
በኮልፌ ክፍለ ከተማ ማህበረሰቡን በማስተባበር የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮች ተግባራዊ በማድረግ ለህብረተሰቡ ምቹ የመኖሪያ አከባቢ መፍጠር መቻሉን ተገለፀ።
ክፍለ ከተማው በ90 ቀናት ውስጥ ለማከናወን በዕቅድ ከተያዙት ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን የመፍጠር ስራ ያለበትን የአፈፃፀም ደረጃ ለመመልከት የክፍለ ከተማው ዋና አመራሮች፣ የማዘጋጃ ቤታዊ እና የክረምት የበጎ ፍቃድ ግብረ ሃይል አባላት በተገኙበት በጋራ በወረዳ 06 እና 07 አስተዳደር የተሰሩ ስራዎች ምልከታ ተካሄደዋል ።
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚ ሙሄ ዓሊ የመስክ ምልከታውን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት በክፍለ ከተማው ውጤታማና የተቀናጀ የሞዴል ብሎኮች መፈጠራቸውን በማስታወስ የተፈጠሩ ሞዴል ብሎኮች ለህብረተሰቡ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር የሰላም ሁኔታን በተሻለ ሁኔታ በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ሀላፊው ጨምረውም ማህበረሰቡን በማስተባበር አካባቢውን ከማልማት አንፃር እያደረገው ያለው አስተዋፅኦ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል።
በመስክ ምልከታው የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን ከመፍጠር አንፃር የተከናወኑ ስራዎች፣ ፅዳና ውብ አከባቢን ከመፍጠር አኳያ፣የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራሞች አፈፃፀም እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የኮሪደር ስራዎች ማለትም ስታንዳርዳይዜሽን የማስጠበቅ ስራዎች፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የመብራት ማስበራት፣ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ የተሟላ የህፃናት መጫወቻና ሌሎች ስራዎች ምልከታ ተደርጎባቸዋል ።
Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
