ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

前往频道在 Telegram
1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
የየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አመራሮች እና የቋሚ ኮሚቴ አባላት በክፍለ ከተማው ከ2013 እስከ 2016 ዓ.ም ተምሳሌት የሆኑ ብሎኮችን ተዘዋውረው ጎበኙ በየካ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት አመራሮች እና የቋሚ ኮሚቴ አባላት በህብረተሰብና በባለሀብት ተሳትፎ ከ2013 እስከ 2016 ዓ.ም ተምሳሌት የሆኑ ብሎኮችን እና ተቋማትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ፣ 5 ፣ 9 ፣ 11 እና 12 ውስጥ የሚገኙ ተምሳሌት ብሎኮች ፣ የመንገድ አካፋይ ፣የኮምፖስ ስራ ማህበራት የጉብኝቱ አካላት ሲሆኑ የፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ህብረተሰቡን እና ባለሀብቱን በማስተባበር ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ብሎኮቹን ሞዴል ማድረግ መቻሉ ተገልጿል። ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደው ውይይት ላይ የምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንደገለፁት የአዩት ነገር የስራ ተነሳሽነት ካለ እና አቅምን አሟጦ መጠቀም ከተቻለ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮችን ማድረግ እንደሚቻል አመላካች መሆኑን በመግለፅ አመራሩ ለስራው ለሰጠው ትኩረት እና ለተሰራው ነዋሪውን የሚጠቅም ውጤታማ ስራ ምስጋና አቅርበዋል። በጉብኝቱ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አመራሮች እና የቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣ ዘርፉ የሚመለከታቸው የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ከ2013 እስከ 2016 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ስር ከሚገኙ 407 ብሎኮች 357ቱ ሙሉ በሙሉ ተምሳሌት ማድረግ መቻሉን እና ቀሪ ብሎኮችን ተምሳሌት የማድረግ ስራ በሒደት ላይ መሆኑን የክፍለ ከተማው ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተሾመ ገልፀዋል። ለበለጠ መረጃ

የኮሚሽን መ/ቤቱን አገልግሎቶች ለማዘመን የተጀመሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች የደረሱበት ደረጃ ተገመገመ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ኮሚሽን መ/ቤቱ የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ለማዘመን እንዲያስችለዉ የተጀመሩ የፕሮጀክት ስራዎች አሁን የደረሱበት ደረጃ አስመልክቶ የከተማዉ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለሞያዎች በተገኙበት ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ተገምግሟል። በግምገማ መድረኩ ላይ የፕሮጀክት ስራዉን ዉል ገብቶ እያከናወነ ያለዉ በኢትዮ ቴሌኮም መ/ቤት በኩል የፕሮጀክት ስራዉ አሁን ያለበት ደረጃ ሪፖርት አቅርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል። በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ በግምገማ መድረኩ እንደተናገሩት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የቀረበዉ ሪፖርት መሻሻሎች ያሳዩ ቢሆንም ኢትዮ ቴሌኮም ካለዉ አቅምና በሌሎች ሀገራዊ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ካለዉ ጠንካራ አፈጻጸም አንጻር የተሻለ አፈጻጸም የሚጠበቅ በመሆኑ በዚህ ፕሮጀክት ላይ የታዩ መዘግየቶች ተሻሽለዉ የተጀመሩ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል። በተያያዘም የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ልማት ቢሮ እና የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች በከኩላቸዉ በሰጡት አስተያየት የፕሮጀክት አፈጻጸሙ መሻሻሎች ያሳዩ ቢሆንም ስራዉ መጠናቀቅ ካለበት ጊዜ አንጻር መዘግየቱን ገልጸዉ ቀሪ ስራዎች ባሉት ጥቂት ጊዚያት እንዲጠናቀቁም ጠይቀዋል። በግምገማ መድረኩ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በአዲስ አበባ ኢንቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በኩል አቶ የማነ ደሳለኝ እና አቶ ምህረቱ ደሳለኝ እንዲሁም የኮሚሽኑ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር አሸናፊ ቶላ ተገኝተዋል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከጀመራቸዉ የለዉጥ ስራዎች መካከል የቴክኖሎጂ ዘርፍ አንዱ በዘርፉ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ለዉጦች ማስመዝገባቸዉም ተመላክቷል።

ፅዱና ማራኪ ከተማ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው-ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን AMN-ግንቦት 7/2016 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የግንዛቤና የህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎችን ያሳተፈ የማነቃቂያ መድረክ አካሂዷል። በንቅናቄ መድረኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን፣ የሀይማኖት አባቶችና የፅዳት አምባሳደሮች ተገኝተዋል። በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን፤ፅዱና ማራኪ ከተማ ለመፍጠር ከተማ አስተዳደሩ ሳይንሳዊ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በመከተሉ ዉጤት እየተገኘ ስለመሆኑ አንስተዋል። ለዚህም የህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል። ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የከተማዋን ፅዳት በሚፈለገው ደረጃ ማስጠበቅ አለመቻሉን ያነሱት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ ናቸው። የከተማዋን ውበት በማስጠበቅ ሂደት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች ዉጤት እያስገኙ ነዉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎችም በየአካባቢዉ የሚያካሂዱትን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። በማነቃቂያ መድረኩ ላይ የህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎች የሚለብሱት የደንብ ልብስም ተዋዉቋል። በትዕግስት መንግስቱ #Addisababa #Ethiopia ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

አገልግሎት የሰጡ የፕላስቲክ ቁሶችን በአግባቡ በማስወገድ፣ አካባቢያችንን ከብክለትና ከጎርፍ አደጋ ስጋት እንከላከል! በየዓመቱ የበልግ እና የክረምት ዝናብን ተከትሎ በመዲናችን ከሚስተዋሉ ክስተቶች መካከል የጎርፍ አደጋ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእርግጥ ዝናብ ተፈጥሯዊ የአየር ንብረት አካል በመሆኑ ማስቆም አይቻልም፡፡ ከዝናብ መጠንና ስርጭት ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለው የጎርፍ አደጋም፣ በተፈጥሯዊ የአየር ንብረት ዑደት ውስጥ የሚታይ ክስተት በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ለመከላከል አዳጋች ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ በከተማችን ውስጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የጎርፍ አደጋ ከፍ ብሎ ከተጠቀሰው መሠረተ-ሃሳብ በተቃራኒ፣ እኛው ራሳችን በምንፈጥረው ያልተገባ ድርጊት ሳቢያ የሚፈጠር ሰው ሰራሽ ችግር ስለመሆኑ የተለያዩ ማሳያዎችን በማንሳት ማሳየት ይቻላል፡፡ ለአካባቢ ብክለትም ሆነ ለጎርፍ አደጋ መከሰት አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደሩ ከሚገኙ አማጭ ምክንያቶች መካከል በዘፈቀደና በግዴለሽነት፣ በመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮችና ድልድዮች አካባቢ የምንጥላቸው ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ቁሶች ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይም እሽግ ውሃ የሚቀርብባቸው የፕላስቲክ ኮዳዎች እና የእቃ መያዣ ፌስታሎች በቀላሉ የማይበሰብሱናባሉበት ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ በመሆኑ፤ የድሬኔጅ መስመሮች እንዲደፈኑ እና የዝናብ ውሃ ወደ መንገድ ገንፍሎ ለጉዳት እንዲዳርግና የከተማችን ገፅታ እንዲበላሽ ከማድረጋቸውም በላይ፣ ክቡር በሆነው የሰው ልጅ አካልና ህይወት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደርጋሉ፡፡ ስለሆነም የፕላስቲክ ቁሶችን ከተጠቀምን በኋላ በኃላፊነትና በአግባቡ በማስወገድ፤ አካባቢያችንን ከብክለት፣ ህይወትና ንብረታችንን ከጎርፍ አደጋ ስጋት እንከላከል! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et Boost this post to reach up to 12809 more people if you spend $10.

ዋርካ | በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተደረገ የህዝብ የውይይት መድረክ ክፍል 2 ዛሬ ምሽት 2፡30 ይጠብቁን! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - ግንቦት 7/2016 ዓ.ም

በጽዳት መስክ የመጣውን ለውጥ በጠንካራ መሠረት ላይ ለማነጽና በዘላቂነት ለማስቀጠል ሞዴል የሆኑ ጽዱ ብሎኮችና ወረዳዎች የመፍጠሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በም/ከንቲባ ማእረግ የከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን አስገነዘቡ። ክብርት ሂክማ ከይረዲን ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው እለት ከ2ሺህ በላይ ለሚሆኑ የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎች በተካሄደው የደንብ ልብስ ይፋ ማድረጊያና የአቅም ግንባታ ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ ነው። አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹና ጽዱ ከተማ ለማድረግ ሰፊ ስራ መሰራቱንና በዚህም የላቀ ዉጤት መመዝገቡን አመልክተው መዲናችን የአፍሪካ ተምሳሌነቷን እንዲሁም አለም ዓቀፋዊ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን በሚመጥን ደረጃ ጽዱ እና ውብ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል። ከዚሁ ጎን ለጎን የከተማችን ጽዳት በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት በተገቢው ካለመወጣት በመነጨ ደረቅም ይሁን ፍሳሽ ቆሻሻን በዘፈቀደ በየጎዳናውና በየአካባቢው በማስወገድ በሚያቆሽሹ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ላይ አስተዳደሩ መውሰድ የጀመረውን ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም በአፅንኦት ገልፀዋል። ክብርት ወ/ሮ ሂክማ አክለውም የግንዛቤ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ባለሙያዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በ" ጽዱ ጎዳና " "ኑሮ በጤና " ኢኒሼቲብ የከተማችን ነዋሪዎች በብሎኮች፣ በወረዳዎችና እስከ ክፍለ ከተሞች ተገቢውን ግንዛቤ በመፍጠር በየደረጃው ሞዴል እንዲሆኑ ማድረግና ደረጃ በደረጃም ሙሉ ከተማዋን ውብና ጽዱ የማድረግ ሂደት ላይ ከፍተኛውን ድርሻ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.go

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን በጋራ ለመስራት በሚያሰችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አካሄዱ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት እና የኢትዮጵያ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን በቅድመ አደጋና በድህረ አደጋ ጊዜ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ዉይይት የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም አካሂደዋል ። በዉይይቱ መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራዉ ተ/ማርያም እንዳስታወቁት ኮሚሽን መ/ቤታቸዉ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋም ከሆነዉ ከአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በቅድመ አደጋ እና በድህረ አደጋ ወቅት በጋራ ለመስራት እንዳቀዱ ጠቅሰዉ በተለይም የኮሚሽኑን ማስልጠኛ ማዕከል ለማዘመንና ለማደራጀት ከፍተኛ በጀት መመደባቸዉን አስታዉቀዋል። በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ የሰዎችን ህይወትና ንብረት ከአደጋ ለመጠበቅ እያደረገ ያለዉን ጥረት ለመደገፍ በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል እየተደረገ ያለዉን ጥረት አድንቀዉ ቀሪ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዉ በፍጥነት ወደተግባር እንዲገባም አሳስበዋል። በተቋማቱ ስምምነት የተደረሰባቸዉን ተግባራት የማስፈጸሚያ ሰነድ የሚያዘጋጁ ቴክኒካል ኮሚቴዎች ከተቋማቱ የተወከሉ ሲሆን ሰነዱ አስከ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቆ የፊርማ ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድም ተገልጿል። የሰነድ ዝግጅቱና አተገባበሩ ላይ ከሁለቱ ተቋማት በተጨማሪ የሸገር ከተማ አስተዳደርም የስምምነቱ አካል እንደሆነም ተመላክቷል። በዉይይቱ መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ነሲቡ ያሲን፣ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ እንዲሁም በኮሚሽኑ የማስልጠኛ ማዕከል ኃላፊ ኮማንደር አለማየሁ ጦፉ ተገኝተዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!

በከተማዋ ጽዳት ላይ ያተኮረ የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ ተሰጠ። የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በመዲናችን ባሉ ሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በተመረጡ ወረዳዎች ያለውን የፅዳት ሁኔታ አስመልክቶ ያካሄደውን የመስክ ምልከታ ውጤት መሠረት ያደረገ ግብረ መልስ ላይ ያተኮረ ውይይት ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች ጋር በዛሬው እለት ተካሄደ። በጽ/ቤቱ ያለፉት 9 ወራት የተጠሪ ተቋማት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከተካሄደ በሗላ በከተማው ጽዳት ረገድ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና የተመረጡ ወረዳዎች የተከናወኑ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ የተቋሙን አመራሮች ባካተተ ቡድን የተካሄደው የመስክ ምልከታና ሱፐፐርቪዥን የተደገፈ ግብረ መልስ ለኤጀንሲው ተሰጥቷል። በዚህ መነሻነት በተካሄደ ዉይይት ላይ በመስክ ምልከታውም ወቅት በፅዳት ሞዴል ብሎኮች፤ የጽዳት ሞዴል ወረዳዎች፣የጽዳት ማህበራት፤ በመልሶ መጠቀም፣ኮምፖስት ስራዎች እና የቅብብሎሽ ጣቢያዎች በጥንካሬና በክፍተት የታዩ በሪፖርት ተካቶ ቀርቧል። በዚሁ ወቅት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ መጎልበት እንደሚገባቸው ጠቁመው ክፍተት የታየባቸዉን ደግሞ ኤጀንሲው በየክ/ከተሞችና በወረዳዎች ላለው መዋቅር በአፋጣኝ ግብረመልሱን በመስጠት በፍጥነት ማረም እንደሚገባ ጠቁመዋል። የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ጽ/ቤቱ ያካሄደው ክትትልና ድጋፍ አስተማሪ የሆነና ለኤጀንሲውም ቀጣይ ስራዎች ጉልበትና ጥንካሬ የሚሆን ነው ሲሉ አድንቀው በጽዳት ረገድ የሚታይ ህገወጥነትን ከመከላከል ጋር በተያያዘ ፣ ከጊዜያው የቅብብሎሽ ጣቢያና ከፍሳሽ ቆሻሻ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ቅንጅታዊ ስራን የሚጠይቁ በመሆኑ በዚህ ረገድ ጽ/ ቤቱ ቀጣይ እገዛ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ለ #ጽዱኢትዮጵያ ስራችን ሃምሳ ሚሊዮን ብር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልናዋጣ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር ከ154 ሚ
+1
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ለ #ጽዱኢትዮጵያ ስራችን ሃምሳ ሚሊዮን ብር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልናዋጣ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊዮን ብር በላይ ማዋጣት ችለናል። ኢትዮጵያን ሲያኮሩ የኖሩ አትሌቶች፣ ስፖርተኞች እና ደጋፊዎች፣ የዘወትር አገልጋይ የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ለኅሊናም ለአካባቢም ንፅህና የሚቀኙ ከያንያን፣ ምሁራን፣ ባለሃብቶች በቴሌቶኑ ስፍራ በመገኘት ላደረጉት አስተዋጽዎ እነሆ ምስጋና። በመላው አለም ሆነው በዛሬዋ ጀምበር በዲጂታል ቴሌቶኑ የተሳተፉ ከአርባ ሺህ በላይ ዜጎች ለፅዱ ኢትዮጵያ ያላቸው ምኞት መግለጫ የሆነው አስተዋፅዖ በተግባር በየአካባቢው በሚገነቡ የሕዝብ መፀዳጃዎች ይታወሳል። ይህ ትውልድ ጀምበር ወጥታ በገባች ቁጥር ለመጪው ትውልድ መስፈንጠሪያ የሚሆን ብሩህ እና ፅኑ መሰረት ደልድሎ ያወርሳል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ ር አቢይ አህመድ አሊ

በአዲስ አበባ ከተማ #ጽዱኢትዮጵያ የአንድ ጀንበር 50 ሚሊዮን ቴሌቶን በአጠቃላይ 46.34 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጏል:: በዚህም መሰረት:- - የመዲናችን ህዝብ ተሳትፎ 1. ቦሌ - 7 ሚሊዮን ብር 2. ቂርቆስ - 3.3 ሚሊዮን ብር 3. ንፋስስልክ ላፍቶ - 2 ሚሊዮን ብር 4. አዲስ ከተማ - 2.6 ሚሊዮን ብር 5. አቃቂቃሊቲ - 2.9 ሚሊዮን ብር 6. ለሚኩራ - 3.2 ሚሊዮን ብር 7. ኮልፌ ቀራኒዮ - 1.8 ሚሊዮን ብር 8. ጉለሌ - 1.08 ሚሊዮን ብር 9. አራዳ - 1.2 ሚሊዮን ብር 10. ልደታ - 1.9 ሚሊዮን ብር 11. የካ - 920 ሺሕ ብር 12. በከተማ ደረጃ - 6.5 ሚሊዮን ብር - የመዲናችን ተቋማት እና ባለሃብቶች ተሳትፎ 1. ያደታ ጁነዲ - 5 ሚሊዮን ብር 2. ቲ ኤፍ ጂ ጄነራል ትሬዲንግ- 2 ሚሊዮን ብር 3. መሃመድ ላሎ(ፋሂም ጄነራል ትሬዲንግ) 1ሚሊዮን 4.ተመስገን ደብረወርቅ- 1 ሚሊዮን ብር 5. ማህደር ገ/መድህን ሃደራ - 500 ሺሕ ብር 6. አንዋር ኤሊያስ አግዛ -300 ሺሕ ብር 7. መላክ ቢምረው ገ/ሚካኤል -200 ሺሕ ብር 8. ሙዜፋ አብዱልካፍ ሙሳ -200 ሺሕ ብር 9. አስራት ገለቴ ዱግዳ- 200 ሺሕ ብር 10.ጌታቸው አበበ ወ/ጊዮርጊስ- 200 ሺሕ 11.ደረጀ ዘውዱ አበበ - 100 ሺሕ ብር 12.ሕይወት ጸጋዬ ቤካ -100 ሺሕ ብር 13. ዲሪባ ደፈርሻ ጄነራል ኮንስትራክሽን - 100ሺሕ ብር 14. ምህረት ይርዳው ገ/ዮሃንስ- 100 ሺሕ ብር 15. ዮሃንስ ገመዳ ዳሜሳ- 100 ሺሕ ብር 16 ክንፈ ሳህሉ ወ/መስቀል 100ሺሕ ብር 17 እስመለዓለም ዘውዴ መርጊያ 200 ሺሕ ብር 18 ዋቅጂራ አመንቴ ሁንዴ 100 ሺሕ ብር 19. ከተማ ጌታቸው ግራኝ- 50 ሺሕ ብር 20. አሸናፊ ቦጋለ ዴምሲሳ- 50 ሺሕ ብር 21. ዘቢደር ገሰሰ በርሄ -50 ሺሕ ብር 22. መስፍን ቢረዳ ባደንጋ -50 ሺሕ ብር 23. መለሰ በዳዳ ጉዲሳ -50 ሺሕ ብር 24.ንጉሴ ተሰማ ፈረጃ -50 ሺሕ 24. ኢያሱ ጌቱ ቀነኒ -20 ሺሕ ብር 25. መቅደስ ግርማ መኮንን -10 ሺሕ ብር 26. ቴዎድሮስ ይላቅ 50 ሺሕ ብር 27. መሃመድኑር አብዱ ኢብራሂም 50 ሺሕ ብር እናመሰግናለን! #ፅዱኢትዮጵያ #ፅዱጎዳናኑሮበጤና (ዛሬ ባንኮች ዝግ በመሆናቸው በሞባይል ባንኪንግ ከተላለፉ ገንዘቦች ውጪ ያሉ ትራንስፈር የተደረጉ ገንዘቦች ወደ ዋናው የሂሳብ ቁጥር ነገ ጠዋት ሙሉ በሙሉ ገቢ የሚደረጉ ይሆናል)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በመሆን ከአራት አመት ተኩል በፊት ግንባታው የተጀመረውን የአባይ ድልድይ መርቀዋል። ይህ ዘመናዊ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ ነው። የባህርዳር ከተማ ታላቅ መለያ ምልክት እንዲሆን የተገነባው የአባይ ወንዝ ድልድይ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እድገት ብሎም የመገናኛ አውታር የሚያነቃቃ ይሆናል።

Addis Ababa City Manager Office - Telegram 频道 @aacitymanager 的统计与分析