1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በቀጣይ 90 ቀናት በሚተገበረው የማዘጋጃቤታዊ እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች መዲናችን የዓለምአቀፍ ደረጃ እና ስታንዳርድ ያሟላች ጽዱ፣ማራኪ እና ምቹ በማድረግ ሂደት ወንዞቻችን ከብክለት የጸዱ ማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚፈፀም በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በቀጣይ 90 ቀናት በሚተገበሩ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች የእቅድ ትግበራ ከሚመለከታቸው የከተማ ሴክተር ተቋማት እና የክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በዛሬው እለት በእቅዱ አተገባበር እና በልዩ ትኩረት በሚፈፀሙ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
አክለውም በዚሁ እቅድ በከተማችን አብዛኛው ወረዳዎች ፅዱ፣ ከአደጋ ስጋት የተጠበቁ፣ በመሠረተ ልማት የተሳሰሩ፣ ውብ፣ አረንጓዴ፣በህብረተሰቡ ተሳትፎ በሁሉም መስክ ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ የማድረግ ስራዎች በመጪዎቺ 3 ወራት በልዩ ትኩረት ሊፈፀም የሚገባ ዋነኛ ተግባራችን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የቀጣይ 90 ቀናት የክረምት የበጎ ፈቃድ እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ንቅናቄ ስራዎችን በተለይም በክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ነባራዊ ሁኔታቸውን ባገናዘበ እና ከመደበኛ ዕቅድ ጋር አሰተሳስሮ እና ከመላው መዋቅር ጋር የጋራ ተግባቦት ፈጥሮ በመናበብ እና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ተግባሩን በልዩ መሰጠት እና ቁርጠኝነት ሊፈፀም እንደሚገባም አሳስበዋል።
በክረምቱ መርሀግብር የሰራናቸውን ተግባራት ቀጣይነታቸውን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ በባለቤትነት እንዲጠብቃቸውና እንዲያለማቸው ከህብረተሰቡ ጋር ርክክብ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከተማ አስተዳደራችን ባስቀመጠው ልዩ የንቅናቄ ስራዎች መነሻነት የተቃዱ እቅዶች እና የተቀመጡ አቅጣጫዎች እንዲሳኩ በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር የጋራ መደረጉ ለተግባሩ ስኬት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው የቅንጅታዊ አሰራሮቻችን አጠናክረን ዕቅዳችንን በቁርጠኝነት በማሳካት የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት ለማሳካት የድርሻችንን መወጣት እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።
በቀጣይ 90 ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና በጎ ፈቃድ ስራዎች ጋር በተቀናጀ አግባብ የሚፈፀሙት ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የከተማ ፅዳት፣የውበት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፥የአደጋ ስጋት መለየት እና መከላከል፥ የፋይዳ ምዝገባ ስራን ማጠናከር፣ የማእድ ማጋራት ፣የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ፣የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ እና ወረዳዎች መሠረተ ልማት ማሟላት እና ጥበቃን እና የህብረተሰብ ተሳትፎን ማጠናከር አንዲሁም የኮሙዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ስራን ማጠናከር በልዩ ትኩረት እንደሚፈፀሙ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ለቀጣይ 90 ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ልዩ የንቅናቄ አጀንዳን መሠረት ያደረገ እቅድ ቀርቦ ከተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄዶበታል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚህ መድረክ ላይ ለቀጣይ 90 ቀናት የክረምት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ከበጎ ፈቃድ ስራዎች ጋር በተቀናጀ አግባብ መፈፀም በሚቻልበት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ዋና ዋና የሥራ እቅድ ቀርቦ ከተቋማት አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት ተካሂዶበታል።
በቀጣይ 90 ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና በጎ ፈቃድ ስራዎች ጋር በተቀናጀ አግባብ የሚፈፀሙት ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የከተማ ዕዳት፣የውበት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፥የአደጋ ስጋት መለየት እና መከላከል፥ የፋይዳ ምዝገባ ስራን ማጠናከር፣ የማእድ ማጋራት ፣የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ፣የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ እና ወረዳዎች መሠረተ ልማት ማሟላት እና ጥበቃን እና የህብረተሰብ ተሳትፎን ማጠናከር አንዲሁም የኮሙዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ስራን ማጠናከር በልዩ ትኩረት እንደሚፈፀሙ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶበታል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት የቀጣይ 90 ቀናት የክረምት የበጎ ፈቃድ እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስራዎች እንዲሁም ሌሎችንም የንቅናቄ ስራዎች ከመደበኛ ዕቅድ ጋር አስተባብሮ እና አሳተሳስሮ መምራት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫ አስቀምጠው እቅዱን ከመላው መዋቅር ጋር የጋራ ተግባቦት ፈፈጥሮ በመናበብ እና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ተግባሩን በልዩ ተነሳሽነት እና መሰጠት ሊፈፀም እንደሚገባም አመልክተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሁለት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል ::
በዚህም መሰረት ፤-
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም በጀት 350 ቢሊየን ብር ሆኖ ለምክር ቤት እንዲቀርብ ፤ ውሳኔ አሳልፏል።
ረቂቅ በጀቱ በዋናነት ደህነት ቅነሳ ላይ በማትኮር ለዘላቂ ልማት፣ የስራ እድል ለሚፈጥሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ከከተማው ነዋሪ በተለያየ መንገድ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለሚሰጡ አገልግሎትና አቅርቦት ድጎማዎችን አካቶ ካፒታል በጀት 249.9 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጠባን መሰረት ላደረገ የመደበኛ በጀት ደግሞ 100.1 ቢሊዮን ብር የበጀት ጣሪያ ወስኗል፡፡
2ኛ. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተጠንቶ በቀረበዉ የመሬት ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ ዋጋ ላይም ተወያይቶ በኮሪደር ልማት በለሙ አካባቢዎች የመሠረተ ልማት አቅርቦት ደረጃ ከፍ በማለቱ እና የኮሪደር ልማቱ በከተማ ዉስጥ የነበረዉን የመሬት ዋጋ ከመረጋጋት አንፃር እና የቀጣይ የከተማዋን የመልማት ፍላጎት በማጥናት የቀረበውን የመሬት ሊዝ ዋጋ ማሻሻያ አፅድቋል፡፡
የጎርፍ መከላከል ሥራዎች በአካባቢያቸው ጎርፍ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ነዋሪዎች አስታወቁ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጎርፍ ስጋትን ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
See less
ጥበባት ለሀገር ማንነት እና እድገት ቁልፍ ናቸው። ባሕላዊ ሀብትን ጠብቀው ያቆያሉ። ለማኅበራዊ አንደነት አበክረዉ በመስራትም ብዝኃነት ላላቸው ማኅበረሰቦች ድምፅ ይሆናሉ። በትምህርት ረገድም ጥበባት ፈጠራን እና ምክንያታዊ አስተሳሰብን ያሳድጋሉ። በኢኮኖሚ ረገድም ጥበባት ፈጠራን፣ ቱሪዝምን እና ስራ ፈጠራን የመምራት አቅምም አላቸው።
ዛሬ ጠዋት ከመላው ኢትዮጵያ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ የጥበቡ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደናል። ተወካዮቹ በተለያየ ደረጃ እየተካሄደ በመጣውና በዘርፉ ያሉ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመለየት በረዳው ሰፊ የውይይት መርሃግብር የተሳተፉ ናቸው። የዛሬው መድረክም የውይይት ግኝቶቹን በማጠናከር የከፍተኛ አመራሩን ትኩረት እና መፍትሔ የሚሹ እንዲሁም በዚህ መስክ የተሰማሩ አካላት ሚናቸውን የሚወጡባቸው ጉዳዮችን በመለየት ላይ ያተኮረ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ለኢትዮጵያ ጤና ስርአት የተሰጠ በረከት!
እንኳን ደስ አለን!
ዛሬ በሀገራችን በአይነቱ ልዩ፣ የላቀ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ 25 ሚለዮን ዶላር /3.5 ቢለዮን ብር/ ወጪ የተደረገበትን የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ መርቀን ለአገልግሎት ክፍት በማድረጋችን እጅግ በጣም ደስ ብሎናል።
ይህ የሜድካል ፕላዛ በኢትዮጵያ ጤና ሥርዓት ላይ በርካታ እሴቶችን የሚጨምር፤ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ ህክምና ተደራሽነትንና ጥራትን ከፍ በማድረግ ከሃገር ውጭ ህክምና ለማገኘት የሚያጋጥሙ ወጪዎችን የሚቀንስ፤ በተለይም እንደ ኢትዮዽያ የመጀመሪያው የአጥንት መሳሳት መመርመሪያ እንዲሁም በአፍሪካ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነ የልብ፣ የአንጎል እና በሰውነት ላይ የሚከሰቱ የደም ስር ችግሮችን ያለ ቀዶ ህክምና (አፕሬሽን) መስራት የሚያስችል አርተፊሻል ኢንተለጀንስ የተገጠመለት፤ በድምጽ መታዘዝ የሚችሉ በአይነታቸዉ የመጀመሪያ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎች የተገጠሙለት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ።
ከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ለሚሰሩት ስራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ሲሆን አበረታች ውጤቶችም እየተመዘገቡ ይገኛሉ ።
የከተማችን የጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ ሚና መጫወት የሚያስችለው የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ መስራችና ባለቤት የሆኑትን ሚስ ጄን ሊ ይህንን ዘመኑን የዋጀ የጤና ተቋም ገንብተው ለአገልግሎት ስላበቁ እያመሰገንኩ፣ በቀጣይ ለመገንባት ላቀዱት ተጨማሪ የምዕራፍ ሁለት ስራ የከተማ አስተዳደራችን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
Sirna fayyaa Itoophiyaaf eebba kenname!
Baga Gammadne!
Har'a biyya keenyatti akaakuun adda kan ta'e, tajaajila yaalaa olaanaa kan kennu Doolaara miliyoona 25 (Birrii biliyoona 3.5) baasii kan itti ta'e Beetsaayidaa Ameerikaan Meedikaal Pilaazzaa eebbisnee tajaajilaaf banaa taasisuun keenyaan baay'ee gammadneerra.
Meedikaal Pilaazzaan kuni sirna fayyaa Itoophiyaa irratti bu'aawwan hedduu kan dabalu yaala Arteefishaal Intalajansiin deeggarame qaqqabiinsaa fi qulqullina kan ol kaasu taasisuun baasii yaala biyyaan alaa argachuuf qunnamu kan hir'isu; keessattuu akka Itoophiyaatti qorannaa lafee jalqabaa akkasumas akka Afrikaatti kan jalqabaa kan ta'e Onnee, sammuu,rakkoolee qaama namaa irratti uumaman fi hidda dhiigaa jalaa baqaqsanii yaluun ala hojjechuu kan danda'u Arteefishaal Intalajensiin kan godhameef; sagaleen ajajamuu kan danda'an akaakuun kan jalqabaa kan ta'an meeshaaleen yaalaa kan galaniif ta'uun adda isa taasisa.
Magaalaa keenya giddu gala tuurizimii fayyaa taasisuuf dameelee mootummaa fi dhuunfaatti hojiiwwan hojjetemaniif xiyyeeffannoo laanne hojjechaa kan jirru yemmuu ta'u milkaa'inoonni jajjabeessoonis galmaa'aa jiran.
Tajaajila fayyaa magaalaa keenyaa qulqullinaa fi qaqqabiinsa irratti gahee olaanaa xaphachuu kan dandeessisu hundeessaa fi abbaan qabeenyaa Betasaayid Ameerikaan Meedikaal Pilaazzaa kan ta'an Mis Jeen Liin dhaabbata bara waliin deemu kana ijaaranii tajaajilaaf waan geessisaniif galateeffataa, fuuldurattis ijaaruuf kan karoorsaniif hojii boqonnaa 2ffaaf bulchiinsi magaalaa keenyaa waan isaan barbaachisu hunda deeggarsa gochuuf qophii ta'uu mirkaneessuun barbaada.
Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Haa Eebbisu
በመዲናችን 35ኛው የአፍሪካ የሕፃናት ቀን በዓል በተለያዩ ሁነቶች በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ
የቀዳማይ ልጅነት ሣምንት እና በአፍሪካ ለ35ኛ እንደ ሃገር ለ34ኛ ጊዜ”የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማነጽ ሕፃናት ተኮር ተግባራትን እናከናውን!” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
መንግስት ህፃናትን ለማስደግ መዲናችን አዲስ አበባን ምርጧ አፍርካዊት ከተማ በማድረግ ረገድ ቁርጠኛ አቋም ወስዶ ሕፃናት ለሃገር ያላቸዉ ተስፋ እውን እንዲሆን ከማኅፀን ጀምሮ በሚደረግ እንክብካቤ፣ በአልሚ ምግብ፣ በጨዋታ መማር፣ በትምህርት ቤት ምገባ፣ በቤተሰባዊ ትስስር መልካም ዕድገት በማስረፅ፣ ሁለንተናዊ መብቶቻቸዉ ተከብረዉ በሀገራዊ ግንባታ፣ ልማቶች እና ዕድገቶች ውስጥ ተሳትፎአቸዉ እዉን ለማድረግ በርካታ ስራዎችን ሠርቶ ተጨባጭ ለዉጦችን እያስመዘገበ ይገኛል::
በዚህም መሰረት:-
👉በቀዳማይ ልጅነት በ2015፦45 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች
👉በ2016፦277 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች
👉በ2017፦1131 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች
👉ከ2015እስከ 2017 ድረስ በድምሩ፦1453 ዘመናዊ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ሲሆኑ
👉በሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ በየሳምንቱ የሚዘጉ 132 የሰንበት ዝግ መንገዶች ከፍተኛ ቀጥር ያላቸው ሕፃናት የሚጫወቱበት፤
👉 በየወሩ በዝቅተኛ የንሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 11900 ነብሰ-ጡር ሴቶች አጥቢ እናቶችና እድሜያቸው እስከ 3ዓመት ለሆኑ ሕፃናት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ የሚያገኙበት፤ እንዲሁም
👉በተለያየ 822 በላይ በሆኑ የሕፃናት የቀን ማቆያዎች 15,712 ሕፃናት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ታዉቋል።
