1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በአዲስ አበባ ከተማ ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ መንስኤ የሆኑ 5 ዋና ዋና ምክንያቶች
**************
በአዲስ አበባ ከተማ በኃይልና በንብረት አጠቃቀምና አያያዝ እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች እየደረሱ ያሉ ጎርፍን ጨምሮ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች በሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ።
በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ የደረሱ 127 የእሳት፣ የጎርፍና ሌሎች አደጋዎች ለ22 ሰዎች ሞት፣ ለ12 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ምክንያት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሸነር አቶ ጥላሁን ቶላ በተለይ ለኢበሲ ሳይበር ገልፀዋል።
አደጋዎቹ 94 ሚሊዮን ብር በሚገመት ሀብት ላይ ውድመት ማስከተላቸውንና 2.46 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ግን ማዳን መቻሉን ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።
በ2016 ዓ.ም ከደረሱ 523 ድንገተኛ አደጋዎች ኮሚሽኑ በወሰዳቸው ፈጣን እርምጃዎች 37 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ማዳን ቢቻልም፤ 1.26 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ወድሟል።
በአንድ ተቋም ወይም ግለሰብ ሳቢያ በሚከሰቱ አደጋዎች ለአብነትም በአቃቂ፣ በሾላ እና በመርካቶ አከባቢዎች በድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት ከፍተኛ ውድመት ደርሷል ብለዋል።
በከተማዋ ለሚከሰቱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች ዋናዎቹ መንስኤዎች 5 መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ጥላሁን ቶላ፤ ከነዚህ አንደኛው የኃይል አጠቃቀምና አያያዝ ክፍተት መሆኑን አንስተዋል።
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=8224
ሀሰተኛ ሰነዶችን የሚያዘጋጅ ግለሰብን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ዝግታ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ አንድ ግለሰብ ልዩ ልዩ ማህተሞችና ቲተሮችን በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደሚያዘጋጅ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በጥናት ላይ የተመሠረተ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ከሰራ በኃላ የተገኘ ውጤት መሆኑን ከፖሊስ መምሪያው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
ፖሊስ ተገቢውን የህግ ስርዓት ተከትሎ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ/ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባደረገው ብርበራ በርካታ የተዘጋጁ እና ሊዘጋጁ የተሰናዱ ሀሰተኛ ሰነዶችን እንዲሁም ግለሰቡ ሀሰተኛ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምባቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችም ተይዘዋል፡፡
ተጠርጣሪው ሀሰተኛ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምባቸው የመንግስትና የግል ተቋማት 51 ክብ ፣ 73 የግርጌ ማህተሞች፣ አምስት ፕሪንተሮች ፣ አንድ ኮምፒተር፣ አንድ ላፕቶፕ እንዲሁም በሃሰተኛ መንገድ የተዘጋጁ የ8ኛ ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል እንዲሁም የዲፕሎማ፣ የዲግሪ፣ የማስተርስ የትምህርት ማስረጃዎችን በተጨማሪነት መያዙን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
አዲስ አበባ ፖሊስ በሀሰተኛ ሰነድ አማካኝነት የሚፈፀሙ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመከላከል ህገ-ወጦችን ተጠያቂ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቆ የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባና ተቋማት ለተለያዩ ጉዳዬች የሚቀርቡላቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት ሊያረጋግጡ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
አንድ ደላላ እና ሁለት ፈፃሚዎች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ሰልፍ በመያዝ እና ተገልጋይ በመመዝገብ ገንዘብ የሚሰበስብ በፓርኪንግ ስራ ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ እና ከደላላ ጋር ተመሳጥሮ በሌብነት ላይ የተሰማራ አንድ የንግድ ቢሮ የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኛ እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲዋሉ ተደርጓል።
ለከተማ አሰተዳደሩ ከነዋሪ በደረሰ ጥቆማ መነሻ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በሰራው ኦፕሬሽን ካድረጉት የስልክ የድምፅ ልውውጥ ጋር በኤግዚቢትነት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ኤጀንሲው አክሎም ፖሊስ በጉዳዩ ላይ መረጃ በማሰባሰብ ምርመራ እያደረገ እንዳለ ጠቅሶ ጥቆማውን ለሰጠው ነዋሪም ምስጋና አቅርቧል።
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በነጻ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ውብ፣ ጽዱ፣ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ከተማ፣
አዲስ አበባ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
See less
በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ መሸኛ አስገብታችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተገልጋዮች ያቀረባችሁትን መረጃ የማጥራት ሂደት በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ከህዳር 1 ጀምሮ ለመጀመር ዝግጅት ተደርጓል ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከነገ ጥቅምት 14/2017ዓ.ም ጀምሮ በነዋሪነት ለመመዝገብ ያመለከታችሁ የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት የወረዳ ጽ/ቤታችን እስከ ጥቅምት 22 ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅና ምዝገባው በኤጀንሲው ጽ/ቤት የሚከናወን በመሆኑ የክ/ሃገር መልቀቅያ ባስገባችሁበት ወቅት ከጽ/ቤታችን የተሰጣችሁን ማስረጃ ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአክብሮት እንገልፃለን ሲል አመልክቷል።
ኤጀንሲው አክሎም በዚህ የማጥራት ሂደት ያላለፈ አመልካች በነዋሪነት ተመዝግቦ አገልግሎት ማግኘት የማይችል መሆኑን በመገንዘብ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን ሲልም አስገንዝቧል።
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በነጻ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ዛሬ ጠዋት ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጌያለሁ። በውይታችን ወቅት ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበት ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ገልጫለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)
ዛሬ ጠዋት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግር ያደረጉበት ''የተጠናከረ የባለብዙወገን ግንኙነት ለሚዛናዊ የአለም ልማት እና ደኅንነት'' በሚል ጭብጥ የ16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ዝግ ስብሰባ ተካሂዷል።
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 ወደብሪክስ እንዲቀላቀሉ ከተጋበዙት ሀገራት መካከል መሆኗ ይታወቃል። ከጥር 2024 ጀምሮም የአባልነታችን እንቅስቃሴ በይፋ ጀምሯል።
በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው በአጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላከይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።
አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍና ተባባሪነት ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ እንሚያሳውቅም አስታውቋል፡፡
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
”
በመርካቶ ሸማ ተራ የደረሰው የእሳት አደጋ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ
