1 474
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-2130 天
帖子存档
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ 2ኛውን የአካባቢ ብክለት መከላከል ሀገራዊ ንቅናቄ በይፋ አስጀምረዋል።
አቶ አደም ፋራህ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የአካባቢ ጥበቃ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የብልጽግናችን መሰረት ነው ብለዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የዜጎች ጤና እንዲጠበቅና ማህበራዊ ኑሯቸው እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸው መንግስት ጽዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ በኮሪደር ልማት፣ በታዳሽ ኃይል አጠቃቀም ላይ በርካታ ስራዎች መስራቱን ተናግረዋል።
በንቅናቄው የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የማህበረሰብን ተሳትፎ ማጎልበት፣ የህግና ሥርዓት ተገዥነትን ማስፈን አና መልካም ለሰሩ እውቅና የመስጠት ስራዎች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የታደሙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ ከአረንጓዴ አሻራ፣ወንዞች ዳርቻ ልማት፣ ታዳሽ ሀይል አጠቃቀም እና ከተማ ፅዳት አንፃር የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራትን በማስመልከት ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም በዓለም ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ገልጸው፤ በሀገራችን ይህንን ተግዳሮት ለመቀነስ እንዲያስችል በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸውን አንስተዋል።
በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ የደን ሽፋን ከነበረበት የ2.8 በመቶ ወደ 20 በመቶ ማሳደግ መቻሉን አንስተው÷ በአካባቢ ጥበቃና ጽዱ ከተማ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።በከተማዋ በጽዳት፣ በውሃ ፍሳሽ አወጋገድ፡ በብዙኃን ትርስንስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች መከወናቸውንም አብራርተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ አዲስ አበባን ጨምሮ አምስት ተቋማት ፅዱ ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ረገድና እና አረንጓዴ ኢኒሼቲቭን ለማሳካት ባከናወኑት ውጤታማ ስራዎች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዛሬ ጠዋት፣ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ያሉትንና በስሎቬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት የሆኑትን የተከበሩ ናታሻ ፒሪክ ሙሳርን በጽሕፈት ቤቴ ተቀብዬ በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
እንኳን ለ1446ኛው የአረፋ(ዒድ አል አድሃ) በዓል አደረሳችሁ
በአረፋ በዓል ወቅት የሚታወሱ ሁለት ዕሴቶች፣ ለምንገነባት የበለጸገች ኢትዮጵያ እጅግ በጣም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡
የአረፋ በዓል መሥዋዕትነት የሚታሰብበት በዓል ነው፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸው ኢስማኤልን በፈቃዳቸው ለፈጣሪ መሥዋዕት ለማድረግ ፍጹም ቆራጥነታቸውን ያሳዩበት በዓል ነው - አረፋ፡፡ ልጅን ለፈጣሪ መሥዋዕት ከማድረግ በላይ መታዘዝም፣መሰጠትም የለም፡፡
ሀገር የምትጸናው በመሥዋዕትነት ነው፡፡ ያውም የምንወደውን ነገር መሥዋዕት በማድረግ፡፡ ሀገር ማለት ቀዳሚው ትውልድ ለተተኪው ትውልድ ሲል መሥዋዕትነት የሚከፍልባት ናት፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት በማዘጋጀታቸው በምትኩ የሚሠዋ በግ ከአላህ አግኝተዋል፡፡ ሌላ መሥዋዕት ለማግኘት ራስን መሥዋዕትነት ማድረግ ይገባል፡፡ በኢብራሂም ልቡና እስማኤል ተሠዉቷል፡፡ ለሀገሩ የሚሠዋን ትውልድ የሚፈጥረው ለሀገሩ ቀድሞ የተሠዋ ትውልድ ነው፡፡
እናቶቻችንና አባቶቻችን ለሀገራቸው ነጻነትና ሉዓላዊነት መሥዋዕትነትን ከፍለዋል፡፡ በዚያ መሥዋዕትነታቸው ሰማያዊና ታሪካዊ ዋጋ ያገኙበታል፡፡ ተመጣጣኝ ምድራዊ ምንዳ ግን አያገኙም፡፡ ለሕይወት የሚመጥን ምንም ዓይነት ምንዳ ስለሌለ፡፡ የእነርሱን ምንዳ የምንቀበለው እኛ ነን፡፡ የእኛንም ምንዳ ተተኪው ትውልድ ይመነዳዋል፡፡
አረፋ “ወአረፍተኒ ወአረፍቱ” “አወቅሺኝ፤ ዐወቅኩህ” የተባለበት በዓል ነው፡፡ አደምና ሐዋ ከጀነት ከወጡ በኋላ ለረዥም ዘመን ተለያይተው ኖረዋል፡፡ የተገናኙት በአረፋ ዕለት ነው፡፡ አረፋ የተለያዩ የሚገናኙበት በዓል ነው፡፡ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ አሳዛኙ ነገር መለያየቱ ሳይሆን፣ ተለያይቶ መቅረት ነው፡፡ ሐሳብ፣ አመለካከት፣ ቅሬታ እና ያለፈ ታሪክ በአንድም በሌላም መንገድ አለያይተውን ይሆናል፡፡ ነገር ግን የአንድ ሀገር ልጆች እንደመሆናችን መጠን ተለያይቶ መቅረት ሳይሆን እንደ አደምና ሐዋ የመገናኛ መንገድ ያስፈልገናል፡፡
ለእኛ የመገናኛ መንገዳችን ሀገራዊ ምክክር ነው፡፡ ሀገራዊ ምክክር ሐሳቦቻችን እና ፍላጎቶቻችን የሚገናኙበት መድረክ ነው፡፡ አንዱ ሌላውን የሚረዳበት፣ አንዱ ሌላውን የሚያስረዳበት፣ አንዱ በሌላው ጫማ የሚቆምበት፣ አንዱ የሌላውን ሕመም የሚታመምበት፤ በመገናኘት “ዐወቅሺኝ፣ ዐወቅኩህ” የምንባባልበት ሰላማዊ መድረክ ነው፡፡
በመሆኑም የአረፋን በዓል ስናከብር ለሀገርና ለነገ ትውልድ የምንከፍለውን መሥዋዕትነት እያሰብን፤ በሀገራዊ ምክክሩም የምንገናኝበትን መድረክ ይበልጥ እያጠናከርን እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
በድጋሚ መልካም የአረፋ በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ ር አቢይ አህመድ
ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ዛሬ የስሎቬኒያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ናታሻ ፒርስ ሙሳር በአደዋ ድል ጀግኖች መታሰቢያ ሀውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
እኛም "እንኳን ደህና መጡ” ብለን በክብር ተቀብለናቸዉ የአደዋ ድል መታሰቢያን አስጎብኝተናቸዋል።
በጉብኝታቸው ወቅትም ለኢትዮጵያ ነጻነትና ሉዓላዊነት ውድ ህይወታቸውን በሰዉ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ጀግንነትና ታሪክ እጅግ መደነቃቸዉን ገልፀዋል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1446ኛውን የኢድአል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻ በቂርቆስ ወረዳ 07 እስቴዲየም ዙሪያ ተካሄደ
በፅዳቱ ንቅናቄ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ ነገ ለሚከበረው ለ1446ኛው በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው በዓሉ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚጠናከርበትና መተሳሰብ የሚጎለብትበት እንዲሆንም ተመኝተዋል።
አክለውም ከተማችንን ስናፀዳ አብሮነትን፣መቻቻልን መደጋገፋችንን የሚጎዱ አስተሳሰቦችን አብረን ማፅዳት የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ዶክተር አዲሱ በማስቀጠልም ከተማችንን ስናፀዳ አብሮነትን፣መቻቻልን መደጋገፋችንን የሚጎዱ አስተሳሰቦችን አብረን ማፅዳት የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል።
የፅዳቱ ዋና ዓላማ ስለ ኢትዮጵያችን በጋራ የምናስብ ፣በጋራ የምንሰራ መሆናችንን ለማሳየት መሆኑን የተናገሩት የክፍለ ከተማው ስራ አስክያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ዘይዳ ነስረዲን ይህንን ስናደርግ ኢትዮጵያዊነታችን እየጎለበተ መተሳሰባችን እየበረታ ይሄዳል ብለዋል።
እኛ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ በትብብር በመከባበር የኖርን ህዝቦች በመሆናችን የአንዱ ደስታ ደስታችን፣ የሌላው ሀዘን ሀዘናችን ሆኖ ኖሯል።
የዛሬው የፅዳት ዓላማም ነገ የሚከበረውን የዐረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ በመሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ በማለት በፅዳቱ ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
በፅዳት ዘመቻው ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የፅዳት ሰራተኞችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆያታ የሰጡት ማብራሪያ ክፍል አንድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰጡት ማብራሪያ ክፍል አንድ
#ebc #etv #ebcdotstream #abiyahmed #pmabiy #interview #7years
See less
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 4ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት፡-
1. የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኃላ አጽድቋል።
2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግል ትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርዓት ረቂቅ ደንብ አጽድቋል።
3. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶ በሰፊው ከተወያየ በኃላ የውሳኔ ሀሳቡን አጽድቋል።
በመዲናችን አዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ከማዘመን እና ከማሳደግ ባለፈ ከአደጋ ስጋት የተጠበቀች፣ ጽዱና ውብ በማድረግ ረገድ ያለውን ጉልህ ፋይዳ አስመልክቶ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከኢቢሲ ኤፍኤም 97.1 ሬድዮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ይከታተሉ👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም የተሰማሩ 3ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ባለፉት 10 ወራት ብቻ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ከዘርፉ ማግኘት ችለዋል!
በወረቀት መልሶ መጠቀም ዘርፍ የሚሰራው አንዲማማ መንግስታዊ ያልሆነ ፕሮጀክትፕሮጀክቱ የተመሰረተበትን 4ኛ ዓመት አከበረ።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አንዲ ማማ ጋር በመተባበር መዲናዋ የምታመነጨውን የወረቀትና ካርቶን ተረፈ ምርት በመሰብሰብና ለእናቶች የስራ ዕድል በመፍጠር በመልሶ መጠቀም ዘርፍ በርካታ ተግባራትን በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ስለሆነም አለም አቀፍ የእናቶች ቀንን በማስመልከት እና የእናት ፍቅር ፕሮጀክት የተመሰረተበትን 4ኛ ዓመት ክብረ በዓል አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት አክብሯል
በመርሀግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ የሀገር ዕድገት የሚረጋገጠው በዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ መሆኑን ጠቁመው አንዲማማም እየሰራ ያለው የዜጎችን ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም አቶ ተፈራ ከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ፍትሃዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል እንዲኖራቸው እየሰራ ላለው ስራ አጋዥ በመሆናቸው አመስግነው ከተማ አስተዳደሩ ለፕሮጀክቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተ ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ በተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደርና ቆሻሻን ወደ ሀብትነት መቀየር ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራቱ በዘርፉ 3ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ተሰማርተው ባለፉት 10 ወራት ብቻ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ማገኘት መቻላቸውን ገልፀዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም አንዲማማ ከኤጀንሲው ጋር በአጋርነት የሚሰራ እንደመሆኑ የአገር ዋልታ የሆኑት እናቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱ ከሌሎች ተቋማት እንዲለይ አድርጎታል። ሁሉም እንደ አንዲማማ በኃላፊነት ከሰራ ከተማ አስተዳደሩ ከተማችንን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተሰራ ላለው ስራ አቅም መሆን ይቻላል ብለዋል።
በመጨረሻም በፕሮጀክቱ የተሰሩ የመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ስራዎችን በተዘጋጀው የኤግዚቢሽ አውደርዕይ ለጉብኝት ቀርቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በ2017 በጀት አመት በተጠሪ ተቋማትና በክፍለ ከተሞች እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር የተከናወኑ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ያሉበት ደረጃን ለማረጋገጥ የሚያስችል የኢንስፔክሽን ስራ ለማከናወን ለባለሙያዎች ኦሬንቴሽን ሰጠ።
በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ የኢንስፔክሽን ተግባር ላይ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች በሰጡት ገለፃ ኢንስፔክሽኑን ማካሄድ ያስፈለገው በአፈፃፀም ሪፖርት የሚገለፁ ስራዎች በተጨባጭ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተደገፉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል።
በእሳትና በድንገተኛ አደጋዎች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋት አደጋዎችን ቀድሞ ሳይደርሱ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ከ10ሩም ወረዳ ለተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በ2017 በአደጋ ትግበራ ዙሪያ የፓናል ውይይት አካሄዷል ፡፡
በፓናል ውይይቱ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት ክፍለ ከተማው ከአደጋ ስጋት ነጻ የሆነ እዲሆንና ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ህብረተሰቡን ለአደጋ ተጋላጭነትን የተለዩ ችግሮችን አብዛኛውን በመፍታት አበረታች ሰራዎች መከናወናቸውን አንስተው የህብረተሰብን የአደጋ አስቀድሞ መከላከል ግንዛቤ በማሳደግ አደጋዎችን ቀድሞ ከመድረሳቸው በፊት ቀድሞ በመከላከል ትኩረት ሰጥቶ መስራተ እደሚገባ ተናግረዋል ፡፡
የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ነጋሽ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በክረምት ወራት ለመሬት መንሸራተትና ለእሳት አደጋ ተጋላጭ የሆኑ 27 ቦታዎችን በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን እየተሰራ እንደሆነ በመግለጽ ህብረተሰቡ በአደጋ ስጋት ላይ ግንዛቤውን በማስፋት ከአስተዳደሩ ጋር በጋራና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂሩት ሽፈራው በበኩላቸው እሳት አደጋ በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰው ሰብአዊና አካላዊ ጉዳቶችን ለመከላከልና ለመቀነስ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡
በስልጠናው ስለ አደጋ ምንነት ፣ሰለ አደጋ አይነቶች ፣ አደጋ በህብረተሰቡ የሚያደርሰው ሰብአዊ ፣ አካላዊ፣ ሰነ ልቦናዊ ጉዳቶች ፣ አደጋን በምን መልኩ መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት ተካሄዷል፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ልዩ አራት ክፍሎች ያሉት ቃለ መጠይቅ ነገ ረቡዕ ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 መተላለፍ ይጀምራል። እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል።
Prime Minister Abiy Ahmed’s special four-part interview with ETV begins airing tomorrow, Wednesday, June 4, 2025, at 8:30 PM. Don’t miss it—tune in!
