ch
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

前往频道在 Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

显示更多

📈 Telegram 频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias 的分析概览

频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 949 名订阅者,在 医学 类别中位列第 1 157,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 681

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 949 名订阅者。

根据 27 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -557,过去 24 小时变化为 -23,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 26.07%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.79% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 203 次浏览,首日通常累积 1 354 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

凭借高频更新(最新数据采集于 28 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 医学 类别中的关键影响点。

19 949
订阅者
-2324 小时
-1257
-55730
帖子存档
በአዲሱ "ጉንፋን" መሳይ በሽታ ዙርያ ለህዝብ መረጃ ሊሰጥ ይገባል! ከሰሞኑ ጉንፋን መሰል በሆነ በሽታ እጅግ በርካታ ሰዎች ተይዘዋል። በሽታው በሀገራችን እንዲሁም በአንዳንድ ጎረቤት ሀገራት ተከስቷል
በአዲሱ "ጉንፋን" መሳይ በሽታ ዙርያ ለህዝብ መረጃ ሊሰጥ ይገባል! ከሰሞኑ ጉንፋን መሰል በሆነ በሽታ እጅግ በርካታ ሰዎች ተይዘዋል። በሽታው በሀገራችን እንዲሁም በአንዳንድ ጎረቤት ሀገራት ተከስቷል፣ በርካታ ሰዎችም በዚህ ዙርያ ማህበራዊ ሚድያ ላይ መረጃ እያጋሩ ይገኛሉ። ትናንት ዶ/ር ፋሲል መንበረ በተባሉ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ባልደረባ ከተሰጠ አንድ መረጃ ውጪ ይህ ጉዳይ በሚመለከታቸው የጤና ሚኒስትርም ሆነ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እስካሁን በሽታው ዙርያ የተሰጠ ማብራርያ የለም። እየሰማነው ያለው አስደንጋጭ ነው፣ በቢሮዎች እና የስራ ቦታዎች በግምት ከ50% በላይ የሚያስል፣ የሚያስነጥስ እና በህመም ላይ የሚገኝ ሰው እየተገኘ ነው። ይባስ ብሎ አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ማንም ሰው በዚህ ሰበብ ከስራ እንዳይቀር እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ታድያ ይህ ሁሉ ሲሆን ሰፊ ምርመራ ተደርጎ የበሽታው ምንነት ለህዝብ ሊነገር አይገባም? ምልክቱ ከኮቪድ-19 ጋር የሚመሳሰል ስለሆነ የላብራቶሪ ማረጋገጫ ሊደረግ ግድ አይልም? በሌሎች ሀገራት እንዲህ አይነት ወረርሽኝ ሲከሰት በፍጥነት ምርመራ ተደርጎ የመከላከያ እና መጠንቀቂያ እርምጃዎች ይወሰዳሉ። ይህን ማድረግ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም፣ ስለዚህ ለህዝብ መረጃ ይሰጥ።

ደም ማነስ(Anemia) ምንድን ነው? -ደም ማነስ የምንለው ችላ መባል የሌለበት፣አደገኛ ፣ በደም ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ሴሎች ቁጥር መሆን ከሚገባው በታች ሲያንስ ወይም በቀይ የደም ሴል ውስጥ የሚገኘው የ ሄሞግሎቢን የተባለው የደም ፒግመንት ከመጠን በላይ ማነስ ነው። -ሄሞግሎቢን የምንለው በደም ሴል ውስጥ የሚገኝ ብረትን(iron) የያዘ እና ኦክሰጅን ከአንዱ የደም ክፍል ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል ተሸክሞ የሚያጓጉዝ ነው።ስለዚህ የሄሞግሎቢን እጥረት ሲኖር የሰውነት አካሎቻችን በትክክል ለመስራት የሚፈልጉትን ያህል ኦክስጅን ስለማያገኙ ነው። ማንን ያጠቃል? -ለአቅመ ሄዋን የደረሱ ሴቶችን በተለይም በብረት እጥረት ምክንያት (iron deficiency) የምንለው አይነት የደም ማነስ በተለየ ሁኔታ የተጋለጡ ናቸው።ይህም የሚሆነው በወር አበባ ጊዜ የደም መፍሰስ ስለሚኖር እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ የደም ፍላጎት ስለሚጨመር ነው።ለዚህም ነው እናቶች በእረግዝና ክትትል ወቅት የብረት (iron) እንክብል የሚሰጠው።ምክንያቱም አንድ ነፍሰጡር እናት ለከፍተኛ የደም ማነስ ከተጋለጠች ፅንሱ የሰውነት መቀጨጭ እና ያለ ጊዜ መወለድ ሊከሰት ይችላል።ከዚህም በተጨማሪ ህፃኑ ከተወለደ በዃላም ለደም ማነስ ተጋላጭ ይሆናል። -እንደ WHO ከሆነ በአለም ላይ 45% የሚሆኑ እድሚያቸው ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት እንዲሁም 40% የሚሆኑ ነፍሰጡር እናቶች ለደም ማነስ ተጋላጭ ናቸው። -ከባድ በሽታ ያላቸው እና እድሜያቸው የገፋ ሰዎችም ተጋላጭ ናቸው። መንስኤዎቹስ? -ከ400 በላይ የደም ማነስ አይነቶች ሲኖሩ መንሰኤዎቹን በ 3 ከፍለን ማየት እንችላለን። 1.የቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ(decreased RBC production) በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ በብረት እጥረት ምክንያት(iron deficiency)፣ቫይታሚን ቢ12 እና ፎሌት እጥረት፣የኩላሊት ችግር፣ካንሰር 2.የቀይ የደም ሴሎች ውድመት(increased RBC destruction) 3.በደም መፍሰስ(blood loss) አይነቶቹስ? -ጥቂቶቹን ለማየት ያክል 1.በብረት ምክንያት የሚመጣ (iron deficiency) ይህም በአመጋገብ ችግር፣በከፍተኛ የደም መፍሰስ፣ ሲኖር ባልተለመደ ሁኔታ ወረቀት፣ቆሻሻ ለመመገብ መፈለግ፣የጥፍሮቻችን መሰባበር፣የአፍ መሰነጣጠቅ እና መቁሰል ሊኖር መፍሰስ ። 2.በቫይታሚን ቢ-12 ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ በእጅ እና እግር ላይ መርፌ የመወጋት እና የመጠዝጠዝ ስሜት፣የምላስ ህመም ስሜት መኖር፣የመዳሰስ ስሜት ማጣት፣መነቀጥቀጥ፣ለመራመድ መቸገር፣የአስተሳሰብ መለዋወጥ ይኖራል 3.በሊድ መመረዝ የሚከሰት የደም ማነስ ሲኖር ሰማያዊ ወይም ጥቁር መስመር በድድ ላይ መኖር፣የሆድ ህመም፣ድርቀት አና ማሰታወክ ሊኖር ይችላል 4.ሲክል ሴል(sickle cell anemia) የድካም ስሜት ፣ለኢንፌክሽን መጋለጥ፣በህፃናት ላይ እድገት መዘግየት፣ 5.ሄሞላይቲክ(hemolytic anemia) ሲኖር የሽንት መጥቆር፣የአይን ቢጫ መሆን፣የጣፊያ እና የጉበት እብጠት እንዴት ማወቅ ይቻላል? -የደም ምርመራ በማድረግ የደም ሃሞግሎቢን መጠን እና የተለያዩ ከደም ላይ የሚሰሩ ምርመራዎች ለምሳሌ peripheral morphology,reticulocyte index፣የደም ብረት መጠን እና የመሳሰሉትን እንዳስፈላጊነቱ በማድረግ ማወቅ ይቻላል። ምልክቶቹስ? -እንደ የደም ማነስ አይነቶች የሚለያይ ሲሆን የጋራ የሆኑ ምልክቶች የምንላቸው *የድካም ስሜት *በእቅስቃሴ ጊዜ ያልተለመደ ፈጣን የልብ ምት *እራስ ምታት *የማዞር ስሜት *ትኩረት ማጣት *የቆዳ መገረጣት *ትንፋሽ ማጠር *ጆሮ ላይ የመጮህ ስሜት *የምግብ ፍላጎት መቀነስ ህክምናውስ? -እንደ ደም ማነስ አይነት የሚወሰን ሲሆን በተለይ የደም ማነሱን ያመጣውን ችግር ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ማወቅ እና ማከም ተገቢ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመጋገብ ላይ ትኩረት በማድረግ በብረት የበለፀጉ ምግቦች ለምሳሌ ቀይ ስጋ፣አትክልት እና ፍራፍሬ ለምሳሌ ካሮት፣አቮካዶ፣ጉበት፣አሳ፣የጥራጥሬ እህሎች፣ባቄላ፣አተር እና የመሳሰሉትን መመገብ አንዱ የህክምና አካል ነው። -በብረት እጥረት ምክንያት ከሆነ በአመጋገብ ስርአት ድክመት፣በደም መፍሰስ፣የአንጀት ቁስለት፣ሁክ ዎርም፣የጨጓራ መድማት፣የአንጀት እና የጨጓራ ካንሰር፣የወር አበባ በብዛት የደም መፍሰስ ሊከሰት ስለሚችል የደም ማነሱን ያመጣውን በሽታ ማ

ከዕለታት ግማሽ ቀን ላይ ያለው ስንፈተ ወሲብ ============================ ገፅ 16 ላይ "...ጠይም እግሮቿ ከጉርድ ወታደራዊ ቆዳ ጫማዋ ጀምሮ...ጉልበቷን አልፎ ታፋዋ...ብሎም የውስጥ ሱሪዋ ድረስ ቁልጭ ብሎ ይታያሉ። ...አንዳች የማላውቀው ንዝረት መላ ሰውነቴን ሲወረው ተሰማኝ። የኢንስፔክተር መንበረ የውስጥ ሱሪ ቀይ ነው..." ይልና ገፀባህሪው በሽንቁር አጮልቆ የተመለከተው ቀይ የውስጥ ሱሪ አእምሮው ላይ እንደተቀረፀ ይገልፃል። ከዛ ገፅ 20 ላይ ገፀባህሪው አድጎ ከሌላ ሴት ጋር ፆታዊ ግንኙነት ሊያደርግ ሲል ያጋጠመውን ይተርካል "...የለበሰችውን ቀሚስ፣ በእኔው እርዳታ ያወለቀች ጊዜ ምን አጋጠመኝ? ...ነጭ የጡት ማስያዣና ነጭ የውስጥ ሱሪ...በረዶ የመሰለ እና በረዶ ያደረገኝ...ድንገት ነበር የቀዘቀዝኩት። "ምን ሆንክ?" አለችኝ በአየር ላይ የቀረ መንሰፍሰፌ ሲጠወልግ አይታ መሆን አለበት..." ምንድነው ያጋጠመው? ገፀባህሪው ወደ አእምሮ ህክምና ቢመጣ የህመሙን/የተከሰተውን ነገር በደንብ ለመረዳት ብዙ ጥያቄዎች እንጠይቀው ነበር። ነገር ግን ገፀ ባህሪ ስለሆነ መፅሀፉ ላይ በተሰጠን መረጃ ከሁለት ሁኔታዎች አንዱ የመሆን እድሉ ከፍ ያለ ነው። 1) ሁኔታዊ ስንፈተ ወሲብ (Situational erectile dysfunction) አንዳንድ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲከሰቱ ሁኔታዊ ስንፈተ ወሲብ ሊከሰት ይችላል። ገፀባህሪው በአእምሮው የሳለውና ያጋጠመው ነገር መለያየት ሁኔታዊ ስንፈተ ወሲብ አጋጥሞታል። ጥሩነቱ በቀጣይ አእምሮውን ሲያዘጋጅ ችግሩን የመቀረፍ እድሉ ከፍ ያለ መሆኑ ነው። 2) ፌቲሺዝም (Fetishism)- የእነዚህ ሰዎች የወሲብ ፍላጎታቸው የሚቀሰቀሰው ከድርጊቱ ይልቅ ተያያዥ በሆኑ ልብሶች ወይም እቃዎች ነው። ለምሳሌ፦ ረጅም ታኮ ጫማ፣ የጡት መያዣ፣ የውስጥ ሱሪ...ወዘተ። በህፃንነታቸው ተገቢ ያልሆነ ፆታዊ ግንኙነት የተመለከቱ ልጆች ለዚህ ህመም ተጋላጭ እንደሚሆኑ ይታወቃል። ሲጠቃለል፦ ሁኔታዊ ስንፈተ ወሲብ ሁኔታዎች ሲስተካከሉ የሚሻሻል ሲሆን ፌቲሺዝም ግን ረዘም ያለ ህክምና ያስፈልገዋል።

የሰሞኑ ጉንፋን! የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ግን ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው በተጨማሪም እነዝህ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡ • ብርድ ብርድ ማለት • የመገጣጠሚያ ህመም • የጀርባ ህመም • የጡንቻ ህመም • ምግብ ፍላጎት መቀነስ • ኃይለኛ ራስ ምታት • ፍዝዝ ማለት ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ? ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው። ለምሳሌ÷ ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው። ስለዚህ ምን እናድርግ? • የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ • ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን ይሽፍኑ • የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ • ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ • ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ • መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው? • ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠልየአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት • ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣ • ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት • ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ • የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ • ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን • ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል። ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው ? • ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል • ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ • ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም • በቂ እረፍት ማድረግ • የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ • እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡ ዶ/ር ፋሲል መንበረ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም Credit : ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

ሰላጣን መመገብ የሚያስገኛቸው የጤና በረከቶች ያለንበት ወቅት በተለይም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፆም ወቅት እንደመሆኑ ሰላጣ በብዛት ለምግብነት ሲውል ይስተዋላል። በቀላሉ እና በፍጥነት በቤታችን አዘጋጅተንም ይሁን በምግብ ቤቶች ውስጥ አዘን መጠቀም ክምንቻላቸው ምግቦች ተርታ የሚመደበው ሰላጣ በርከት ያሉ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉትም የተለያዩ ጥናቶች አመላክተዋል። ሰላጣን አዘውትሮ መመገብ ከሚሰጣቸው የጤና ጠቀሜታዎችም፦ 1. ክብደትን ለመቀነስ:- ሰላጣ በውስጡ ባለው ፋይበር አማካኝነት ምግብ በቶሎ እንዲፈጭ በማድረግ ሰውነታችን እንዳይወፍር እና ክብደታችን እንዳይጨምር ያደርጋል፡፡ 2. ጤነኛ ልብ እንዲኖረን ደርጋል:- በሰላጣ ውስጥ ያሉት ቪታሚን ሲ፣ ቤታ ካሮቲን ፎሌት እና ፋይበር ንጥረ ነገሮች አማካኝነት ልባችን ጤነኛ እንዲሆን ደርጋሉ። 3. በሽታንና ያለእድሜ የሚከሰት እርጅናን ለመከላከል:- በሽታ ተከላካይ ምግቦች ከሚባሉት የሚጠቀሰውን ሰላጣን አዘውትሮ መመገብም በሽታን እና ያለ እድሜ የሚከሰት እርጅናን ለመከላከል እንደሚረዳም ተነግሯል። በተለይም የተጠበሰ ዱባ፣ አቮካዶ እና ለውዝ የመሳሰሉትን ከሰላጣ ጋር አንድ ላይ አዋህዶ መጠቀም ደግሞ የምናገኘውን የጤና ጠቀሜታ ከፍ ያደርገዋል ነው የተባለው። 4. ለአጥንት ጥንካሬ:- የቫይታሚን ኬ እጥረት አጥንታችን ጥንካሬ እንዳይኖረው የሚያድርግ ሲሆን፥ እንደ ሰላጣ ያሉ ምግቦችን በእለታዊ መግባችን ውስጥ አዘውትሮ መጠቀም ግን እንዲህ ላሉ ችግሮች እንዳንጋለጥ እና ጠንካራ አጥንት አንዲኖረን ይረዳልም ተብሏል። 5. የእንቅልፍ እንጦት ችግርን ለመከላከል:- የእንቅልፍ ማጣት ችግር ያለባቸው ሰዎች ሰላጣን አዘውትሮ መመገብ ተመራጭ መፍትሄ መሆኑንም ነው የተነገረው። ከዚህ በተጨማሪም ሰላጣ አነስተኛ ካሎሪ ስላለው እና በውስጡ ምንም ስብ ስለሌለው እንዲሁም በፕሮቲንና ማዕድናት የበለፀገ በመሆኑ አዘውትሮ መመገቡ ጠቀሜታ እንዲኖረው ያደርጋል ነው የተባለው

የጨው መብዛት የሚያመጣው የጤና ጣጣ!!! ጨው 40 በመቶ [40%] ሶዲየም እና 60 በመቶ [60%] ክሎራይድ በውስጡ የያዘ ሲሆን በጣም በትንሹ (trace) ካልሲየም፣ ፖታሽየም፣ ብረትና ዚንክ ሊይዝ
የጨው መብዛት የሚያመጣው የጤና ጣጣ!!! ጨው 40 በመቶ [40%] ሶዲየም እና 60 በመቶ [60%] ክሎራይድ በውስጡ የያዘ ሲሆን በጣም በትንሹ (trace) ካልሲየም፣ ፖታሽየም፣ ብረትና ዚንክ ሊይዝ ይችላል። በአብዛኛው ጨው አዮዲን ተጨምሮበት ለፍጆታ ይቀርባል። አብዛኛው ምግብ ውስጥ ጨው አለ። ምንም ነገር በልኩ መጠቀም ትክክል ቢሆንም 90 በመቶ (90%) የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ግን ጨውን ከልክ በላይ ይጠቀማል። በመሆኑም ከታች ለዘረዘርኳቸው በሽታዎች ይጋለጣል። 1. የልብ ድካምና ተያያዥ በሽታዎች የጨው በደም ውስጥ ከፍ ማለት ውሃ ከሚፈለገው በላይ ወደ ደም ስር በመሳብ የደም ግፊትን ከፍ ያደርጋል። የደም ግፊት ደሞ በልብ ላይ ጫና በመፍጠር ከጊዜ ወደ ጊዜ ልብን ያደክማል። ማንኛውም ሰው የጨው መጠንን በመቀነስ የሚጠቀም ሲሆን የደም ግፊትና የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች ግን ከአንድ ማንኪያ ወይም ከ6 ግራም በታች እንዲወስዱ ይመከራል። 2. የጨጓራ ካንሰር በአለማችን በገዳይነት በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጠው የጨጓራ ካንሰር ጨው በብዛት በሚጠቀሙ ሰዎች ይበዛል። ጨው በብዛት የሚጠቀሙ ስዎች በልኩ ከሚጠቀሙ ሰዎች አንዛር ሲታይ በጨጓራ ካንሰር የመያዝ እድላቸው በ 68 በመቶ {68%} ከፍ ይላል። ለዚህ ብዙ ማብራሪያ ቢኖረውም የኤች ፓይሎሪ ባክቴሪያ ማደግና የጨጓራ ግድግዳ መቁሰል በዋንኛነት ይጠቀሳሉ። 3. ስትሮክ (ወደ አንጎል የሚሄድ ደም መቋረጥ ወይም አንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ)፣ ይህም ችግር ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር ይያያዛል። 4. የደም ግፊትና እሱን ተከትሎ የሚመጣው የጤና እክል። ለሌሎች ያጋሩ! ህይወት ያድኑ!

ፎቢያዎች ፎቢያ ለአንድ ነገር ወይም ሁኔታ ምክኒያታዊ ያልሆነ ከፍተኛ ፍርሀት ማለት ሲሆን የአንዳንድ ሰዎችን ህይወት ከባድ ሊያደርገው ይችላል። የተወሰኑ ፎቢያዎች እነሆ •አኩሎፎቢያ (Achulopho
ፎቢያዎች ፎቢያ ለአንድ ነገር ወይም ሁኔታ ምክኒያታዊ ያልሆነ ከፍተኛ ፍርሀት ማለት ሲሆን የአንዳንድ ሰዎችን ህይወት ከባድ ሊያደርገው ይችላል። የተወሰኑ ፎቢያዎች እነሆ •አኩሎፎቢያ (Achulophobia)- የጨለማ ፍርሀት •አክሮፎቢያ (Acrophobia) የከፍታ ፍርሀት •አውቶፎቢያ (Autophobia) የብቸኝነት ፍርሀት •ክላስትሮፎቢያ (Claustrophobia) ትፍግፍግ ያለ ቦታ ፍርሀት •ሳይኖፎቢያ (Cynophonia)የውሻ ፍርሀት •ኢሉሮፎቢያ (Elurophobia) የድመት ፍርሀት •ጋሞፎቢያ (Gamophobia)የትዳር ፍርሀት •ሄሞፎቢያ (Hemophobia)የደም ፍርሀት •አያትሮፎቢያ (Iatrophobia)የዶክተር ፍርሀት •ሎኪኦፎቢያ (Lockiophobia)የምጥና የመውለድ ፍርሀት •ሙሶፎቢያ (Musophobia)የአይጥ ፍርሀት •ኔክሮፎቢያ (Necrophobia)የሞተ ነገር ፍርሀት •ኦፊዲኦፎቢያ (Ophidiophobia)የእባብ ፍርሀት •ፓቶፎቢያ (Pathophobia)-መታመምን መፍራት •ፊሎፎቢያ (Philophobia)የፍቅር ፍርሀት •ፎቦፎቢያ (Phobophobia)የፍርሀት ፍርሀት •ፖለቲኮፎቢያ (Politicophobia) የፓለቲከኞች ወይም የፓለቲካ ሂደት ፍርሀት •ስኮሊኦኖፎቢያ (Scolionophobia) የትምህርት ቤት ፍርሀት •ትሪፓኖፎቢያ (Trypanophobia)መርፌ የመወጋት ፍርሀት •ታናቶፎቢያ (Thanatophobia)የሞት ፍርሀት •ዜኖፎቢያ (Xenophobia)መጤ የሆነ ሰው ፍርሀት ፎቢያዎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብቻዎን እንዳልሆኑ ያስታውሱ፡፡ ከመቶ ሰዎች አስሩ የሆነ አይነት ፎቢያ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ያለ መድሀኒት በንግግር ህክምና specifically behavioral therapy) ሊታከሙ ይችላሉ፡፡

➥ ፎሊክ አሲድ የቫይታሚን B9 ሰው ሰራሽ ቅርጽ ነው፣ እንዲሁም ፒትሮይልሞኖግሉታሚክ አሲድ በመባልም ይታወቃል። እንደ ዱቄት እና የቁርስ ምግቦች ባሉ ተጨማሪዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል እና በተዘጋ
➥ ፎሊክ አሲድ የቫይታሚን B9 ሰው ሰራሽ ቅርጽ ነው፣ እንዲሁም ፒትሮይልሞኖግሉታሚክ አሲድ በመባልም ይታወቃል። እንደ ዱቄት እና የቁርስ ምግቦች ባሉ ተጨማሪዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል እና በተዘጋጁ የምግብ ምርቶች ላይ ይጨመራል። እንደ ፎሌት ሳይሆን ሁሉም የሚበሉት ፎሊክ አሲድ ወደ ቫይታሚን B9 - 5-MTHF - ወደ የምግብ መፍጫ ስርዓትዎ አይለወጥም። በምትኩ፣ ወደ ጉበትዎ ወይም ወደ ሌላ ቲሹ መቀየር አለበት። ሆኖም, ይህ ሂደት በአንዳንድ ሰዎች ላይ ቀርፋፋ እና ውጤታማ አይደለም። ➥ ከፍተኛ መጠን ያለው ያልተመጣጠነ ፎሊክ አሲድ ከበርካታ የጤና ችግሮች ጋር ተያይዞ በመምጣቱ ይህ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ ፎሊክ አሲድ ከሌሎች ቢ ቪታሚኖች በተለይም ቫይታሚን B6 መውሰድ ለውጡን የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል። ✍️ ያልተመጣጠነ ፎሊክ አሲድ ጎጂ ነው? ➥ ለረጅም ጊዜ ከፍ ያለ የ ፎሊክ አሲድ ያልተዋሃደ መጠን በጤና ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊኖረው ይችላል ፣ ከእነዚህም መካከል 📌📌 የካንሰር አደጋ መጨመር - ከፍተኛ መጠን ያለው ያልተመጣጠነ ፎሊክ አሲድ ከካንሰር ስጋት ጋር ይያያዛል። 📌📌 ያልታወቀ B12 እጥረት - በአረጋውያን መካከል ከፍተኛ የፎሊክ አሲድ መጠን የቫይታሚን B12 እጥረትን ሊደብቅ ይችላል። ያልታከመ የቫይታሚን B12 እጥረት ለአእምሮ ማጣት አደጋን ይጨምራል እና የነርቭ ተግባርን ይጎዳል። 400 mcg ትንሽ እና ዕለታዊ ልክ መጠን እንኳ ያልተዋሃደ ፎሊክ አሲድ በእርስዎ ውስጥ እንዲከማች ሊያደርግ ይችላል። ➥ ባጠቃላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ያልተመጣጠነ ፎሊክ አሲድ በጤና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችል ጥናቶች አመልክተዋል። ➥ ከፍተኛ መጠን ያለው ፎሊክ አሲድ መውሰድ ያልተዋሃደ ፎሊክ አሲድ በደም ውስጥ እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል።

የጨጓራ ባክቴሪያ ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ የሚባለዉ ባክቴሪያ የጨጓራ ኢንፌክሽን እንዲከሰት የሚያደርግ የባክቴሪያ አይነት ሲሆን ይህ ኢንፌክሽን በብዛት የሚከሰተዉ በልጅነት የዕድሜ ክልል ነዉ፡፡ ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ቁስለት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሁነኛ መንስዔዎች ዋነኛዉ ሲሆን ኢንፌክሽኑ በአለማችን ከግማሽ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ አንደሚታይ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ የህመሙ ምልክቶች ብዙዎች የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ እንፌክሽን የተፈጠረባቸዉ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አይታይባቸዉም/ላይኖራቸዉ ይችላል ፡፡ የህመም ምልክቶችም ከታዩ የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ • የሆድ ላይ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት • ጨጓራዎ ባዶ ሲሆን የሚባባስ የጨጓራ ላይ ህመም • ማቅለሽለሽ • የምግብ ፍላጎት መቀነስ • በተደጋጋሚ ማስገሳት • የሆድ መንፋት • የክብደት መቀነስ (ለመቀነስ ሳይፈልጉ) መከሰት ናቸዉ፡፡ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚጠበቅብዎ መቼ ነዉ? ጤና ተቋማትን መጎብኘት የሚያስፈልጎት • ከፍተኛና የማያቋርጥ የሆድ ላይ ህመም ካጋጠመዎ • የመዋጥ ችግር ካለዎ • ደም የተቀላቀለበት ወይም የአስፋልት ሬንጅ የመሰለ/ የጠቆረ ሰገራ ከወጣ • ቀይ ወይም የቡና አተላ የመሰለ ነገር ካስታወከዎ በአፋጣኝ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ ለኢንፌክሽኑ ሊያጋልጥዎ የሚችሉ ነገሮች • በተፋፈገ/በተጨናነቀ ቦታ መኖር • ንፁህ የዉሃ አቅርቦት በሌለበት መኖር • ንፅህናዉ በማይጠበቅ ሁኔታ ዉስጥ መኖር • የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ባክቴሪያል እንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች • የደም ምርመራ • የትንፋሽ ምርመራ/ዩሪያ ብሬዝ ቴስት • የሰገራ ምርመራ ናቸዉ፡፡ ሊደረግ የሚችል ህክምና የባክቴሪያዉ እንፌክሽን መኖሩ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያዎ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባክቴሪያዉን ሊያጠፋ የሚችሉ መድሃኒቶች ሊታዘዝልዎ ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ሊያደርሰዉ የሚችለዉ ጉዳት/ Complications ከጨጓራ ባክቴሪያ እንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶች • ቁስለት፡- የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራዎን መከላከያ እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ የጨጓራ አሲዱ ጨጓራዎ ላይ ቁስል አንዲከሰት ያደርጋል፡፡ • የጨጓራ ሽፋን እንዲቆጣ ያደርጋል- የጨጓራ ባክቴሪያ ጨጓራዎን በመቆጥቆጥ እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡ • የጨጓራ ካንሰር፡- የጨጓራ ባክቴሪያ ለተወሱ የጨጓራ ላይ ካንሰሮች መከሰት ዋነኛ መንስኤ ሊሆን ይችላል።

የትግሬ ወራሪ ያለቁበትን ታጣቂዎች ንፁሃን አድርጎ ድራማ መስራት ጀምሯል! በጦር ሜዳ ያለቁበትን ጭኖ ወስዶ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸው ናቸው እያለ ትኩስ ቀብር እያሳየ ነው። በዚህ ወቅት ትግራይ ውስጥ ከ
የትግሬ ወራሪ ያለቁበትን ታጣቂዎች ንፁሃን አድርጎ ድራማ መስራት ጀምሯል! በጦር ሜዳ ያለቁበትን ጭኖ ወስዶ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸው ናቸው እያለ ትኩስ ቀብር እያሳየ ነው። በዚህ ወቅት ትግራይ ውስጥ ከእሱ ውጭ ማንም ኃይል የለም። ውሸት የለመደበት ቡድን ግን አዲስ ቀብር እያሳየ ተጨፈጨፉብኝ እያለ ነው። በየግንባሩ በመኪና እየጫነ የወሰደው አስከሬን ብዙ ነው። ይህን ሁሉ እንደ አዲስ እየቀበረ ንፁሃን ተጨፈጨፉብኝ እንደሚል ቀደም ብሎ የተገመተ ነው። በፎቶው የሚታየው ትናንት እንደ አዲስ አጀንዳ አድርጎ በሚዲያ ያሳየው ቀብር ነው። ጦርሜዳ አምጥቶ ያስፈጃቸውን በጅምላ ቀብሮ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፀመብኝ እያለ ነው።

✍የአይን ቆብ ላይ የሚፈጠር እብጠት 👉 ይህ ማለት የላይኛው የአይን ቆብ ብግነት ወይም መቆጣት መቅላት ማበጥ ማለት ሲሆን ይህ ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ አይደለም፡፡ 👉 👉 መንስኤዎች 📌 በ
✍የአይን ቆብ ላይ የሚፈጠር እብጠት 👉 ይህ ማለት የላይኛው የአይን ቆብ ብግነት ወይም መቆጣት መቅላት ማበጥ ማለት ሲሆን ይህ ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ አይደለም፡፡ 👉 👉 መንስኤዎች 📌 በባክቴሪያ ኢንፌክሽን 📌 የአይን እጢ በአግባቡ ስራውን አለመስራት 📌 የአይን መድረቅ 📌 የአይን ቆብ በፈንገስ መጠቃት 📌 አብዛኛው መንስኤዎች የሚያያዙት ከባክቴሪያ እና የታችኛው ቆብ ከመጠን በላይ እድገት ጋር ነው፡፡ 👉 👉 ምልክቶች 📌 ቀይ ያበጠ የአይን ቆብ 📌 የሚነሳ ወይም የሚቀራረፍ የአይን ቆብ 📌 የሚያሳክክ የአይን ቆብ 📌 የእንባ ማፍሰስ 📌 ብርሃን መጥላት 📌 አይን ውስጥ የመቆርቆር ስሜት 📌 የአይን ብዥታ 👉 👉 እንዴት መከላከል ይቻላል 📌 የፊት እና እጅ ንፅህናን መጠበቅ 📌 የአይን አካባቢ የውበት መጠበቂያዎችን ከመተኛትዎ በፊት ይታጠቡ 📌 ከአይን ዕንባ ሲኖር በንጹህ ጨርቅ መጥረግ

➥ ኢፍሎርኒቲን (ቫኒካ) ይህ የመድሃኒት ማዘዣ ክሬም በተለይ በሴቶች ላይ ከመጠን በላይ ለሆኑ የፊት ፀጉር የተዘጋጀ ነው። በቆዳው ላይ የሚተገበር, አዲስ የፀጉር እድገትን ለመቀነስ ይረዳል, ነገር ግን ያለውን ፀጉር አያስወግድም። ➥ ዮጋ - ዮጋ ለጥንካሬ፣ ተለዋዋጭነት እና ሚዛን በጣም ጥሩ ነው። በተጨማሪም ክብደትን ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል, ይህም ሆርሞኖችን ለመቆጣጠር ይረዳል። እንዲሁም አንዳንድ የአኗኗር ለውጦች ማድረግ ይችላሉ። 📌📌 ክብደትን ይቀንሱ - በሴቶች ውስጥ ያለው ሚዛናዊ የሰውነት ክብደት የወር አበባዎን መደበኛ እንዲሆን እና የመፀነስ እድሎዎን ከፍ ሊያደርግ ይችላል። የወንዶች ክብደት መቀነስ የብልት መቆም ተግባርን ለማሻሻል ይረዳል። 📌📌 በደንብ ይመገቡ - የተመጣጠነ አመጋገብ ለአጠቃላይ ጤና አስፈላጊ አካል ነው። 📌📌 የሴት ብልት ምቾትን ይቀንሱ - ከፓራበን ፣ ከግሊሰሪን እና ከፔትሮሊየም ነፃ የሆኑ ቅባቶችን ወይም እርጥበት ማድረቂያዎችን ይጠቀሙ። 📌📌 ያልተፈለገ ፀጉርን ያስወግዱ - ከመጠን በላይ የሆነ የፊት ወይም የሰውነት ፀጉር ካለብዎ ያስወግዱት።

✍️ "የሆርሞን መዛባት ችግር" 🔷 "በቅንነት ሼር በማድረግ ሌላውንም አስተምሩ" ➥ ሆርሞኖች የሰውነትዎ ኬሚካላዊ መልእክተኞች ናቸው። በኤንዶሮኒክ እጢዎች ውስጥ የሚመረቱ እነዚህ ኃይለኛ ኬሚካሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሕብረ ሕዋሳትን እና የአካል ክፍሎችን በመንገር በደምዎ ውስጥ ይጓዛሉ። ሜታቦሊዝምን እና መራባትን ጨምሮ ብዙ የሰውነትዎ ዋና ሂደቶችን ለመቆጣጠር ይረዳሉ። የሆርሞን መዛባት ሲያጋጥምዎ የተወሰነ የሆርሞን መጠን በጣም ብዙ ወይም በጣም ትንሽ ነው። ጥቃቅን ለውጦች እንኳን በመላ ሰውነትዎ ላይ ከባድ ተጽእኖ ይኖራቸዋል። አንዳንድ የሆርሞን ደረጃዎች በህይወትዎ በሙሉ ሲለዋወጡ እና የተፈጥሮ እርጅና ውጤት ብቻ ሊሆን ይችላል፣የእርስዎ endocrine እጢዎች የምግብ አዘገጃጀቱን ሲሳሳቱ ሌሎች ለውጦች ይከሰታሉ። ✍️" የሆርሞን መዛባት ምልክቶች " ➥ ሆርሞኖች በአጠቃላይ ጤንነትዎ ላይ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። በዚህ ምክንያት የሆርሞን መዛባትን የሚያመለክቱ ሰፋ ያሉ ምልክቶች አሉ። በወንዶች እና በሴቶች ላይ የሚከሰቱ የተለመዱ የሆርሞን መዛባት ሁኔታዎች የሚያስከትሉት ምልክቶች፦ 📌📌 የክብደት መጨመር 📌📌 በትከሻዎች መካከል የስብ ክምችት ያልተገለፀ, እና አንዳንድ ጊዜ ድንገተኛ የሆነ 📌📌 ክብደት መቀነስ 📌📌 ድካም 📌📌 የጡንቻ ድክመት 📌📌 የጡንቻ ህመም 📌📌 ግትርነት 📌📌 በመገጣጠሚያዎችዎ ላይ ህመም, ጥንካሬ ወይም እብጠት 📌📌 የልብ ምት መጨመር ወይም መቀነስ 📌📌 ማላብ 📌📌 ለቅዝቃዜ ወይም ለሙቀት ስሜታዊነት መጨመር 📌📌 የሆድ ድርቀት 📌📌 በተደጋጋሚ ሽንት 📌📌 የውሀ ጥማት መጨመር 📌📌 የረሃብ ስሜት መጨመር 📌📌 የወሲብ ፍላጎት መቀነስ 📌📌 የመንፈስ ጭንቀት ወይም ብስጭት 📌📌 ብዥ ያለ እይታ 📌📌 መሃንነት 📌📌 ቀጭን ፀጉር ወይም የተሰባበረ ጸጉር እና 📌📌 ደረቅ ቆዳ በሆርሞን መዛባት ምክንያት የሚከሰቱ ምልክቶች ናቸው ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች አሉ ማለት ቀጥታ የሆርሞን መዛባት አለባችሁ ማለት አይደለም። ✍️ በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች ➥ በመውለድ ዕድሜ ላይ ባሉ ሴቶች ውስጥ በጣም የተለመደው የሆርሞን መዛባት ፖሊስቲክ ኦቭቫርሪ ሲንድሮም (PCOS) ነው። በነዚህ ደረጃዎች ውስጥ መደበኛ የሆርሞን ዑደትዎ በተፈጥሮ ይለወጣል። በጉርምስና ፣ እርግዝና ፣ ጡት በማጥባት እና በማረጥ ወቅት የሆርሞን ለውጥ ይኖራል። በሴቶች ላይ የሚታዩ የሆርሞን መዛባት ምልክቶች፦ 📌📌 ከባድ ወይም መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ 📌📌 ተደጋጋሚ የወር አበባን ጨምሮ hirsutism፣ ወይም በፊት፣ አገጭ፣ ወይም ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ ከመጠን ያለፈ ፀጉር መውጣት 📌📌 በደረት ወይም በላይኛው ጀርባ ላይ ብጉር 📌📌 የፀጉር መርገፍ 📌📌 የቆዳ መጨለም(መጥቆር) ፣ በተለይም የአንገት እብጠቶች ፣ ብሽሽት ውስጥ እና ከጡቶች በታች የቆዳ ለውጦች 📌📌 የሴት ብልት መድረቅ 📌📌 በወሲብ ወቅት ህመም 📌📌 የለሊት ላብ 📌📌 ራስ ምታት ይከሰታሉ። ✍️ በወንዶች ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች ➥ ቴስቶስትሮን በወንዶች እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል። በቂ ቴስቶስትሮን ካላመረቱ, የተለያዩ ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል። በአዋቂ ወንዶች ውስጥ የሆርሞን መዛባት ምልክቶች፦ 📌📌 gynecomastia, ወይም የጡት ቲሹ እድገት 📌📌 የጡት ልስላሴ 📌📌 የብልት መቆም ችግር (ED) 📌📌 የጢም እድገት እና የሰውነት ፀጉር እድገት መቀነስ 📌📌 የጡንቻን ብዛት ማጣት 📌📌 የአጥንት ክብደት መጥፋት 📌📌 የማተኮር ችግር ✍️ የሆርሞን መዛባት መንስኤዎች ➥ የሆርሞን መዛባት ብዙ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች አሉ። መንስኤዎቹ በየትኞቹ ሆርሞኖች ወይም እጢዎች ላይ ተመርኩዘው ይለያያሉ። የሆርሞን መዛባት የተለመዱ ምክንያቶች፦ 📌📌 የሆርሞን ሕክምና መድሃኒቶች 📌📌 እንደ ኪሞቴራፒ ያሉ የካንሰር ሕክምናዎች 📌📌 እብጠቶች 📌📌 ካንሰርም ሆነ አደገኛ ፒቱታሪ ዕጢዎች 📌📌 የአመጋገብ መዛባት 📌📌 ውጥረት/ጭንቀት እና 📌📌 የሰውነት ጉዳት የተለመዱት የሆርሞን መዛባት መንስኤ ናቸው። እንደ የስኳር በሽታ ያሉ ህመሞች መጀመሪያ ላይ በሆርሞን አለመመጣጠን ምክንያት ሊከሰቱ ቢችሉም, ሁኔታዎቹ መኖራቸው ተጨማሪ የሆርሞን መዛባት ሊያስከትል ይችላል። ✍️ በሴቶች ላይ የሆርሞን መዛባት የሚያስከትሉ ብዙ ምክንያቶች ከመራቢያ ሆርሞኖች ጋር የተያያዙ ናቸው። የተለመዱ መንስኤዎች 📌📌 ማረጥ 📌📌 የመጀመሪያ ደረጃ የእንቁላል እጥረት ይህም ያለጊዜው ማረጥ ተብሎም ይታወቃል 📌📌 እርግዝና 📌📌 ጡት ማጥባት 📌📌 PCOS 📌📌 እንደ የወሊድ መከላከያ ክኒኖች ያሉ የሆርሞን መድኃኒቶች ✍️ የህክምና ሁኔታ ➥ የሆርምን መዛባት ሲኖር የደም ምርመራ ይደረጋል ይህ በሰውነታችሁ ያለውን የታይሮይድ፣የኤስትሮጂን እና የቴስቴስትሮን መጠን ለማወቅ ይረዳል። በተጨማሪም እንደ ባዮፕሲ ፣MRI፣ ኤክስሬይ እና የወንድ የዘር ህዋስ ምርመራ ይደረጋል። ➥ የሴት ብልት ኢስትሮጅን በጾታ ግንኙነት ወቅት የሴት ብልት መድረቅ ወይም ህመም እያጋጠመዎት ከሆነ የኢስትሮጅን ክሬም፣ ታብሌት ወይም ቀለበት ለመጠቀም መሞከር ይችላሉ። ይህንን የአካባቢ ሕክምናን በመጠቀም በደም ውስጥ ወደ ትክክለኛው የአካል ክፍል ከሚጓዙት ከስርዓታዊ ኢስትሮጅን ወይም ከኢስትሮጅን ጋር የተያያዙ ብዙ ስጋቶችን ያስወግዳል። ➥ የሆርሞን የወሊድ መከላከያ - የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ የወር አበባ ዑደትን ለመቆጣጠር ይረዳል። የሆርሞን የወሊድ መከላከያ ዓይነቶች 📌📌 የወሊድ መከላከያ ክኒን 📌📌 የወሊድ መከላከያ መርፌ 📌📌 የሴት ብልት ቀለበት እና 📌📌 በማህፀን ውስጥ ያለ መሳሪያ (IUD) ያጠቃልላል። በተጨማሪም ብጉርን ለማሻሻል እና ለፊት እና በሰውነት ላይ ተጨማሪ ፀጉርን ለመቀነስ ይረዳል። ➥ ፀረ-አንድሮጅን መድኃኒቶች - አንድሮጅንስ በሴቶች እና በወንዶች ውስጥ የሚገኙ የወንድ የፆታ ሆርሞኖች ናቸው። ከፍተኛ androgen መጠን ያላቸው ሴቶች androgens የሚያስከትለውን ውጤት የሚገድብ መድሃኒት ለመውሰድ ሊመርጡ ይችላሉ። ። ➥ የታይሮይድ ሆርሞን ሕክምና - ሃይፖታይሮዲዝም ካለብዎ ሰው ሰራሽ የሆነው የታይሮይድ ሆርሞን ሌቮታይሮክሲን የሆርሞን መጠን ወደ ሚዛን እንዲመለስ ሊያደርግ ይችላል። ➥ Metformin - Metformin የPCOS ምልክቶች ያለባቸውን አንዳንድ ሴቶች ሊረዳቸው የሚችል ዓይነት 2 የስኳር በሽታ መድኃኒት ነው። ይህ መድሀኒት የ androgen ደረጃዎችን ለመቀነስ እና እንቁላልን ለማበረታታት ይረዳል። ➥ ፍሊባንሰሪን (ADD) እና ብሬሜላኖቲድ እና ቪሊሲ በቅድመ ማረጥ ሴቶች ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎትን ለማከም የሚረዱ መድሃኒቶች ናቸው። እነዚህ መድሃኒቶች እንደ ከባድ የማቅለሽለሽ እና የደም ግፊት ለውጦች ካሉ ከአንዳንድ ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች ጋር ሊመጡ ይችላሉ።

ሲጋራ ለማቆም የሚረዱት ሁለቱ መድሀኒቶች መግባት አለባቸው ======================================== የሲጋራ ሱስ በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት የሚታወቅ ቢሆንም ሱሱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን ለማቆም ይቸገራሉ። ለዚህ ዋነኛው ምክኒያት ሲያቆሙ የሚከሰተው "አምጣ አምጣ" የሚለው ግፊትና የሚፈጠረው የመቅበጥበጥ ስሜት ጭንቀት ስለሚፈጥሩ ግለሰቡ ሲጋራ ለማጨስ ይገፋፋል። ከዚያም ሲያጨስ ስሜቱ ይረጋጋና ደስ ይለዋል። እሽክርክሪቱ ይቀጥላል። ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ለማቆም ከመወሰናቸው በፊት ሲያቆሙ ስለሚፈጠረው የስሜት መረበሽ መገንዘብና እቅድ ማውጣት አለባቸው። እንደዛ ካልሆነ ለማቆም የሚደረገው ጥረት ውጤታማነቱ ዝቅተኛ ነው። እንደሱሱ አይነት ለማቆም የሚያግዙ መድሀኒቶች አሉ። የሲጋራ ሱስን ለማቆም የሚረዱት ሁለት መድሀኒቶች ቫሬኒክሊን (Vareniclin) እና ዌልቡትሪን(Wellbutrin) ናቸው። የመጀመሪያው መድሀኒት ከሲጋራ የሚገኘውን እርካታ ያጠፋል። ግለሰቡ ቢያጨስም ምንም ስሜት ስለማይሰጠው ለመተው ይገፋፋል። ሁለተኛው መድሀኒት ደግሞ ማጨስ ሲያቆሙ የሚፈጠውን የመቅበጥበጥና የድብርት ስሜት ይቀርፋል። አንዳንድ ሰዎች በግላቸው ከውጭ አስመጥተው ካልሆነ በስቀር ሁለቱም መድሀኒቶች በሀገራችን አይገኙም። ምክኒያቱ ደግሞ "ውድ ናቸው" የሚል ነው። አንድ ግለሰብ በሱስ ምክኒያት ሲታመም ከባድ ምርመራዎችና ከባድ ህክምናዎች ይሰጡታል። በዛ ላይ የሌሎች ታካሚዎችን ወረፋ ያስረዝማል። ለምሳሌ ከሱስ ጋር የተያያዘ አንድ ሰው ፅኑ ህክምና ክፍል ከተኛ አንድ በህይወትና በሞት መሀከል ያለ ሌላ ሰው "ምንም ማድረግ አንችልም ፅኑ ህክምና ክፍል ውስጥ አልጋ የለም።" ይባላል። ዋጋውን በደንብ ካሰላነው ሱስ ለማቆም የሚግዙት መድሀኒቶች "በጣም ውድ" እንዳልሆኑ ይገባናል። ለማንኛውም የሱስ ህክምና በተመላላሽና በአስተኝቶ ህክምና ዘውዲቱ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ክፍል ይሰጣል። ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም! ዶ/ር ዮናስ ላቀው

አስቤ አስቤ ያልገባኝ ህመም ================ አንዳንድ ህመም ውስብስብ ነው። ጠለቅ ብለው ካልመረመሩት ለመረዳት ይከብዳል። ዛሬ የምነግራችሁ ህመም አስቤ አስቤ አልገባኝም። አንቶን ሲንድረም (Anton syndrome) ይባላል። ይህ ህመም የሚከሰተው እይታን የሚቆጣጠረው የአእምሮ ክፍል ውስጥ የደም ቧንቧ ሲዘጋ ወይም ደስ ሲፈስ ነው። አንቶን ሲንድሮም ያለባቸው ሰዎች ማየት ባይችሉም ማየት እንዳልቻሉ ግን አያውቁም። "በጭራሽ ማየት አላቃተኝም እያየሁ ነው!" ብለው ድርቅ ይላሉ። አእምሯቸው ሲመረመር የእይታ ማእከሉ ቢዘጋም እይታን የሚያገናዝበው ክፍል ግን በራሱ ስራውን ቀጥሏል ማለት ነው። ደግነቱ ህመሙ የመከሰት እድሉ እጅግ ዝቅተኛ ነው። ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም! ዶ/ር ዮናስ ላቀው