ch
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

前往频道在 Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

显示更多

📈 Telegram 频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias 的分析概览

频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 946 名订阅者,在 医学 类别中位列第 1 156,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 680

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 946 名订阅者。

根据 28 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -539,过去 24 小时变化为 -5,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.64%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.06% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 115 次浏览,首日通常累积 1 408 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

凭借高频更新(最新数据采集于 29 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 医学 类别中的关键影响点。

19 946
订阅者
-524 小时
-1197
-53930
帖子存档
ክብደት ለመቀነስ ማስወገድ የሚገቡን ምግቦች ጠቃሚ መረጃ እባኮ ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ ክብደት መቀነስ ቀላል ተግባር ባይሆንም ሰዎች ክብደት በመጨመራቸው የሚመጡባቸውን የጤና ችግሮች ለማስወገድ ጥረት ሲያደርጉ ያስተውላሉ፡፡ ክብደታችን ከልክ ሲያልፍ ከሚመጡብን ወስብስብ የጤና ችግሮች መሃከል የልብ በሽታ፣ስትሮክ፣የስኳር በሽታ ፣ድብርት እና ካንሰር ይጠቀሳሉ ፡፡ ክብደት መቀነስ ውስብስብ የጤና ችግሮችን ከመቀልበስ ባሻገር በየጌዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ጤነኛ አመጋገብ የተስተካከለ ክብደት እንዲኖረን ያደርጋል ፡፡ በአንፃሩ የምንመገበውን ምግብ አለማወቅ የምንፈልገውን ክብደት ለመቀነስ አዳጋች ያደርግብናል፡፡ ከታች የተዘረዘሩት ምግቦች ደጋግመን ከተመገብናቸው ክብደት የመቀነስ አላማችን ግቡን እንዳይመታ ያደርጉብናል፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ፡፡ ቺፕስ እና ፍሬንች ፍራይስ (ድንች ጥብስ) ከፍተኛ የሆነ የካሎሪና የቅባት መጠን ያለው በመሆኑ ክብደት ለመቀነስ ለሚያስብ ሰው የሚመከሩ አይደሉም፡፤የተጠበሰ ድንች የደም ውስጥ የስኳር እና ኢንሱሊንን መጠን በመጨመር የምግብ አወሳሰዳችንን የተዛባ ያደርገዋል፡፡ ድንች መመገብን ከወደዱ ከመጥበስ ይልቅ የተቀቀለ ቢሆን ጤነኛ ይሆናል ፡፡ የሶዳ መጠጦች በሶዳ መጠጦች ውስጥ የሚገኙ አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች የረሃብ ስሜትን በመፍጠር አብዝተን እንድንመገብ ያደርጉናል ፡፡ ጥማችንን ለሙቁረጥ ንፁህ ውሃ አልያም ውሃ በሎሚ አማራጭ ብናደርግ ለጤናችን አሰብን ማለት ነው ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሶዳ መጠጦችን አብዝቶ መጠጣት የሆድ አካባቢ ስቦችን ይጨምራል ፡፡ ቅባት የበዛበት ስጋ ጮማ እንዲሁም የአሳማ ስጋ እጅግ ብዙ ስብ ስለሚኖረው ክብደትን ይጨምራል ፡፡ ፈንዲሻ ዘይት አብዝቶ ስለሚወስድ ደጋግሞ መመገብ ክብደት መቀነስ ለሚፈልግ ሰው አይመከርም፡፡ ማርጋሪን ማርጋሪን ከቅቤ የበለጠ እጅግ በቅባት የተሞላና በምግብ ይዘቱም ደካማ ነው ፡፡አብዝተን እና ደጋግመን ከወሰድነው ክብደት ከመጨመር ባሻገር ለልብ በሽታ ያጋልጠናል፡፡ ነጭ ዳቦ (ፉርኖ) በምግብ ይዘቱ እጅግ ደካማ ሲሆን በውስጡ የያዘው ካርቦሃይድሬት ውፍረትን ያስከትላል ፡፡ ስንመገበው የማጥገብ ሳይሆን ቶሎ ቶሎ የመራብ ስሜትን ይፈጥርብናል፡፡ በመሆኑም ተፈጥሮአዊ የሆነውን ከስንዴ የሚዘጋጅ ዳቦ ብንጠቀም ይመከራል ፡፡ፓስታ እና የመሳሰሉትንም አዘውትረን ከመመገብ መቆጠብ አለብን ፡፡ የአልኮል መጠጦች የአልኮል መጠጦች ምንም አይነት የምግብ ይዘት የሌላቸው ሲሆን የካርቦሃይድሬት ፣ የስብና የፕሮቲን መፈጨት ሂደትን በማዘግየት ተጨማሪ ስብ በሰውነታችን እንዲከማች ያደርጋል ፡፡ የታሸጉ ጭማቂዎች የታሸጉ የፍራፍሬ ጭማቂዎች ጁስ በመደረግ ሂደት ተፈጥሮአዊ የምግብ ይዘታቸውን ከማጣታቸው ባሻገር የያዙት የስኳር መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ክብደትን ይጨምራሉ፡፡

ለሴቶች... . የእርግዝናን መከላከያዎችን የሚመለከቱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው :- . 1) በወር አበባ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ቢደረግ እርግዝና ይከሰት ይሆን ? የወር አበባን በምታይ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት የማርገዝ ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አይከሰትም ለማለት አይቻልም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የወር አበባ ከማለቁ በፊት እንቁላል ሊፈጠር ስለሚችልና ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር በማኅፀን ውስጥ እስከ 3 ቀን ወይንም ከዚያ በላይ የሚቆይበት አጋጣሚ ስለሚኖር ነው፡፡ 2) ጡት ማጥባት እርግዝናን ይከላከላል ? ጡት ማጥባት የእንቁላል መፈጠርን የሚከላከል ቢሆንም የሚቆይበት ጊዜ ግን ለጥቂት ወራት ብቻ ስለሆነ ሰውነት ወደቀድሞ ሁኔታው በሚመለስ ጊዜ የማርገዝ ዕድልም አብሮ ስለሚመለስ ጡት ማጥባት እርግዝናን የሚከላከልበት ጊዜ ውስን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ 3) የመጀመሪያ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ላልተፈለገ እርግዝና ያጋልጣል ? አዎን! ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላልተፈለገ እርግዝና ላያጋላጥ ይችላል ብለው የሚያስቡ አንዳንዶች ያሉ ቢሆንም ይህ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ሕመምና ደም መፍሰስ ሊያጋጥም የሚችል ቢሆንም እርግዝናን ከመከላከል ጋር ግን ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 4) የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ምን ያህል እርግዝናን ይከላከላሉ ? የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በትክክለኛው መንገድ ከተተገበሩ ከ90% በላይ የሚሆን የመከላከያ አቅም ያላቸው ሲሆን ተአቅቦ ግን ጥርጥር የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጣሪያ ለመጠቀም በሚታሰብ ጊዜ የትኛውን ዓይነት እንደምንመርጥና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሐኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡ 5) በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሁለት ኮንዶሞች ደርቦ መጠቀም በእርግጥ እርግዝናን የበለጠ ይከላከላል? አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሁለት ኮንዶምን ደርቦ በመጠቀም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ሲሆን ይባስ ብሎ በሚፈጠረው ፍጭት (Friction) ምክንያት የኮንዶም መቀደድ በማስከተል ላልተፈለገ እርግዝና ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥን ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሁለት ኮንዶሞችን ደርቦ መጠቅም አይመከርም፡፡ 6) የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን መውሰድ ወዲያውኑ እርግዝናን ይከላከላል? የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች አጠቃቀም እና የሚወሰዱበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ እርግዝናን ለመከላከል ጠቃሚ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወር አበባ በመጣ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን ውስጥ መጀመር ወዲውኑ ከአልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ሲሆን፣ ከዚያ ጊዜ ውጭ ከመጀመሩ ግን ወዲያውኑ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው ኮንዶምን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ 7) ሁሉም የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ከአባለዘር በሽታዎች ይከላከሉ ይሆን? ከወሊድ መቆጣጠሪያዎች ውስጥ ኮንዶምን መጠቀም ብቻ ከአባላዘር በሽታ ራስን መከላከል የሚቻልበት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡ 8) የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች የሰውነት ክብደት ይጨምራሉ? አንዳንድ ሴቶች የሰውነት ክብደት መጨመርን እንዳስከተለባቸው የሚናገሩ ሲሆን ምክንያቱም የምግብ ፍላጎትን መጨመርን ማስከተሉና ፈሳሽ በሰውነታችን እንዲቀመጥ ማድረጉ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠነኛ የሚባል የሰውነት ክብደት መጨመርን ያስከትላሉ፡፡ 9) የወሊድ መቆጣጠሪያን መጠቀም መሃንነትን ያስከትላል? አያስከትልም! ሆርሞኖችን በውስጣቸው የያዙ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ መሃንነትን ያስከትላሉ ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም እነዚህን የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መካንነትን እንደማያስከትሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡ 10) ኮንዶምን በሌሎች ቁሳቁሶች መተካት ይቻላል? በፍፁም አይቻልም! በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በሌሎች እንደ ላስቲክ፣ ፈኛ፣እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ተክቶ መጠቀም በፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ከአልተፈለገ እርግዝናም ሆነ ከአባላዘር በሽታም በጭራሽ እንደማይከላከል ሊያውቁት ይገባል፡፡

ትራኮማ(trachoma)ምንደድን ነው ? """"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" የትራኮማ በሽታ ችላሚድያ ትራኮሚተስ በተባለ ባክቴሪያ የሚመጣ ለአይነ ስውርነት የሚዳርግ በሽታ ነው።ለመጀመሪያ ግዜ በሽታው የታወቀው በ ግብፅ ሀገር በ 15 BC ነው። በአብዛኛው የላይኛውን የአይን ውስጠኛ ክፍል ያጠቃል።በተደጋጋሚ ቁስለቱ ጠባሳን ስለሚፈጥር የአይናችን ጭራ ወደውስጥ ተቀልብሶ የአይናችንን ብሌን ወይም መስታወት ስለሚፈገፍገው ብሌኑ ብርሀንን ማስተላለፍ ስለማይችል አይናችን እይታን ይከለክለናል። ትራኮማ 5ደረጃወች አሉት እነዝህም .ትራኮማ ፎሊኩላይተስ-በአይን ቆብ የውስጠኛው ክፍል 5 ና በላይ ነጫጭ ነጠብጣብ መፈጠር .ትራኮማ ኢንፍላሜሽን--የውስጠኛው አይን ቆብ መቁሰል .ትራኮማ ስካሪንግ-ጠባሳ መፍጠር .ትራኮማ ትሪኪያሲስ-የአይን ጭራ ወደ ውስጥ መቀልበስ .ኮርኒያል ኦፓሲቲይ-የአይን ብሌን ብርሀን ማሳለፍ አለመቻል ናቸው። ትራኮማ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በዋናነት የፊታችንን ንፅህና በአግባቡ ባለመጠበቃችን በሽታው በቀላሉ ከበሽተኛው ሰው ወደ ጤነኛው ሰው በንክኪ ና በዝንቦች አማካኝነት ይተላለፋል። ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በብዛት ይያዛሉ። በአለማችን እስከ 8 ሚሊዮን ሰወች በዚህ በሽታ አይነ ስወውር ሲሆኑ 80 ሚሊየን ሰው ደግሞ በበሽታው ተይዞ ይገኛል። በአለማችን በ 53 ሀገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ በሽታው ይገኛል። ይህን በሽታ ያደጉት ሀገሮች በ20 ኛው ክፍለ ዘመን ሙሉበሙሉ ያጠፉ ሲሆን WHO በ2020 በሽታውን የህብረተሰብ ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ እየሰራ ይገኛል። በአመትብቻ በአለም ላይ 8 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለዚህ በሽታ ወጭ ይደረጋል። የበሽታው ምልክቶች """""""""""""""""""""""""""""""""""" የአይን -መቅላት -መቆጣት - ህመም -ማበጥ -ፈሳሽ -ጭራ መቀልበስ ና የመሳሰሉት ናቸው መከላከያ """""""""""""""" የፊት ንፅህናን መጠበቅ አካባቢን ማፅዳት ና ዝንቦችን ማጥፋት ምልክቱ እንደታየ በቶሎ ተመርምሮ መድሀኒቱን መውሰድ ከፍተኛ የበሽታው ስርጭት ባለበት ስፍራ የዚትሮማክስ መድሀኒት መካላከያ መውሰድ መፀዳጃ ቤትን በአግባቡ መጠቀም ና መያዝ ትራኮማ በሽታ የቤተሰብ ና አካባቢ ንህናን በመጠበቅ ብቻ በቀላሉ መከላከል ይቻላል። ጤና ለሁሉም መልካም ጤንነት

ኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱ ህጻናት ይህችን ዓለም በሁለት መንገድ ይቀላቀላሉ፡- በምጥ ወይም ደግሞ በኦፕሬሽን (surgical delivery by Caesarean section)፡፡ በአሁን ወቅት የህክምና አማራጭ ያላቸው እናቶች አምጦ ከመውለድ ይልቅ በኦፕሬሽን መውለድን እንደተሻለ አማራጭ ሲወስዱት ይታያል፡፡ አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችም በሁለቱም መንገድ መውለድ ያለውን ጠቀሜታና የጎንዮሽ ጉዳት አስረድተው ውሳኔውን ለእናቶች ከመተው ይልቅ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ እናቶችን ሲገፋፉ ይታያል፡፡ ለመሆኑ በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መፈቀድ አለበት? ያለው ጥቅምና ጉዳቱስ ምንድን ነው? በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መወሰን አለበት? 1. አምጦ መውለዱ ለእናትየው ወይም ደግሞ ለህፃኑ ህይወት አደጋ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ሲታመንበት 2. ጽንሱ በጣም የፋፋ/የወፈረ/ ከሆነ እና የእናትየው ማህጸን ጠባብ ከሆነ 3. የጽንሱ አቀማመጥ በትክክል ካልሆነ ማለትም በእርግዝና የመጨረሻዎች ቀናት ጭንቅላቱ ወደታች ካልመጣ 4. በምጥ ወቅት ጽንሱ በቂ ኦክስጅን ካላገኘና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው 5. መንታና ከዚያ በላይ ጽንስ ሲኖር 6. የተራዘመ ምጥ ሲኖር እና 7. እናትየው ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባት፤ የስኳር በሽተኛ ከሆነች፡ የHIV ቫይረስ ካለባት ጥቅሙ፡- በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እናቶችን እና የጽንስን ህይወት ይታደጋል፡፡ እናቶች በምጥ ወቅት ሊሰማቸው የሚችለውን የተራዘመ ስቃይ ያስቀራል። ጉዳቱ፡- 1. ጽንሱን ለማውጣት የሚቀደደው የሰውነት ከፍል ለመዳን ጊዜ ይወስዳል፤ በሰውነት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚድን አይደለም። 2. የእናቶችን የሆስፒታል ቆይታ ያራዝማል፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በፍጥነት አገግመው ልጆቻቸውን ለማጥባትም ሆነ ለመንከባከብ ይቸገራሉ። 3. የመጀመሪያ ልጃቸውን በኦፕሬሽን የወለዱ እናቶች ቀጣይ ልጆችን በተመሳሳይ ሂደት እንዲወልዱ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህም በማህጸን ግድግዳ ላይ ተደጋጋሚ ጠባሳዎች ያስከትላል፤ ቁስሉ በቶሎ ካልዳነ ደግሞ የማህጸን ግድግዳ ከሌላ የሰውነት ከፍል ጋር ሊጣበቅ ይችላል። 4. በምጥ ከሚወልዱ እናቶች ይልቅ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች ለከፍተኛ ደም መፍሰስና እንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በምጥ ከሚወልዱ እናቶች የመሞት ዕድላቸው ሶስት አጥፍ የሰፋ ነው። 5. በኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ የሽንትና የሰገራ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሊጎዱ ይችላሉ ****ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር እናቶች አምጠው መውለድን ቢመርጡ ይመከራል፡፡ አምጠው የሚወልዱ እናቶችም የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንዳለቸው ይናገራሉ፡፡ ዶክተር ሶፊ መልካም ጤንነት ለመላው ኢትዮጵያዊያን

ተቡም፣ በበሽታው ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ የትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ተመርምሮ ሳይታወቅ ያልፋል ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ጉንፋን በሚመስል ምልክት ስለሚጀምር፤ ሆኖም ግን ለሳምንታት ወይም ወራት የሚዘልቅ ተከታታይ የሆነ የሳል ጥቃቶች ሊለወጥ ይችላል። መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ፣ አንዳንዶቹ በትክትክ/ደረቅ ሳል ሊያስተላልፉት ይችላሉ፡፡ አንድ ሀኪም የትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታን ከጠረጠረ፣ በሽታውን በምርመራ ለማረጋገጥ ምርመራ ሊደረግ ይችላል፡፡በምርመራ የማወቅ ሂደቱ አስቀድሞ ከተደረገ፣ የበሽታው ምልክቶች ከባድነት ለመቀነስና አንዳይተላለፍ ለማድረግ የፀረ-ነፍሳት(አንቲባዮቲክስ) መድሃኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ የርስዎ ወይም የልጅዎ ሳል ትክትክ/ደረቅ ሳል ነው ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ከህፃን ኣጠገብ ስለመሆን ጉዳይ ሀኪሙን ማናገር ኣስፈላጊ ነው፡፡ልጅዎ በትክትክ/ደረቅ ሳል በሽታ ተለክፏል ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ ወድያውኑ ሀኪም ዘንድ ይሂዱ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንድ ህፃን አመላካች የሆነውን ሳል ወይም ትክትክ የሚል ድምፅ አይኖረውም፣ ስለዚህ ከባድ የማስተንፈስ ችግር አንዳይኖር በንቃት ያስተውሉ። 3.3.የሳይነስ ቁስል ሳይነስ ቁስል ከፊት ጀርባ የሚገኙት በአየር የተሞሉት ቀዳዳዎች (sinuses) መቁሰል (inflammation) ነው፡፡ ይህ ቁስል በአብዛኛው በራሱ ጊዜ የሚድን ሲሆን በአፍንጫ እና በአይን ዙሪያ ህመምን ያስከትላል፡፡ ከፊትህ ጀርባ በአፍንጫ ቀዳዳ ዙሪያ አራት ጥንድ የሆኑ ቀዳዳዎች(sinuse) ይገኛሉ፡፡እነዚህ ቀዳዳዎች ንፍጥ (mucus) በሚያመርቱ ህዋሳት የተሸፈኑ ሲሆን ይህም ንፍጥ በትንንሽ ፀጉሮች ተገፍቶ ወደ አፍንጫ ይገባል፡፡እነዚህ ቀዳዳዎች ከአፍንጫ ጋር የሚገናኙበት ትንንሽ በሮች አላቸው፡፡እነዚህም አየር፣ ፈሳሽ እና ንፍጥ እንደፈለገው እንዲሄድ ይረዳሉ፡፡ቀዳዳዎቹ ውስጥ የሚመረተው ንፍጥ በጤናማ ጊዜ ቀዳዳዎቹ ውስጥ አይጠራቀምም፡፡ነገር ግን ቀዳዳዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከተዘጉ አሊያም የትንንሽ ፀጉሮቹ እንቅስቃሴ ከተገታ ፈሳሹ በመጠራቀም የሳይነስ በሽታ ምልክቶች እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ጉንፋን ሲይዝህ/ሽ ቀዳዳዎቹን የሚሸፈነው የላይኛው ክፍል በማበጥ ከአፍንጫ ጋር የሚያገናኛቸውን በሮች ይደፍናቸዋል፡፡ስለዚህም ቀዳዳው ውስጥ የሚመረተው ንፍጥና ፈሳሽ እዛው ውስጥ ይጠራቀማል፡፡ይኼ የተጠራቀመ ፈሳሽ ለጀርሞች ምቹ መራቢያ ቦታን ይፈጥራል፡፡ ሁለት አይነት የሳይነስ ቁስል አይነቶች ሲኖሩ እነሱንም በሚኖራቸው የጊዜ ቆይታ እንከፍላቸዋለን፡፡ ከሁለት ሳምንት በላይ የሚቆየው አይነት ሳይነስ መቁሰል በአብዛኛው በቀላል ህክምና የሚድን ሲሆን ሌላኛው አይነት ደግሞ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ እና በተለያዩ መድሃኒቶች በቀላሉ የማይድን ሲሆን አስቸጋሪ በሽታ ነው፡፡አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች በተለየ በዚህ በሽታ በተደጋጋሚ ይጠቃሉ፡፡በተፈጥሮ ለብዙ ነገሮች አለርጂክ የመሆን ባህሪ ካላቸው የሳይነስ ቁስል በተደጋጋሚ ያጠቃቸዋል፡፡እንደ አስም በሽታ ሁሉ ለአበባ ብናኝ፣ ለአዋራ እና ለመሳሰሉት ነገሮች አለርጂክ መሆን በነዚህ ሰዎች ላይ የሳይነስ መቁሰልን ሲያስከትል ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአለርጂ ምከንያት በቀዳዳዎቹ ውስጥ የሚጠራቀመው ፈሳሽ ውስጥ ጀርሞች በመራባት በሽታውን የበለጠ ያጎሉታል፡፡ ስለዚህም በተደጋጋሚ በዚህ በሽታ ይጠቃሉ፡፡ የሳይነስ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? በሽታው የሚከሰተው ሳይነስ ቀዳዳዎች ሲደፈኑ አሊያም ትንንሾቹ ፀጉሮች እንቅስቃሴን የሚያግድ ነገር ሲከሰት ነው፡፡ ኢንፌክሽን ወይም ኢንፌክሽን ያልሆኑ መንስኤዎች ሲኖሩት በአብዛኛው የላይኛው የመተንፈሻ አካላት በሽታን ተከትሎ ይከሰታል፡፡ኢንፌክሽን ካልሆኑት መንስኤዎች መካከል አለርጂ፣ የማቁሰል ብቃት ላላቸው ኬሚካሎች ተጋላጭ መሆን፣ አፍንጫ ላይ የሚወጡ የተለያዩ እንግዳ ነገሮች፣ ካንሰር ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ እንደ አስም ሁሉ ለተለያዩ ነገሮች አለርጂ መሆንን ተከትሎ የሚመጣው አይነት የሳይነስ ቁስል ወቅትን ተከትሎ የመባባስ አዝማሚያ አለው፡፡ በአስም በሽታ የሚጠቁ ሰዎች ይኼኛው በሽታም ያጠቃቸዋል፡፡ በኢንፌክሽን የሚመጣው በባክቴሪያ፣ በቫይረስ አሊያም በፈንገስ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ በቫይረስ የሚመጣው በሽታ በጣም በብዛት የሚታየው እና በራሱ የመዳን ባህሪ ያለው ነው፡፡ከጥርስ ኢንፌክሽን ተነሰተው ወደቀዳዳዎቹ በመግባት የሳይነስ ቁስል የሚያመጡ ባክቴሪያዎች አሉ፡፡ፈንገስ ደግሞ መጀመሪያውኑ የበሽታ የመከላከል አቅሙ በተዳከመ ሰው ላይ ለምሳሌ ለካንሰር በሽታ መድሃኒት (ኬሞቴራፒ) ላይ ያለ ሰው ላይ ይከሰታል፡፡ይህም ከቀላል ሳይነስ ይልቅ ለህይወት የሚያሰጋ ኢንፌክሽን ያመጣል፡፡ የሳይነስ ቁስል ምልክቶች ምንድን ናቸው የሳይነስ መቁሰል በብዛት ከላይኛው የመተንፈሻ አካላቶች በሽታ ጋር ተያይዞ ስለሚከሰት ምልክቶቹን ለብቻው ለይቶ ለማወቅ ይከብዳል፡፡ ጉንፋን የያዘው ሰው የሳይነስ ቀዳዳዎች ቁስለትም አብሮት መከሰቱ አይቀሬ ነው፡፡የሳይነስ በሽታ አፍንጫ በፈሳሽ መታፈን፣ የፊት ህመም፣ እራስ ምታት ይኖረዋል፡፡የሚኖረው ህመም ጎንበስ ሲባል ወይም በጀርባ ሲተኛ የመባስ ባህሪ አለው፡፡ ወፍራም፣ ቢጫ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ ካለ የባክቴሪያ መንስኤነትን ያመላክታል፣ ነገር ግን በቫይረስ በሚመጣው ጉንፋን መጀመሪያ አካባቢም የዚህ አይነት የአፍንጫ ፈሳሽ ሊያስከትል ስለሚችል ለባክቴሪያ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ሌሎች ምልክቶች ለምሳሌ ማስነጠስ፣ ሳል እና ትኩሳትን የመሳሰሉ ምልክቶችም ሊኖሩት ይችላል፡፡ የጥርስ ህመም እና የአፍ ሽታም በባክቴሪያ ከሚመጣው ሳይነስ ጋር ተያያዥነት አላቸው፡፡ አይን እንቅስቃሴን ተከትሎ የሚኖር ህመም ይኖራቸዋል፡፡ የማሽተት አቅምህም ከበፊቱ ሊቀንስ አሊያም እስከነጭራሹ ሊጠፋ ይችላል፡፡ በአለርጂ የሚመጣው በሽታ ደግሞ ወቅትን እየተከተለ ይነሳብሃል፡፡ በክረምት እና በፀደይ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሊያስቸግርህም ይችላል፡፡ የሳይነስ በሽታ ከያዘኝ በኋላ ምን ላድርግ ? በሽታው በብዛት በራሱ የሚድን ሲሆን የተዘጋውን ሳይነስን እና አፍንጫን የሚያገናኘውን በር መክፈት ጥሩ የህክምናው መንገድ ነው፡፡ ውሃ አሙቆ እንፋሎቱን መታጠን ውስጥ የተጠራቀመውን ንፍጥ ስለሚያቀጥን ፈሳሹን በቀላሉ ማስወጣት ትችላለህ፡፡ ንፁህ (ተፈልቶ የቀዘዘ ) ውሃ ቀጭን አፍ ባለው እቃ አድርጎ የአፍንጫን የውስጥ ክፍል ማጠብ ጥሩ መንገድም ነው፡፡ ብዙ ፈሳሽ መጠጣትም ይመከራል፡፡ ከሳምንት ለበለጠ ጊዜ የሚቆይ ከሆነ አሊያም በጣም ሀይለኛ ህመም ካለው ወደሆስፒታል ሄዶ መታየቱ ተመራጭ ነው፡፡በጀርሞች የሚመጣው በቀላል መድሃኒቶች ስለሚድን ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉብህ/ሽ ወደሆስፒታል ሄደህ/ሽ መመርመር ጠቃሚ ነው፡፡ ከሱ በተጨማሪም በአለርጂ ምክንያት የሚመጣው ቁስለት ከሆነ በሽታውን ከሚያባብስብሽ ነገር እራስሽን መጠበቅ ጠቃሚ ነው፡፡ የሳይነስ ቁስለት አንዴ ከያዙ በኋላ ህመሙን በተለያዩ መንገዶች መቀነስም ይቻላል፡፡ የሙቀት እና ቅዝቅዜ መለዋወጥ ህመሙን ስለሚያብሰው በተቻለ አቅም በጣም ሞቃት እና ቀዝቃዛ ቦታዎች ላይ አለመሆን ተገቢ ነው፡፡ከጉንፋን ጋር ተያያይዞ በሳይነስ በሽታ በተደጋጋሚ የምትጠቂ ከሆነ ደግሞ በምትተኚበት ጊዜ ጭንቅላትሽን ከፍ የሚያደርግ ትራስ ማድረግ የሳይነስ በሮች እንዳይዘጉ በማድረግ ሊረዳሽ ይችላል፡፡ መልካም ጤንነት ሰላማቹ ይብዛ ዶክተር ሶፊ ነኝ

የአጥንት ቲቢ የአጥነት ቲቢ የሚባለው እንደሌሎቹ የቲቢ አይነቶች ሁሉ የአጥንት ቲቢም የሚከሰተው በእዚሁ ማይኮባክቴርየም ቲዩበርክሎሲስ በሚባለው ባክቴሪያ አማካይነት ነው። አጥንታችን በእዚህ ባክቴሪያ ሲጠቃ አጥንቱ ከትክክለኛው ስራ ውጭ ይሆናል፡፡ በእዚህም ምክንያት አጥንቱ መግል ሊይዝ ወይም ሊጣመም ይችላል፡፡ በአጥንቱ ላይ እንዲህ አይነት ምልክቶች ከታዩ በኋላ ቲቢ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት የሚደረጉ ምርመራዎች አሉ፡፡ በምርመራዎቹ ባክቴሪያው በአጥንት ላይ መገኘቱን፤ በሽታውም ቲቢ መሆኑን ይረጋግጣል፡፡ ይህ ባክቴሪያ በማንኛውም ሰው ሰውነት ውስጥ ያለና የማይጠቅም የማይጎዳ ባክቴሪያ ነው፡፡በተለያየ አጋጣሚ የሰዎች የበሽታ መከላከል አቅም ሲቀንስ ወደ በሽታ አምጪነት በመቀየር በሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ሆነ አጥንት ላይ ሊገለጥ ይችላል፡፡ ከእዚህም ባሻገር ከአንድ የሳንባ ቲቢ ህመምተኛ ባክቴሪያው በትንፋሽ ወደ ጤነኛ ሰው ሲተላለፍ ባክቴሪያው ለይቶ አጥንትን ሊጎዳ ይችላል፡፡ አንድ ሰው በአጥንት ቲቢ ሲያዝ የሚታዩ ምልክቶች ምንድን ናቸው ? ከአጥንት ቲቢ ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ፦ · የአጥንት ቅርፅ መዛባት፣ · የአረማመድ መቀየር እና ጉዳት የደረሰበት የአጥንት ክፍል ስራውን በአግባቡ ማከናወን ማቃት፣ · ሌሊት ላይ ማላብና አልፎ አልፎ ሳል ሊከሰት ይችላል። · የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የአጥንት ማበጥ፣ · የአጥንት መተጣጠፍ ማቃት ወይም ደርቆ መቅረት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ · በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ የመደንዘዝ ፣ የማሳከክ እና የመለብለብ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ አንድ ህመምተኛ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታው መዳን የሚችለው በምን ዓይነት ህክምና ነው? ለየትኛውም የቲቢ አይነት ህክምናው መጀመሪያ የሚሰጠው ለተከታታይ ስድስት ወራት ነው፡፡ መድሃኒቶቹም አራት አይነት ናቸው፡፡ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የሚወሰዱት አራት አይነት መድሃኒቶች በኪኒን መልክ ለአወሳሰድ እንዲመቹ ተጣምረው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ታካሚው እንዲወስድ የሚደረገው የመድሃኒቶቹ ብዛት ሁለት፤ሶስትና አራት ተብለው የሚወሰኑት እንደታካሚው የሰውነት ክብደት ነው፡፡ በቀጣዮቹ ከሶስት እስከ ስድስት ወራት ባሉት ጊዜያት የሚወሰዱት መድሃኒቶች ደግሞ ሁለት አይነት ናቸው፡፡ በእነዚህ ስድስት ወራት የታዘዙለትን መድሃኒት በአግባቡ የተከታተለ ማንኛውም የቲቢ ታካሚ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታው ይድናል፡፡መድሃኒቱን በአግባቡ በማይከታተሉ ታካሚዎች ላይ በሽታው የሚያስከትለው ችግር አለ።ባክቴሪያው መድሃኒቱን ለመልመድ የተጋለጠ ነው፡፡መድሃኒቱ ተጀምሮ የሚቋረጥ ከሆነ ባክቴሪያው መድሃኒቱን በፍጥነት ይለምዳል፡፡ህመሙም ከመዳን ይልቅ ይባባሳል፡፡ በእነዚህ መድሃኒቶች በአጭር ጊዜ አክሞ ለማዳን ያስቸግራል። ህመሙም መድሃኒቱን ወደ ተለማመደ ቲቢ ወይም ኤምዲ አር ቲቢ ስለሚሸጋገር በመደበኛው መድሃኒት በስድስት ወራት ውስጥ አክሞ ለማዳን አይቻልም፡፡ በቅርብ ወደ ሀገራችን በገባውና ከበድ ወዳለው ኤም ዲ አር ቲቢ ህክምና በመሸጋገር ቀስ በቀስ ነው ሊታከም የሚችለው፡፡ በእዚህ ህክምና ጊዜ የሚታየው ትልቁ ችግር የበሽተኞች ህመም መባባሱ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛው ህክምና ለመዳን ያስቸግራል፡፡ ለሁሉም የቲቢ ዓይነቶች መከሰት ምክንያቱ ተመሳሳይ ባክቴሪያ ከሆነ ለይቶ አጥንትን እንዲያጠቃ የሚያደርገው ምንድን ነው? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል።በሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ሆነ በአጥንት ላይ እንዲከሰት ስለሚያደርገው ምክንያት በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን የህመምተኛው የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም የቲቢውንም አይነት ከበድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ለምሳሌ በጭንቅላት ቲቢ የሚጠቁ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በሌሎች በሽታዎች የተጠቁና የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከሙ ናቸው፡፡ በተለይ እንደ ኤች አይ ቪ ኤድስ አይነት በማይድኑ በሽታዎች የተያዙ ሰዎች ላይ ከበድ ባሉ ቦታዎች ይከሰታል፡፡ አንድ ሰው በአጥንት ቲቢ ተይዞ ሳያውቀው ከቆየና በአፋጣኝ ህክምና ካላገኘ ምን ይፈጠራል? የአጥንት ቲቢን ጨምሮ በሌሎችም ቲቢዎች ህመምተኛው ቶሎ ወደ ህክምና ካልመጣ በሽታው ስር ሰዶ ወደሌላ የሰውነት ክፍል ስለሚሰራጭ በህክምና ቶሎ ላይድን ይችላል፡፡ ከእዚህም ባለፈ የአጥንት ቲቢ ቶሎ ካልታከመ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ባክቴሪያው ቶሎ ሊድን ቢችል እንኳን ጥሎ የሚሄደው ጉዳት አይድንም፡፡ የአጥንት ቲቢ በዚህኛው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ነው ጎልቶ የሚከሰተው ለማለት ያስቸግራል፡፡ ዋናው መከሰቻ ምክንያቱ የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም በመሆኑ በእዚህ የህብረተሰብ ክፍል ያመዝናል ማለት አይቻልም፡፡ ለአጥንት ቲቢ የሚሰጠው ህክምና ከማንኛውም የቲቢ ህመም ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለዚህ የመድሃኒት ችግር የለም፡፡ ነገር ግን ታካሚዎች ህመማቸውን ለመግለፅ ስለሚቸገሩና ሀኪሙም ስሜቶቹን ከሌሎች በሽታዎች ለመለየት ስለሚቸገር አንዳንዴ ነርቭ ነው እየተባለ የሚዘገይበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ የአጥንት ቲቢ መሆኑን ለመለየት ጊዜ ይወስዳል፡፡ በሽታው ሳይከሰት አስቀድሞ መከላከል የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ለሌሎች የቲቢ አይነቶች ከምናደርገው ጥንቃቄ የተለየ አይደለም፡፡ በቲቢ የተያዙ ሰዎች ባክቴሪያውን ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ አፋቸውን በመሸፈን እንዲያስሉና እንዲያስነጥሱ ይመከራል፡፡ ሰዎች በብዛት የሚገኙባቸው ቤቶችና መጓጓዣዎች መስኮቶች መከፈት አለባቸው በቂ አየር እንዲገባ፡፡ እንደ ኤች አይ ቪ ኤድስና ስኳር ባሉ የማይድኑ ህመሞች የበሽታ መከላከል አቅምን ስለሚቀንሱ በበሽታዎቹ የተያዙ ሰዎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ አንድ ሰው ለሌላ በሽታ ምርመራ ወደ ሀኪም ቤት ሲሄድ በተያያዥ ሌሎቹንም መታየት ይኖርበታል፡፡ 3.2.የትክትክ /ደረቅ ሳል (ፐርቱሲስ) በሽታ – Pertussis ይህ ሳል ትክትክ / ደረቅ ሳል ስለሆነ፣ እንዲሁም ለረጂም ግዜ የሚዘልቅ በመሆኑ “ የ 100-ቀን ሳል ” በመባል ይታወቃል፡፡ ትክትክ / ደረቅ ሳል ( ፐርቱሲስ )– ከባድና በጣም ተዛማች የመተንፈሻ አካል በሽታ ሆኖ፣ ምልክቱም ተከታታይና ከባድ የሳል ጥቃት ሲሆን ልዩ መግለጫው በሽተኛው አየር ወደ ውስጥ ሲያስገባ የሚሰማው “ የመጮህ አይነት ” ድምጽ ማስከተሉ ነው፡፡ በማንኛውም ሰው ላይ ጉዳት ያደርሳል፣ ሆኖም ግን በልጆች ላይ ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡ደግነቱ ግን፣ የትክትክ በሽታን መከላከል የሚችሉ ክትባቶች አሉ፡ የሚነሶታ የጤና ቢሮ (MDH) ጨቅላዎችና ልጆች ከትክትክ / ደረቅ ስል፣ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ፣ አንዲሁም መንጋጋ ቆልፍ (DPT) በሽታዎችን በማካተት የሚከላከል በ2 ወር፣ 4 ወር፣ 6 ወር፣ አንዲሁም ከ15-18 ወር የልጅነት ዕድሜ የሚሰጥ ክትባት መውሰድን ይመክራሉ፡።የDPT ማጠናከርያ ክትባት ከ4-6 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ይሰጣል፡፡በቅድመ-ወጣትነት ዕድሜያቸው የDPT ክትባት ያልወሰዱ አዋቂዎች አሁን አንድ ክትባት መውሰድ አለባቸው፡፡በዕድሜ ከፍ ያሉ ልጆችና አዋቂዎች እራሳቸውን በመከላከል፣ ዕድሜያቸው በጣም ትንሽ በመሆኑ በDPT ክትባት ሙሉ መከላከያ ማግኘት ለማይችሉ በዙሪያቸው ለሚኖሩ ህጻናቶች የመከላከያ ክበብን መፍጠር ይችላሉ።የትክትክ/ደረቅ ሳል ክትባቶች በጣም ውጤታማ ናቸው፣ ሆኖም ግን እንደ ሁሉም ዓይነት ክትባቶች፣ 100% ውጤታማ አይደሉም፡፡ምንም እንኳ ቢከ

በውስጥ መስመር በተደጋጋሚ ከሚጠየቁ ጥያቄዎች መካከል ስለ ግለ ወሲብ(Masturbation) ጀባ ልበላቹ። ጥያቄ፦masturbation ከጀመርኩ ወራቶች አለፋ።አሁን አሁን ግን በሂወቴ ላይ ጣልቃ ገብቶ ከዚህ ነገር ለመውጣት አልቻልኩም፣ከመቼው ቤት ገብቼ እስከማደርግ ነው የምቸኩለው ፣ይህ ነገር ሱስ ሆኖብኝ ይሆን? ጥያቄያችሁ ተገቢነት ያለው ሲሆን ስለዚህ ትንሽ ነገር ልበላችሁ። Masturbation( ግለ ወሲብ ) የምንለው ወንዶችም ፣ሴቶችም የእራስን የወሲብ ፍላጎት(sexual desire) ለመጨመር እራስን በመነካካት እራስን ለማርካት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። -Masturbation በአብዛኛው የወሲብ ሂወት የሌላቸው ሰዎች ያደርጋሉ ተብሎ ይታሰባል።በሳይንሳዊ አገላለፅ "natural and safe way to explore your body,feel body,feel pleasure and release built up sexual tension" ብሎ ይተነትነዋል።ነገር ግን ሱስ(addiction) ሊሆን የሚችል፣ሱስ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ጉዳቱ የሚያመዝን የእለት ከእለት እንቅስቃሴን እስከማወክ የሚያደርስ ነው። -አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው በአለም ላይ ከ75% በላይ adult ሰዎቸ ግለ ወሲብ ይፈፅማሉ። -አንድ ሰው masturbation ሱስ ከተያዘ በቀን እስከ 5 ጊዜ፣ከዚህም በላይ ሊያደርግ ይችላል። -በmasturbation ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ የሚለቀቁ hormone እና chemicals ለምሳሌ Dopamine,Endorphin,Oytocine,Testosterone, prolactine እንዲለቀቁ ያደርጋል።እነዚህ hormomes ደስታን የሚሰጡ፣stress የሚቀንሱ፣እና እንቅልፍ እንድንተኛ የሚያደርጉ ናቸው። Masturbation ጤናማ አደለም የምንለው መቼ ነው? -የእለት ከእለት ሂወታችን ላይ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ -የፍቅር ግንኙነት እና ማህበራዊ ሂወት ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ከሆነ -ህዝብ በተሰበሰበት ቦታ ማድረግ -ስለ እሱ አለማሰብ አለመቻል የጎንዮሽ ጉዳቱስ? -ሱስ(addiction) ሊሆን ይችላል -የጥፋተኝነት ስሜት(Guilt) -ከባህል፣ከሀይማኖት አና እምነት ጋር ይጻረራል -መገለልን ያስከትላል -ስራ ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል -የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ መቸገር -አእምሮ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል -ደስታው ከእራስ ጋር ብቻ ይሆናል አንዳንድ ጥናቶች masturbation ለወሲብ የማነቃቂያነት፣ጭንቀትን ለማስታገስ፣ጊዚያዊ ደስታን ይሰጣል፣እንዲሁም የprostate cancer አደጋ ይቀንሳል፣የወሲብ ፍላጎት የሌላቸውን ሴቶች የቅባት መጠን(lubricant)ለመጨመር እና ወንዶች ላይ erectile function ያሳድጋል ይላሉ። ከmasturbation ሱስ እንዴት መውጣት ይቻላል? ከ masturbation ሱስ ለመውጣት ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።በጣም ወሳኙ ነገር እራስን ማሳመን ታጋሸ ፣ ግልፅ እና ቁርጠኛ መሆን ያሰፈልጋል።ከዚህ በተጨማሪ በተቻለ መጠን -ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎችን እና ቪድዮ አለመመልከት -ሁል ግዜ ንቁ እና እራስን busy ለማድረግ መሞከር -እራስን መንከባከብ፣ጤናማ አመጋገብ መከተል -ብቻዎትን የሚያሳለፋትን ጊዜ መቀነስ፣ከጓደኛ፣ከቤተሰብ፣ አንዲሁም ከማህበረሰብ ጋር መቀላቀል -የአካል በቃት እንቅስቃሴ ማድረግ -እንደ አስፈላጊነቱ የስነ ልቦና እና የስነ አእምሮ ባለሙያ ማማከር ተገቢ ነው። በአጠቃላይ የmasturbation ሱስ እራስን በጣም የሚጎዳ እና ተፅእኖ የሚያሳድር ችግር ስለሆነ መጠንቀቅ ይገባል እስቲ እናንተም ሀሳቦትን ያካፍሉኝ 🙏 ጤና ይብዛሎ ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርምያስ

የአፍንጫ አለርጂ *********** የማሽተት ችሎታን ከመከላከል በላይ ሌሎች የአፍንጫን ስራዎች ያስተጓጉላል። አንድ ግለሰብ የአለርጂ ችግር ካለበት ወደ አፍንጫ የሚገቡ አንዳንድ የሚቆጠቁጡ አካላት ሲገጥሙት የመቆጥቆጥ ስሜት በአፍንጫ ዉስጥ ይፈጠራል። የሰውነት በሽታ ተከላካይ አካላት በበኩላቸዉ ይህንን ለመቋቋም ንጥረ ቅመሞችን (ለምሳሌ ሂስታሚንና ሊውኮትሪንስ) ይለቃሉ። የደም ቧንቧዎች ያብጣሉ። በዚህ ምክንያት የአፍንጫ መደፈንንና የንፍጥ መብዛትን ያስክትላል። የአፍንጫ አለርጂ መነሻዎች፦ ብዙ ጌዜ ለዚህ ችግሮች ለመጋለጥ የሚከተሉት ሁኔታዎች በምክኒያትነት ይነሳሉ: • አቧራ • የአበባ መፈንዳት • ሰዉነት የሚለቃቸው አንዳንድ ንጥረ ቅመሞች • ሞቃታማ ፣ ደረቃማና ዝናባማ ወቅቶች • በበቤተሰብ የዘር ሃረግ መሃል ችግሩ ከነበረ የአፍንጫ አለርጂ ምልክቶች ወዲያዉኑ ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች፦ • የአፍንጫ፣የአፍ አካባቢ፣የጉሮሮ፣የቆዳ ወይም የሌሎች የማናቸዉም የአካል ክፍሎች መቆጥቆጥ • ለማሽተት መቸገር • ለረጅም ጊዜ የማያቋርት ቀጭን ንፍጥ • ማስነጠስ • የአይን ማልቀስ ቀስ በቀስ ሊታዩ የሚችሉ፦ • የአፍንጫ መደፈን • ሳል • የጆሮ መደፈን • የጉሮሮ ህመም • ጥቁርና ክብ ቅርፅ ያለዉ ምልክት በአይን ላይ መታየት • የአይን ማበጥ • የራስ ምታት ወዘተ የአፍንጫ አለርጂን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶች: • በተለይ ፊትን ከምንካት በፊት አጅን መታጠብ • በችግሩ ከተያዙ ሰዎች በተቻለ መጠን መራቅ • ፎጣዎችን፣የመመገቢያ ቁሳቁሶችን አና ዉሃ መጠቻዎችን በአፍንጫ አለርጂ ከተያዙ ሰዎች ጋር በአንድነት አለመጠቅም • አለርጂን የሚያስከትሉ ነግሮችን ጠንቅቀን ማወቅና መጠንቀቅ • አበባ በሚፈነዳበትና ቤት ዉስጥ በሚቆይበት ወቅት መስኮትንና በርን ዝግ ማድረግ • ከማራገቢያ ይልቅ አየር መቆጣጠሪያ መጠቀም አና በመኪና ጉዞ ላይ መስኮት አለመክፈት

✍ አልኮልና ጤና! ┈┈•✦•┈┈┈ . ☞ የአልኮል መጠጥን አብዝቶ በመጠጣት ምክንያት የሚጎዱ የሰውነት ክፍሎች: . ➤ ልብ ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥ ማዘውተር የልብ ጡንቻዎችን በማዳከም #የደም_ፍሰት መዛባትን ያሰከትላል፡፡ በአልኮል መጠጥ ብዛት የሚከሰት የልብ ሕመም የትንፋሽ ማጠር፤ የተዛባ የልብ ምት፤ ድካም፤ የማያቋርጥ ሳልን ያስከትላል። በተጨማሪም ለደም ግፊት እና ለድንገተኛ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ይዳርጋል፡፡ . ➤ አንጎል የአልኮል መጠጥ በአንጎል ላይ #መልዕክት መተላለፍን ያዘገያል፡፡ አልኮል መጠጥን ማዘውተር የተለያዩ የአንጎል ክፍሎችን ስለሚጎዳ የባሕርይ ለውጦችን እንደ መደበት፤ ጭንቀት እና የመርሳት ችግር የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ . ➤ ጉበት ጉበት የምግብ መፈጨት፤ ንጥረ ነገሮችን ማከማቸት፤ ኢንፌክሽን የመቆጣጠር እና #መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት የማስወገድ ተግባርን የሚያከናውን የሰውንት ክፍል ነው፡፡ ታድያ አልኮልን የምናዘወትር ከሆነ በጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እናደርሳለን፡፡ . ➤ ኩላሊት የአልኮል መጠጥ በብዛት መውሰድ በኩላሊት የሥራ ሂደት ላይ መዛባትን ስለሚፈጥር በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች መመጣጠንን በመረበሽ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ይህም ለከፍተኛ #የደም_ግፊት መጠን መጨመር ይዳርጋል፡፡ ኩላሊትንም ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ . ➤ ቆሽት ልክ እንደ አንጎል ሁሉ ከፍተኛ አልኮልን መውሰድ የቆሽትን ሥራ ያዛባል፡፡ ቆሽት የሚያመነጫቸው ኤንዛየምዎች (Enzymes) በውስጡ እንዲጠራቀም በማድረግ ቆሽት እንዲቆጣ ያደርጋል፡፡ ይህም የሆድ ሕመምን፤ ማቅለሽለሽና ማስመለስ፤ የልብምት መጨመር ተቅማጥና ትኩሳት ያስከትላል፡፡ የቆሽት መቆጣት በሚቆይ ጊዜ የቆሽትን ሥራ ስለሚያስተጓጉል ለስኳር ሕመም አልፎም ለሞት ይዳርጋል፡፡ . የአልኮል መጠጥ ማዘውተር ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችም ጉዳቶችን ስለሚያስከትል ለጤንንትዎ ሲሉ ከተቻለ እንዲያቆሙ አልያም እንዲቀንሱ ይመከራል፡፡

ክብደት/ዉፍረት በጤናማ መንገድ መጨመር Healthy way of gaining weight የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን በቴሌግራም ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

የጡት ካንሰር ======= የጡት ካንሰር በአብዛኛው በሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ወንዶችንም የሚያጠቃ የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ብዙ ሴቶች ስለጡት ካንሰር ምንነት ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?ህክምናውስ?የማይድን በሽታ ነው ይባላል….. የጡት ካንሰር በሽታ ምንድን ነው? ካንሰር ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የህመም አይነቶች አጠቃላይ መጠሪያ ስም ነው፡፡ በሽታው ከሌሎች በሽታች ተለይቶ የሚታወቀው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ማደጉና ሌሎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመውረር በመቻሉ ነው፡፡ የጡት ካሰርም በቅድሚያ በጡት ላይ በመከሰት በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት የከፋ ችግር ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡ ጡት በተፈጥሮ በውስጡ ወተት ለማመንጨት የሚያስችሉ በርካታ ከረጢት መሰል ነገሮች እንዲሁም እነዚህን ከጡት ጫፍ ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች አሉት፡፡እነዚህ ቱቦዎች በእርግዝና ወቅት ወተት ለማመንጨት ትልቅ ሚናን የሚጫወቱ ናቸው፡፡የጡት ካንሰር በአብዛኛው ማደግ የሚጀምረው በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ነው፡፡የጡት ካንሰር ተፈጠረ የሚባለው አንድ ጤነኛያልሆነ ህዋስ በሰውነት ውስጥ ተፈጥሮ ከገደብ በላይ መራባት ሲጀምር ነው፡፡የተራባው ህዋስም በጊዜ ሂደት ጤነኛ የነበሩ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ህብረ ህዋሳትን በማጥቃት በሽተኛ ያደርጋቸዋል፡፡ ለጡት ካንሰር የሚጋለጡ እነማን ናቸው? የጡት ካንሰር በብዛት ሴቶችን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን የሚመጣበት ምክንያት ለጊዜው በውል አይታወቅም፡፡የሚከተሉት ሴቶች ግን የበለጠ ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ በዘር ሀረግ በጡት ካንሰር የተያዘ ቤተሰብ ያላቸው ካንሰር ያልሆኑ ሌሎች የጡት በሽታዎች አጋጥሟቸው ከነበሩ የአልኮል መጠጥ የሚያበዙ የወር አበባቸውን ቀድመው/በልጅነት ያዩ ከ30 ዓመት በኋላ ልጅ የሚወልዱ ወይም ከነጭራሹ የማይወልዱ ከሚገባው እድሜ በጣም ዘግይተው ያረጡ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚያዘወትሩና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው በከፍተኛ ጨረር ውስጥ ያለምንም መከላከያ የሚሰሩ፡፡ የጡት ካንሰር ምልክቶች የጡት ካንሰር ሲጀምር ህመም ሆነ ምልክቶች የሉትም፡፡ምልክቶቹን ማወቅ በሽታውን በወቅቱ እንድናውቀው ምርመራና ህክምና በማረግ ህይወታችንን እንድንታደግ ይረዳ፡፡አብዛኛዎቹ የጡት እብጠቶች ካንሰር ባይሆኑም ዋነኛው የጡት ካንሰር ምልክት ግን በጡት ላይ የሚከሰት ጠጣር እብጠት ሲሆን የሚከተሉት ደግሞ ተጨማሪ ምልክቶች ናቸው፡- ከጡት ጫፍ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ መውጣት ከጡት ጫፍ አካባቢዎች መቅላትና ወደ ውስጥ መሰርጎት በጡት አካባቢና በብብት ውስጥ እብጠት መከሰትና ሙቀት ያለው መሆን የጡት ቆዳ መሸብሸብ/ወደ ውስጥ መግባት ወይም እንደብርቱካ ልጣጭም ዓይን ማውጣት የጡት ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች የጡት ካሰር ተሰራጭቶ ወደ ሌላ የሠውነት አካል ከመድረሱና ከመባዛቱ በፊት ከተደረሰበት ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል በሽታ ነው፡፡ የማሞግራም ምርመራ ማድረግ፡-ይህ ምርመራ ጡትን ራጅ በማንሳት የሚደረግ የምርመራ ዘዴ ሲሆን አስተማማኝ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴ ነው፡፡ማንኛዋም ሴት ከ40ዓመት እድሜ በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም ከ20 ዓመት እስከ 40ዓመት ለሆኑ ደግሞ በየሶስት ዓመቱ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ሐኪም በመዳሰስ የሚያደርገው ምርመራ፡-ሐኪም ጋር በየስ ድስት ወሩ በመቅረብ፣የሚሰማ ስሜት በመግለጽና ጡትን በማስዳሰስ ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ የራስ ጡት በራስ የመመርመር ዘዴ፡- በመስተዋት ፊት በመቆም ከወገብ በላይ በማውለቅ እጅን ጎን ላይ በማድረግና ቀጥ ብሎ በመቆም በሁለቱም ጡቶች ላይ ያትን ለውጦች መከታተል፡፡የጡቶች ጫፎች የሰረጎዱ፣በተለየ መልኩ የቐሉ፣ሁለቱ ጡቶች ካላቸው የተፈጥሮ ልዩነት በስተቀር ሌላ የመጠንም ሆነ የቅርጽ ልዩነትና የጓጎለ እብጠት እንዳላቸው ማየት ሁለቱንም እጆች በጭንቅላት ትክክል ከፍ አድርጎ በመያዝ ከላይ የተዘረዘሩት ዓይነት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉ ማስተዋል፡፡ አንደኛውን እጅ ከጭንቅላት በላይ ከፍ በማድረግና በሌላኛው እጅ ደግሞ በተቃራኒው ያለውን ጡት በመዳሰስ እብጠት ወይም ለየት ያለ ነገር መኖሩን ማረጋገጥ በጀርባ በመተኛት አንደኛውን እጅ በመንተራስ በሌላኛው እጅ በተቃራኒው ያለውን ጡትበመጀመሪያ ዙሪያውን ቀጥሎም የላይኛውን ክፍልና በመጨረሻ የጡት ጭራ የሚባለውን ብብት ውስጥ በመግባትና በመዳበስ የጓጎለ ነገርና እብጠት መኖሩን መመርመር የጡቶችን ጫፍ በማለብ ደም ወይም ያልተጠበቀ ፈሳሽ መኖሩን ማየት ይገባል፡፡

የስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እንዲሁም እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቱ ምን ይሆን ??? በአለማችን ከ60-80 ሚሊዮን የሚሆኑ ጥንዶች ልጅ ያለመውለድ ችግር ያጋጥማቸዋል ለዚህ ችግር ከሚጋለጡበት ምክንያት አንዱ ፡- • የእስፐርም መጠን ማነስ • እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ • ትክክለኛ ቅርፅ የሌለው እስፐርም • የማህፀን ቱቦ ጠባሳ መኖር • የማህፀን እጢ መኖር • የእንቁላል ምርት ላይ ችግር ካለ • የሆርሞን ችግር መኖር • ለረጅም ጊዜ መድሀኒት መውሰድ ከላይ ከጠቀስናቸው ውስጥ ለዛሬ የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ እንገልፅላችሆለን • የሆርሞን ችግር • ኢንፌክሽን ካለ • ብልት አካባቢ ጉዳት ከደረሰ • ያልወረደ የዘር ፍሬ • ከዚህ ቀደም ሰርጀሪ ተሰርተው ከነበረ • ብልት አካባቢ የሚገኝ የደምስር እብጠት • የውስጥ ደዌ ህመሞች • ካንሰር ወይም ካንሰር ያልሆኑ እባጮች መኖር • ጭንቀት ፣ ድብርት • አብዝቶ የአልኮል መጠጥ መጠቀም ፣ ማጨስ • ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መጨመር ውድ የዶክተር አለ ተከታታይ በዛሬው ፁሁፋችን የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ልንገልፅላችሁ ወደናል

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias - Telegram 频道 @drsofonias 的统计与分析