ch
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

前往频道在 Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

显示更多

📈 Telegram 频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias 的分析概览

频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 949 名订阅者,在 医学 类别中位列第 1 157,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 681

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 949 名订阅者。

根据 27 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -557,过去 24 小时变化为 -23,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 26.07%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.79% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 203 次浏览,首日通常累积 1 354 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

凭借高频更新(最新数据采集于 28 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 医学 类别中的关键影响点。

19 949
订阅者
-2324 小时
-1257
-55730
帖子存档
ለምን ይሆን የአይናችን ከለር የሚቀየረውና ምክኒያቱሰ? ሄፒታይተስ ቢ የብዙ ሰው ጥያቄ ስለሆነው ሄፓታይተስ ቢ ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀርበናል በያላችሁበት ተከታትሉን ሀሳብ አስተያየተዎን ያቅርቡልን። ምክንያቱ በፊት እንደተጠቀሰው የበሽታው ምክንያት የሂፕታይተስ ቢ ቫይረስ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ የበለጠ የሚያሰጋውና ሁላችንም ተገቢውን ትኩረት እንድንሰጠው የሚገባው Hepatitis B ከኤች አይ ቪ በተለየ ሁኔታ በፍጥነትና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው መሰራጨት መቻሉ ነው፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነም ከHIV በተለየ ከ100-1000 ጊዜ በፍጥነት የመተላለፍ አቅም አለው፡፡ ለዚህም ዋና ተጠቃሽ የሆነው ምክንያት ቫይረሱ ከHIV ያነሰ መሆኑ ነው፡፡ ደግሞም በየትኛውም የሰውነት ፈሳሽ ውስጥ መገኘቱ ነው፡፡ ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው ከሚተላለፍባቸው ዋነኛ መንገዶች መካከል፡ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም ደም በመለገስና በመቀበል መርፌን በመጋራት ከእናት ወደ ልጅ በወሊድ ወቅት የግል ቁሶችን በጋራ መጠቀም (የጥርስ ብሩሽና ምላጭ) በሽታው በተንሰራፋበት አካባቢ መኖር ወ.ዘ.ተ ቫይረሱ በጣም አደገኛና እጅግ ተላላፊ ቢሆንም፤ እጅ በመጨባበጥ፣ የምግብና የመጠጥ ቁሶችን በመጋራት፣ አብሮ በመመገብ፣ በመሳሳም፣ በመተቃቀፍ፣ በማሳል፣ በማስነጠስ፣ ወይም ጡት በማጥባት ፈጽሞ አይተላለፍም፡፡ ምልክቶቹ ቫይረሱ ጉበትን ከመግደሉ በፊት ምንም አይነት ይሄ ነው የተባለ የጤና መታወክ ወይም ምልክቶችን አያሳይም፡፡ ድምጽ አልባ ገዳይ ነው፡፡ የሚያስከትላቸውን የኢንፌክሽን አይነቶች በሁለት ልንከፍላቸው እንችላለን፡ 1- ዘላቂ ኢንፌክሽን (Chronic Infection): ይህ አይነቱ ኢንፌክሽን ለብዙ አመታትና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የኢንፌክሽን አይነት ነው፡፡ በዚህ የበሽታው አይነት ምንም አይነት ምልክት ላይታይበት ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ የጉበት መንገብገብን (Inflammation) ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህ አይነቱ ኢንፌክሽን በጉበት ካንሰር የመያዝን እድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል፡፡ ለዚህም ነው የዚህ ታማሚዎች የአልኮል መጠጥ ጋር እንዳይቀርቡ የሚመከረው፡፡ 2- ውስን አደገኛ ኢንፌክሽን (Acute Infection): ይህ አይነቱ ኢንፌክሽን ለጥቂት ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን በሰውነት ላይ ጠቅለል ያለ የጤና መታወክ ያስከትላል፡፡ ከሚያሳየው ምልክቶች ውስጥም፡- የምግብ ፍላጎት ማጣት ማቅለሽለሽ ማስመለስ የሰውነት መዝለፍለፍ ትኩሳት ጠቆር ያለ ሽንት የቆዳ እና የአይን ቢጫ መሆን ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡ አንዳንድ ታማሚዎች ከፍ ባለ የጉበት ህመም ምከንያት ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል፡፡ ኢንፌክሽኑ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ ሊያልፍም ይችላል፡፡ ምርመራው የሂፕታይተስ ቢ በሽታ እንዳለና እንደሌለ በደም ምርመራ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ የቫይረሱ ምርት የሆኑ ፕሮቲኖች ወይም ሰውነታችን ቫይረሱን ለመግደል የሚያመነጫቸው ፕሮቲኖች በደም ውስጥ ከተገኙ የሂፕታይተስ ቢ ኢንፌክሽን ተከስቷል ማለት ነው፡፡ ዶክተሮች የጉበት መበላሸት ጥርጣሬ ካለባቸው የጉበት ናሙና በመርፌ ወስደው መመርመር ይችላሉ፡፡ ይህ ቴክኒክ liver biopsy በመባል ይታወቃል፡፡ መከላከያው በሽታውን ለመከላከል ብዛት ያላቸው ክትባቶች በሳይንቲስቶች ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ ክትባቶች እንደማንኛውም ክትባት ከደከመ ቫይረስ ወይም የቫይረሱ አካል የሚጠነሰሱ ናቸው፡፡ ከ85 - 90% የሚሆኑ የክትባቱ ተጠቃሚዎች በቫይረሱ እንዳይጠቁ የሚያደርግ የመከላከያ አቅም አግኝተዋል፡፡ ስለሆነም ሕፃናትም ሆነ አዋቂዎች ክትባቱን መከተብ ይኖርባቸዋል፡፡ Hepatitis B እንደ Hepatitis A በተበከለ ውሃና ምግብ ሳይሆን በሰውነት ፈሳሾች የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለዚህም በሽታውን ለመከላከል ያሉት አማራጭ እንደ ጥንቃቄ የጎደለው ግብረ-ስጋ ግንኙነት፣ የደም መለገስና መቀበል፣ የተበከሉ መርፌዎችን መጠቀም የመሳሰሉትን ማስወገድ ነው፡፡

የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ከመውሰዶ በፊት ጥቅሙን እና ጉዳቱን ያውቃሉ? የወሊድ መከላከያ እንክብሎች ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ከሚጠቅሙን አማራጮች ውስጥ አንዱ በአፍ የሚወሰድ ወይም ኪኒን ተብሎ የሚጠራው የመከላከያ አይነት ነው፡፡ የተወሰኑ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች ኢስትሮጂንና ፕሮጀስትሮን /Estrogen and progesterone/ የተባሉ ሁለት ዓይነት ሆርሞኖችን ይይዛሉ፡፡ እነዚህ እንክብሎች ቅልቅል /Combination/ እንክብሎች ሲባሉ ሌሎች ደግሞ ከፕሮጀስትሮን (Progesterone) ብቻ የተሰሩ እንክብሎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ አብዛኛዎቹ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ወሳጅ ሴቶች ቅልቅል እንክብሎችን ይወስዳሉ፡፡ ጥቅሙ - ወቅቱን የጠበቀ የወር አበባ መታየት - ለመውሰድ ቀላል ነው - ዘጠና በመቶ (90%) ያህል አስተማማኝና ተስማሚ ነው፡፡ - የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ችግር አለመፍጠር - እርግዝናን አለማዘግየት - ከሌሎቹ የእርግዝና መከላከያ አይነቶች ጋር ሲነፃፀር በአንፃራዊ መልኩ ትንሽ የሚባል የደም መፍሰስ መኖር - ቅልቅል እንክብሎች (Combination)ተጨማሪ ጥቅሞች ይሰጣሉ ብጉርን፣ የአጥንት መሳሳትን፣ ካንሰር ያልሆነ የጡት ማደግ፣ ከማህፀን ውጭ እርግዝናን፣ የማህፀን ካንሰርንና ሌሎች ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም ከብረት ማዕድን ማነስ የሚመጣ የደም ማነስን በመከላከል በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ ጉዳት - በየቀኑ ግንኙነት ባይደረግ እንኳን እንክብሉን መውሰድ - ማቅለሽለሽና ማስታወክ ፣ የጡት ህመም - ሆድ መንፋት፣ የባህሪ መለዋወጥ በ2-3 ወራት ዉስጥ ሊሻሻል ይችላል - ከ2-3 ወር የሚቆይ የወር አበባ መዛባትና መጠን መቀነስ (አንዳንዴ ጠብታ ብቻ መታየት) ፡፡ የወሊድ መከላከያ እንክብልዎን መርሳትም ይህን ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡  እነዚህ የወሊድ መከላከያ እንክብሎች መወሰድ የሚኖርባቸው የወር አበባ መፍሰስ ከጀመረበት ከአምስተኛው ቀን ጀምሮ በየእለቱ ያለማቋረጥ ለሀያ አንድ ቀን ነው፡፡ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን መውሰድ ሲጀምሩ ሰውነትዎ እስኪለማመድ ድረስ መድሀኒቶቹ ለመስራት 7ቀናት ይፈልጋል/ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጀመሪያዎቹ 7ቀናት ተጨማሪ /ሌላ የወሊድ መከላከያ ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል (ለምሳሌ ኮንዶም)፡፡ በመድሀኒቶቹ ምክንያት የሚከሰትን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስና እርግዝናን ለመከላከል እንክብሎቹ መወሰድ ያለባቸው 24 ሰዓታት ባልበለጠ ልዩነት መሆን አለበት፡፡ መልካም አዲስ አመት ይሁንልን

እጆዎን ና እግሮን ደንዝዞት ያውቃል ? የነርቭ ህመም ምልክቶች የነርቭ ህመም ምልክቶች ምን ምን እንደሆኑ ለግንዛብ ይዘን ቀርበናል ተከታተሉን፡፡ 1) መደንዘዝ ስሜታዊ ነርቮች (sensory nerves) መጎዳታቸውን የምናውቅበት የመጀመርያው ምልክት የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት በእጅ፣ በጣት፣ በእግር፣ እና በእግር ጣቶች ላይ ሲፈጠር ነው። ስሜታዊ ነርቮች ስራቸው የስሜት መልእክት መላክ ሲሆን ጉዳት ሲያጋጥማቸው ቆይቶ ወደ መደንዘዝ የሚቀየር የመውረር ስሜት ይሰማናል። በግዜው ተገቢ ህክምና ካላገኘ ይህ ስሜት ወደ ሌሎች የሰውነት አካሎች ሊዛመት ይችላል። 2) ህመም ሌላ የነርቭ ህመም ምልክት የሚሰነጥቅ ወይም የሚያቃጥል የህመም ስሜት ነው። የዚህ አይነት ስሜት እጅ እና እግር ላይ የሚፈጠር ሲሆን ከሌላ የህመም ስሜት ይለያል። ህመሙ የሚፈጠረው ስሜታዊ ነርቮች ላይ በተፈጠረ ጉዳት ነው። ስሜት በአግባቡ ከአእምሮ ወደ ቆዳ መተላለፍ ካልቻለ የተጎዳው ቦታ ላይ ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። 3) የጡንቻ ድካም ጡንቻ እንዲቀሳቀስ የሚያደርገውን መልእክት የሚያስተላልፉ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ ድካም ይፈጥራል። አልፎም ጡንቻን የመቆጣጠር ችሎታ ሊያሳጣ ይችላል። ለጡንቻችን የሚላከው መልእክት በአግባቡ ካልተላለፈ መራመድ እንቸገራለን። በእጃችን እቃዎች ለማንሳት እና ጭብጥ አድርጎ መያዝ ይከብደናል። በነርቭ ጉዳት ምክንያት ጡንቻ ጥቅም ላይ የሚውልበት ግዜ ሲቀንስ እራሱ እየደከመ ይመጣል። 4) የጡንቻ መሸማቀቅ የእንቅስቅሴ (motor nerve) ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ ሊያመጣ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ በራሱ የተጎዱት ነርቮች ላይ በሚፈጥረው እንቅስቃሴ ጉዳቱን ሊያባብስ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ የሚፈጠረው የእንቅስቃሴ ነርቮች በብዛት ሲሰሩ ነው። የመሸማቀቅ ስሜት ክብደቱ ቀላል፣ መሃከለኛም ወይንም በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል። 5) የላብ ችግር የሰውነት አካልን የሚረዱ ነርቮች ሲጎዱ አውቶኖሚክ ኒውሮፓቲ የሚባል ህመም ሊያስከትል ይችላል። አውቶኖሚክ ነርቮች ሲጎዱ የላብ ችግር ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ላብ ሲፈጠር ሌሎች ላይ ደግሞ የላብ መቀነስ ይታያል። ላብ በአግባቡ ካልመነጨ ሰውነታችን ሙቀቱን በአግባቡ መቆጣጠር አይችልም። በከፍተኛ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ችግሩ ይገዝፋል። 6) ሽንት ቤት መመላለስ የሽንት ፊኛ ሽንትን በደንብ እንዲይዝ ብዙ ነርቮች አብረው መስራት አለባቸው። የነርቭ ጉዳት ሲፈጠር የሽንት ፊኛ ሽንትን ቶሎ ቶሎ ለማስወገድ ይሞክራል። የነርቭ ጉዳት የሽንት ፊኛ ጡንቻዎች የሚያደርጉትን መኮማተር እና መላላት በተገቢው መልኩ እንዳያደርጉ ያስተጓጉላል። የሽንት ፊኛ ችግር ሌላ መንስኤ ሊኖረው ይችላል። ልጅ በወለዱ እናቶች እና የስኳር በሽታ ታካሚዎች ላይ የሚፈጠር ችግር ነው። 7) ከባድ ራስምታት የኤሌክትሪክ ንዝረት የሚመስል አጭር ግዜ የሚቆይ ከባድ ራስምታት የነርቭ ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል። ህመሙ የኦሲፒታል ኒውራልጂያ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል። ኦሲፒታል ኒውራልጂያ አንገት ላይ ያለ የነርቭ መቆንጠጥ በሽታ ነው። ህመሙ የላይኛው አንገት ክፍል ወይም ጭንቅላት ጀርባ ላይ ይፈጠራል። 8) የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር ወይም መንገዳገድ ሌላ የነርቭ ጉዳት ምልክት ነው። ወድቀው ሊጎዱ ስለሚችሉ ይህን ምልክት ችላ ማለት የለብዎትም። የነርቭ ጉዳት አእምሮ የሰውነትን እንቅስቃሴ በአግባቡ እንዳይቆጣጠር ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ወድቀው እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል። የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር የፓርኪንሰን ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል። መልዕክቱ ለሌሎችም እንዲዳረስ እባክዎ ሼር ያድርጉ፡፡

#የአፍ #ዉስጥ #ፈንገስ ምላስ ነጭ መሆን መንስኤው ካንዲዳ ከሚባሉ ዩስት ሲሆን የምላስ መንጣት ደግሞ ካንዲዲያሲስ ይባላል፡፡ ካንዲዳ ለሰውነታችን እጅግ ጠቃሚ ናቸው ነገር ግን ከመጠን በላይ በሚያድ
#የአፍ #ዉስጥ #ፈንገስ ምላስ ነጭ መሆን መንስኤው ካንዲዳ ከሚባሉ ዩስት ሲሆን የምላስ መንጣት ደግሞ ካንዲዲያሲስ ይባላል፡፡ ካንዲዳ ለሰውነታችን እጅግ ጠቃሚ ናቸው ነገር ግን ከመጠን በላይ በሚያድጉበት ወቅት ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራሉ ። #መንስኤዎቹን • የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም • ለረጅም ጊዜ አንቲባዮቲክ መድሀኒቶች መጠቀም • የወሊድ መቆጣጠሪያ መውሰድ • ኢንሱሊን (የስኳር በሽታ መድሀኒት) • እርግዝና መኖር • ደካማ የአፍ ጤንነት አጠባበቅ • የአፍ መድረቅ • ትምባሆ መጠቀም • አልኮል መጠቀም • ጣፋጭ ምግቦችን መውሰድ #ምልክቶቹ • እንደ አይብ የመሰለ ነጭ ነገር ምላስ ላይ መታየት • የምግብ ጣእም አለመለየት • በእጅ በሚነኩበት ጊዜ መድማት • በአፍ ዙሪያ መቅላት • ለማኘክ ፣ለመዋጥ መቸገር #የቤት #ውስጥ #ህክምናዎች በደቃቅ ጨው ለአንድ ደቂቃ በጥርስ ብሩሽ ምላስን መቦረሽ፡፡ ከዚያም በሙቅ ውሀ በደንብ መታጠብ፡፡ ሁለት ጊዜ በየቀኑ ይድገሙ እና በሳምንት ውስጥ የሚፈልጉትን ውጤቶች ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ለብ ያለ ውሀ ውስጥ 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ይቀላቅሉ፡፡ በዚህ የጨው ውሀ አፍን በመሙላት ይጉመጥሞጡ ። ሾርባ ላይ እሬት (አሎቬራ)በመጨመር በአፍ ውስጥ መጉመጥመጥ እንዲሁም 1 ማንኪያ የአሎቬራ ጭማቂ ይጠጡ ይህን መድሀኒት በየቀኑ ማድረግ ለ 2 ሳምንታት ያህል ማድረግ ፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https

አዲስ ዓመት እንደስሙ የአዲስ ነገር መጀመሪያ ከመሆኑም በላይ በአዲስ ማንነት እና አስተሳሰብ ወደፊት የምንጓዝበት ልዩ የህይወት ምዕራፍ መክፈቻ ቁልፍ ነው ።አዲስ ዓመት ሲመጣ ልብሱ፣ጫማው፣ቤቱ ብቻ ሁሉ ነገር ይለወጣ፤ አሮጌው ይታደሳል ፣ነገሮች በአዲስ መልኩ ይጀመራሉ።ታድያ ይሄ ሁሉ ዉጫዊ ማንነት ሲቀየር ወደ ውስጣችንም ጓዳ ጎራ ብለን ያረጀ እና እድሳት የሚያስፈልገዉን ማንነት በአዲስ እይታ እና አስተሳሰብ ዘረኝነት፣ጥላቻ፣ቂመኝነት፣ክፋት ፣ምቀኝነት ፣መከፋፈል ፣ራስ ወዳድነትን በይቅርታ ፣በፍቅር ፣በመተሳሰብ ፣በአብሮነት ፣ ልንቀይረዉ እና ልናድሰዉ ይገባል ። ዛሬ ላይ በህይወት ስንኖር የማንቆጭበት ታሪክ ሰርተን ለማለፍ በጎ ህሊና፣መልካም መንፈስ እና ቅን ልቦናን ተላብሰን በእያንዳንዱ ልብ ዉስጥ ትንሿ ኢትዮጵያን በመገንባት አሻራችንን እንጣል።በኢትዮጵያ ተስፋ አይቆረጥም ፤ሊነጋ ሲል መጨለሙ አይቀርምና የንጋቷ አብሳሪዎች ለመሆን ዛሬ በተሰጠን አዲስ ቀን በፍቅር ተያይዘን ወደ ፊት ብቻ መራመድ ይሁንልን፤ነገ መልካም ይሆናል። ጤና፣ፍቅር እና ሰላም ለምድራች ይሁን ። 🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት !!🌼🌼

የተለመደውን ምክሬን ይተግብሩ ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንኳን 2014 በሰላም አደረሳችሁ። የዛሬው መልእክቴ ይህንን ይመስላል ይከታተሉኝ። አመት በዓልና አመጋገባችን :- ነገ ጥዋት ቀኑ የበዓል እንደመሆ
የተለመደውን ምክሬን ይተግብሩ ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንኳን 2014 በሰላም አደረሳችሁ። የዛሬው መልእክቴ ይህንን ይመስላል ይከታተሉኝ። አመት በዓልና አመጋገባችን :- ነገ ጥዋት ቀኑ የበዓል እንደመሆኑ መጠን ከቅባትና ከስጋ ነክ ምግቦች ተለይቶ የቆየ ሰውነታችን ወደ ነበረበት እስኪመለስ መመገብ ያለብን የምግብ አይነት ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የምናዘጋጃቸዉ ምግቦች :- • ቅባት የበዛባቸዉ • ጨው የበዛባቸው • ጣፋጭነት የበዛባቸው • የአልኮል መጠናቸው የበዛ መሆን የለባቸውም በአንጻሩ :- • በልክ እና ከመጠን ባላለፈ መልኩ • ለስለስ ያሉና ለጨጓራ የማያስጨንቁ • ለሆድ የማይከብዱ • በቀላሉ ታኝከው የሚዋጡ • በንጽህና የተዘጋጁ መሆን ይኖርባቸዋል። ተገቢዉን ጥንቃቄ በመዉሰድ ራስዎን እና ቤተሰብዎን ከህመም ይጠብቁ ፡፡ በተረፈ 2014 አዲሱ አመት የጥጋብ የደስታ የመፋቀር የመቻቻል የፍቅር ግዜ እዲሆንልን ምኞቴ ነው። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https

ፈስቡክ ምንም ዳታ ሳይበላብን ለመጠቀም አዲስ አፕ በጣም ፈጣን ሞክሩት እኔ ተመችኛል @telecomBirr

የማንጎ ቅጠል ለስኳር ታማሚዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ ይከታተሉን። ✴✳ የስኳር በሽታ ምልክቶች እነዚህን ይመስላሉ፦ ✅ በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት፡፡ ✅ ከመጠን ያለፈ የውሃ ጥም፡፡ ✅ የፍላጎት እና ትኩረት ማጣት፡፡ ✅ የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት፡፡ ✅ የረሃብ ስሜት መጨመር፡፡ ✅ የክብደት መቀነስ፡፡ ✅ ድካም በእጅና እግር አካባቢ፡፡ ✅ የአይን እይታ መጋረድ/ብዢታ፡፡ ✅ በተደጋጋሚ በኢንፌክሽን መጠቃት፡፡ ✅ የቁስል ማገገሚያ ጊዜ መርዘም፡፡ ✅ ማስመለስ እና የሆድ ህመም ናቸው፡፡ ✴✳ የማንጎ ቅጠል ለስኳር ታማሚዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ 👉🌀 በደም ውስጥ ያለ የስኳር መጠንን መቆጣጣር የስኳር ህመምን ለመቆጣጣር ከሚረዱን መንገዶች ውስጥ አንዱ የደም ውስጥ ያለን የስኳር መጠን መቆጣጣር ነው። የማንጎ ቅጠል ሰውነታችን ኢንሱሊን የማምረት አቅም እና የግሉኮስ ስርጭት እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን፥ ይህ ደግሞ በደማችን ውስጥ ያለን የስኳር መጠን ለመቆጣጣር ይረዳል ነው የተባለው። 👉🌀 የኮሌስትሮል መጠንን ለመቆጣጣር የስኳር በሽታ ታማሚ ከሆንን በሰውነታችን ውስጥ ያለ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን የልባችን ጤንነት ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ሆኖም ግን የማንጎ ቅጠል በፔሲተን፣ ቪታሚን C እና ፋይበር ንጥረ ነገሮች የበለፀገ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ይረዳል። 👉🌀 በስኳር ህመም ምክንያት የሚከሰት የአይን ህመም የማንጎ ቅጠል ቪታሚን A የበለጸገ በመሆኑ ለአይን ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታም ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የማንጎ ቅጠል የስኳር ህመም ምልክቶች የሆኑትን በእንቅልፍ ሰዓት ቶሎ ቶሎ የመሽናት፣ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መቀነስ እና የአይን እይታ መደብዘዝ ችግሮችን ለመቀነስም ይረዳል ተብሏል። የማንጎ ቅጠልን እንዴት መጠቀም አለብን…? ✴ ከማንጎ ዛፍ ላይ የተቆረጠ ከ10 እስከ 15 ቅጠል ማዘጋጀት ✴ ውሃ ማፍላት፤ በሚፈላው ውሃ ውስጥ የማንጎ ቅጠሉን በመጨመር አንድ ላይ እንዲፈላ በማድረግ ማሳደር ✴ ጠዋት ከእንቅልፋችን እንደተነሳን ሌላ ምግብም ይሁን መጠጥ ከመውሰዳችን በፊት የማንጎ ቅጠል ሻዩን መጠጣት ✴ ይህንን ለሁለት ወይም ሶስት ወራት ያለማቋረጥ የእለት ከለት ተግባራችን ውስጥ በማካተት በቀላሉ የስኳር ህመምን መቆጣጣር ያስችለናል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

መሰላቸትን ለራስህ ፍቀድ ================ የአብዛኞቻችን ሕይወት ስራችንን ብንተው እንኳን ትኩረታችንን በሚሰርቁ ድርጊቶች የተሞላ ከመሆኑ የተነሣ ለትንሽ ደቂቃ እንኳን ምንም ሣንሰራ ዘና ብለን መቀመጥ አንችልም። አንድ ጓደኞዬ “ሰዎች ሰብአዊ ፍጡራን መሆን አቁመው ሰራተኛ ፍጡራን ሆነዋል” ብሏል። አልፎ አልፎ መሰላቸት የሚኖረውን ጥቅም የተረዳሁት ከዋሽንግተን ወጣ ብላ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ውስጥ የንግግር የስነ ልቦና ሕክምና በምማርበት ጊዜ ነው። ከተማዋ ትንሽ ስለነበረች ብዙ የሚደረግ ነገር አልነበረም። የመጀመሪያ የትምህርት ጊዜ እንዳለቀ አስተማሪዬን “እዚህ አካባቢ ማታ ማታ ምን ማድረግ እችላለሁ?” አልኩት። እሱም “ራስህን እንድትሰላች ፍቀድለት። ምንም አታድርግ። በዛ ላይ መሰላቸትን መልመድ የትምህርትህ አንድ አካል ነው።” አለኝ። በመጀመሪያ እየቀለደ መስሎኝ ነበር። “ለምንድነው በገዛ እጄ እንድሰላች የማደርገው?” ብዬ ጠየቁት። እሱም እራሴን ለአንድ ሰዓት ያህል እንኳን እንድሰላች ከፈቀድኩለት እና የሆነ ጊዜ ማሣለፊያ ነገር ከማድረግ ከተቆጠብኩኝ የመሰላቸቱ ስሜት ወደ ሰላማዊ ስሜት እንደሚለወጥ አስረዳኝ። ሳይዋጥልኝ ተቀበልኩት። ከሞከርኩት በኋላ እሱ እንዳለኝ መሆኑን ሣይ በጣም ተገረምኩ። መጀመሪያ መሰላቸቱን መቋቋም ከባድ ነበር። ጊዜ ማሣለፊያ የሆነ ነገር ማድረግ ስለለመድኩ መጀመሪያ ላይ ዘና ለማለት ተቸግሬ ነበር። ከትንሽ ጊዜ በኋላ እየለመድኩት መጣሁ። ከዛ እንደውም በጣም እያዝናናኝ መጣ። እየተናገርኩ ያለሁት ለሰዓታት ያለ ስራ በስንፍና ስለመቀመጥ ሣይሆን ዘና የማለትን ጥበብ ስለመማር ነው። ምንም ነገር ሣያደርጉ እራስን ሆኖ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዘና ማለት። የተለየ ዘዴ አያስፈልገውም በቃ አስበንበት ለተወሰነ ጊዜ ምንም አለመስራት ብቻ ነው። ረጋ ብሎ ተቀምጦ ሀሣባችንንና ስሜታችንን ማጤን። መጀመሪያ ላይ የተወሰነ ሊጨንቀን ይችላል። በተለማመድነው ቁጥር እየቀነሰልን ይመጣል። የምናገኘው እርጋታ ደግሞ ከፍተኛ ነው። አብዛኛው ጭንቀቶች የሚፈጠሩት አዕምሯችን በጣም እየሰራ፣ የሚያተኩርበት ነገር ፍለጋ ሲባዝን ነው። አንድ ስራ እየሰራ ስለሌላ ስራ ያወጣል ያወርዳል። “ከዛስ?” ሲለን ምሣ እየበላን ቡና የት እንደምንጠጣ እናስባለን። ቡና እየጠጣን ስንጨርስ የት እንደምንሄድ እናውጠነጥናለን። ሳምንቱ ሊያልቅ ሲል ቅዳሜና እሁድ ምን እንደምንሰራ እናቅዳለን። ቤታችን እንደገባን በቀጥታ ቲቪ ወይም ፌስ ቡክ እንከፍታለን፤ ወይ ስልክ እንደውላለን፤ ወይ መፅሀፍ እንገልፃለን፤ ወይ የሆነ ነገር መስራት እንጀምራለን። ለደቂቃ እንኳን ምንም ነገር ሣንሰራ መቀመጥ የሚያስፈራን ነው የሚመስለው። ምንም ነገር ሣይሰሩ መቀመጥ እንዴት ዘና ማለት እንደምንችልና አዕምሯችን አንዴት ተረጋግቶ ማሰብ እንደሚችል ያስተምረናል። መሰላቸት ማለት ለአዕምሯችን “ቆይ አሁን አይደለም” ብለን ዘና የምንልበት ነፃነት እንደመስጠት ነው። ልክ እንደአካላችን አዕምሮአችንም ከጥድፊያ ኑሮ ጋብ የሚልበት እረፍት ያስፈልገዋል። አዕምሮአችን እረፍት ስንሰጠው በጣም ጠንካራ፣ ፈጣንና ትኩረት ማድረግ የሚችል ሆኖ እናገኘዋለን። እንድንሰላች ለራሣችን ስንፈቅድ በያንዳንዱ ቀን በየአንዳንዱ ደቂቃ መስራት ያሉብን ነገሮች ከሚያሳድሩብን ከፍተኛ ጫና አእምሯችን ለተወሰነ ጊዜ “እፎይ” እንዲል እናደርገዋለን። ከሁለቱ ልጆቼ አንዳቸው እኔ ጋር መጥተው “አባዬ ሰለቸኝ።” ሲሉኝ “በጣም ጥሩ ለትንሽ ጊዜ እንደዚሁ ቀጥሉ ይጠቅማችኋል” እላቸዋለሁ። እንደዚህ ማለት ከጀመርኩ በኋላ እየመጡ የሆነ ነገር እንዳደርግ መጠየቃቸውን አቁመዋል። የሆነ ሰው “እራስን እንድትሰላች ፍቀድ” ይለኛል ብላችሁ አስባችሁ አታውቁ ይሆናል። ያ የሂደቱ መጀመሪያ ይመስለኛል። ከ"ቀላሉን ነገር አታካብድ" መፅሀፍ የተወሰደ

የታይሮይድ ሆርሞኖች ምርመራ ምንነት ታይሮይድ የፊትለፊት የአንገት ክፍል የሚገኝ ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑትን T3 እና T4 የተባሉ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ እጢ(gland) ነው። በደም ምርመራ የሚታ
የታይሮይድ ሆርሞኖች ምርመራ ምንነት ታይሮይድ የፊትለፊት የአንገት ክፍል የሚገኝ ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑትን T3 እና T4 የተባሉ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ እጢ(gland) ነው። በደም ምርመራ የሚታወቁት T3 እና T4 ሆርሞኖች መጠን ከፈም ዝቅም ማለት በሰውነታችን ብዙ ውስብስብ ችግሮችን ይፈጥራል። የነዚህ ሆርሞኖች ማነስ በህክምና አጠራሩ ሀይፖታይሮይዲዝም ይባላል። ምልክቶችም ከመጠን በላይ መወፈር፣ከፍተኛ የድካም ስሜትና ድብርት ዋናዎቹ ናቸው።የተለያዩ በሽታዎች የሆርሞቹ መጠን እንዲቀንሱ ቢያደርጉም የእጢው በኦፕሬሽን መወገድ ግን ዋነኛው መንሴ ነው። ታይሮክሲን የተባለ የሚዋጥ መድኃኒት በመውሰድ ይታከሙታል። የT4 እና T3 ከመጠን በላይ ከፍ ማለት ሀይፐርታይሮዲዝም ይባላል።ያልታሰበበት የክብደት መቀነስ ፣በቀላሉ መጨናነቅና መንቀዥቀዥ፣የእጅ መንቀጥቀጥ እና የሰገራ መቅጠን ዋና ዋና ምልክቶች ናቸዉ። የተለያዩ የህክምና አማራጮች ሲኖሩት መድኃኒት መውሰድ እና ኦፕሬሽን መደረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የT3 እና T4 ሆርሞኖች ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት ሳይታከሙት ለረጅም ጊዜ ከቆየ የልብ ድካም እና ሌሎች ችግሮችን በመፍጠር የጤና እክል ያስከትላል። ለዚህም ሲባል ባደጉ ሀገሮች ማንኛውም ህፃን ሲወለድ የነዚህ ምርመራዎች ይደረግለታል። የነዚህ ሆርሞኖች ትክክል አለመሆን በህፃናት እድገት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። ሌላው ከT3 እና T4 አብሮ የሚታዘዘው ምርመራ TSH ሲሆን የዚህ ሆርሞን ዝቅ ማለት የT4 እና T3 ሆርሞኖች ከፍ ማለትን ሲያሳይ TSH ከፍ ካለ ደሞ T3 እና T4 መጠን ዝቅ ማለታቸውን ያመለክታል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias

በኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱ ህጻናት ይህችን ዓለም በሁለት መንገድ ይቀላቀላሉ፡ በምጥ ወይም ደግሞ በኦፕሬሽን (surgical delivery by Caesarean section)፡፡ በአሁን ወቅት የህክምና አማራጭ ያላቸው እናቶች አምጦ ከመውለድ ይልቅ በኦፕሬሽን መውለድን እንደተሻለ አማራጭ ሲወስዱት ይታያል፡፡ አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችም በሁለቱም መንገድ መውለድ ያለውን ጠቀሜታና የጎንዮሽ ጉዳት አስረድተው ውሳኔውን ለእናቶች ከመተው ይልቅ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ እናቶችን ሲገፋፉ ይታያል፡፡ ለመሆኑ በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መፈቀድ አለበት? ያለው ጥቅምና ጉዳቱስ ምንድን ነው? በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መወሰን አለበት? 1. አምጦ መውለዱ ለእናትየው ወይም ደግሞ ለህፃኑ ህይወት አደጋ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ሲታመንበት 2. ጽንሱ በጣም የፋፋ/የወፈረ/ ከሆነ እና የእናትየው ማህጸን ጠባብ ከሆነ 3. የጽንሱ አቀማመጥ በትክክል ካልሆነ ማለትም በእርግዝና የመጨረሻዎች ቀናት ጭንቅላቱ ወደታች ካልመጣ 4. በምጥ ወቅት ጽንሱ በቂ ኦክስጅን ካላገኘና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው 5. መንታና ከዚያ በላይ ጽንስ ሲኖር 6. የተራዘመ ምጥ ሲኖር እና 7. እናትየው ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባት፤ የስኳር በሽተኛ ከሆነች፡ የHIV ቫይረስ ካለባት ጥቅሙ፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እናቶችን እና የጽንስን ህይወት ይታደጋል፡፡ እናቶች በምጥ ወቅት ሊሰማቸው የሚችለውን የተራዘመ ስቃይ ያስቀራል ጉዳቱ፡ 1. ጽንሱን ለማውጣት የሚቀደደው የሰውነት ከፍል ለመዳን ጊዜ ይወስዳል፤ በሰውነት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚድን አይደለም 2. የእናቶችን የሆስፒታል ቆይታ ያራዝማል፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በፍጥነት አገግመው ልጆቻቸውን ለማጥባትም ሆነ ለመንከባከብ ይቸገራሉ 3. የመጀመሪያ ልጃቸውን በኦፕሬሽን የወለዱ እናቶች ቀጣይ ልጆችን በተመሳሳይ ሂደት እንዲወልዱ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህም በማህጸን ግድግዳ ላይ ተደጋጋሚ ጠባሳዎች ያስከትላል፤ ቁስሉ በቶሎ ካልዳነ ደግሞ የማህጸን ግድግዳ ከሌላ የሰውነት ከፍል ጋር ሊጣበቅ ይችላል 4. በምጥ ከሚወልዱ እናቶች ይልቅ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች ለከፍተኛ ደም መፍሰስና እንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በምጥ ከሚወልዱ እናቶች የመሞት ዕድላቸው ሶስት አጥፍ የሰፋ ነው 5. በኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ የሽንትና የሰገራ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሊጎዱ ይችላሉ ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር እናቶች አምጠው መውለድን ቢመርጡ ይመከራል፡፡ አምጠው የሚወልዱ እናቶችም የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንዳለቸው ይናገራሉ፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

የጥርስ ህመም ሲሰማዎት እንዲህ ያድርጉ ምናልባት ሰውነትዎ ላይ ከሚሰሙት የህመም ስሜቶች ምቾት የሚነሳው ጥርስ አካባቢ የሚከሰት ህመም ሳይሆን አይቀርም። መጠዝጠዝ ሲመገቡ፣ ውሃ ሲጠጡ አልያም ንፋስ ሲነካው ከፍተኛ የህመም ስሜት ማስተናገድ የዚህ ችግር መገለጫዎች ናቸው። ብዙ ጊዜ ማስታገሻ በመውሰድ ከሚከሰተው የህመም ስሜት ለመገላገል የሚወሰድ የመፍትሄ እርምጃ ነው። አልፎ አልፎም ህክምና ተቋም በመሄድ የተበለሻውን ጥርስ ማስነቀል እና ማስወገድም የዚህ መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከዚህ ባለፈ ግን ጥርስ ሳይቦረቦርና ሂደቱ ሲጀምረው የሚሰማን ከፍተኛ የጥርስ ህመም ለማስታገስ ነጭ ሽንኩርት እና ቅርንፉድን በመጠቀም ማከም ይቻላል። ሁለቱም ባላቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ ምክንያት ለዚህ መሰል ችግር እጅጉን ተመራጭ እና የሚመከሩ ናቸው። ይህን ለማግኘት ደግሞ በቀላሉ ህመም የሚሰማዎት ቦታ ላይ ቅርንፉዱን ወይም ነጭ ሽንኩርቱን ማስቀመጥ እና ለተወሰነ ደቂቃ መያዝ። ከዚያም ረጠብ ሲሉ በተጎዳው ጥርስ ማኘክ እና የተወሰነ ጊዜ ይዞ ማቆየትና ማስወገድ። ወይም ደግሞ ሁለቱን እጽዋት ረጠብ አድርጎ በመጭመቅ እና በዘይት መልክ በማዘጋጀት በንጹህ ጥጥ የተጎዳው ቦታ ላይ ማፍሰስ። ከዚያም ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማቆየትና ሳይጉመጠመጡ መትፋት፤ ከ15 ደቂቃ እስከ ግማሽ ሰአት ያክል የዞ ማቆየት ያስፈልጋል። ይህንን በማድረግ ከሚሰማዎት የጥርስ ህመም ስሜት መገላገል ይችላሉ። እነዚህ ሁለት እጽዋት ከጥንት ጀምሮ ለተለያዩ ህመምች መፍትሄነት የሚወሰዱ ሲሆን፥ በተለይም ደግሞ ከአፍ ጋር ለተያያዘ የጤና ችግር መፍትሄዎች ናቸው። ለምሳሌ ነጭ ሽንኩርት ለተስተካከለ የደም ዝውውር ስርአት የሚረዳውን ኢውግነል የተባለ ውህድን በውስጡ ይዟል። ይህ ደግሞ ለመላው የሆድ እና የአፍ ጤንነት እጅጉን የሚረዳ አስፈላጊ ንጥረ ነገር ሲሆን፥ ከዚህ ባለፈም ለአጥንት ጥንካሬ የሚረዱ በርካታ ውህዶችን ይዟል። ባክቴሪያዎችንና አላስፈላጊ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድና ለማጥፋትም ይህ እጽ እጅጉን ይረዳል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

ራስ ምታት መቼ ያሰጋል? AFRODOCTORS ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ራስ ምታት በአብዛኛው በራሱ በሽታ ከመሆን ይልቅ የሌላ በሽታ መገለጫ ነው፡፡ ብዙ የራስ ምታት አይነቶች ቢኖሩም ሁሉም አንድ የሆነ መለያ አላቸው፡፡ይኸውም ህመም ማስከተላቸው ነው፡፡ አንዳንዶቹ በራስ ህመም ብቻ ሲያቆሙ ሌሎቹ ደግሞ እንደ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ የመሳሰሉትን ያስከትላሉ፡፡ ራስ ምታት በብዛት አደጋ የሌለውና በቀላሉ ልትከላከለው የምትችለው ነገር ነው፡፡ የራስ ምታት መነሻ ምክንያቶች እና የተወሰኑ ምክንቶች • መጠጥ/አልኮል፡- በተለይ ቀይ ወይን • የእንቅልፍ መለዋወጥ/ የእንቅልፍ ማጣት • ጭንቀትና የመሳሰሉት ካለዎ የህመሙ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ • ድንገተኛ የሳይነስ ኢንፌክሽን • በጭንቅላት ዉስጥ ደም መርጋት • በጭንቅላት ዉስጥ የደም ቧንቧ መወጠር/መስፋት መከሰት • የጭንቅላት ዉስጥ ዕጢ • በካርቦንሞኖኦክሳይድ መመረዝ፡- ለምሳሌ የከሰል ጭስ • የፈሳሽ ዕጥረት(ዲሃይድሬሽን) • የጥርስ ችግር • የጆሮ ኢንፌክሽን.....ወዘተ…. ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ? የራስ ምታት እንደ ስትሮክና የማጅራት ገትር ለመሳሰሉ በጣም አደገኛ/ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር ሊያመጡ ለሚችሉ ህመሞች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም በህይወትዎ አይተዉት የማያዉቁት የራስ ምታት ስሜት፣ በድንገት የመጣና ከፍተኛ የራስምታት አይነት ካለዎና የሚከተሉት ምልክቶች ከራስምታቱ ጋር ተያይዞ ካለዎ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ድንገተኛ የህክምና መስጫ ተቛም ባስቸኳይ መሄድ ይገዎታል፡፡ ራስ ምታት መቼ ሊያሰጋኝ ይገባል? ከአንድ ሳምንት በላይ ከቆየ፣ ምንም እንኳን በተደጋጋሚ ማስታገሻ ብትወስድም ከመሻል ይልቅ እየባሰ ከሄደ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሃይለኛ ራስ ምታት ሲያምህ ከሃምሳ አመት በላይ ከሆንክ፣ ከዚህ በፊት የነበረውን አይነት ቀይሮ አዲስ ፀባይ ካመጣ፣ ህመሙ ከየእለት ኑሮህ የሚያስተጓጉልህ ከሆነ፣ ለምሳሌ ስራ ለመስራት የማያስችል አይነት ህመም ካለህ፣ ከራስ ምታቱ በተጨማሪ የተለያዩ የበሽታ ምልክቶች ለምሳሌ.... ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ፣ ሳል • እራስን መሳት • የመቀበጣጠር ወይም የሰዎችን ንግግር መረዳት ያለመቻል • ከፍተኛ ትኩሳት • ባንድ በኩል ያለዉ የሰዉነት ክፍልዎ የመደንዘዝ፣ የመስነፍ ወይም ሽባ ከሆነ • የአንገት ያለመታጠፍ ችግር ካለዎ ( Stiff neck) • የዕይታ ችግር • የመናገር ችግር • የመራመድ ችግር • ማቅለሽለሽና ትዉከት የመሳሰሉት …ከታዩብህ ወደሆስፒታል ሄደህ ዶክተርህን ማማከር አለብህ፡፡ ማስታገሻውስ? • በቂ እንቅልፍ ማግኘት፡- በእያንዳንዱ ሌሊት በቂ እንቅልፍ ለማግኘት መቻል ነዉ እንጂ ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ መተኛት የለብዎትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ወደ አልጋ ለእንቅልፍ የሚሄዱበትና ሲነጋ የሚነሱበት ሰዓት ተመሳሳይ ቢሆን ይመረጣል፡፡ • እረፍት ማድረግና ዘና ማለት፡- ያለው ራስምታት ሚግሬይን ከሆነ ከተቻለ ፀጥ ያለና ጨለማ ክፍል ቢያርፉ ይመረጣል፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias