ch
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

前往频道在 Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

显示更多

📈 Telegram 频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias 的分析概览

频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 967 名订阅者,在 医学 类别中位列第 1 154,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 678

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 967 名订阅者。

根据 26 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -547,过去 24 小时变化为 -20,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 24.05%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.27% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 805 次浏览,首日通常累积 1 453 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

凭借高频更新(最新数据采集于 27 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 医学 类别中的关键影响点。

19 967
订阅者
-2024 小时
-1217
-54730
帖子存档
የጥርስ መቦርቦርና መበስበስ የጥርስ መቦርቦር በጥርስ መበስበስ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን ችግሩ በጊዜ ሂደት የሚመጣ ነዉ። የጥርስ መበስበስ እንዲከሰት የሚያደርጉ ነገሮች ❤️ በጥርሱ ላይ የሚጋገር ነገር ሲኖር፦ በጥርስ ላይ የሚጋገሩ ነገሮች የሚከሰቱት ብዙ ስኳርና ስታርቾችን ከተመገቡ በኃላ ጥርስዎን በደንብ ባለማጽዳት ምክንያት ነው።ስኳርና ስታርቾች ከጥርሶችዎ ላይ ካልፀዱ ባክቴሪያዎቹ በፍጥነት ይመገቡትና ጥርሱ ላይ ንጣፍ ይፈጥራሉ። በጥርሶችዎ ላይ የሚቆዩ ንጣፎች ከድድ መስመርዎ ስር ወይም በላይ በመጠራቀም ጠንካራ ነገር ይፈጥራሉ። ይህም ጠንካራ ንጣፉን ለማስወገድ የበለጠ አስቸጋሪ ከማድረጉም በላይ ለባክቴሪያዎች መከላከያ ሆኖ ያገለግላል። ❤️ የንጣፉ ጥርስን መጉዳት፦ በንጣፉ ዉስጥ ያለዉ አሲድ በጥርስዎ ጠንካራ ክፍል ወይም ኢናሜል ላይ ጉዳት በማድረስ መዓድኖችን ያስወግዳል። ይህ ትናንሸ ቀዳዳዎችን በጥርሱ ላይ እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ኢናሜሉ ከተጎዳ በኃላ ባክቲሪያዎቹና አሲዱ ቀጣዩን የጥርስ ንጣፍ( ዴንቲን)ና ለስላሳዉን የጥርስ ክፍል ያገኙታል። ይህ ክፍል ከጥርስ ስርና ነርቭ ሩት ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሚያደርገዉ ክፍል ነው። ❤️ የጉዳቱ መቀጠል፦ አንዴ ጥርሱ መበስበስ ከጀመረ ባክቴሪያና አሲዱ የሚያደርጉትን ጉዳት በመቀጠል የዉስጠኛዉ የጥርስ ክፍል የሆነዉንና የደም ቧንቧና ነርቮችን ያያዘዉ ክፍል ወይም ፐልፕ ላይ ጉዳት ማድረስ ይጀምራሉ። በዚህም ምክንያት ፐልፑ ያብጣል፣ይቆጣል፣ ነርቩ ህመም እንዲመጣ ያደርጋል። ህመሙ ከጥርሱ አልፎ አጥንቱ ላይ መሰማት ይጀምራል። አጋላጭ ምክንያቶች ማንኛዉም ጥርስ ያለዉ ሰዉ የጥርስ መቦርቦር መከሰት ተጋላጭ ቢሆንም የሚከተሉት ምክንያቶች ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጉዎታል፦ ❤️ የጥርሱ ቦታ፦ የጥርስ መበስበስ በብዛት የሚከሰተዉ ከፊትለፊት ጥርሶች ይልቅ በሰተጀርባ ባሉ መንጋጋ ጥርሶች ላይ ነዉ። የመንጋጋ ጥርሶች የምግብ ቅንጣቶች ሊጠራቀሙበት የሚችሉ ብዙ ጎድጓዳ ቦታዎች ሰላላቸዉና በደንብ ለማፅዳት አስቸጋሪ ናቸው። ❤️ የተወሰኑ ምግቦችና መጠጦች፦ በጥርስዎ ላይ ረዘም ላለ ጊዜ ሊለጠፉ የሚችሉ ምግቦች እንደ ወተት፣ አይስክሬም፣ ማር፣ስኳር፣ሶዳ፣ የደረቁ ፍራፍሬዎች፣ ኬክ፣ ከረሜላዎችና ችፕሶች በቀላሉ በምራቅ ከሚለቁት ወይም ከሚታጠቡት ይልቅ የጥርስ መበስበስ እንዲከሰት ያደርጋሉ። ❤️ በተደጋጋሚ የሚጎነጩ ነገሮችንና መክሰስ መጠቀም፦ ስኳር የበዛባቸው መጠጦችን ያለማቋረጥ ሲመገቡ ወይም ሲጠጡ፣ ጥርስዎን የሚያጠቁ እና የሚያደክሙ አሲዶችን ለማምረት ለአፍ ባክቴሪያ ተጨማሪ ጉልበት ይሰጣሉ። ❤️ ልጆችን በእንቅልፍ ላይ እያሉ መመገብ፦ ህፃናትን እንቅልፍ ተኝተዉ ሳለ ወተትን ጨምሮ ስኳር ያላባቸዉ ፈሳሾችን በጡጦ መመገብ ምግቡ ጥርሳቸዉ ላይ ብዙ ሰዓታት አንዲቆይ ስለሚያደርግ ለጥርሳቸዉ መበስበስ ምክንያት ይሆናል። ❤️ በበቂ መጠን ጥርስን ያለመቦረሽ፦ ጥርስዎን ከምግብና ከመጠጥ በኃላ የማያፀዱ ከሆነ ጥርስዎ ላይ ስለሚጋገር ጥርሱን ለጉዳት ይዳርጋል ❤️ በቂ ፍሎራይድ አለማግኘት፦ፍሎራይድ የጥርስን መቦርቦር አደጋ ሊቀንስ የሚችል ሲሆን ገና መቦርቦር የጀመረ ጥርስም ካለ ለማስተካከል ይጠቅማል። ከዚህ የተነሳ የቧንቧ ዉሃ ፍሎራይድ የሚጨመርባት ሲሆን በጥርስ ሳሙናዎችና የአፍ መጎመጥመጫ ፈሳሾች ዉስጥም ይገኛል። ነገር ግን በብዙዎቹ ታሽገዉ በሚሸጡ ዉሃዎች ዉስጥ ፍሎራይ አይኖርም። ❤️ ልጆችና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ፦ በጊዜ ብዛት ጥርስ እየወለቀና ድድም እየሸሸ ይሄዳል፤ ይህም ለጥርስ ስሮች መበስበስ ይበልጥ ተጋላጭ ይሆናሉ። በተጨማሪም በእድሜ የገፉ ሰዎች የምራቅ መመንጨትን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን ሊወስዱ ይችላሉ። ይህም ለጥርስ መበስመስ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ❤️ የአፍ ድርቀት፦ የምራቅ መቀነስ ለአፍ ድርቀት ይዳርጋል። በምራቅ ዉስጥ ያለዉ ኬሚካልም በበክቴሪያዎች የሚመረትን አሲድ ሊቀንሱ ይችላሉ። ❤️ ቃር፦ ቃር ወይም ጋስትሮኢንተስቲናል ሪፍሌክስ ዲዚዝ የጨጓራ አሲድ ወደላይ ተመልሶ በመምጣት የጥርስ ኢናሜልን ሊጎዳ ይችላል። ❤️ የአመጋገብ ችግር ያለባቸዉ፦ አኖሬክሲያና ቡሌሚያ የሚባሉ የአመጋገብ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ለጥርስ መቦርቦር ችግር ተጋላጭ ናቸዉ። በተደጋጋሚ ማስታወክ ካለ የጨጓራ አሲድ የጥርሱን ኢናሜል በቀላሉ እንዲበላ ያደርገዋል። የአመጋገብ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ምራቅ የማምረት ችግርም ይኖራቸዋል።

የወር አበባ ዑደት ስለወር አበባ ዑደት ትክክል የሆነዉና ያልሆነዉ ነገር ምንድን ነዉ? የወር አበባዎን መከታተል ስለእርስዎ የወር አበባ ዑደት ትክክል የሆነዉን ለመረዳት፣እንቁላል ከአብራኳ የምትወጣበትን ጊዜ ለማወቅና ሌሎች አስፈላጊ ለዉጦችን ለመለየት ይጠቅምዎታል፡፡ ለምሳሌ የወር አበባ ዑደት መዘግየትን ለማወቅ ወይም ቀኑን ያልጠበቀ የወር አበባ መፍሰስ የመሳሰሉትን ለመከታተል ይረዳል፡፡ ምንም እንኳ የወር አበባ ዑደት መዛባት ሊከሰት የሚችል ነገር ቢሆንም አንዳንዴ የህመም ማሳያም ሊሆን ይችላል፡፡ ስለወር አበባ ዑደት ትክክል የሆነዉ/ኖርማል ነገር ምንድነዉ? የወር አበባ ዑደት የሚቆጠረዉ መፍሰስ ከጀመረበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከሚቀጥለዉ የወር አበባ ዑደት የመጀመሪያ ቀን ሲሆን ይህ ርዝማኔ በሁሉም ሴቶች ላይ አንድ አይነት አይደለም፡፡ ኖርማል የሚባለዉ የወር አበባ ዑደት በየ 21 እስከ 35 ቀን ባለዉ ጊዜ ዉስጥ የሚመጣ ሲሆን መፍሰሱ ከሁለት እስከ ሰባት ቀናት ሊቆይ ይችላል፡፡ የወር አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት በጀመሩበት ጊዜያት/ዓመታት ያሉ የወር አበባ ዑደቶች ርዝማኔ አጫጭር ሲሆኑ እድሜዎ እየጨመረ ሲመጣ ግን እየተስተካከለ ይመጣል፡፡ እድሜዎ እየጨመረ መጥቶ ወደማረጥ ሲቃረቡ ደግሞ የወር አበባ ዑደቱ ተመልሶ እየተዛባ ሊመጣ ይችላል፡፡ እድሜዎ እየጨመረ ሲመጣ ለማህፀን ካንሰር የመጋለጥ እድሉ እየጨመረ ስለሚመጣ የወር አበባ መዛባት በዚነህ ጊዜያት ካለዎ የጤና/ህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ የወር አበባ ዑደቱን እንዴት መከታተል ይቻላል? የራስዎን የወር አበባ ዑደት ትክለኛዉን እርዝማኔ ለማወቅ የወር አበባ ዑደትዎን በካላንደር ላይ መመዝገብ ይጀምሩ፡፡ ይህም የወር አበባ ዑደቱ በትክክል መምጣቱንና አለመምጣቱን ለመከታተል እንዲረዳዎ የወር አበባ ዑደቱ መፍሰስ ከጀመረበት ቀን ጀምረዉ ለተከታታይ ወራት (ቢያንስ ለ6 ወራት) በየወሩ በመደዳ ይመዝግቡ፡፡ ስለሆነም ስለወር አበባ ዑደትዎ የሚያሳሰውብዎ ነገር ካለ በሚከተሉትን ነገሮች ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ይመዝግቡ • የመጨረሻ ቀን፡- • የወር አበባ ዑደቱ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል? • ከተለመደዉ የዑደት እርዝማኔ ማጠር ወይም መርዘም አለዉ ወይ? • የአፈሳሰሱ ሁኔታ፡- • የወር አበባ ዑደቱ የአፈሳሰስ መጠን ከተለመደዉ በላይ ነዉ ወይስ በታች? • የንፅህና መጠበቂያዉን በቀን ምን ያህል ጊዜ ይቀይራሉ? የረጋ ደም ይፈሳል ወይ? • ያልተለመደ ከብልት ደም መፍሰስ ካለዎ፡-በወር አበባ ዑደትዎ መሃል ከብልት ደም መፍሰስ አለዎ? • ህመም፡- ከወር አበባ ዑደቱ ጋር ተያያዥነት ያለዉ ህመም አለዎ? ህመሙ ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ የተባባሰ ነዉ? • ሌሎች ለዉጦች ካሉ፡- የባህሪይ ወይም ፀባይ/ሙድ/ መቀያየር ገጥሞታል? የወር አበባ ዑደት ለዉጥ በነበረበት ወቅት አዲስ የተቀየረ ነገር አለ? የወር አበባ ዑደት ያለመስተካከልን/መለዋወጥን የሚያመጡ ነገሮች ምንድናቸዉ? የወር አበባ ዑደት መለዋወጥን የሚያመጡ/ የሚያስከትሉ የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ እነርሱም እርግዝና/ጡት ማጥባት፡- • የወር አበባ ዑደት መዘግየት ካለ የእርግዝና ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ • ከእርግዝና በኋላ ጡት ማጥባት የወር አበባ ዑደት ተመልሶ ሳይመጣ እንዲዘገይ ሊያደርግ ይችላል፡፡ • ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም/ Polycystic ovary syndrome (PCOS)፡-የዚህ የሆርሞን መዛባት ችግር ያላቸዉ ሴቶች ያልተስተካከለ የወር አበባ ዑደት የእንቁሊጤ መጠን መጨመር ሊታይ ይችላል ( የመጠን መጨመሩ እንቁሊጤዋ ዉሃ ስለምትቋጥር ነዉ፡፡) • የዳሌ ዉስጥ መቆጥቆጥ /Pelvic inflammatory disease (PID)፡- • የመራቢያ አካላት ኢነፌክሽን ለዚህ አይነት ችግር ሊዳርግ ይችላል፡፡ • የማህፀን ላይ እጢ፡- የማህፀን ላይ እጢ ካለዎ የወር አበባ ዑደት መጠን መብዛትና መራዘም እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ የተወሰኑ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎች፡- የወሊድ መከላከያ እንክብሎች፣ ሉፕና ሌሎችም የወር አበባ ዑደቱን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡ የወር አበባ ዑደት መዛባት እንዳይከሰት እንዴት መከላከል ይቻላል? ለአንዳንድ ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል መዉሰድ የወር አበባ ዑደቱ ተስተካክሎ እንዲመጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የሚከተሉት ለዉጦች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡ እርግዝና ሳይኖር የወር አበባ ዑደትዎ ከ90 ቀናት በላይ መቋረጥ ካጋጠመዎ ተስተካክሎ ይመጣ የነበረዉ የወር አበባ ዑደት መዛባት ከጀመረ የወር አበባ ዑደት ከሰባት ቀናት በላይ መፍሰስ ካለዉ ከተለመደዉ መጠን በላይ የደም መፍሰስ ካለ ወይም በቀን ዉስጥ ከተለመደዉ ቁጥር በላይ የንፅህና መጠበቂ/የወር አበባ ደም መቀበያ ፓድ መቀያየር ካጋጠመዎ የወር አበባ ዑደት እርዝማኔዉ/የሚመጣበትገዜ/ በየወሩ ከ21 ቀናት በታች ካጠረ ወይም ከ35 ቀናት በላይ መዘግየት ካለዉ በወር አበባ ዑደት መካከል የደም መፍሰስ ካለዎ ናቸዉ፡፡

የአጥንት ኢንፌክሽን (ኦስቲኦሜይላይትስ) ምንድን ነው? ኦስቲኦሜይላይትስ አብዛኛውን ጊዜ የኢንፌክሽን ውጤት ሲሆን የአጥንት ሕብረ ሕዋስ መቆጣት ወይም እብጠትን ያስከትላል። የአጥንት ኢንፌክሽን በብዙ የተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ሲሆን በልጆችም ሆነ በአዋቂዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፡፡ ኦስቲኦሜይላይትስ በባክቴሪያ የደም ሥር ኢንፌክሽን ምክንያት ሊከሰት ይችላል ፡፡ ይህ ዓይነቱ ኢንፌክሽን በሕፃናት እና በልጆች ላይ በጣም የተለመደ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ረጃጅም አጥንቶቻቸውን ያጠቃል ፡፡ ኦስቲኦሜይላይትስ በአዋቂዎች ላይ በሚከሰትበት ስአት ብዙውን ጊዜ በአከርካሪው አምድ በኩል የአከርካሪ አጥንትን ያጠቃል ፡፡ ምንም እንኳን በተለያየ ባክቴሪያ ወይም የፈንገስ አካላት ምክንያት የሚከሰት ቢሆንም የደም ኢንፌክሽኑ ምንጭ ግን ብዙውን ጊዜ ስታፊሎኮከስ አውሩስ (staphylococcus aureus) የሚባል ባክቴሪያ ነው፡፡ ኦስቲኦሜይላይትስ በተለያዩ ምክንያቶች እና በአቅራቢያ ካለው የሰውነት አካል ኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጣ ይችላል፡፡ ከነዚህም መካከል በድንገተኛ ጉዳት ፣ በተደጋጋሚ ከሚሰጡ የመድኃኒት መርፌዎች ፣ ከቀዶ ጥገና ጋር ተያይዞ ወይም በሰውነታችን ውሰጥ የተቀበረ ሰው ሰራሽ መሣሪያን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል፡፡ በተጨማሪም በእግር ላይ ቁስለት ያላቸው የስኳር በሽታ ያለባቸው ግለሰቦች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ በማንኛውም ሁኔታ ተሕዋስያን ወደ ተጎዳው አጥንት ለመግባት ቀጥተኛ መግቢያ በር ይኖራቸዋል ፡፡ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ግለሰቦች በኦስቲኦሜይላይትስ የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ ነው ፡፡ እነዚህም የታመመ ሴል በሽታ ፡ኤች.አይ.ቪ (HIV) ፡እንደ ኬሞቴራፒ ወይም ስቴሮይድ ያሉ በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎችን ያጠቃልላል፡፡ ኦስቲኦሜይላይትስ እንደ ኢንፌክሽኑ ምንጭ ላይ በመመርኮዝ ድንገተኛ ክስተት ሊኖረው ይችላል ፣ ዘገምተኛ እና ቀላል ጅምር ወይም ሥር የሰደደ ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ ኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች ምንድ ናቸው? የኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች እንደ መንስኤው እና እንደ በሽታው ይለያያሉ፡፡ የሚከተሉት በጣም የተለመዱ የኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች ናቸው; ሆኖም እያንዳንዱ ግለሰብ የሕመም ምልክቶችን በተለየ መንገድ ሊያጋጥመው ይችላል-  ትኩሳት (ኦስቲኦሜይላይትስ እንደ ደም ኢንፌክሽን ውጤት ሲከሰት ትኩሳቱ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል)  በተጎዳው አካባቢ ህመም ይኖረዋል  ህመምን መግለጽ በማይችሉ ሕፃናት ላይ መነጫነጭ አና በቀላሉ መበሳጨት ይታያል  የተጎዳው አካባቢ ላይ እብጠት ሊኖር ይችላል  በተጎዳው አካባቢ ላይ መቅላት እና ሙቀት ሊኖረው ይችላል  በተጎዳው አካባቢ አቅራቢያ የሚንቀሳቀሱ መገጣጠሚያዎች ማንቀሳቀስ ያስቸግራል  ክብደት የመሸከም ወይም የመራመድ ችግር ሊኖረው ይችላል  ማስነከሰ ሊኖር ይችላል  የኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች ከሌሎች የሕክምና ሁኔታዎች ወይም ችግሮች ጋር ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፡፡ ለምርመራ ሁልጊዜ ዶክተርዎን ያማክሩ ፡፡ ለኦስቲኦሜይላይትስ በሽታ የሚደረግ ሕክምና ለኦስቲኦሜይላይትስ የሚደረግ ልዩ ሕክምና ከታች የተዘረዘሩትን በመመርኮዝ በዶክተርዎ ይወሰናል ፡፡ o የእርስዎ ዕድሜ ፣ አጠቃላይ የጤና እና የህክምና ታሪክ o የበሽታው ስፋት o ለተወሰኑ መድሃኒቶች, ቀዶ ጥገናዎች እና ህክምናዎች የመቻል አቅምዎ o ለህክምናው ውጤት ያለዎት ግምት o የእርስዎ አስተያየት ወይም ምርጫ ለኦስቲኦሜይላይዝስ የሚደረግ ሕክምና ዓላማው ኢንፌክሽኑን ለመፈወስ እና ማንኛውንም የረጅም ጊዜ ውስብስብ ችግሮች ለመቀነስ ነው ፡፡ ሕክምናው የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል o መድሃኒቶች መስጠት፡-በደም ስር ወይም ደግሞ በአፍ የሚወሰዱ መድሀኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ. ሆስፒታል ተኝቶ መታከም ወይም የተመላላሽ ታካሚ መርሃግብር ሊሰጥ ይችላል፡፡ ህክምናው ለብዙ ሳምንታት ሊቆይ ይችላል፡፡ o ተከታታይ የራጅ እና የደም ምርመራዎች ቁጥጥር ይደረጋል o የህመም ማስታገሻ ይሰጣል o የአልጋ እረፍት (ወይም የተጎዳው አካባቢእንቅስቃሴ መቀነስ ) ያስፈልጋል o ቀዶ ጥገና፡- አንዳንድ ጊዜ የተጠራቀሙ ፈሳሾችን/መግል ለማፍሰስ ወይም የተጎዱትን ሕብረ ሕዋሳት እና አጥንቶች ለማስወገድ የቀዶ ጥገና ህክምና አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ፡፡ የኦስቲኦሜይላይትስ የረጅም ጊዜ ችግሮች ኦስቲኦሜይላይትስ የሚከተሉትን ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ለመከላከል የረጅም ጊዜ እንክብካቤን ይፈልጋል ፡፡እነዚህም፡-  የተጎዳው አጥንት ስብራት  በልጆች ላይ የተዳከመ እድገት (ኢንፌክሽኑ የእድገቱን ንጣፍ የሚነካ ከሆነ)  በተጎዳው አካባቢ የጋንግሪን ኢንፌክሽን  ኢንፌክሽኑ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል መሰራጨት  ካንሰር ሊያመጣ ይችላል የሕክምና ባለሙያየን መቼ ማናገር አለብኝ  የኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶችን ካዩ  በሕክምና ለይ እያሉ ለውጥ ከሌለወት  የአጥንት ኢንፌክሽን አነድ ጊዜ ስር ከሰደደ ለማስወገድ ከባድ ስለሚሆን ምልክቶቹን ካዩ ቶሎ ብለው ህክምና ያግኙ፡፡

ሰላም ሰላም እደምን አመሻችሁ የተከበራችሁ የገፃችን ተከታዮች በእናተ ጥቆማ በተነሳ ስለ ማይግሬን ሰፋያለ ማብራሪያ ይዤ ቀርቤላችሁለው በጥሞና ያንብቡት ፁሁፉ ትንሽ እረዘም ስለሚል እዳትሰላችሁ መልካም ንባብ • ማይግሬን ምንድን ነው? (ከፍተኛ ራስ ምታት) 📍ማይግሬን ከፍተኛ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት ራስ ምታት ነው። የተለያዩ ምክንያቶችን ተከትሎ የሚነሳ እና እነዚህ ምክንያቶች ሲወገዱ ደግሞ የሚቀንስ በሽታ ነው፡፡ 📍 የነዚህ የደም ስሮች እብጠት በዙሪያቸው ከሚገኙ ነርቮች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲለቁቀ ያደርጋል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ እነዚህ የተመረቱ ንጥረ ነገሮች አእምሮአችን ለህመም ያለውን ስሜት ከፍ ያደርጉታል፡፡ በመሆኑም ለትንሽ የህመም መንስኤ ከፍተኛ የህመም ስሜት እንዲሰማ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ የሚመጣ ህመምም ወጋ ወጋ የሚያደርግ አይነት ነው፡፡ • በየትኛው እድሜ ይከሰታል ? 📍 ይህ በሽታ ከ40 አመት በፊት ይጀምር እና ከ60 በላይ ሲሆኑ በተለይ በሴቶች ዘንድ ይቀንሳሉ እስከመጥፋትም ይደርሳል፡፡ በዚህ በሽታ ህፃናት ተጠቂ ሊሆኑ ቢችሉም በብዛት ግን አይታይባቸውም፡፡ ምንም እንኳን ፈውስ የሌለው በሽታ ቢሆንም በተለያዩ መድሃኒቶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች ልትቆጣጠረው ትችላለህ፡፡ •የማይግሬን ምልክቶች ምንድናቸው ? 📍 ከፍተኛ የሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ እና በመሃል እረፍት የሚሰጥ አይነት የራስ ምታት የመጀመሪያው ምልክት ነው፡፡ህመሙ ቀስ በቀስ የሚጨምር ሲሆን ከእቅልፍህ ስትነሳ እያመመህ ከሆነ ግን ከፍተኛው የህመም ደረጃ ላይ ልታገኘው ትችላለህ፡፡ 📍📍📍 በጭንቅላትህ ግማሽ ክፍል ብቻ የሚኖር ህመም የተለመደ መገለጫው ሲሆን ከግራ ወደቀኝ (ወይም በተቃራኒው) እያለ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ክፍልን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ህመሙ ከአራት ሰአት እስከ ሁለት እና ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከጭንቅላት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ይባባሳል፡፡ ሰውነትህን ሁሉ ከመክበድ ባለፈ ሊያስመልስህም ይችላል፡፡ በተጨማሪም ለሽታዎች፣ ለድምፅ እና ለብርሃን ያለህን ስሜት ይጨምራል፡፡ 📍ህፃናት ላይም ተመሳሳይ ምልክቶች ሲኖረው የሚቆይበት ጊዜ ግን አጠር ይላል ይህም ከግማሽ ሰአት እስከ አንድ ቀን ቢሆን ነው፡፡ 📍 ራስ ምታቱ ከመምጣቱ አስቀድሞ የሚታዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ሁሉም ህመምተኞች ላይ የሚከሰቱ ባይሆኑም ለሚታዩባቸው ሰዎች ግን ማይግሬን ሊነሳባቸው እንደሆነ ጥሩ ማመላከቻዎች ናቸው፡፡ በአማካይ ከአንድ ቀን በፊት በጣም ንቁ የመሆን በአንዳንዶች ላይ ደግሞ ቶሎ የመድከም ፣ የመናደድ፣ ጣፋጭ ምግቦችን የመፈለግ እና የመሳሰሉ ባህሪዎችን ያሳያሉ፡፡ የአይን ብዥታ፣ የእጅ ጣት መጠዝጠዝና መደንዘን፣ የንግግር መጓተት የመሳሰሉት ምልክቶች ማይግሬን ከመምጣቱ ከጥቂት ደቂቃወች በፊት ይታያሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ከታዪ በኋላ ማይግሬን ሊከተል ወይም ደግሞ ምንም እንኳን ያልተለመደ ቢሆንም ማይግሬኑ ላይከሰትም ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ራስ ምታቱ ሊነሳ እንደሆነ አስቀድመው ያውቃሉ፡፡ ማይግሬኑ ከሄደ በኋላም ድካም፣ ቶሎ መናደድ፣ መደበት ብሎም የተለያዩ የቆዳ ክፍሎችህን መበለዝ ልታስተውል ትችላለህ፡፡ •የማይግሬን መንስኤዎች ምንድን ናቸው ? ከ 50% በላይ የሚሆኑ በማይግሬን የተያዙ ህመምተኞች ከቤተሰባቸው ይወርሱታል፡፡ ስለዚህ በቤተሰብሽ ውስጥ የማይግሬን በሽተኛ ካለ በተለይ ደግሞ እናት፣አባት፣እህት፣ወንድም በዚህ በሽታ ተጠቂ ከሆኑ አንቺም በበሽታው ተጠቂ የመሆን እድልሽ ይጨምራል፡፡ በሽታው ከተለያዩ ሆርሞኖች ጋር ተያያዥነት ስላለው ሴት መሆን በራሱም በበሽታው የመጠቃት እድልን በትንሹ ይጨምራል፡፡ •ማይግሬንን የሚቀሰቅሱ ምክንያቶች ምንድናቸው? 📍📍📍 የተለያዩ በሽታዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚነሱ ሁሉ ማይግሬንም የራሱ ቀስቃሽ ምክንያቶች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከል ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው ጭንቀት ነው፡፡ ጭንቀት በራሱ ራስ ምታትን የሚያመጣ ሲሆን ማይግሬን ላለበት ሰው ግን ዋና ቀስቃሹ ነው፡፡ ረሃብ፣ የፈሳሽ ምግብ ብቻ ተመጋቢ መሆን ወይም የተዘበራረቀ የምግብ ፕሮግራም በሽታውን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ አልኮል መጠጦች፣ ኮምጣጣ ምግቦች፣ ቸኮሌት እና ቺዝ የመሳሰሉ ምግቦች በሽታንውን ያሰነሳሉ፡፡ ብዙ ወይም ትንሸ እንቅልፍ፣ የአየር ሙቀት ለውጦች፣ ሀይለኛ ሽታ፣ፀሃይ፣ ከፍተኛ ድምፆች በሽታውን ከሚያስነሱ ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በሴቶች በኩል ደግሞ የወር አበባ ኡደትን ተከትለው የሚጨምሩ እና የሚቀንሱ የሴት ሆርሞኖች ይህንን በሽታ ያባብሱታል፡፡ በተለይ የወር አበባሽ በሚመጣበት ጊዜ በሽታው ከድሮው በበለጠ ይጨምራል፡፡ ስለዚህም አንድ ሴት ስታርጥ የማይግሬን በሽታዋ ከመቀነስ አልፎ ሊጠፋም ይችላል፡፡ እርግዝናም የራሱ የሆነ ለውጥ ያስከትላል፡፡ •ማይግሬንን እንዴት ልከላከል? 📍📍📍 ማይግሬን የማይድን በሽታ ቢሆንም የሚከሰትባቸውን ጊዜያት ለመቀነስ የተለያዩ ነገሮች ማደረግ ትችያለሽ፡፡ በሽታውን ምን እንደሚያስነሳብሽ ለይተሸ ማወቅ እና ከነዚህ ነገሮች እራስሽ መጠበቅ የመጀመሪያው እና ዋናው ተግባርሽ ሊሆን ይገባል፡፡ ራስ ምታቱ በሚጀምርሽ ጊዜ መቼ እንደጀመረሽ፣ ህመሙ ሀይለኛ ወይስ ለዘብ ያለ እንደነበር፣ መድሃኒት ወስደሽ ከሆነ የወሰድሽውን መድሃኒት፣እና ሌሎች ምክንያቶችን በመፃፍ እና በተለያዩ ጊዜያት የወሰድሻቸውን ማስታወሻዎች በማመሳከር ምክንያቶቹን በቀላሉ ማወቅ ትችያለሽ፡፡ 📍📍📍 ከዚህ በተጨማሪ የአኗኗር ዘይቤሽን መቃኘት ተገቢ ነው፡፡ጭንቀትን ማስወገድ፣ ምግብ በሰአቱ መብላት፣ እንቅልፍ በልኩ መተኛት፣ አልኮል መጠጦችን ማስወገድ እና ከላይ የተጠቀሱ ምግቦችን ባለመብላት ራስ ምታቱን መቀነስ ትችያለሽ፡፡ የተለያዩ ረጋ ያሉ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን መስራት እና እራስን ከማዝናናት በተጨማሪ ደረቅ መርፌ (acupuncture) መጠቀምም ሊረዳሽ ይችላል፡፡ •ራስ ምታቱ ከጀመረኝ በኋላ ምን ላደርግ እችላለሁ? አንዴ ራስ ምታቱ ከጀመረህ በኋላ መድሃኒት በመውሰድ ፀጥ እና ጨለም ያለ ቦታ ላይ እረፍት አድርግ፡፡ ቀዝቃዛ ነገር ለምሳሌ በፎጣ የተጠቀለለ በረዶ ግምባርህ ላይ ማድረግ እንዲሁም ቡና መጠጣት ሊረዳህ ይችላል፡፡ • የማይግሬን ህክምና ምንድን ነው? ምንም እኳን በሽታው የማይድን ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ብዙ መድሃኒቶች እየተፈበረኩ ሲሆን ከብቃታቸው አንፃር ስናይም በጣም ጥሩ ናቸው፡፡ አንዳዶቹ ራስ ምታቱ ከመጀመሩ በፊት የሚከላከሉ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ህመሙ ከጀመረ በኋላ ህመሙን የመቀነስ ስራ ይሰራሉ፡፡ ነገር ግን መድሃኒት ከመጀመርሽ በፊት ሀኪምሽን ማማከር አለብሽ፡፡ ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን

ዝርዝር የጤና መረጃውን ከላይ ያንብቡት!
ዝርዝር የጤና መረጃውን ከላይ ያንብቡት!

✍️ " የሰውነት ሸንተረር/መስመር ምክንያት እና መፍትሄ " 🔷 " በቅንነት ሼር በማድረግ ሌላውንም አስተምሩ " ➥ የሰውነት ሸንተረር በቆዳዎ ላይ እንደ ትይዩ መስመሮች ሆነው ይታያሉ። እነዚህ መስመሮች ከተለመደው ቆዳዎ የተለየ ቀለም እና ሸካራነት አላቸው, እና ከሐምራዊ እስከ ደማቅ ሮዝ እስከ ቀላል ግራጫ ቀለም አላቸው። አንዳንድ ጊዜ ማሳከክ ወይም ህመም ሊሰማችሁም ይችላል። እነዚህ መስመሮች ብዙውን ጊዜ በእርግዝና ወቅት ወይም በኋላ ወይም በሰውነት በክብደትዎ ላይ ድንገተኛ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ይታያሉ። እንዲሁም በፍጥነት በማደግ ላይ ባሉ በጉርምስና ዕድሜ ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ የሚከሰቱ ናቸው። የሰውነት ሸንተረር ብዙ ጊዜ በጊዜ ሂደት ይጠፋሉ። በማንኛውም ቦታ ሸንተረር ሊኖር ይችላል፣ ነገር ግን በጨጓራዎ፣ በጡቶችዎ፣ በክንዶችዎ እና በጭንዎ ላይ በጣም የተለመዱ ናቸው። ✍️ የሰውነት ሸንተረር የሚያመጣው ምንድን ነው? ➥ ሸንተረር የቆዳ መወጠር እና የኮርቲሶን ስርዓትዎ መጨመር ውጤቶች ናቸው። ኮርቲሶን በአድሬናል እጢዎችዎ በተፈጥሮ የተፈጠረ ሆርሞን ነው። ይሁን እንጂ ይህ ሆርሞን ከመጠን በላይ መውሰድ ቆዳዎ የመለጠጥ ችሎታውን እንዲያጣ ያደርገዋል። በተወሰኑ ሁኔታዎች ውስጥ የሸንተረር ምልክቶች የተለመዱ ናቸው። ብዙ ሴቶች በእርግዝና ወቅት የሸንተረር ምልክቶች ያጋጥማቸዋል ምክንያቱም ቆዳ በተለያዩ መንገዶች በመለጠጥ በማደግ ላይ ላለው ህጻን ቦታ ይሰጣል። ይህ የማያቋርጥ መጎተት እና መወጠር የሸንተረር ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል። ➥ አንዳንድ ጊዜ ክብደትዎን በፍጥነት ሲጨምሩ ወይም ሲቀንሱ የሸንተረር ምልክቶች ይታያሉ። Corticosteroid ክሬም፣ ሎሽን እና እንክብሎች የቆዳን የመለጠጥ አቅም በመቀነስ የሸንተረር ምልክቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ➥ በሰውነታችሁ ላይ ሸንተረር የሚያስከትሉ አንዳንድ ምክንያቶች አሉ እነዚህም፦ 📌📌 ሴት መሆን 📌📌 ነጭ ሰዎች(የገረጣ ቆዳ ያላቸው) 📌📌 በዘር ሸንተረር ካለ 📌📌 እርጉዝ መሆን 📌📌 ትልቅ ልጆችን ወይም መንታ ልጆችን መውለድ 📌📌 ከመጠን በላይ መወፈር 📌📌 ከመጠን በላይ ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር ➥ የሸንተረር ምልክቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠፉ ይሄዳሉ። መጠበቅ ካልፈለጉ, መልካቸውን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ሕክምናዎች አሉ። ይሁን እንጂ ምንም ዓይነት ሕክምና የሸንተረር ምልክቶችን ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ሊያደርግ አይችልም። የሸንተረር ምልክቶችን ገጽታ ለማሻሻል ብዙ መንገዶች አሉ እነዚህም 🔷 ትሬቲኖይን ክሬም (Retin-A, Renova) - ቆዳዎ የመለጠጥ ችሎታ እንዲኖረው የሚረዳውን ኮላጅን የተባለውን ፋይበር ፕሮቲን ወደነበረበት በመመለስ ይሰራል። ይህ ክሬም የቆዳ መቆጣት ሊያስከትል ይችላል። እርጉዝ ከሆኑ, የ tretinoin ክሬም መጠቀም የለብዎትም። ➥ በሐኪም የታዘዙ መድሃኒቶች የሸንተረር ምልክቶችን ለመፈወስ ዋስትና አይሰጡም, እና ውድ ሊሆኑም ይችላሉ። የሸንተረር ምልክቶችን ለማስወገድ ብዙ ምርቶች እና ሂደቶች አሉ, ነገር ግን እስካሁን ድረስ ውጤታማነታቸው የተረጋገጠ አደለም። ቆዳዎን ማራስ የሸንተረር ምልክቶችን ማሳከክን ለማስታገስ ይረዳል። ምንም እንኳን በመደበኛነት ቅባቶችን ቢጠቀሙም የሸንተረር ምልክቶችን ሙሉ በሙሉ ለመከላከል ምንም መንገድ የለም። ነገር ግን በአግባቡ በመመገብ እና አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ክብደትዎን ጤናማ በሆነ ክልል ውስጥ በማቆየት በድንገተኛ የሰውነት ክብደት መጨመር ወይም መቀነስ ምክንያት የሚመጡ የሸንተረር ምልክቶችን ለመከላከል ይረዳል። 1, ስኳር እና የኮኮናት ዘይት ➥ ግማሽ ስኒ ስኳር እንደ የአልሞንድ ዘይት ወይም የኮኮናት ዘይት ጋር ያዋህዱ። ዘይቱን በስኳር, በትንሹ በትንሹ ይቀላቅሉት። እስከ ግማሽ ኩባያ ዘይት መጨመር ያስፈልግዎ ይሆናል። ውህዱን በሸንተረር ምልክቶች ባሉበት የሰውነትዎ ክፍል ላይ በቀስታ ይቅቡት። በየሳምንቱ 2 ወይም 3 ጊዜ ይድገሙት። ከቀባችሁት በኋላ በሚገባ ማሳጅ ወይም በደንብ እሹት። ከደቂቃዎች ቡሀላ በሞቀ ውሀ ይታጠቡት። 2, እሬት ➥ ገላዎን ከታጠቡ በኋላ በየቀኑ ንፁህ እሬትን በሸንተረር ምልክቶችዎ ላይ ይቀቡት። 3, የኮኮናት ዘይት ➥ የኮኮናት ዘይት ለቆዳ አንዳንድ የታወቁ ጥቅሞች አሉት። የቆዳዎ መከላከያን ለመጠበቅ ሊረዳ ይችላል። የኮኮናት ዘይት ደረቅ ቆዳን እና አንዳንድ የቆዳ በሽታዎችን ያሻሽላል። የኮኮናት ዘይት በቆዳዎ ላይ በቀስታ ማሸት የሸንተረር ምልክቶችን ሊከላከለው ይችላል። 4, ክብደትዎን ይቆጣጠሩ ➥ ነፍሰ ጡርም ሆንሽ የሸንተረር ምልክቶችን ለመከላከል በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ ነው። በፈጣን ክብደት መጨመር ምክንያት ቆዳዎ በፍጥነት ሲገነጠል የሸንተረር ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። እንዲሁም በጣም ክብደት ከቀነሱ በኋላ የሸንተረር ምልክቶችን ሊያስተውሉ ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች በእድገት ጅምር ወቅት ለምሳሌ በጉርምስና ወቅት የሸንተረር ምልክቶችን ያስተውላሉ። ሌሎች ሰዎች፣ እንደ የሰውነት ግንባታ/Body building በመስራት ወይም ስቴሮይድ በመጠቀም ትልቅ ትርፍ ካገኙ በኋላ ያስተውሏቸዋል። ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲረዳዎ ጤናማ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ። 5, እርጥበት ይኑርዎት ➥ በቂ ውሃ መጠጣት ቆዳዎ እርጥብ እና ለስላሳ እንዲሆን ይረዳል። ለስላሳ ቆዳ እንደ ደረቅ ቆዳ የመለጠጥ ምልክቶችን የመፍጠር አዝማሚያ የለውም። እንደ ቡና ያሉ ካፌይን ያላቸው መጠጦችን መጠጣት የሸንተረር ምልክቶችን ይጨምራል። ቡና ከጠጡ፣ የፈሳሽ መጠንዎን ከብዙ ውሃ፣ ከዕፅዋት ሻይ እና ከሌሎች ካፌይን-ነጻ ፈሳሾች ጋር ማመጣጠንዎን ያረጋግጡ። 6, በንጥረ-ምግብ የበለጸገ ምግብን ተመገቡ ➥ የተመጣጠነ ምግብ ከሌለዎት የሸንተረር ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። የቆዳ ጤንነትን የሚጨምሩ ምግቦችን መመገብ ሊረዳ ይችላል። አመጋገብዎ ቫይታሚን ሲ ፣ ቫይታሚን ዲ ፣ ቫይታሚን ኢ ፣ ዚንክ እና ፕሮቲንን በመደበኛነት ይመገቡ። 7, በአመጋገብዎ ውስጥ ቫይታሚን ሲን ያካትቱ ➥ ኮላጅን ቆዳዎ እንዲጠነክር እና እንዲለጠጥ በማድረግ ሚና ይጫወታል። የፊት መጨማደድን ገጽታ ለመቀነስ ይረዳል፣ነገር ግን የሸንተረር ምልክቶችን ለመከላከል ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ቫይታሚን ሲ ለኮላጅን እድገት ጠቃሚ ንጥረ ነገር ነው። ቫይታሚን ሲ በብዙ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ውስጥ ሊገኝ ይችላል። እንደ ብርቱካን እና ሎሚ ያሉ የሎሚ ፍራፍሬዎች በተለይ ጥሩ የቫይታሚን ሲ ምንጮች ናቸው። 8, የተወሰነ ቫይታሚን ዲ ውሰዱ ➥ ጤናማ የቫይታሚን ዲ መጠንን መጠበቅ የሸንተረር እድሎትን ሊቀንስ ይችላል። ቫይታሚን ዲ ለማግኘት ቀላሉ መንገድ ለፀሐይ መጋለጥ ነው። ብዙውን ጊዜ ቫይታሚን በዳቦ ውስጥ ይጨመራል።ጥራጥሬዎች እና እንደ ወተት ወይም እርጎ ያሉ የወተት ተዋጽኦዎችንም ይውሰዱ። 9, በዚንክ የበለፀጉ ምግቦችን ይመገቡ ➥ ዚንክ ለቆዳ ጤንነት ጠቃሚ ንጥረ ነገር ነው። እብጠትን ለመቀነስ ይረዳል እና ቁስሉን በማዳን ሂደት ውስጥ ሚና ይጫወታል። በአመጋገብዎ ውስጥ በዚንክ የበለጸጉ ምግቦችን ለምሳሌ እንደ ለውዝ እና አሳ የመሳሰሉትን ጨምሮ የቆዳዎን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል። 10, ሃያዩሮኒክ አሲድ

የእንቅልፍ አተኛኘት አቅጣጫ ጥሩ እና መጥፎ ጎናቸው! 1. በጀርባቸው የሚተኙ! 🔻 ጥቅሙ በጀርባ መተኛት ትራስ አከርካሪን የመደገፍ ሥራውን በትክክል እንዲወጣ ይረዳዋል። በትክክለኛው አለም ሁሉም ሰው ትራስ ሳይጠቀም በጀርባው መተኛት ይፈልጋሉ፤ ይህም አቅጣጫ አንገታችን ነፃ አቅጣጫ ላይ እንዲሆን ይረዳዋል። ከመጠን በላይ/ብዙ ትራስ መጠቀም የአተነፋፈስ ሥርዓትን አስቸጋሪ ያደርገዋል። በጀርባ መተኛት ውበትን ከመጠበቅ አንፃር ይመከራል፤ ሌሊቱን ሙሉ ፊታችን ለንጽህ አየር እንዲጋለጥ በማድረግ ይረዳል። የተጠቀምነው የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲክስ በትራሱ እንዳይጠረግ ከማድረጉ በተጨማሪ የፊት መሸብሸብን ወይም መጨማደድን ይቀንሳል። 🔻 ጉዳቱ ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ እጦት በጀርባ ተንጋሎ ከመተኛት አቅጣጫ ጋር ይያያዛሉ። በነገራችን ላይ በጀርባ መተኛት ከእንቅልፍ እጦት ጋር በቅርበት የተገናኘ ነው ለዚህም ነው ዶክተሮች በጎን አቅጣጫ በኩል መተኛትን እንደመፍትሄ የሚመክሩት። በጀርባችን በምንተኛበት ወቅት የመሬት ስበት ሃይል የምላሳችን ሥር ወደ አየር ቧንቧ አቅጣጫ እንዲታጠፍ ያስገድደዋል ይህም ሥርዓተ ትንፈሳን በማስተጓጎል ጎረቤትን እንቅልፍ የሚነሳ አስቀያሚ ማንኮራፋት እንዲፈጠር ያደርጋል። ጥሩ እንቅልፍ የሚተኙ እና ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎችን በማነፃፀር የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፦ ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎች አብዛኛውን የመኝታ ጊዜ የሚያሳልፉት በጀርባቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል። 2. በጎናቸው የሚተኙ! 🔸 ጥቅሙ በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች በአንድ ላይ! ማህፀን ውስጥ እንዳለ ጽንስ እግራቸውን እጥፍጥፍ አድርገው የሚተኙ እና እግራቸውን ዘርግተው የሚተኙ ሰዎች፤ አብዛኛው ማህበረሰብ በጎን በኩል እንደሚተኙ ሪፓርት ተደርጓል። በእርግዝና ወቅት በግራ ጎን በኩል እንዲተኙ ዶክተሮች ይመክራሉ፤ ምክንያቱም ወደ ልብ ያለውን የደም ፍሰት ስለሚጨምር ነው ይህም ለእናት እና ልጅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። በእርግዝና ወቅት በጎን በኩል እንድትተኚ ይመከራል ምክንያቱም በጀርባ በኩል መተኛት የታችኛው ጀርባ ላይ ግፊት ይፈጥራል (በአብዛኛው ፌንት እንድታደርጊ አስተዋጽዎ ያድርጋል)። እንደሚታወቀው በእርግዝና ወቅት በሆድ በኩል መተኛት አይቻልም። 🔸 ጉዳቱ በተመሳሳይ ሁኔታ በግራ ጎን በኩል መተኛት ሆድ እና ሳንባ ላይ ጫና እንዲፈጠር ያደርጋል። ሁሉም በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች እንደሚያውቁት በዚህ አቅጣጫ በሚተኙበት ወቅት የእጅ መደንዘዝ ሊያጋጥም ይችላል። ጭንቅላትን እጅ ላይ አስደግፎ መተኛት የተለመደ አቅጣጫ ነው። ነገር ግን በጡንቻ እና ነርቭ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያስከትላል። ጭንቅላትን (አጠቃላይ ሰውነትን) በአንድ እጅ ላይ ማሳረፍ የደም ፍሰትን ይከለክላል በተጨማሪም ነርቭን ወደታች ይጫናል። 3. በሆዳቸው የሚተኙ! 🔹 ጥቅሙ በሆድ በኩል መተኛት ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ ችግርን ያስቀራል። ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባለው ጎኑ በሌሊት ሠዓት ቦርጫችን ወደ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል። 🔹 ጉዳቱ በሆድ በኩል መተኛት በአብዛኛው እንደሚታወቀው በጣም አስቀያሚ የሚባል የአተኛኘት አቅጣጫ ነው። የአከርካሪ የተፈጥሮ መንጋደድን በማዛባት ቀጥ እንዲል ያደርገዋል ይህም የታችኛው ጀርባ ህመምን ያስከትላል። ሌሊቱን ሙሉ ጭንቅላትን ወደ አንድ አቅጣጫ አድርጎ መተኛት የአንገት ህመምን ያስከትላል። ይህ የአተኛኘት አቅጣጫ ምርጫዎ ከሆነ ትራስ በመጠቀም ሰውነትዎ በአንድ አቅጣጫ መተኛትም ያለማምዱት።

የስንፈተ ወሲብ ችግር በወንዶች ላይ ብቻ የሚከሰት ችግር ነው ብለን የምናስብ ስንቶቻችን ነን? (በዶክተር ሶፊ) የሴቶች የወሲብ ችግር የተከበራችሁ ወዳጆቻችን፤ በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ ብዙዎቻችሁ ስለሴቶች የወሲብ ችግር መረጃ እንድንሰጣችሁ አስተያየቶቻችሁን ኢንቦክስ ባደረጋችሁልን መሰረት በሴቶች የወሲብ ችግር ላይ የተወሰኑ መረጃዎች እነሆ:­ ቀጣይነት ያለዉ ተደጋጋሚ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት ያለመኖር ችግር እርስዎን ወይም ግንኙነትዎን ካወከዎ በህክምናዉ የሴቶች የወሲብ ችግር አለ ልንል እንችላለን፡፡ ብዙ ሴቶች በህይወት ዘመናቸዉ በሆነ ጊዜ የወሲብ ችግር ሊገጥማቸዉ የሚችል ሲሆን ይህ ችግር በየትኛዉም የዕድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል፡፡ የሴቶች የወሲብ ችግሮች የሚከተሉትን የሚያጠቃልል ሲሆን አንዲት ሴት አንድ ወይም ከአንድ በላይ ችግሮች ሊኖሩዋት ይችላል፡፡ • ዝቅተኛ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት( Low sexual desire) ፡­ የፍላጎት መቀነስ ወይም ጭራሹኑ ያለመኖር ችግር • የግብረስጋ ፍላጎት የመነቃቃት ችግር( Sexual arousal disorder)፡­ የግብረስጋ ፍላጎት ችግር ላይኖር ይችላል፡፡ ችግሩ ያለዉ ለግብረስጋ ግንኙነት የመነቃቃት ላይ ሲሆን ይህም ለመነቃቃት መቸገር ወይም ጭራሹኑ መነቃቃት ያለመኖር ችግር ሊሆን ይችላል፡፡ • የመርካት ችግር( Orgasmic disorder)፡­ በቂ የሆነ የስሜት መነቃቃት ቢኖርም ለረጅም ጊዜ ወይም በተደጋጋሚ ያለ የመርካት ችግር ሲኖር • በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም መኖር( Sexual pain disorder) የሴቶች የወሲብ ችግር ምልክቶች የሴቶች የወሲብ ችግር በየትኛዉም ዕድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን ይህ ችግር ብዙዉን ጊዜ የሚመጣዉ የሆርሞኖች መዛባት በሚኖርበት ወቅት ነዉ፡፡ ለምሳሌ ልጅ ከወለዱ በኃላ ወይም የወር አበባ ዑደት በሚቛረጥበት ወቅት(በሚያርጡበት ወቅት)፡፡ በተጨማሪ የወሲብ ችግር የተለያዩ እንደ የስኳር ህመም፣ የልብ ችግር፣ የደም ቧንቧ ችግርና ካንሰር የመሳሰሉ የጤና ችግሮች በሚኖርበት ወቅትም ሊከሰት ይችላል፡፡ ከሚተሉት አንዱ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ምልክቶች ካለዎት የወሲብ ችግር አለዎት ተብሎ ሊወሰድ ይችላል • የግብረስጋ ግነኙነት የማድረግ ፍላጎትዎ ከቀነሰ ወይም ጭራሹኑ ከሌለ • የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት እያለዎ ለግንኙነት የስሜት መነቃቃት ችግር ካለዎ • በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ምንም እርካታ ከሌለዎ • በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ካለዎ የህክምና ባለሙያ ማየት የሚገባዎ መቼ ነዉ? የወሲብ ችግርዎ የአዕምሮ ሰላምዎን ከነሳዎ፣ የትዳር/ፍቅር ግንኙነትዎን ካወከዉ የህክምና ባለሙያ እንዲያማክሩ እንመክርዎታለን፡፡ ለሴቶች ወሲብ ችግር መንስዔዎች ለወሲብ ችግር ሊያጋልጡ የሚችሉ የተለያዩ መንስዔዎች ያሉ ሲሆን እርስ በርሳቸዉ ግንኙነት ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡ • አካላዊ ምክንያቶች፡­ የመገጣጠሚያ ችግሮች( arthritis)፣ የዳሌ ዉስጥ ቀዶ ጥገና፣ ድካም፣ የራስምታት፣ የሽንትና የአንጀት ችግሮች፣ የነርቭ ችግሮችና ሌሎች የጤና ችግሮች፡፡ ለድብርት፣ ለደም ግፊት፣ ለአለርጂ ህክምና የሚሰጡ እንደ አንታይሂስታሚንና ለካንሰር ህክምና የሚወሰዱ መድሃኒቶች የወሲብን ችግር ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ • ሆርሞኖች፡­ የሆርሞኖች መለዋወጥ የተለያዩ የወሲብ ችግሮችን ሊያመጡ ይችላሉ (በእርግዝና፣ ጡት ማጥባትና የወር አበባ ዑደት በሚቛረጥበት ወቅት) • ስነልቦናዊና ማህበራዊ ችግሮች፡­ ህክምና ያላገኘ ጭንቀትና ድብርት ካለ፤ ለረጅም ጊዜ የቆየ በወሲብም ይሁን በሌላ ምክንያቶች ከትዳር/ፍቅር አጋረዎ ጋር ያለመስማማት ካለዎ፤ በእርግዝና ወቅትና አዲስ እናት ሊኮን ሲል ያሉ ጭንቀቶች፤ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና የሰዉነት ቅርፅ ጉዳዮች ለሴቶች የወሲብ ችግር ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች • ጭንቀት ወይም ድብርት • የልብና የደም ቧንቧ ችግሮች ካሉ • የነርቭ ችግሮች ካሉ፡­ ለምሳሌ በህብለ ሰረሰር ላይ ችግር/ጉዳት ሲደርስ • የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ካሉ • መድሃኒቶች፡­ ለድብርትና ለደም ግፊት የሚሰጡ መድሃኒቶች • ስነልቦናዊና ስሜታዊ ጭንቀቶች ካሉ፡­ በተለይ ከትዳር/ፍቅር አጋርዎ ጋር ያለዎት ግንኙነት • ከዚህ በፊት ወሲባዊ ጥቃት ደርሶቦት ከሆነ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች • የህክምና ባለሙያዎ ስለእርስዎ ወሲባዊና የህክምና ታሪክዎን ይጠይቅዎታል፡­ ስለግል ሚስጥርዎ ለህክምና ባለሙያዎ ማዉራት ሊከብድ ይችላል፡፡ ነገርግን ይህን ማድረግዎ ሊደረግለዎ ስለሚገባዉ ህክምና አጋዥና ዋነኛዉ ክፍል ስለሆነ ምንም ሳያፍሩ መነጋገር ያስፈልግዎታል፡፡ • የማህፀን ምርመራ፡­ በዚህ የምርመራ ወቅት በብልትዎ አካባቢ ያለና ለችግሩ መንስኤ የሆነ ነገር እንዳለና እንደሌለ ለማረጋገጥ ምርመራ ሊደረግልዎ ይችላል፡፡ • የሆርሞን ምርመራ ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች ለወሲብ ችግር ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች የተለያዩ የዉስጥ ደዌ፣ ስነልቦናዊና ማኅበራዊ ችግሮችን ሊቀርፉ የሚችሉ የህክምና መንገዶችን በጋራ መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ከመድሃኒት ዉጪ ሊደረጉ የሚችሉ የወስብ ችግር ህክምናዎች • መናገርና ማድመጥ፡­ ከትዳር/ፍቅር አጋርዎ ጋር ግልፅና በእምነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ማድረግ በወሲብ እርካታዎ ላይ ትልቅ ለዉጥ ያመጣል፡፡ ከዚህ በፊት ስለሚወዱትና ስለማይወዱት ነገር የመወያየት ልምድ ባይኖርም ግንኙነትን በማያዉክ መልኩ ይህን ማድረግ መጀመርና ግብረመልስ መሰጣጣት ለቅርብርቦሽ ትልቅ ሚና አለዉ፡፡ • ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መለማመድ፡­ አልኮል በብዛት ያለመጠጣት(በብዛት መጠጣት የወሲብ ህይወትዎን ስለሚጎዳ)፣አለማጨስ(ማጨስ ወደብልትዎ የሚሄደዉን የደም ዝዉዉር ስለሚቀንስ ለግብረስጋ ግንኙነት መነቃቃትን ይቀንሳል)፣የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ(ስሜቶትን ለማነቃቃትይረዳል)፣ጭንቀትን ለመቀነስ መጣር • የምክር አገልግሎት ማግኘት • ማለስለሻዎችን መጠቀም፡­ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ካለዎት ወይም የብልት ፈሳሽ ከሌለዎ የብልት ማለስለሻዎችን መጠቀም ይችላሉ በመድሃኒት የሚደረግ የወሲብ ችግር ህክምና ለችግሩ እልባት ለመስጠት ለችግሩ መንስኤ የሆነዉን መሰረታዊ የውስጥ ደዌ ወይም የሆርሞን ችግር መታከም አለበት፡፡ መሰረታዊ የጤና ችግሮችን ለማከም የህክምና ባለሙያዎ ማማከር። • ለወሲብ ችግር ሊዳርጉ የሚችሉና እየወሰዱት ያለ መድሃኒት ካለ እንዲለወጥ ወይም እንዲስተካከል ሊያደርግ ይችላል • የታይሮይድ ወይም ሌሎች የሆርሞን ችግሮች ካሉ እንዲታከሙ ይደረጋል • ድብርት ወይም ጭንቀት ካለዎ ተገቢዉን ህክምና እንዲገኙ ይደረጋሉ • የዳሌ ዉስጥ ህመም ወይም ሌሎች ህመሞች ካለዎ ህክምና እንዲያገኙ ይደረጋሉ ከሆርሞን መዛባት ጋር የተገኛኘ የወሲብ ችግር ካለዎ • የኢስትሮጂን ሆረሞን ህክምና • የአንድሮጂን ሆርሞን ህክምና ሊደረጉ ይችላሉ የኑሮ ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና • ብዙ አልኮሆል ያለመዉሰድ • ሲጋራ ያለማጨስ • አካለዊ ንቃት እንዲኖሮት ማድረግ፡­ተከታታይነት ያለዉ የሰዉነት እንቅስቃሴ ማድረግ ስሜትዎን ከማነቃቃቱም በላይ የሰዉነት ቅርፅዎ እንዲስተካከል ያደርጋል • ለመዝናናትና ለመፍታታት ጊዜ መያዝ፡­ይህን ሲያደርጉ ጭንቀትን ይቀንሳሉ፣ፈታ ስለሚሉ የቀን ተቀን የኑሮ ጭንቀትን ይቀንሳሉ፡፡ ዘና ማለት በወሲብ ልምድዎ ላይ ትከረት ለመስጠት ስለሚያግዝዎ ጥሩ የሆነ የወሲብ መነቃቃትንና እርካታን አንዲገኙ ይረዳዎታል፡፡ መልካም ጤንነት!!!

⬆️ ይህን ልብ ሰባሪ ታሪክ ተባብረን እንቀይረው! (በዶክተር መሐመድ በሽር፣ በጅማ ዩኒቨርስቲ የህፃናት ሐኪም የተፃፈ) አንድ አባት ልጅ ታሞበት አገኘውት፣ እባካችሁ እርዱኝ እያለ ይማፀናል። አይዞህ ብለን ካርድ አውጥተን ልጅን ምርመራ ጀመርን። በምርመራውም ልጅ በደረት ውስጥ በቋጠረ ፈሳሽ መተንፈስ አቅጦት እያጣጣረ ነው። በተጨማሪም የሚጥል በሽታ እንዳለበት መድሃኒት እየወሰደ እንደሆን እንዲሁም የምግብ እጥረት እና የኦቲዝም ህመም ተጠቂ እንደሆነ ተረዳን። የልጁን ህይወት ለማትረፍ የኢመርጀንሲ እክምና ያስፊለገዉ ነበር። የቀዶ ሃኪሞች እንዲተባበሩ ካደረኩኝ በኃሏ በደረት ውስጥ ቲቦ ገብቶለት የቋጠረው ፊሳሽ ወጣለት የልጅም አተነፋፍስ ማገገም ጀመር እኔም ደስ አልኝ። ቀጥሎም የክፍሉ ሃኪሞች መጥተው 11 አይነት መድሃኒቶች አዘው ሄዱ። አባት እያለቀሰ ደውሎ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ልጁ ከሞተም ይሙት ብሎ ወደ ቤት ሊገባ እንደሆነ ሲነግረኝ ተረጋጋ ብዬ መድሃኒቶች እግዛለዉ አልኩት። ወደ ፋርማሲ ሄጄ ዋጋ ብጠይቅ ዋጋው የሚቀመስ አይደለም። የእንዱ ደም ማቅጠኛ ዋጋ 750 ብር ነው። እንግዲህ ከገባሁበት አልኩና 6,000 አዉጥቼ ገዛሁኝ። ለአባት ስሰጠው በምድር ፈተና አትፈተን አለኝ። ቀጥሎም የሶስት ልጅ አባት እንደሆነ ሶስቱም የአይምሮ ታማሚ የኦቲዝም ተጠቂ እንድሆኑ በልጆቹ ምክንያት ስራ እንደተባረር ነገረኝ። በልጆቹ ውስብስብ ችግር እናት እና እባት የአይምሮ ጭንቀት ተጠቂ እንድሆኑ ነገረኝ እንባዬ መጣ። የአይምሮ መድሃኒት ተጠቃሚ ናችው። ልጆቹ በጣም ስልሚጮሁ ማንም ቤት አክራይ እንደማይፊልግ ነገረኝ። በነዚ ልጆች ምክንያት ሰርግ ለቅሶ ሳይሆን የገዛ ወንድሞች ጋር እንደማይሄዱ ነገረኝ። እነሱንም ማቆያ ተቋም እንደሌለ ነገረኝ። አዲስ አበባ የኦቲዝም ማህከል ሄዶ እንደነበርም ይሁንና እንደዚህ እራሳቻውን የማይችሉ ልጆች እንደማይቀብሉ ነገረኝ። እጅግ ከባድ ነው። ይህን የተገነዘቡ የህፃናት ህክምና ሬዚደንቶች ልብስም እቅማቸው የቻለውን 1,600 ብር ስብስብው አስረከቡት። ምስጋና ይገባቸዋል። አላህ ሁሉንም ይፊትናል እኛንም ነገ ሊፊትነን ይችላል። አይተናል ሰምተናል እንድረስላቸው። አላህ በሰጠን ፀጋ ሁሌም ማመስገን አለበን። [ከልጆቹ አባት የተላከ አጭር መልዕክት] ስሜ ደርቤ በየነ በዳኔ የትውልድ ዘመን 1955 ዓ/ም የትውልድ ቦታ በጅማ ዞን አጋሮ ከተማ ነው። የትምህርት ዝግጅት የመጀመሪያ ዲግሪ በግብርና ምርቶች ገበያ ትስስር ነው። ባለትዳርና የአራት ወንዶች ልጆችና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነኝ። ከተወለዱት አምስት ልጆቼ መካከል ሶስቱ በአእምሮ ህመም እየተሰቃዩብኝ ከጅማ ሆስፒታል በሪፈር ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመመላለስ ያለኝን ንብረት ሳይቀር አሟጥጬ በመጨረስ በቅርብ የልጆቼን ሕክምናና ት/ት በአዲስ አበባ ከነቤተሰቦቼ በመግባት ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጥቁር እንበሳ ሆ/ል ቦርድ በቀን 17/10/2013 ዓ/ም በቁጥር Ref:PD/MF/408/20 ወስኗል። እኔም ይህንን ውሳኔ ለመተግበር አቅም የሌለኝ መሆኔን ተረድታችሁልኝ የልጆቼን ጤናና ት/ት ማስተካከል ይቻላል ብለው ቦርዱ ስላመነበት የችግሬን ስፋትና ጥልቀት የተረዳችሁልኝ ወገኖቼ በኢት/ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000018421813 በስልክ ቁጥር 0941880187/0917062442 በምክር ፥ በፀሎት ፥ በገንዘብ እርዳታችሁ እንዳይለየኝ በፈጣሪ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። [በቤተሰብ ፍቃድ የተወሰደ] * እኔም ከደቂቃዎች በፊት አቶ ደርቤ በየነን በስልክ አዋርቼያቸው አሳዛኝ ታሪካቸውን ካሉበት የጅማ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሆነው አጋርተውኛል። የአቅማችንን ድጋፍ በመስጠት እንደግፋቸው፣ እኔም የአቅሜን በማድረግ ተካፍያለሁ። Story via Hakim Facebook page @EliasMeseret

ቋቁቻ (Pityriasis _Versicolor) _____ >> ቋቁቻ ማላሰዚአ (Malassezia) የሚባል ፈንገስ የሚመጣ በሽታ ነው። >> ይህ አይነት ፈንገስ በተፈጥሮ በሰው እና በእንስሳት በላይኛው የቆዳ ክፍል የሚገኝ ሲሆን በተለያየ ምክንያት በተወሰኑ ሰዎች ቋቁቻ የሚባል የቆዳ ህመም ያመጣል። የቋቁቻ መስፋፋት >> አብዛኛው ግዜ ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው አከባቢዎች የተለመደ ሲሆን አንዳንድ ግዜ እስከ 50% ከፍተኛ ሙቀት ባለው አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች በዚህ በሽታ ሊጠቁ ይችላሉ። >> በሰለጠኑ አገሮች ዝርጋታው በመካከለኛ ከ 2-8% ሊደርስ ይችላል። >> በስፋት ከ 15-24 አመት የእድሜ ክልል ይከሰታል። ምክያቱም ደግሞ በከፍተኛ የስራ ጫና ቅባት የሚያመነጩ እጢዎች (Sebaceous glands) ምከንያት ነው። ቋቁቻ የመከሰት ምክንያት >> አብዛኛው ግዜ በጤናማ ሰዎች ይከሰታል። ነገርግን የተለያዩ ሁኔታዎች ቋቁቻ እንዲከሰት በር ይከፍታሉ። ከነዚህ አንዳንዶቹ ፦ > ቤተሰባዊነት ወይም በዘር (Genetic predisposition) >በሞቃታማ አከባቢ መኖር > የበሽታ መቋቋም ብቃት ማነስ (Immunodeficiency) > አቅም ማነስ (በኤችአይቪ ኤድስ ፣ስኳር ፣ኮርቲኮስትሮይድ ምክንያት ወዘተ...(immunosuppression ) > የምግብ እጥረት > እርግዝና > ቅባት የበዛበት ምግብ ማዘውተር > ኩኩሺንግ የሚባል ህመም ወዘተ... የቋቁቻ ምልክቶች >የቆዳ ቀለም ነጭ መሆን ወይም ጠቆር ጠቆር ማለት * አብዛኛው ግዜ በደረት እና ጀርባ አከባቢ መፈጠር። አንድአንድ ግዜ ደግሞ በፊት ፣እጅና እግር ሊከሰት ይችላል። > በጥቂት ሰዎች ቆዳ ማሳከክ እና መቆጣት ሊኖር ይችላል። የቋቁቻ ህክምና(Treatment) >> ለቋቁቻ የሚሰጡ መድሀኒቶች በህመሙ አይነት ይወሰናል። > የሚቀቡ ፣በአፍ የሚዋጥ ክኒኖች እና የተለያየ አይነት መድሀኒት አለው። የሚወሰድበት ግዜ ከ 2 ሳምንት እስከ 1 ወር እና ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል። ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ከኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ያገኛሉ !!

በእርግዝና ጊዜ ከማህፀን ደም መፍሰስ ችግር እንዴት ይከሰታል ማንኛውም ከ28 ሳምንት እርግዝና በኃላ የሚከሰት ከማህፀን ደምመፍሰስ ሲኖር በፍጥነት ወደጤና ተቋም መምጣት ተገቢ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ከመሀፀን የሚመጣ መድማት በፍጥነት ህክምና ካልተደረገ ለህይወት አደገኛ የሆነ የደም መፍሰስና ለፅንሱ መውረድ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡ከ 2-5% እርግዝና ላይ ይህ ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ * ብዙ ምክንያቶች ይህን የደም መፍሰስ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ከ50% በላይ በውል ምክንያቱ ባይታወቅም ዋና ዋናዎቹ 1. የእንግዴ ልጅ ከመሀፀን ግድግዳ ጋር በትክክል ካልተያያዘ ወይም የተያያዘው ክፍል በጥቂቱ ሲለቅ 2. የእንግዴ ልጅ ከመሀፀን ግድግዳ ከላይ ክፍል መያያዝ ሲኖርበት ከህፃኑ ጭንቅላት ቀድሞ ከታች ሲጣበቅ 3. የእንግዴው ልጅ የራሱ ሆኑ የአፈጣጠር ችግሮች ሲኖሩት 4. የማህፀን ወይም የማህፀን በር ጫፍ ኢንፌክሽንየመውደቅ ወይም 5. ማንኛውም ማህፀንን ሊነካ የሚችል ምት ወይም ግፊት 6. የደም ህዋሳት በሽታ 7. የማህፀን እንዲሁም ተያያዥ ክፍሎች ካንሰር እነዚህን ምክንያቶች ብዙውን ጊዜ የደም መፍሰስ እስኪከሰት ድረስ ሌላ ምልክቶች ቀድመው አያሳዩም፡፡ ስለዚህም ለእናቶች ቀድሞ ለማወቅና ለመጠንቀቅ አዳጋች ናቸው፡፡ነገር ግን በየጊዜው የቅደመ ወሊድ ክትትል በማድረግ ችግሮች የከፋ ሳይሆን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ መከላከያ መንገዶች . በጣም ሰውነትን ጫና የሚፈጥሩ ስራዎችን አለመስራት . በተደጋጋሚ የቅድመወሊድ ክትትል ማድረግ . እርግዝና ከመምጣቱ በፊት ሙሉ የጤና ምርመራ ማድረግ . ማህፀን እረፍት እንዲያደርግ እርግዝናን ቢያንስ 2አመት ማራራቅ . የታዘዙ መድሀኒት ካለ በተገቢው መውሰድበደንብ እረፍት ማግኘት . የመውደቅ ወይም የመመታት አደጋ ካጋጠመ መድማት እንኳን ባይኖር የጤና ተቋም ሄዶ መታየት * የሚያመጣው ችግር . ከጊዜው በፊት ምጥ ማምጣት . የፅንሱን አስተዳደግ መቀነስ . የሽንት ውሀ ማነ . ስሽንት ውሀ ከጊዜው በፊት መፍሰስ(ምጥ ከመምጣቱ በፊት) . በኦፕሬሽን እንድትወልድ ግዴታ መሆን . ከወሰደች በኃላ ደም መፍሰስ . የማህፀን መሰንጠቅ . የፅንስ መውረድ የእናት ሞት * ህክምና ከላይ እንደተጠቀሰው ማንኛውም አይነት ደም መፍሰስ ሲኖር በአፋጣኝ የጤና ተቋም መምጣት የሁሉም እናት ተቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት፡፡ በጤና ተቋም በመጀመሪያ የደሙን ቀለም አብሮት የሚመጣ ህመም መኖር አለመኖሩን ብዛቱንና ከዚህጋር ተያያዞ የደም ግፊት የልብ ምት ሰላም መሆኑን ማጣራት አለበት፡፡ ከዚያ በአልትራሳውንድ እንዲሁም ተያያዥ ምርመራዎች ምክንያቱ መታወቅ ይኖርበታል የፅንሱ ሁኔታም በተለያዩ መንገዶች ይጣራል፡፡ ከነዚህ ምርመራዎች በኃላ እደምክንያቶቹ ህክምና ከመደረጉ በፊት በደም ስር ፈሳሽ ወይም ደም ካስፈለገ ሊሰጣት ይችላል፡፡ ከዚያም እንደአስፈላጊነቱ በመድሀኒት ህክምና ብቻ የሚስተካከል ከሆነ መድሀኒት በመስጠት በእረፍት የሚቀነስ ወይም የሚጠፋ ከሆነ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ በፍጥነት ልጅ መውለድ ካለበት ድንገተኛ ቀዶ ጥገና በማድረግ እርዳታ ልታገኝ ትችላለች፡፡ ባጠቃላይ ማንኛውም እርጉዝ የሆነች ሴት ከማህፀን ደም የመፍሰስ ችግር ካጋጠማት አፋጣኝ እርዳታ ማግኘት ተቀዳሚ ተግባሯ አድርጋ ተያያዥ የሆኑትን ችግሮች መከላከል ትችላለች፡ መልካም ጤንነት

ጠቃሚ ምክር ሴጋ(Masturbation) እና መዘዙ (ብዙም ስለማናወራው ነገር ግን ስለምናደርገው ጎጂ ልማድ ለምክክር እንዲረዳ በግለጽ ቋንቋ የተጻፈ ነውና ምቾት የሚነሳህ መስሎ ከተሰማህ ያለማንበብ ምርጫው ያንተ ነው) ጀግናው ወንድሜ! ዛሬ ስለ ግለ-ወሲብ ከአሁን በኋላ ሴጋ እያልኩ የምጠራውን ጎጂ ልማድ በአንተ እና በትዳርህም ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ ላወራህ እፈልጋለሁ። ይኽ ጎጂ ልማድ ከሚያመጣው መዘዞች ውስጥ መንፈሳዊ ጉዳቱን ሳይኾን አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ጠባይዓዊ.. ) ኪሳራውን ላወያይህ ፈልጌያለሁ። ይኼም ጽሑፍ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ጽሑፎቼ ከራሴ ሕይወት የተማርኩትን በንባብም ያዳበርኩትን እውቀት ያማከለ ነው። እነኾ.... ሴጋ (በወንዱም ኾነ በሴቷ) መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ የእድሜ ልክ ክፉና ጎጂ ልማድ ነው። ክፉ አልኩት ይኽ ዐመል አንዴ ከተጠናወተ(ሴቷንም ኾነ ወንዱን) ለመተው እጅግ ከባድ ነውና፤ ጎጂም አልኩት አንተን አለመልቀቁ ሱሰኛም ማድረጉ አንተ ላይ አካላዊ፣ አእምሮኣዊና ስነልቦናዊ ጉዳትን ያመጣልና ነው። ሴጋና ልጆች ሴጋ ከሚያስከትለው ዘለቄታዊ አንዳንዴም(በወቅቱ ካልቆመ) የእድሜ ልክ ችግር ከመኾኑ አንጻር ልጆች ወደ ጉርምስና እድሜያቸው እየተቃረቡ ሲሄዱ ስለወሲብ ጸጋነትና አግባባዊ አጠቃቀሙ መማር አለባቸው። በተለይም አኹን ባለንበት ነባራዊ ዘመን የወንዶች ወንዳወንድነት ባሽቆለቆለበትና አባቶችም ወንዳወንድ ጠባይ በማያሳዩበት በዚህ ወቅት ልጆች በተለይም ሴቶች ልጆች ቶሎ ለመጎርመስና ለተሳሳተ የወሲብ ግንዛቤና ድርጊት ይጋለጣሉ። ከዚህ በተጨማሪም ዘመን በወለዳቸው የቴክኖሎጂ ውጤት በኾኑ መሣሪያዎች የምናገኛቸው የወሲብ ትዕይንቶች(Pornography) ችግሩ ላይ ቤንዚን ያርከፈክፋሉ። ምንም እንኳ ሴጋ በአብዛኛው የወንዶች ክፉ ልማድ ቢኾንም ከወሲባዊው አብዮት ወዲህ ግን የሚለማመዱት ሴቶቹም ቁጥር ጨምሯል። አንተ ታዲያ ሚስትህንና ልጆችህን(ወንዱንም ኾነ ሴቷን) ስለወሲብና ትክክለኛ(አግባባዊ) አፈጻጸሙ፣ ስለሴጋም ጎጂነት ታስተምር ዘንድ አንተ መጀመሪያ አውቀኸው(ጉዳቱንም ጭምር) ራስህንም ጠብቀህ ልትገኝ ይገባል። በዚህም መሠረት ሚስትህም ኾነች ልጆችህ በዚህ ልማድ እንዳይገኙ ሥርዓትን ልትሠራላቸው፣ ልትመክራቸው ፈጽመውት ቢገኙ ደግሞ ልትቀጣቸው ይገባሃል። የሴጋ ጎጂ ልማድነት(ከወንዶቹ አንጻር) ጉዳት ፩ አካላዊ ጉዳት ውዱ ወንድሜ! ሴጋ በቋሚነት የምትመታ ከኾነ የሰውነትህን ፈሳሽ፣ ወዝህን፣ ጉልበትህን አሟጦ ይጨርሰዋል። ይኽም ማለት ከሴጋህ በኋላ ሰውነትህ ይልፈሰፈሳል፣ አይንህ ይፈዛል(ስብር ይላል)። "እንዴዬ ወሲብስ ከሚስቴ ጋር ስፈጽም ይደክመኝ የለ?" ብትለኝ አዎን ወሲብም ከሚስትህ ጋር ብትፈጽም ይደክምሃል። ነገር ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ሰውነትህን የማይመጥ ጉልበትህንም የማይጨርስ ይልቁንስ መታደስ ያለበት ነው። ይኽ የሚኾነው ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ሴጋህን የሚያስረሳ እርካታውም የጋራ መኾን ያለበት እንጂ ዝምብለህ እንደነገሩ ተንደፋድፈህ መነሳት ከኾነ ውጤቱ ከሴጋው ብዙም አይለይም። ጉዳት ፪ አእምሮአዊ ጉዳት በተለይም በዚህ ዘመን ለሴጋ ወሲባዊ ትዕይንቶች(Pornography) ከፍተኛ መንሴዔዎች ናቸው። በስሜት ሕዋሶቻችን የተቀበልናቸውን መልእክቶች ተንተርሶ አስፈላጊው አጸፋዊ ምላሽ በሚመለከተው የሰውነት ክፍል እንዲሰጥ የሚያዘው አእምሮ ነው። በወሲባዊ ትዕይንቶች የተነካው(መልእክት የተቀበለው) የአእመሮአችን ክፍል የልብ ምታችን እንዲጨምር፣ ደምም በፍጥነት እንዲዘዋወር (በተለይም ወደ ብልታችን) ከዚህም የተነሳ እንዲነቃቃ ያደርጋል። ይኽን ልማድ ያደረገው አእምሮህ ታዲያ ሚስትህን ስታይ፣ ጠረኗ ሲሸትህ፣ ሰውነቷን ስትዳብስ(ስትዳብስህ)፣ ለወሲብም ወደምንጣፍህ ስትወጣ አእምሮህ ሰውነትህን ለማዘዝ ይዘገያል(አያዘውም)። ምክንያቱ ደግሞ እርሱ የሚያውቀውና የለመደው ስሜት መቀስቀሻ ሌሎች ወሲብ ሲፈጽሙ ማየት ነውና። ጉዳት ፫ ስነልቦናዊ ጉዳት ሴጋ ስትመታ "ወሲቡ"(ከተባለ) አንተ በራስህ ለራስህ ብቻ የምትፈጽመው የምትወዳትን ሚስትህን ያላሳተፈ ነውና በራስወዳድነት ማዕበል እየተንገላታህ ለሚስትህ ያለህ ናፍቆትና ስስትም እየቀነሰ ይሄዳል። አለባበሷን ማድነቅ፣ የናፍቆትና የፍቅር ቃላትን መናገር፣ ፈቃዷን መፈጸምና ፍላጎቷንም በአግባቡ ማርካት ይሳንሃል። ምክንያቱ ደግሞ የእነዚህ ምንጭ የኾነውን ወሲባዊ ስሜት (መነቃቃት) በሴጋ አድርቀኸዋልና ነው። ጉዳት ፬ ከሴት ያርቅሃል ሴጋን በቋሚነት ለሚመታ ወንድ ሴቶችን መቅረብ(መጥበስ)፣ ማናገር(መጀንጀን) ይሳነዋል። የመጠየቅ፣ የመነጋገርና የመግባባት ብሎም የመፋቀርን ሽልማትና እርካታ በዋዛ በሴጋ ያገኘዋልና(ምንም እንኳ ሴጋ ለወሲብ ምትክ ባይኾንም)። ጉዳት፭ ወኔህን ይሰልበዋል ፈርጀብዙ የኾነ አባወራዊ ሚናህን የምትወጣበትን ወኔ ይገድለዋል። እያደርም ለቤትህ፣ ለሚስትህ፣ ለልጆችህ ግድ የሌለህ በራስወዳድነት ባሕር ሰምጠህ እንድትቀርም ያደርግሃል። ጉዳት ፮ ለስንፈተ ወሲብ ይዳርግሃል ውድ ወንድሜ! እኔ ይኼን ስጽፍልህ ትማርበት ዘንድ በእርሱም ፈጣሪ የሰጠህን ጸጋ በአግባቡ ተጠቅመህ በትዳርህ አንድነትህን ታጠነክርበት ዘንድ ነው። እርግጠኛ ኾኜ የምነግርህ ሴጋ ለስንፈተ ወሲብ እንደሚዳርግህ ነው። እንዴት? .... ይቆየን።

ምስር የድም ስኳርን ለመቆጣጠርና ካንሰርን ለመከላከል አንዱ መፍትሔ ሆኗል ምስር ብዙ ፋይበር፣ፕሮቲን፣ዚንክ፣ ብረት፣ፖታሲየም፣ ፎሌት እና ቫይታሚን ቢ ይዟል፡፡ 1. ምስር በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠኖዎን ይቆጣጠራል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ምስር ከፍተኛ የፕሮቲንና የፋይበር ይዘት ካላቸው legume family ከሚባሉት ባቄላ፣ አተርና ሽምብራ ቤተሰብ የሚመደብ ድብለ እፀዋት( አባዝርት- አበባ ዝርት) አንዱ ነው፡፡ በምስር ውስጥ ያለው ከፍተኛ ፋይበር የደም ስኳር መጠንን የሚቆጠጠር ነው፡፡ በምስር ውስጥ ያለው ፋይበር በደም የሚመጠጠውን ምግብ ቀስ እንዲል በማድረግ የስኳር መጠንን ወጥ በሆነ መልኩ ይቆጣጠራል፡፡ 2. በምስር ውስጥ ያለው ከፍተኛ ፋይበር ከዚህ በተጨማሪ ጤናማ የሆነ የምግብ መፈጨት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ይህ በምስር ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የማይሟሟ ፋይበር በምግብ የመፈጨት ስርዓት ውስጥ ያለውን ውሃ ይመጣል እንዲሁም ቆሻሻን ከምግብ መፈጨት ስርዓት ተሸክሞ ያስወግዳል፡፡ በዚም የተነሳ ምስር ድርቀትን ፣የአንጀት ብግነት በሽታንና ተቅማጥን ለመከላከል ይረዳል፡፡ ይሁንና ከምስር ጥሩ ጠቀሜታ ለማግኘት ምስር ከተመገቡ በኃላ በዛ ያለ ውሃ መጠጣት ይኖርቦታል፡፡ ምክንያቱም ፋይበሩ ብዙ ውሃውን ለመምጠጥ ይቻለዋልና፡፡ 3. የተላያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እንደ ምስር ያለ ከፍተኛ በፋበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ በልብ በሽታ የመጠቃት አደጋን ይቀንሳል፡፡ ምክንያቱም ምስር በማግኒዝየምና በፎሌት በእጅጉ የበለፀገ ስለሆነ ለልብ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ፎሌት ለልብ በሽታ የሚያጋልጠውን ሆሞሳይስቲን መጠን በመቀነስ የልብ በሽታን ይከላከላል፡፡ ማግኒዚየሙ ደግሞ የደም ፍሰቱን እንዲሻሻል ፣ምግብና ኦክስጂን በመላው ሰውነታችን እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ 4. ሴሊነም በብዙ ምግቦች የማይገኝ ነገር ግን በምስር ውስጥ ያለ ማዕድን ነው፡፡ ሴሊነም ብግነትን የሚከላከል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን የማያሻሻልና የዕጢ ዕድገትን ለመቀነስ የሚስችል በሽታ ተከላካይ የሆነውን ቲ-ሴል( ቲ -ሕዋስ) የሚያነቃቃ ነው፡፡ 5. ምስር በብረት የበለፀገ ስለሆነ ካርቦ አይድሬት ቀስ ብሎ እንዲቃጠል እና የሰውነቶ የብረት ክምችትን በመጨመር ሰውነቶ በሃይል እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ በተለይ በወር አበባ ጊዜ በብረት ማነስ የሚጎዱ ሴቶች የብረት ክምችታቸውን ያጠናክርላቸዋል፡፡ብረት ሂሞግሎቢን የተሰኘው የደም ሤል ኦክስጅን ወደ ሁሉም ሰውነታችን እንዲደርስ ያግዛል፡፡ ብረት በተለይ ለሚያጠቡና ለነፍሰጡር ሴቶች በጣም ስለሚያስፈልግ ምስርን በታዘውትሩ ይመከራከል፡፡ በተለይ ከቀይ ስጋ በተጨማሪ፡፡ 6. ምስር በፎሊክ አሲድ የበለፀገ ነው፡፡ ፎሊክ አሲድ ወይም ፎሌት ነፍሰ ጥሩ እናቶች በብዛት እንዲወስዱት የሚመከረ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ይህን ንጥረነገር በቀላሉ ከምስር የሚገኝ ነው፡፡ ስለሆነም ነፍሰጡ ሴቶች ምስር በብዛት ቢመገቡ ከወሊድ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል ይረዳቸዋል፡፡ 7. ምስር ክብደት ለመቀነስ ይረዳዎታል፡፡ ምስር ከፍተኛ ፕሮቲን፣ ፋይበር፣ቫታሚንና ማዕድናት እንደመያዙ መጠን በአንፃሩ ዝቅተኛ ቅባትና ካሎሪስ ስላለው ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ! እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን! ምስጋናችን ከልብ ነው።