ch
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

前往频道在 Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

显示更多

📈 Telegram 频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias 的分析概览

频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 919 名订阅者,在 医学 类别中位列第 1 159,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 693

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 919 名订阅者。

根据 30 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -533,过去 24 小时变化为 -18,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 27.17%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.18% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 412 次浏览,首日通常累积 1 431 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

凭借高频更新(最新数据采集于 01 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 医学 类别中的关键影响点。

19 919
订阅者
-1824 小时
-1207
-53330
帖子存档
✍️ #የአፍንጫ #መደፈን 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የአፍንጫ መደፈን(መታፈን) የሚከሰተው በአፍንጫ እና በአጎራባች ሕብረ ሕዋሳት እና የደም ሥሮች ከመጠን በላይ በሆነ ፈሳሽ ሲያብጡ የታፈነ ስሜት ይፈጥራሉ። የአፍንጫ መታፈን የአፍንጫ ፈሳሽን ወይም “ንፍጥ” ን ሊያካትት ወይም ላያካትት ይችላል። ⏩ #የአፍንጫ መታፈን ብዙውን ጊዜ እንደ የሳይነስ ኢንፌክሽን ያለ ሌላ የጤና ችግር ምልክት ነው፤ እንዲሁም በተለመደው ጉንፋን ምክንያትም ሊሆን ይችላል። 👉#መንስኤዎቹ 🔺 ሳይነሳይትስ 🔺 የአፍንጫ አለርጂ 🔺 ጉንፋን 🔺 አልኮል 🔺 ወደ አፍንጫ የሚሄድ አየር መድረቅ 🔺 ወደ አፍንጫ ባዕድ ነገር ሲገባ 🔺 የሆርሞን ለውጠጥ 🔺 ለሌላ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች (ለግፊት፣ ለድብርት፣ለሚጥል በሽታና ሌሎችም..) 🔺 አፍንጫ ላይ የሚወጡ ስጋዎች 🔺 አስም 🔺 እርግዝና 🔺 ጭንቀት 🔺 የታይሮይድ ችግር 🔺 ሲጋራ ማጨስ 👉 #መከላከያዎቹ 🔺 አርጂ የሚስነሱ ነገሮችን መከላከል 🔺 እንደ ሲጋራ ያሉ የሚረብሹ ነገሮችነን መራቅ 🔺 በቂ ውሃ መጠጣት የአፍንጨጫ እስፕሬዎች መጠቀም 🔺 ሌሎች የተለዩ ምክንያቶች ካሉ ማከም 👉 #እንዚህን #ምልክቶች #ካዩ #ወደ #ጤና #ተቋም #ይሂዱ! 🔺 የአፍንጫ መደፈኑ ከ 10 ቀናት በላይ ከቆየ 🔺 የአፍንጫ መደፈኑ ከ 3 ቀናት በላይ ከቆየ እና ተያይዞ ከፍተኛ ትኩሳት ካለዉ 🔺 ከአፍንጫ አረንጓዴ ወይም ቢጫ ፈሳሽ ከሳይነስ ህመም እና ትኩሳት ጋር ካለ 🔺 የበሽታ የመከላከል አቅማቸዉ ዝቅተኛ የሆነ እና አስም ያላቸዉ 👉👉 #ይህን መሰል እና ማንኛዉም ተያያዥ የጤና ጥያቄ ካሎት ወደ ጥሪ ማዕከላችን በመደወል ከጤና ባለሙያ ጋር ይማከሩ! ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ስጦታ)

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ቆዳ ሳይከፈት የዳሌ እና የታችኛው አከርካሪ ስብራት ቀዶ ሕክምና ለሦሥት ታካሚዎች ሰጥቷል። ይህም በሪፈራል ሆስፒታሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመ ነው ተብሏል
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ቆዳ ሳይከፈት የዳሌ እና የታችኛው አከርካሪ ስብራት ቀዶ ሕክምና ለሦሥት ታካሚዎች ሰጥቷል። ይህም በሪፈራል ሆስፒታሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመ ነው ተብሏል። እድሚያቸው 17፣ 43 እና 88 ለሆኑ ሦሥት ታካሚዎች አገልግሎቱ መሰጠቱን የአጥንትና የመገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመኪና አደጋ ምክንያት የዳሌ እና የታችኛው አከርካሪ ስብራት ሕክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመዋል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምናውን መጀመሩ አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ የሚደረግ ጉዞን ያስቀራል ብለዋል። #ጎንደርዩኒቨርሲቲ

✍️ #ዝቅተኛ #የወንድ #የዘር #ህዋስ(#oligospermia) 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የወንድ የዘር ፈሳሽ ህዋስ ማነስ የሚባለው የሚለቀቀው ህዋስ ቁጥሩ /መጠኑ ከመደበኛ ያነሰ ሲሆን ነው ፡፡ ትክክለኛ የስፐርም መጠን 15 ሚሊየን በ 1 ሚ.ሊ ፈሳሽ ውስጥ ነው፡፡ በህክምና አጠራሩ የዘር ፈሳሽ ህዋስ ማነስ (oligospermia) ሲባል የዘር ፈሳሽ ህዋስ ሙሉ በሙሉ አለመኖር ደግሞ (azoospermia) ይባላል። በአንድ የወንድ የዘር ፈሳሽ ከ 15 ሚሊዮን ያነሰ የወንድ የዘር ፈሳሽ ህዋስ ካለዎት የወንዱ የዘር ፈሳሽ ህዋስ መጠን ከወትሮው ዝቅተኛ ነው ተብሎ ይገመታል ። ዝቅተኛ የወንድ የዘር ፈሳሽ ዋናው ምልክት ልጅን ለመፀነስ አለመቻል ነው ፡፡ ሌላ ምንም ግልጽ ምልክቶች ላይኖሩ ይችላሉ ። ⏩ #ምልክቶቹ 🔹የዘር ፍሬ ከረጢት ላይ ህመም ወይም እብጠት መኖር 🔹 ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት መኖር 🔹የፊት ወይም የሰውነት ፀጉር መቀነስ /የሆርሞን መዛባት ⏩ #መንስኤዎቹ 🔹 ያልተለመዱ የወንዱ የዘር ቅርፅ መኖር (morphology) 🔹 እንቅስቃሴት(motility) ችግሮች 🔹 ኢንፊክሽን 🔹 የሆርሞን አለመመጣጠን 🔹 መድሃኒቶችን ለረጅም ጊዜ መጠቀም 🔹 የደም መልስ ትቦዎች አብጦ መታየት 🔹 ጭንቀት ( የስራ ውጥረት) 🔹 ለጨረር የመጋለጥ እድል መኖር 🔹 ማጨስ ፣ መጠጣት 🔹 የሰውነት ክብደት መጨመር ⏩ #ምርመራው 🔹 የዘር ፈሳሽ ምርመራ(sperm analysis) 🔹 አልትራሳውንድ 🔹 የሆርሞን ምርመራ ⏩ #ህክምናው 🔹 በኢንፊክሽን ምክንያት የመጣ ከሆነ ኢንፊክሽኑን ማከም 🔹 የሆርሞን ህክምና 🔹 ቀዶ ህክምና ⏩ #መከላከያ #መንገዶች 🔹 ጭንቀትን ማስወገድ 🔹 የአመጋገብ ዘይቤን ማስተካከል 🔹 የሰውነት ክብደትን ማመጣጠን 🔹 አለማጨስ 🔹 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ 👉👉 #ያለመውለድ ችግር አጋጥሞ ችግሩ ከወንዱ ሊሆንባቸው ከሚችሉባቸው አጋጣሚዎች ዋነኛ መንስኤው በመሆን ይጠቀሳል ስለሆነም ስለችግሩ በቂ ግንዛቤ ለማግኘት 8809 ላይ ይደውሉ ባለሙያ ይምከሩ ! ከዚህና ተያያዥ በሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ካሎት በቤቶ ሆነው ወደ 8809 ላይ በመደወል ከባለሞያዎችን በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ፡፡ ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

#ከእርግዝና #በፊት #መቋረጥ #ያለባቸው #5 #ጎጂ #ልማዶች ልጅ ወልደው መሳም የሚፈልጉ ሴቶች የሚያዘወትሯቸውን መጥፎ ተግባራት ማስወገድ እንዳለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ። በእርግዝና ወቅትም ጎጂ ነገሮችን አለማድረግ ፅንሱ እናቱን እንዲያመሰግን የሚያስችል ሲሆን ለእናትም ጤናን ይሰጣል ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ፤ ገንዘብንም ይቆጥባል ተብሏል፡፡ በመሆኑም ልጅ ወልዳ መሳም የምትፈልግ እናት ከሚከተሉት አምስት መጥፎ ልማዶች መራቅ ይገባታል፡፡ 1. ሲጋራ ማጨስ በእርግዝና ወቅት ከሚያጋጥም የተዛባ የደም ዝውውር፣ የአተነፋፈስ ችግር፣ የሳንባ ጉዳት በመጠበቅ ፅንሱ ተገቢውን ደም፣ ምግብ እና ኦክስጅን እንዲያገኝ ለማድረግ ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ ይህም መሆን ያለበት ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ወቅት እና ከወሊድ በኋላ ሲሆን፥ ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ እና ኒኮቲንን በውስጡ የያዘውን ሲጋራን በመራቅ ለእርግዝና መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑ ተመክሯል፡፡ በእርግዝና ወቅትም እናት እና ልጅ ጤናማ እንዲሆኑ የሚረዳ ሲሆን፥ በድህረ ወሊድ ጊዜም በፅንስ ጊዜ የሚያጋጥሙ በሽታዎች በልጅ ላይ እንዳይከሰቱ፣ ክብደታቸውም ጥሩ እንዲሆን ያደርጋል ሲል የአሜሪካ የእርግዝና ማህበር ጠቁሟል፡፡ 2. አልኮልን ወይም አነቃቂ ዕፆችን መጠቀም በእርግጥ በእርግዝና ወቅት አልኮል መጠጣት ላይ ያለው አተያይ የተለያየ ቢሆንም፥ ራስን ከአልኮል ማቀቡ ለጤና መልካም መሆኑን ብዙዎች ያሰምሩበታል፡፡ የአሜሪካው የእርግዝና ማህበር በበኩሉ አልኮል ከእናት የእንግዴ ልጅ አልፎ በልጅ ወይም በፅንሱ ላይ ጉዳት ያስከትላል ነው የሚለው፡፡ ይህም ማለት አበው ሲናገሩ "የሚታይ እንጂ የማይበላ ፍሬ" እንዲሉ የማይወለድን ፅንስ በአልኮል መጠጥ ማሳደግ እንደ ማለት ነው ይላል ማህበሩ፡፡ አልኮል መጠጣትን በቅድመ እርግዝና ወቅት ማቆም ካልተቻለ ጎጂ ልማዱ በእርግዝናም ወቅት ቀጥሎ፥ ሽሉ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር ከመደበኛው ጊዜ ቀድሞ መወለድን፣ የፅንስ መጨናገፍን፣ የህጻኑን ክብደት መቀነስን እና የእድገት መቀጨጭን ሁሉ እንደሚያስከትል ነው ያነሳው ማህበሩ፡፡ 3. ተገቢ ያልሆነ አመጋገብ "ሰዎች የሚመገቡትን ይመስላሉ" የሚል የፈረንጆች አባባል አለ፤ ታዲያ በሆዷ ውስጥ ሰውን ያህል ፍጡር የተሸከመች እርጉዝ እናት ከእርግዝናዋ በፊትም ሆነ በእርግዝናዋ ወቅት አመጋገቧን መለየት አለባት፡፡ በተለይም ከእርግዝና በፊት የተገኘውን ሁሉ የመመገብ ልማድ ካላት፥ በእርግዝና ወቅት ጣጣ እንዳያስከትል ጥንቃቄ እና ውሳኔ ማድረግ ያስፈልጋታል፡፡ በመሆኑም አንዲት እርጉዝ እናት በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በኋላ ስላለው ተገቢ እና የተመጣጠነ አመጋገቧ ትኩረት ማድረግ ይኖርባታል፡፡ አትክልት እና ፍራፍሬን፣ ጥራጥሬ ምግቦችን፣ ፕሮቲኖችን እና ሌሎችም ገንቢ እና ኃይል ሰጪ ምግቦችን መውሰድ ለራሷም ሆነ በሆዷ ውስጥ ላለው ልጇ ጤና ፋይዳው ብዙ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሶዲየም እና የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች፣ በማምከኛ ውስጥ ያልገቡ የስጋ እና ወተት ተዋፅኦዎችን እና በአግባቡ ያልታጠቡ ምግቦችን እንድትጠቀም አይመከርም፡፡ 4. ከመጠን በታች ወይም ከመጠን ያለፈ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለእለት ተዕለት ጤናችን መልካም ነው፡፡ ከፍተኛ የስብ መጠንን ለማስወገድ፣ የስኳር በሽታን ለመቀነስ፣ ኃይል እና ጥንካሬን ለመጨመር፣ የጀርባ ህመመን ለማስታገስ ሁሉ ይረዳል፡፡ ሆኖም በጣም አድካሚ በሌላ በኩልም በጣም ትንሽ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በተለይም ሴቶች ከመጠን በላይ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ፥ እንቁላል እንዳያመርቱ፣ የወር አበባም እንዳያዩ በማድረግ የእርግዝና ህልማቸውን ሊያቀጭጭባቸው ይችላል፡፡ በጣም ትንሽ የአካል እንቅስቃሴ ደግሞ ለውፍረት እና ለስኳር በሽታ ሊያጋልጥ እንደሚችል፥ ይህ ደግሞ ሴቶች እንዳያረግዙ የሚያግድ ሌላ ጣጣ እንደሚያመጣባቸው ጠቁመዋል፡፡ ስለሆነም ልጅ ወልደው መሳም የሚፈልጉ ሴቶች በአቅማቸው ልክ፥ በተለይም እስከ 30 ደቂቃ የሚደርስ የተመጠነ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ነው ባለሙያዎች የሚመክሩት፡፡ 5. ድካም ሲኖር እረፍት አለማድረግ የትኛዋንም እናት ብትጠይቁ ልጅ ማሳደግ ከባድ ኃላፊነት ነው፤ በመሆኑም ለሆርሞን ምጣኔ እና ለማንኛውም ጤና እናት እረፍት ያስፈልጋታል ይላል የአሜሪካው ብሔራዊ የእንቅልፍ ፋውንዴሽን፡፡ በመሆኑም በየቀኑ በትንሹ ለ20 ደቂቃ የእንቅልፍ ሸለብታ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ እርጉዝ ሴት ድካም ሲሰማት በደመነፍስ የእግር ጉዞ ከማድረግ ይልቅ ሸለብታን የግድ መጠቀም አለባት የሚል ምክር አለው ፋውንዴሽኑ፡፡

መዉለድ እየፈለጉ አለመውለድ ያለመቻል ምክኒያቶች ና ችግሮች ባጭሩ -Female infertility መዉለድ ያለመቻል ማለት ተጋቢዎች ለአንድ አመት ያህል ተከታታይነት ያለዉ የግብረስጋ ግንኙነት እያደረጉ እርግዝና መከሰት ያለመቻል ማለት ነዉ፡፡ መዉለድ ያለመቻል ከስድስት ጥንዶች አንዱን ሊያጠቃ የሚችል ነዉ፡፡ ማርገዝ ያለመቻል ከወንድየዉ፣ ከሴቷ ወይም ከሁለቱም ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ በሴቷ ምክንት የሚከሰት መዉለድ ያለመቻል አንድ ሶስተኛዉን እጅ የሚይዝ ሲሆን በወንዶችም ምክንያት የሚከሰተዉ ተመሳሳይ ቁጥርን ይሸፍናል፡፡ ቀሪዉን መዉለድ ያለመቻል ምክንቶች በሁለቱም ተጋቢዎች መዉለድ ያለመቻልና ወይም ጭራሹኑ ምክንያቱ ያልታወቀ ሊሆን ይችላል፡፡ ምልክቶች፡-ዋናዉ የችግሩ ምልክት ከላይ እንደተጠቀሰዉ ተጋቢዎች ለአንድ ዓመት ለማርገዝ ብለዉ ተከታታይነት ያለዉ የግብረ ስጋ ግንኙነት አድርገዉ እርግዝና ያልተከሰተ ከሆነ ነዉ፡፡ የረዘመ የወር አበባ ዑደት( ከ35 ቀናት በላይ የሚቆይ)፣ በጣም ያጠረ/ቶሎ ቶሎ የሚመጣ( ከ21 ቀናት በታች)፣ያልተስተካከለ ወይም ጭራሹኑ የቆመ የወር አበባ ዑደት አለ ማለት እንቁላል ከአብራኳ እየወጣች አይደለም ማለት ነዉ(not ovulating)፡፡ ይህ ደግሞ እርግዝና እንዳይኖር/እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ ምክንያቶች 1.እንቁላል ከአብራኳ ያለመዉጣት(ovulation) ችግሮች፡- ይህ ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ • የሆርሞን ያለመስተካከል/መዛባት • በዕጢ ምክንያት • የአመጋገብ ችግሮች(Eating disorders)፡- ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ምግብ ያለመመገብ(አኖሬክሲያ፤ቡሊሚያ) • አልኮሆል/አደንዛዥ ዕፅ የሚጠቀሙ • የታይሮይድ ዕጢ ችግሮች • ከፍተኛ የሆነ የሰዉነት ክብደት/ዉፍረት • ጭንቀት • ከመጠን ያለፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ • የተዛባ የወር አበባ ዑደት መኖር 2. በእንቁላል መተላለፊያ ቱቦና ማህፀን ላይ ችግር ሲኖር፡- የእንቁላል መተላለፊያ ቱቦዉ ከተዘጋ ወይም ችግር ካለበት የወንድ ዘር ፈሳሽ ከእንቁላል ጋር መገናኘት አይችልም/ጽንስ ቢፈጠር እንኳ ፅንሱ ወደ ማህፀን ገብቶ እድገቱን መቀጠል አይችልም፡፡ የማህፀንና የዘር መተላለፊያ ቱቦ ላይ ችግር እንዲከሰት ሊያደርጉ የሚችሉ፡- • የዳሌ ዉስት ህመም ( Pelvic inflammatory disease)፡- የዘር መተላለፊያ ቱቦና የማህፀን ኢንፌክሽን በሚከሰትበት ወቅት የሚመጣ • በማኅፀን፣ በሆድና በዳሌ አካባቢዎች ቀዶ ጥገና ከነበረ • በመራቢያ አካላት ላይ በሚከሰት ቲቢ • የማህፀን እጢዎች፡- ይህ በተለይ በዘር መተላለፊያ ቱቦ አካባቢ ከሆነ የመተላለፊያ መንገዱን የመዝጋት አቅም ሊኖረዉ ይችላል፡፡ • ተፈጥሮያዊ የሆኑ የማህፀን ችግሮች እንዲሁም የማህፀን በር ጥበት ለችግሩ ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች፡- • እድሜ፡- እድሜ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የእንቁላል ብዛትና ጥራት እየቀነሰ ይመጣል፡፡ • ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ የእንቁላል መተላለፊያ ቱቦንና የማህፀን አንገትን ከመጉዳቱ በተጨማሪ ዉርጃ እንዲፈጠርና ከማህፀን በላይ እርግዝና እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የዘር ማምረቻ ከረጢት(ኦቫሪ) ያለጊዜዉ እንዲያረጅና የእንቁላሉ ብዛት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ • የሰዉነት ክብደት፡- ከመጠን በላይ መወፈር ወይም ከመጠን በላይ ክብደት መቀነስ የእንቁላል ከአብራኳ የመዉጣት ሂደትን ይጎዳል፡፡ ስለሆነም የተስተካከለ የሰዉነት ክብደት እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡ • ኢንፌክሽን፡- እንደ ጨብጥና ክላሚዲያ የመሳሰሉ የአባለዘር ህመሞች ከነበሩ የዘር መተላለፊ ቱቦን ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ይህ ደግሞ የመዉለድ ችግር እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ መልካም ጤንነት

የጨጓራ ህመም በእንግሊዘኛ መጠርያው ጋስትራይቲሰ ማለትም የጨጓራ ቁስለት ባሁን ሰዓት በሀገራችን አንገብጋቢ የጤና ችግር እየሆነ መቷል፡፡ ሰለጨጓራ ህመም ያለን እና ሀሳብ ግንዛቤ ጨጓራችንን ጤንነት ከመታመማችን በፊት እድንጠነቀቅ አድርጎናል፡፡ ለማንኛውም እስቲ ስለጨጓራ ቁስለት ወይም የጨጎራ ህመም ቀንጨብ አድርግን እናስርዳዎት፡፡ የጨጎራ ቁስለት/ህመም ምንድን ነው??? የጨጎራችን የላይኛው ሽፋን በተለያዩ ምክንያቶች መላጥ መጎዳትና መቁሰል ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡ ለጨጎራ ቁስለት/ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድን ናቸው?? 1. የተዛባ የእመጋግብ ስርአት 2. ለጨጎራ ጸር የሆኑ መድሀኒቶች NSAID,TB መድኃኒቶች…. 3. የጨጎራ ባክቴርያ በጨጎራችን ውስጥ መኖር 4. የሚያቃጥሉና የሚለበልቡ ምግቦች ማዘውተር 5. እርግዝና የጨጓራ ቁስለት(ህመም)ምልክቶች 1.ደረት መሀል ወይም ጡትና ጡት መሀል የሚኖር፣የሚያቃጥል እና ምቾት የሚያሳጣ ህመም 2.ግሳት እና ማስታወክ 3.ሆድ መንፋትና ቃር 4.ጀርባ፣እግርና ሰውነትን የሚያቃጥል ስሜት መኖር 5.ምግብ ሲበሉ ወይም ሳይበሉ ሲቀሩ የሚኖር የደረት ህመም የጨጎራ ህመም ምርመራዎች ምንድን ናቸው? 1. የጨጎራ ህመም እንዳለብን ከተጠረጠረ መጀመርያ የሚደረገው የባክቴርያ (H.pylory) ምርመራ ነው፡፡በደም ወይም በሰገራ የሚደረግ ምርመራ ሲሆን ውጤቱም +ve (አለ) ወይም _ve (የለም) በመባል ይገለጻል፡፡ 2. UBT(uria breath test) የትንፋሽ የጨጔራ ባክቴርያ ምርመራ ነው፡፡ 3. ENDOSCOPY ይሄ ምርመራ በአፍ በሚገባ ትቦ (ማሽን)አማካኝነት የጨጔራ ቁስለትን ወይም የጨጔራችንን የተጎዳ ክፍል በኮንፒተራይዝድ መሳሪያ የምናይ ሲሆን ህመሙ ለተደጋገመባቸውና በቀላሉ ሊድኑ ላልቻሉ የጨጔራ ህመምተኞች እንጠቀማለን፡፡ 4. syndromic approach ይህንን ዘዴ የምንጠቀመው የላብራቶሪ ምርመራዎች በሌሉበት ቦታና አንዳንዴም ጨጔራ ህመም አለ ብለን እርግጠኛ በሆንንበት ሰአት ነው፡፡ የጨጎራ መድሀኒቶች ጥቅም ምንድን ነው 1. የጨጎራ አሲድን ማቅጠን የበዛ የጨጎራ አሲድ በሚኖርበት ሰአት ጨጎራችን ራሱ በዚህ አሲድ ሊጎዳ ስለሚችል እነዚህ መድሀኒቶች ወደ ጨጎራ በመሄድ አሲዱን አቅጥነው ደረት አካባቢ የሚኖረውን ህመም ይቀንሳሉ፡፡ 2. የጨጎራ ግርግዳን በማከም ህመሙን መቀነስ 3. የጨጓራ ባክቴሪያ መድሀኒቶች በቁጥር 3 አይነቶች ሲሆኑ ባክቴሪያውን ለመግደል ብሎም ቁስለቱን ለማከም ተብለው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ -መድሀኒቶ በታዘዘልን ሁኔታና ሰአት በትክክል ካልወሰድናቸው እንዲሁም ከዛ በኋላ የአመጋግብ ስርአታችንን ካላስተካከልን የመደጋገምና ወድያው ለተመሳሳይ ህመም ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ የጨጓራችንን ጤንነት እንዴት ልጠብቅ??? 1. ጭንቀትን ማስወገድ 2. አመጋገባችንን ማስተካከል 3. የሚያቃጥሉ ምግቦች እና መጠጦች አለመጠቀም 4. አልኮልና ሲጋራ ማስወገድ 5. ፈሳሸ በብዛት መውስድ 6. በሃኪም የሚታዘዙልንን መድሃኒቶች ጨጎራን በማይነኩ መድሃኒቶች ማስቀየር 7. የተደጋግመ የጨጎራ ሕመም ካለብዎ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ የጨጎራ ባክቴሪያ ህክምናዎችን መውሰድ - ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” የሚባለውን ብሂል ሁላችንንም ለማስተማር የታለመ ነው፡፡የጨጎራ ሕመም ከቀላል መድሃኒቶች እስከ ከባዱ ቀዶ ጥገና ድረስ ሊያደርሱ የሚችሉ የጤና መዘዞች አሉት፡፡ -በጤናችን ላይ የምናስተውላቸውን ማንኛዎችንም ለውጦች ችላ ብለን ያለፍናቸው ነገሮች ሁሉ ጤናችንን አውከው አልጋ ላይም ሊያስቀረን ትችላለች፡፡ ስለዚህም በምግብ እና በአኖኖር ዘይቤ ለውጥ ምናስተካክለውን ጨጎራ ህመም ችላ ብለን ታላቅ የጤና ቀውስ አንዲያመጣብን አንፍቀድለት፡፡ መልካም የጤና ግዜ ይሁንልዎ

የልብ ድካም በሽታ ልብ ድካም ማለት የልብ አካል ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም የአሰራር ለዉጥ ምክንያት ለተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች የሚሰራጨዉ ደም በቂ ሳይሆን ሲቀር የሚከሰት የጤና መታወክ ነዉ፡፡ የልብ አካል ጉዳት ሲባል የልብ ቫልቮች መጥበብ ወይም መስፋት የልብ ደም ስሮች መጥበብ የልብ ጡንቻና ማቀፊያ መጎዳት ሊሆን ይችላል፡፡ ✔የልብ ድካም መንስኤዎች ተፈጥሮአዊ የልብ በሽታ ወይንም ከጊዜ በኋላ በሚመጣ የልብ በሽታ ሊሆን ይችላል፡፡ -በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በተጨናነቀ አካባቢ የሚኖሩ ህፃናት በተደጋጋሚ በቶንሲል ህመም ይጠቃሉ፡፡ ለዚህ ቶንሲል በሽታ የተመረቱ አንቲቦዲ የተባሉ በሽታ ተከላካዮች የልብ ቫልቮች መጥበብና መስፋት ጋር ተያይዞ ለልብ ድካም ይዳርጋሉ፡፡ -ከፍተኛ የደም ግፊት ከልብ ጡንቻና ልብ ማቀፊያ በሽታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ከልብ ደም ቧንቧ መጥበብ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉ የልብ ድካም በአብዛኛዉ በዕድሜ በገፉና በወንዶች ላይ ይከሰታል፡፡ -በተጨማሪ በቤተሰብ ታሪክ ተመሳሳይ በሽታ መኖር፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ዉፍረት፣ ስኳር በሽታ፣ ኮሊስትሮል መብዛትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ለዚህ በሽታ የመጋለጥ ዕዱልን ይጨምራል፡፡ • ሲጋራ ማጨስ ሲጋራ ለደም ቧንቧዎች መጥበብ እንደሚያጋልጥ በጥናት ተረጋግጧል፡፡ • ከፍተኛ የደም ግፊት ለረዥም ጊዜ ሳይታከም የቆየ ከፍተኛ የደም ግፊት የልብ ደም ቧንቧዎችን በማጥበብና የልብ ጡንቻዎችን በማወፈር ለልብ ድካም ይዳርጋል፡፡ • ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ሥርዓት ከእንሰሳት ተዋጽኦ የሚገኙ ስብና ቅባቶችን አብዝቶ መመገብ ደም ዉስጥ የኮሌስትሮል መጠንን ከፍ በማድረግ ለደም ቧንቧዎች ጥበት ይዳርጋል፡፡ ✔የልብ ድካም ምልክቶች በቀላሉ መድከምና አቅም ማጣት፣ ያለምንም እንቅስቃሴ ወይም መጠነኛ የአካል እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ሰዓት ትንፋሽ ማጠር በመኝታ ላይ ትንፋሽ ማጠርና ከዚህ ጋር በተያያዘ የመኝታን ራስጌ ከፍ አድርጎ ወይም ትራስ ደራርቦ መጠቀም፤ ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ አስፈሪ እና ከፍተኛ የሆነ ትንፋሽ ማጠር፣ ሌሊት ላይ የሚበረታ ሳል፣ እግር ማበጥ ወይም ከእግር የሚጀምር የሰዉነት ማበጥ የልብ መምታትና የትርታ መጨመር፤ ፌንት ማድረግ፤ ደረት ህመም እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ ማቅለሽለሽ፣ የሆዱ መንፋትና ሆድ ህመም ዋና ዋናዎቹ የልብ ድካም ምልክቶች ናቸዉ፡፡ • የደረት ራጅ፣ ኢ.ስ.ጅ (ECG)፣ ኢኮካሪዲዮ ግራፍና ሌሎች የደም ምርመራዎች የልብ በሽታን በደንብ ለመለየትና ለማከም አስፈላጊዎች ናቸዉ፡፡ ✔ የልብ ድካም ህክምናና የመከላከያ መንገዶቹ የልብ ድካም ቀላል የሆኑ አባባሽ ነገሮችን ከማከም እስከ ከፍተኛ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ሊያስፈልገዉ ይችላል • የልብ ድካምን ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድና ማከም ለምሳሌ፦ የሳንባ ምች፣ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ደም ማነስ፤ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ መድሃኒትን ማቋረጥ፣ እርግዝና፣ አልኮል አብዝቶ መጠጣት፣ ጨዉ አብዝቶ መመገብ የልብ ድካምን የሚያባብሱ ነገሮች ናቸዉ፡፡ • በሀኪም የታዘዙ የልብ ድካም አጋዥ መድሃኒቶችን በሀኪም በታዘዘዉ መሠረት በተገቢዉ ሁኔታ መጠቀም • ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ የልብ ቀዶ ጥገናዎችን በማድረግ በሽታዉን መከላከል ይቻላል፡፡ ✔የልብ ድካም ላለባቸዉ አመጋገባቸዉ ምን መሆን ይኖርበታል • የሚመገቡትን የጨዉ መጠን እንዲቀንሱ ይመከራሉ /በቀን የሚወስዱት የጨዉ መጠን ከ2-3 ግራም መብለጥ የለበትም • ተመጣጣኝና ተጨማሪ ሃይል ሰጪ ምግቦችን በትንሹ መጠን ቶሎ ቶሎ መዉሰድ • አልኮል አለመጠጣት • በሀኪም ትዕዛዝ ካልተከለከለ በስተቀር በርከት ያለ ፈሳሽ መዉሰድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በተመለከተ ከባድ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የልብ ድካም ላለባቸዉ ሰዎች አይመከርም፡፡ ነገር ግን መጠነኛ የሆነ እንቅስቃሴ ማዘዉተር እጅግ ጠቃሚ ነዉ፡፡ መቋቋም የተቻላቸዉን ያህል የአካል እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ ማድረግ ይመከራል፡፡ ✔የልብ ድካም መከላከያ መንገዶች • ከፍተኛ ደም ግፊትን መቆጣጠርና ህክምና ማድረግ • ስኳር በሽታን መቆጣጠር • ሲጋራ አለማጨስ • የሰዉነት ክብደትን መቆጣጠር • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ (አቅምን ያገናዘበ ቢሆን ይመረጣል) • ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን በመድሃኒት መቀነስ • ህፃናት ቶንሲል ሲታመሙ እንዲታከሙ ማድረግ • የታዘዘን መድሃኒት ሳያቋርጡ በአግባቡ መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡

✍️ #የጭንቅላ #እጢ #ምልክቶች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #አብዛኛዎቹ የጭንቅላት እጢ ቀጥለው ከተዘርዘሩት ውስጥ ቢያንስ ከሁለት በላይ ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላል ነገር ግን ምልክቶቹ ሁሉ የእጢ እና ዕጢ ብቻ የማይሆኑበት አጋጣሚም ይኖራል ስለሆነም በምርመራ የትኛው የአእምሮ ክፍል እና ምን አይነት ዕጢ ነው የሚለውን ነገር መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ⏩ #የንቃት #መቀነስ :- የጭንቅላት እጢ ያለበት ሰው የንቃት ደረጃው መቀነስ በደንብ ካለማውራት እስከ ምንም አለመናገር ሊደርስ የእውቀት ችግር ሊሆን ይችላል። ⏩ #የጭንቅላት #መጠን #መጨመር: - አብዛኛው የአንጎል እና የጭንቅላት አጥንት እድገት የሚኖረው በመጀመርያዎቹ ሁለት የዕድሜ ዓመታት ነው። እጢ ወይም ተመሳሳይ እብጠት እና ከነዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር ያላቸው ልጆች ላይ ከልክ ያለፈ የጭንቅላት እድገት ሊኖር ይችላል፤ብዙ ግዜ ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ላይ የሚታይ ምልክት ሲሆን ቀጥታ በእጢው ምክንያት ወይም ከእጢው ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ሁኔታ ሊሆን ይችላል። ⏩ #የማስታወስ #ችግር (#መርሳት) ፡- የቅርብ ወይም የረዥም ግዜ ክንውኖችን የማስታወስ ሁኔታ መቀነስ ፤ ሰው ፣ ቦታ ፣ ግዜ ያለማስታወስ ሁኔታም ሊኖራቸው ይችላል። ⏩ #ራስ #ምታት:- በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ሲሆን ረጅም ወይም አጭር ግዜ የቆየ በማስታገሻ በደንብ የማይቀንስ ፣ ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ፣ ወደ ፊት ሲያጎነብሱ ፣ ሲያስሉ የሚጨምር ራስ ምታት ፤በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ይሆናል፡፡ ⏩ #የሚጥል #በሽታ: - ሁሉም የሚጥል በሽታ ያላቸው ሰዎች በእጢ ወይም በተመሳሳይ እብጠት ምክንያት ነው ማለት አይደለም። ሆኖም ግን የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው እጢ እና ከእጢ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የአንጎል እብጠት አለመኖሩ በምርመራ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ⏩ #ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች አሉ ማለት የጭንቅላት እጢ አለ ሳይሆን በተደጋጋሚ ለነዚህ ምልክቶች ተጋላጭ መሆንና ቢያንሰ ከነዚህ ምልክቶች የተወሰኑትን በራሳችን ላይ የምናስተውል ከሆነ ጤና ተቋም በመሄድ መታየቱ የተሻለ ነው። ለበለጠ መረጃ ዶክተር አለ 8809 ይደውሉ ማንኛውም የጤና ችግሮች ካጋጠመዎት ይደውሉ ምርጫዎ ያድርጉን !!! ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ያበርክቱ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

ውን ደስታ በመንፈጋቸው ሳቢያ ለዘመናት የገነቡትን ትዳር የጠዋት ጤዛ ሲያደርጉት አይተናል፡፡ ምንም እንኳን የስንፈተ ወሲብ ችግር ሳይንሳዊ ምክንያትና መፍትሄ ያለው ቢሆንም፤ ችግሩን በጋራ ለመፍታት መሞከር የተሻለ አማራጭ ነው። ይቀጥላል

#ጤና #ይስጥልኝ #ውድ #የቴሌግራም #ቻላናችን #ተከታታዮቻችን #ለዛሬ #ለእናተ #ይጠቅማል #ያልንውን #ፁሁፍ #እንሆ #ይከታተሉን። በርካታ ባለትዳሮች በግልፅ ለመንገር ባይፈልጉም ከሁለቱ አንደኛው ከወሲብ የሚገኘውን ደስታ በመንፈጋቸው ሳቢያ ለዘመናት የገነቡትን ትዳር የጠዋት ጤዛ ሲያደርጉት አይተናል፡፡ ምንም እንኳን የስንፈተ ወሲብ ችግር ሳይንሳዊ ምክንያትና መፍትሄ ያለው ቢሆንም፤ ችግሩን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ግልፅነት ባለመኖሩ ትዳሮች ፈርሰዋል፡፡ ቤተሰብ ተበትኗል፡፡ ጥያቄው ያለው መፍትሄ ባለው ችግር ለምን ትዳሮች ይናጋሉ? ለምንስ ፍቅረኞች ወደ መለያየት ያመራሉ? የሚለው ላይ ነው፡፡ በቦስተን አካባቢ ባሉ ነጮች ላይ የተጠና ጥናት እንደሚያመላክተው 30 ሚሊየን የሚደርሱ ወንዶች የስንፈተ ወሲብ ችግር አለባቸው፡፡ ጥናቱ ጨምሮ እንዳረጋገጠው የወንዶች እድሜ በጨመረ ቁጥር ችግሩ የበለጠ እየሰፋ ይመጣል፡፡ ለምሳሌ በጥናቱ ከተካተቱት የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ 40 ዓመት ከሞላቸው ወንዶች 40 በመቶ የሚሆኑት እንደዚሁም 70 አመት ከሞላቸው ደግሞ በ70 በመቶዎቹ ላይ የስንፈተ ወሲብ ችግር ታይቶባቸዋል፡፡ የተለያዩ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች ተለያይተው ሲጠኑ ደግሞ፤ ለምሳሌ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው በሶስት እጥፍ የስንፈተ ወሲብ ተጠቂዎች መሆናቸውን በቦስተን በተደረገው ጥናት ተረጋግጧል፡፡ ይህ ጥናት የስነ ልቦና ችግሮችና ውጥረቶች በሚበዛባቸው በአፍሪካና በኤዥያ ሀገሮች ቢሰራ የስንፈተ ወሲብ ችግር ምን ያህል የዓለም ችግር መሆኑን እንደሚያሳይ የአሜሪካዎቹ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ በስንፈተ ወሲብ (Sexual Dysfunction) ምንነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶችና አማራጭ የህክምና መፍትሄው ዙሪያ የሚያተኩር ትንታኔን ቀርቦበታል በጥሞና በትዕግስት አንብበው ወይም አንብቡት፡፡ የስንፈተ ወሲብን ምንነት ስንፈተ ወሲብ (Sexual Dysfunction) የምንለው በተለያዩ ምክንያቶች በሁለቱም ፆታዎች በኩል ወሲብ ለመፈፀም የሚያስችሉ ችግሮች ሲከሰቱ ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ደግሞ አግባባዊ (የሚያረካ) የወሲብ ግንኙነት አለመፈፀም አልያም በሚደረገው የወሲብ ግንኙነት አለመርካት (ጥሩ ውጤት አለማግኘት) ማለት ነው የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚባለው፡፡ እንዴት ይገለፃል? ለሚለው ለግብረ ስጋ ግንኙነት ስሜት ማጣትና ከግንኙነቱ እርካታ አለማግኘት በሁለቱም ፆታዎች ላይ የሚታይ ችግር ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካላት አለመነሳሳትን በተመለከተ በአብዛኛው በወንዱ ላይ ይታያል፡፡ ፍላጎት ማጣት፣ ከግንኙነት በኋላ እርካታን አለማግኘት (የእርካታ መጨረሻ ላይ አለመድረስ) ብዙውን ጊዜ የሴቶች ችግር ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለችግሩ መፈጠር መንስኤዎች የስንፈተ ወሲብን መንስኤ ስነ ልቦናዊና አካላዊ ብለን በሁለት ትላልቅ ጎራዎች ከፍለን መመልከት እንችላለን፡፡ አካላዊ ስንል ከግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካሎች ለውጥ፣ በደም ውስጥ ካሉ ንጥረ ነገሮች መዛባት፣ ከአዕምሮና ከህብለሰረሰር የሚነሱ ችግር ውስጥ ከመግባታቸው ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ እንደዚሁም ከልብ የሚነሱ ደም ስሮች በአግባቡ ወደ ብልት ሄደው የደም ዝውውሩን ውጤታማ ማድረግ ባለመቻላቸውና ብልትን እንዲቆም የሚያደርጉ ነርቮች ባለመስራታቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር ይመጣል፡፡ ሌላውና ከአካላዊ ምክንያት ጋር የሚያያዘው ስሜት ቀስቃሽ ንጥረ ነገሮች (ሆርሞኖች) በሚፈለገው መጠን በሰውነት ውስጥ አለመኖር፣ ስሜት ቀስቃሽ ንጥረ ነገሮች በሚፈለገው መጠን እንዳይሰሩ የሚያደርጉ ሌሎች የሆርሞን አይነቶች በሰውነት ውስጥ በብዛት ሲከሰቱ፣ በብልት ላይ የተለያዩ አደጋዎች ሲደርሱ፣ በብልት አካባቢ በሚሰሩ ቀዶ ህክምናዎች ምክንያት በብልት አካባቢ ያሉ ነርቮችና ደም ስሮች ሲጎዱ ለስንፈተ ወሲብ ችግር መጋለጥን ያመጣሉ፡፡ በተጨማሪም ለሌሎች በሽታዎች መፈወሻ ተብለው የሚሰጡ ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ ለጨጓራ፣ ለኮሌስትሮል፣ ለሽንት ማሸኛ፣ ለአዕምሮ ህመሞችና ለሌሎችም በሽታዎች የሚሰጡ መድኃኒቶች ችግሩን የማምጣት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በአጠቃላይ 25 በመቶ የወንዶች ስንፈተ ወሲብ ለሌሎች በሽታዎች በሚሰጡ መድኃኒቶች የሚመጣ ነው፡፡ ከስነ ልቦና አንፃር ደግሞ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ጫና፣ ውጥረትና ቀደም ሲል በነበረ የወሲብ ታሪክ ጥሩ ያልሆነ ክስተት ከነበረ ለምሳሌ በቅርብ ዘመዶችም ሆነ በሩቅ ሰዎች ተገዶ መደፈር ከነበረ ወሲብን መጥላት ይኖራል፡፡ በወሲብ መፈፀሚያ ቦታዎች አካባቢ ምቾት ማጣት፣ ከማይፈልጉት ሰው ጋር መኖር (ወሲብ መፈፀም) የወሲብ ስሜት አልባነትን ያመጣል፡፡ እንደዚሁም በአንድ ወቅት በሆነ ምክንያት ወሲብ ያለመፈፀም ችግር ገጥሞት ከነበረ ሁል ጊዜም ችግሩ አለብኝ ብሎ መጨነቅ ወደ ስንፈተ ወሲብ ችግር በቀጥታ የሚገፋ ሁኔታ ነው፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ መንስኤዎችን ስናየው አካላዊ ወይም ከበሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰተው ስንፈተ ወሲብ በአብዛኛው ከ40 ዓመት በላይ ባሉ ሰዎች ላይ የሚታይ ነው፡፡ በተለይም ከስነ ልቦና ጋር በተያያዘ ችግር ይበልጥ የሚጠቁት ወጣቶች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከስነ ልቦናዊ ምክንያቶች ጋር የተያያዘው የስንፈተ ወሲብ ችግር ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚደርስ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ከ40-80 በመቶ የሚሆነው የስንፈተ ወሲብ ችግር በቂ የሆነ አካላዊ ምክንያት ያለው ነው፡፡ ከላይ በመንስኤነት ከተገለፁ ጉዳዮች በተጨማሪ የሚገልፀው አብዝቶ አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ሐሺሽ እና ለመዝናኛነት ተብለው የሚወሰዱ መድኃኒቶች ችግሩን በማምጣት ረገድ የጎላ ሚና አላቸው፡፡ ስንፈተ ወሲብን በማምጣት ወይም በማባባስ በኩል አስተዋፅኦ ያላቸው የጤና ችግሮች – ኢንፌክሽን – የልብ ህመም – የጉበት ህመም – የኩላሊት ህመም – የስኳር እና – የደም ግፊት በሽታዎች እንደዚሁም – የኮሌስትሮል ከፍ ማለት – የጡንቻ መኮማተር (በተለይ በሴቷ) – የደም ስር ችግሮች – የነርቭ ህመም እና – ሰውነትን የሚያንቀጠቅጥ ህመም (ፓርኪንሰንስ ዲዝዝ) ከላይ የገለፅኳቸው የጤና ችግሮች በአንድ በኩል ስንፈተ ወሲብን ያስከትላሉ፡፡ በሌላም በኩል ቀደም ሲል የተከሰተን ስንፈተ ወሲብ ያባብሳሉ፡፡ ስንፈተ ወሲብ መኖሩን ፍንጭ ከሚሰጡ ምልክቶች ዋና ዋና የሚባሉትን ስናይ – የወሲብ ፍላጎት ማጣት – የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ዝግጁ አለመሆን (አለመቆም) – በተለይም ሴቶች ወንድንም ሆነ ወሲብን መጥላት – ብልት ቶሎ ተልፈስፍሶ መውደቅ ወይም መርገብ – ወሲብ በሚፈፀምበት ወቅት ህመም መኖር – የሴት ብልት ጡንቻ መኮማተርና በሁለቱም ላይ ህመም መፍጠር – ሴቶችን ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርግ ፈሳሽ በበቂ መጠን አለመኖር – እርካታ ላይ አለመድረስ ፈጥኖ እርካታ ላይ መድረስ ከሳይንስ አኳያ ስናየው ፈጥኖ የዘር ፍሬን ማፍሰስ ችግር ያለባቸው በቁጥር ቀላል የማይባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ ዋናዋና የምንላቸው ምክንያቶች አንደኛው ለወሲብ ጉጉ ከመሆን የሚመነጭ ችኩልነት፣ ሁለተኛ ከአሁን አሁን የዘር ፍሬዬ ፈሰሰ ብሎ መጨነቅ፣ ሶስተኛ ራሴንም ሆነ ተቃራኒ ፆታዬን ማርካት አልችልም ብለው በተደጋጋሚ ስለሚያስቡ ስሜታቸውን ነፃ አድርገው ለመጋራት መቸገራቸው አራተኛው ከነርቭ ወይም ከብልት አፈጣጠር ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው፡፡. በርካታ ባለትዳሮች በግልፅ ለመንገር ባይፈልጉም ከሁለቱ አንደኛው ከወሲብ የሚገኘ

ለኩላሊታችን መልካም ጤንነት ስንል ከእነዚህ ልማዶች ብንርቅስ ኩላሊት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ደም በማጣራት በሰውነታችን ውስጥ የማያስፈልጉ ነገሮችን በሽንት መልክ ማስወገድ አንዱ ነው።በሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀመ አላስፈላጊ ውሃን ማስወገድ እና የካልሺየምና የፎስፌት ማዕድናት መጠንን መቆጣጠርም ሌላኛው ስራው ነው። የደም ዝውውርን የሚያፋጥኑና የቀይ ደም ህዋስ መመረት ሂደትን የሚጨምሩ ሆርሞኖችንም ያመርታል። በርካታ ተግባራት የሚከውነው ኩላሊት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥልና ስራውን በተገቢው መንገድ እንዲያከናውን ታዲያ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ነገሮች መራቅ ይገባል። የሽንት ቀለም መቀየር፣ ማስመለስ፣ የአተነፋፈስ መዛባት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ድካም እና የመሳሰሉት የኩላሊት በሽታ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ ይመከራል። 1. ሽንትን ይዞ መቆየት ሽንት ሳይወገድ በፊኛ ለረዥም ጊዜ ከቆየ ለቫክቴሪያዎች መፈጠር ምክንያት የሚሆን ሲሆን፥ ይህም የሽንት ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ይፈጥራል። ስለሆነም በስራ ውጥረትም ይሁን ሌላ የተፈጥሮ ጥያቄን መልስ የሚያዘገዩ ከሆነ ለኩላሊትዎ ሲሉ ከድርጊትዎ ሊቆጠቡ ይገባል እንላለን። 2. በቂ ውሃ አለመጠጣት ኩላሊት አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ ተግባሩ በቂ ውሃ ስለሚፈልግ በቀን ውስጥ በቂ ውሃ አለመጠጣትም ለኩላሊት ህመም ይዳርጋል። ሰውነታችን አስፈላጊውን ያህል ውሃ ካላገኘ ደም ስለሚረጋ ወደ ኩላሊታችን የሚሄደው ደም መጠን ይቀንሳል። ይህም ኩላሊት ከሰውነታችን የሚያስወግዳቸው መርዘኛ ተህዋሳት በበቂ ሁኔታ እንዳይወገዱ ያሰናክላል ማለት ነው። ስለሆነም በየቀኑ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ኩላሊትዎ ጤናማ እንዲሆን ያግዛል። 3. ጨው አብዝቶ መመገብ በተደጋጋሚ ጨው የበዛበት ምግብ መመገብም ለኩላሊት ጤና ፀር ነው ተብሏል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጨውን አብዝቶ መውሰድ በሽንታችን ውስጥ የፕሮቲን መጠን እንዲጨምር በማድረግ ለኩላሊት ህመም ይዳርጋል። በየቀኑ በአጠቃላይ ከምንወስዳቸው ምግቦች ውስጥ የጨው ድርሻ ከ5 ግራም ባይበልጥ መልካም ነው ይላሉ ባለሙያዎች። 4.መድሃኒቶችን/ ማስታገሻዎችን አዘውትሮ መውሰድ ብዙዎቻችን ጉንፋን አልያም ራስ ምታት ሲያመን በሽታ የመከላከል አቅማችንን የሚያጎለብቱ ምግቦችና መጠጦችን ከመውሰድ ይልቅ ኪኒን ስለመዋጥ ነው የምናስበው። መድሃኒቶች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ኩላሊታችን አልያም ሌላ የሰውነት ክፍላችን ሊጉዱ እንደሚችሉ ይነገራል። አንዳንድ ጥናቶች ማስታገሻዎችን በተደጋጋሚ መውሰድ ወደ ኩላሊት የሚሄደውን ደም እንቅስቃሴ ሊቀንሱ እንደሚችሉ አመላክተዋል። 5.ፕሮቲን የበዛባቸው ምግቦች ፕሮቲን ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም፥ ቀይ ስጋና የፕሮቲን መጠናቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን በተደጋጋሚ መውሰድ ለኩላሊት በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል። 6. አልኮል የአልኮል መጠጦችን አብዝተን በምንጠጣበት ወቅት ዩሪክ አሲድ በኩላሊታችን ቱቦ ይከማቻል። ይህም ኩላሊታችን የተለመደ ተግባሩን እንዳያከናውን እክል ይፈጥራል። ስለሆነም ሁሉም በልኩ ነውና በመጠጡም ለጤናዎ ይወቁበት። 7. ሲጋራ ሲጋራ ማጨስ በሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች የሚያደርሰው አስከፊ ጉዳት አጠያያቂ ባይሆንም ለኩላሊት ህመም እንደሚያጋልጥም ይነገራል። ሲጋራ እድሜ እየገፋ ሲመጣ ለሚከሰተው የኩላሊት ህመም መንስኤ ከመሆኑም ባሻገር የኩላሊት ህመምተኞች አጫሾች ከሆኑ ደግሞ በሽታው እጅግ እንዲባባስ እንደሚያደርግ በጥናት ተረጋግጧል። 8. ቡና (ኮፌይን አብዝቶ መጠቀም) ካፌይን አብዝቶ መጠቀም ለደም ግፊት ከመዳረጉም ባለፈ ኩላሊትንም ይጎዳል። ካፌይንን ካለ ልክ መውሰድ ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር ምክንያት የሚሆን ሲሆን፥ የካልሺየም ንጥረ ነገር ከሽንት ጋር በብዛት እንዲወገድም ያደርጋል። 9.ጉንፋንን የመሳሰሉ ህመሞችን ቸል ማለት እንደ ጉንፋን፣ ቶንሲል፣ ኢንፍሊዮንዛ ያሉ ህመሞችን በቸልታ ማለፍ ኩላሊትን ሊጎዱ እንደሚችሉ ይነገራል። እነዚህ ቀላልና የተለመዱ ህመሞችን የሚያመጡ ቫክቴሪያዎችና ቫይረሶች አስፈላጊው ህክምና በወቅቱ ካልተደረገ ኩላሊትን የመጉዳት አቅም አላቸው። 10. እንቅልፍ ማጣት በተጣበበ ጊዜና የስራ ሁኔታ የሚኖሩ ሰዎች እንቅልፍ የሚያስገኘውን የጤና በረከት ይዘነጉታል። በእንቅልፍ ስዓት የአዳዲስ ህዋሳት አሮጌዎቹን የመተካት ተግባር ይከናወናል። በአንፃሩ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት እንደ ኩላሊት ያሉ ሌሎች የሰውነት አካላት ተግባራቸውን በተገቢው ሁኔታ እንዳያከናውኑ ያደርጋል። በተጨማሪም በቂ እረፍት ወይም እንቅልፍ አለመኖር ለደም ግፊት ይዳርጋል።