Halal Branding and Marketing PLC ®
前往频道在 Telegram
🟢 Our Services 🟢 ➜Brand Design ➜Logo Design ➜Flyer Design ➜Business Card ➜Banner Design ➜Broucher Design ➜Letterhead Design ➜Social Media Poster ⚪️For More Information⚪️ •Phone Number: 0978065466
显示更多320
订阅者
无数据24 小时
+17 天
-430 天
帖子存档
አሜሪካ ስለምን የእስራኤል የነፍስ አባት መሆንን መረጠች ? ለመሆኑ ለአሜሪካ የእስራኤል አስፈላጊነትስ እስከምን ነው ?
ባለፈው ፅሁፌ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገው ድጋፍ ምን ያክል ገደብ አልባና በሁሉም ዘርፍ በጣም ግዙፍ መሆኑን ለማሳየት ሞክሪያለሁ ። ዛሬ ደግሞ ለመሆኑ ለምን ሲባል ? የሚለውን ለማየት እሞክራለሁ ።
1 የእስራኤል የማይተካ ስትራቴጂካዊ ቦታነት
አንድ የአሜሪካ ሴናተር እስራኤልን ሲገልፃት " እስራኤል የአሜሪካ የጦር ጀት ተሸሚ መርከብ እንደማለት ናት " ይላታል ። አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ለምታካሒዳቸው ዘመቻዎች እና እንቅስቃሴዎች ሁሉ ቁልፏ ሀገር እስራኤል ናት ። በመካከለኛው ምስራቅ ብቸኛዋ ሙስሊም ያልሆነችውን እስራኤልን የሚያክል ሌላ ታማኝ ሀገር ለአሜሪካ ማግኘት ከባድ ነው ። ዛሬ ወዳጆቿዋ የሆኑት እነ ሳኡዲ ፣ ግብፅ ፣ ኢማራት ወዘተ አንድ ቀን መንግስታቸው ቢቀየር የአሜሪካ ጠላት ሆነው እንደሚነሱ ለመተንበይ የፖለቲካ ጠበብት መሆንን አይጠይቅም ። ስለዚህ እነርሱ ለጊዜ እና ጥቅም ስላስተሳሰራቸው እንጅ ለአሜሪካ አስተማማኝ የቀጠናው አጋር ሊሆኑ አይችሉም ። በዚያ ላይ ህዝቦቻቸው አሜሪካ ጠሎች ናቸው ።
እስራኤል ግን ከዚህ የተለየች ናት ። የፈለገውን ያክል መንግስታት ቢቀያየሩ የአሜሪካ ወዳጅ ከመሆን ውጭ ምርጫ ስለሌላት የአሜሪካን ጥቅም በመካከለኛው ምስራቅ ሳታወላውል ታስፈፅማለች ። ዜጎቿም አሜሪካን ኦንደጠባቂያቸው የሚያዩ በመሆኑ ለአሜሪካ ጥላቻ ያለው እስራኤላዊ የለም ። በመሆኑ በቀጠናው አሜሪካ እስራኤልን በማንም አትተካትም ።
2 የእስራኤል ሎቢዎች ( The Israel lobby )
John Mearsheimer እና Stephen Walt የተሰኙ የፖለቲካ ጠበብቶች በጋራ በፃፉት " The Israel lobby " በተሰኘ መፅሀፋቸው አሜሪካ በዚህን ያክል መልኩ ለእስራኤል ገደብ አልባ ድጋፍ የምታደርገው የእስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያን ያክል አስፈላጊ ሆኖ ሳይሆን የእስራኤል ሎቢዎች በአሜሪካ የሚሰሩት እጅግ ወደር አልባ የማግባባት ስራ ነው ይላሉ ።
በአሜሪካ ትልቁ የእስራኤል ሎቢ America Israel Public Affairs committee( #AIPAC ) ይሰኛል ። ይህ ድርጅት የአሜሪካ ህግ አውጪዎችን በማግባባት እና በማሳመን አሜሪካ ለእስራኤል ያደላ ውሳኔ እንድታሳልፍ የሚያደርገው ትልቁ ተቋም ነው ። ይህ ተቋም በአይሁዳውያን ባለሀብቶች በከፍተኛ ሁኔታ የሚደገፍ ከመሆኑም በላይ ከአሜሪካ ክርስቲያኖች በተለይ ከኢቫንጀሊካኖች ከፍተኛ ድጋፍ ይደረግለታል ። እናም ይህ ተቋም ከባለስልጣናት እስከ ሚዲያዎች ለእስራኤል ያደላ ውሳኔዎችና የሚዲያ ዘመቻዎች እንዲደረጉ ከፍተኛ ግፊት ያደርጋል ።
በዚህ የማይስማሙ የፖለቲካ ሊሂቃን ደግሞ ዋናው የእስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት እና የአሜሪካ ጥቅም አስከባሪነት እንጅ የሎቢ ድርጅቶች ተፅእኖ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ ።
3 ሀይማኖታዊ ምክንያቶችና ኢስላም ጠልነት
እንደውም ትልቁ ምክንያት ይህ ይመስላል ። በአሜሪካ ትልቁን የአማኞች ቁጥር የሚሸፍኑት የኢቫንጀሊካን ፕሮቴስታንት አማኞች በኢስላም ጠልነት ተወዳዳሪ የላቸውም ። ከ 70% በላይ የሚሆነው አሜሪካዊ የኢቫንጀሊካን አማኝ አንድም ሙስሊም በአሜሪካ ማየት አይፈልግም ። እነዚህ አሜሪካዊያን የኢስላም ጠላት ካሉት ጋር ሁሉ ጥምረትና ወዳጅነት ይፈጥራሉ ። በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ ጠላትነት ላወጀ ሁሉ እነርሱ ወዳጅነትን ያውጃሉ ።
ኢቫንጄሊካኖች እስራኤልን የአረቦችና ሙስሊሞች ቀንደኛ ጠላት አድርገው ነው የሚቆጥሩት ። በመሆኑ ለእስራኤል አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ልታደርግ ይገባታል ብለው በፅኑ ያምናሉ ። እናም የእስራኤል ጉዳይ ከነርሱ ጋር ቁልፍ ከሚባሉ ጉዳዮች አንዱ ነው ። የምርጫ ቅስቀሳ ወቅትም ከግምት ከሚገቡ ነገሮች ከቀዳሚዎቹ ለእስራኤል የሚደረግ የፖሊሲ ድጋፍ ነው ።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ሰፊውን የኢቫንጀሊካን ክርስቲያን አማኝ ድምፅ ለማግኘት ለእስራኤል ያዳላ ኦና አረብና ሙስሊሞችን የሚጎዳ ፖሊሲ ይዘው ይቀሰቅሳሉ ።
ኢቫንጀሊካኖች ሙስሊሞችን ኢየሩሳሌምን የወረሩ ፀረክርስቲያኖች ናቸው ብለው ሲያምኑ እስራኤልን ደግሞ ቅዱሶችን ቦታዎች ለማስመለስ የምትታገል በእግዚአብሔር የተላከች ሀገር አድርገው ነው የሚስሉት ። የኢስላም ጥላቻ አሜሪካ ይህንን የበደል ድጋፍ እንድታደርግ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው ።
4 በአሜሪካ የሚኖሩ አይሁዳዊያን
በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ከ 7 ሚሊዮን በላይ አይሁዳዊያን ይኖራሉ ። እነዚህ አይሁዳዊያን ከ 100 አመታት በፊት ከአውሮፓ በተለይም ከጀርመን እና ከምስራቅ አውሮፓ ፈልሰው የሄዱ ናቸው ።
አይሁዳዊያኑ አሜሪካ ከገቡ በሗላ ማንነታቸውን ወደ አሜሪካዊነት ቀይረው ህብረተሰቡን በመቀላቀላቸው አሜሪካዊ ተደርገው ለመወሰድ ጊዜ አልፈጀባቸውም ። ከዚያም አልፎ እነርሱ አሜሪካ በምታደርጋቸው ጦርነቶች ውስጥ በቀዳሚነት በመሰለፍ የአሜሪካን ልብ ማሸነፍ ቻሉ ።
በአንደኛው የአለም ጦርነት ወቅት እንኳ ከ 500,000 በላይ አይሁዳዊያን በአሜሪካ ጦር ውስጥ ተሰልፈው ተዋግተዋል ። ያ ማለት ለጦርነት ብቁ አሆኑ አይሁዳዊያን ውስጥ አብዛኛው ጦርነቱን ተቀላቅሏል ። ይህም የአሜሪካን ልብ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል ።
ጠንካራ ማህበራዊ አደረጃጀት ያላቸው አይሁዳዊያኑ በፖለቲካው ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ በመሆናቸው እጩ ተወዳዳሪዎች የነርሱን ድምፅ ለማግኘት ሲሉ የእነርሱን ፍላጎቶች በተለይ ከእስራኤል ጋር ተያይዞ ያለውን ለማስፈፀም በስፋት ይንቀሳቀሳሉ ።
አብዛኛው አይሁዳውያን የዲሞክራቶች ደጋፊ ናቸው ።
#Seid_Mohammed_Alhabeshiy
http://T.me/ertugrulethiopia
#የአብዱረህማንን
"ኢንሻአላህ በቱርክ ያለውን ፍትህ በእየሩሳሌም እናመጣዋለን! የሰለሀዲንን መንገድ እንከተላለን ጋዛ ፍልስጤም ናት!"
Celal Al 💖
#FreePalestine 🇵🇸
http://T.me/ertugrulethiopia
Anwaariif haa dirmannu !
የድጋፍ ጥሪ ለወገን ደራሽ ወገን ነው!
*******************************
Anwaar Huseen Abbaaduraa jedhama. Dhibee rakkoo oomishamuu dhabuu dhiigaa APLASTIC ANEMIA) jedhamu dhukkubsata. Dargaggoo waggaa 20ti. Yunivarsitii Samaraatti ramadamee sababa dhibee kanaa barumsarraa hafe. Kanaan dura deeggarsa namoota adda addaatiin yaalii argachaa tureera. Amma garuu gara biyya alaa bahee akka yaalamu boordii hospitaala xiqur ambassaatiin murta'eera. Maatiin isaa qarshii yaaliif isa barbaachisu miiliyoona 2.5 kan hin qabneefi humna isaaniiti olidha. Kanaafuu hundi keenyayyuu haga dandeenyeen birmanneefii jazaa isaa Rabbirraa haa eeggannu. Rabbiif jennee Haa birmannuuf! Lakkoofsa herreega armaan gadiitiin deeggarsa ha goonuuf.
የድጋፍ ጥሪ ለወገን ደራሽ ወገን ነው!
********************************
አንዋር ሁሴን ይባላል። የሀያ አመት ወጣት ነው። የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ አመት ተማሪ ነበር። በህመም ምክንያት ትምህርቱን መቀጠል ግን አልቻለም። ለረጅም ጊዜ በቂ በደም ያለመመረት በሽታ(APLASTIC ANEMIA) ምክንያት ሲሰቃይ ቆይቷል፣ እስካሁንም በተለያዩ ቦታዎች ህክምና ሲከታተል ቆይቷል። ሕክምናው በሀገር ዉስጥ ስላልተቻለ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም ካልቻለ ሕይወቱ አደጋ ላይ መሆኑን የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ ወስኗል። ሆኖም ግን ለህክምናው ያስፈልጋል የተባለውን የ2.5 ሚሊዮን ብር ገንዘብ ቤተሰቦቹ አቅም ስለሌላቸው ሕብረተሰቡን እርዳታ ለመጠየቅ ተገዷል። በመሆኑም አላህ(ሱወ) ከመሰል በሽታ ይጠብቅዎት እያልን አላህ ባገራልን መጠን ወንድማችንን በማገዝ እንታደገው።
Lakkoofsa herr. Baankii/የባንክ ሂሳብ ቁጥር
******************************************
1. Baanki Daldala Itiyooppiyaa/የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000018555992/1000337570918
2. Hojii G/Oromiyaa /ኦሮሚያ ህ/ሥራ/ባንክ 1000077415096
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
