ጠቅላላ እውቀት
前往频道在 Telegram
7 291
订阅者
无数据24 小时
+17 天
-1530 天
帖子存档
7 291
#በዕንቅልፍ_ሠዓት_ማንኮራፋትን_ለመቀነስ_የሚረዱ_ሁኔታዎች
♧ ማንኮራፋት በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት የሚመጣ ድምፅ ነው።
♧ ማንኮራፋት አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
♧ በእንቅልፍ ሠዓት ማንኮራፋትን ለመቀነስ የሚከተሉትን መፍትሄዎች ይከተሉ፦
➊ የእንቅልፍ ሠዓትዎን ያስተካክሉ ፦ ለረጅም ሠዓታት ያለ ዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፤ ስለሆነም ለራስዎ በቂ ዕረፍት ይስጡ
➋ ክብደትዎን ይቀንሱ ፦ ከጊዜ ወዲህ በመጣ ክብደት ማንኮራፋት የሚያስቸግርዎት ከሆነ ክብደትዎን በማስተካከል ማንኮራፋትን መቀነስ ይችላሉ
➌ በጎንዎ ይተኙ ፦ በሚተኙበትን ወቅት በጀርባ ከመተኛት ይልቅ በጎንዎ መተኛት የአየር ቧንቧ መጥበብን በመከላከል ማንኮራፋትን መቀነስ ያስችልዎታል
➍ ምቹ ትራስ ይጠቀሙ ፦ በሚተኙበት ወቅት እንደሁኔታው ለእርስዎ የሚመች ትራስ መጠቀም የማንኮራፋት ልምድዎን መቀነስ ያስችልዎታል
➎ በቂ እንቅልፍ ያግኙ
➏ አልኮል መጠጥ አይጠቀሙ ወይም በመጠኑ ያድርጉ ፦ የሚጠጡ ከሆነ ደግሞ ከመተኛትዎ በፊት ከ 2 እስከ 3 ሠዓታት አስቀድሞ መጠጣት፣ ይህም የበዛ የጡንቻ መላላት እንዳይኖር ይረዳል
➐ ሲጋራ አያጪሱ
➑ የአፍንጫ ቀዳዳዎችዎን በደንብ ያፅዱ
➒ የአፍንጫ ወይም የመተንፈሻ አካል አላርጂክ ካለብዎ ሕክምና ይከታተሉ
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#የሐኪም_አይነቶች_ስያሚያቸው 💉 👩⚕️
1. የልብ ሐኪም ➢ ካርዲዮሎጂስት
2. የቆዳ ሐኪም ➢ ደርማቶሎጂስት
3. የአጥንት ሐኪም ➢ ኦርቶፔዲክ
4.
የአእምሮ ሐኪም ➢ ኒውሮሎጂስት
5. የህፃናት ሐኪም ➢ ፔዲትሪያን
6. የዓይን ሐኪም ➢ ኦፕታሞሎጂስት
7. የጥርስ ሐኪም ➢ ዴንቲስት
8. የኩላሊት ሐኪም ➢ ኒፍሮሎጂስት
9. የቀዶ ጥገና ሐኪም ➢ ሰርጂን
10. የካንሰር ሐኪም ➢ ኦንኮሎጂስት
11. የስነ ልቦና ሐኪም ➢ ሳይካትሪስት
12. የጉበት ሐኪም ➢ ሔፓቶሎጂስት
13. የሴቶች ሐኪም ➢ ጃይናኮሎጂስት
14. የሆድ ሐኪም ➢ ጋስትሮንቶሎጂስት
15. የጆሮ ሐኪም ➢ ኦቶራሎንቶሎጂስት
16. የሳንባ ሐኪም ➢ ፑልሞኖሎጂስት
17. የእንስሳት ሐኪም ➢ቬተርነሪያን
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯7 291
#ጥሩ_እንቅልፍ_በብርሃን_ወይስ_በጨለማ?
♧ በተለምዶ ሳይንሳዊ ምክንያቱ ሳይገባን ከልጅነታችን ጀምሮ ስንተኛ መብራት እንድናጠፋ እየተነገረን ነው ያደግነው።
♧ በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች መብራት ጠፍቶ መተኛት የማይችሉ ወይም ድቅድቅ ጨለማ ሲሆን የሚፈሩ አሉ።
♧ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፤ ጤናማ እና ጥሩ የሚባል እንቅልፍ የምንተኛው ከብርሃን ይልቅ በጨለማ ክፍል ውስጥ ነው።
የመብራት ብርሃን ባለበት መተኛት ምን የጎንዮሽ ጉዳት አለው?
♧ በእንቅልፍ ወቅት ለብርሃን መጋለጥ አዕምሮ ተገቢውን እረፍት እንዳያገኝ በመረበሽ የእንቅልፋችንን ጤንነት ይጎዳል።
♧ ከዚያም ለተለያዩ ተጓዳኝ የጤና ችግሮች ያጋልጠናል። ከእነዚህም የጤና እክሎች መካከል:-
1️⃣ ድብርት | Depression:-
♧ ብርሃን ባለበት ሁኔታ ውስጥ መተኛት ከፍተኛ ለሆነ ድብርት የማጋለጥ እድል አለው።
♧ የብርሃኑ አይነት ከተለያዩ ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች የሚመነጨው ሰማያዊ ብርሃን (Blue Light) ሲሆን ደግሞ ነገሩን የበለጠ አስከፊ ያደርገዋል።
2️⃣ ከልክ በላይ ውፍረት | Obesity:-
♧ በሴቶች ላይ በኤን.አይ.ኤች የተደረገ አንድ የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው:-
♧ የቴሌቪዥን ብርሃን ባለበት ክፍል ውስጥ የሚተኙ ሴቶች ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት የመጋለጥ እድላቸው በጨለማ ክፍል ውስጥ ከሚተኙት ጋር ሲነጻጸር ከፍ ያለ ነው።
♧ በቂና ጤናማ እንቅልፍ ያለማግኘት ዘወትር ከምንመገበው የምግብ መጠን በላይ እንድንመገብ ስለሚያደርግ ለከፍተኛ የሰውነት ክብደት መጨመር ከሚያጋልጡ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ሊሆን ይችላል።
3️⃣ አደጋ | Accident:-
♧ በብርሃን ውስጥ መተኛት ጤናማ የሆነ እንቅልፍ እንዳናገኝ ስለሚያደርግ ቀኑን ንቁ ሆነን መዋል ይቸግረናል።
♧ በዚህም ምክንያት ለተለያየ አደጋ የመጋለጥ እድላችን ከፍ ይላል። ህጻናት ልጆች ጨለማን በመፍራት ያለብርሃን መተኛት ይቸገሩ ይሆናል።
♧ ይህ ሁኔታ ሲያጋጥመን ቀስ በቀስ የብርሃኑን መጠን ከቀን ወደ ቀን እየቀነሱ በጨለማ ክፍል ውስጥ መተኛትን ማላመድ ያስፈልጋል።
በብርሃን መተኛት የለመዱ ሰዎች ምን ማድረግ አለባቸው?
♧ በብርሃን የመተኛት የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ሰዎች በአንድ ግዜ ተነስተው በጨለማ ክፍል ውስጥ መተኛትን መላመድ አይችሉም።
♧ ስለዚህ ቀስ በቀስ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በጨለማ ክፍል መተኛት መለማመድ ያስፈልጋል።
♧ ከመኝታ በፊት የመኝታ ክፍልን ብርሃን መቀነስ።
♧ ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎችን ከመኝታ ክፍል ማራቅ።
♧ ቀይ የሌሊት መብራቶችን (Red Nightlight Bulbs) መጠቀም።
♧ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የተለያዩ ቀለሞች ካሏቸው መብራቶች ይልቅ፤ ቀይ መብራት የእንቅልፍ ሆርሞን በሆነው ሜላቶኒን (Melatonin) ላይ ያላቸው ተጽዕኖ ዝቅተኛ ነው።
♧ አልኮል እና ካፌን የበዛባቸውን መጠጦች መቀነስ።
♧ በእንቅልፍ ሰዓት ብዙ ምግብ አለመመገብ።
♧ልብ ይበሉ:- ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት የምንችለው በጨለማ ውስጥ በመተኛት ነው።
♧ ብርሃን ባለበት ክፍል ውስጥ መተኛት ከእንቅልፍ ጤንነት አንጻር የሚመከር ልምድ አይደለም።
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#የጀርባ_ሕመም_እና_መከላከያው
♧ የጀርባ (የአጥንት አከርካሪ) ሕመምን ከአኗኗር ዘይቤያችን ጋር ተያይዞ የሚከሰት በመሆኑ ሕመሙ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡
♧ ሕመሙ በጀርባ አካባቢ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን ቀስ በቀስ ወደ አንገት፣ እጅ፣ እግር በመተላለፍ እንደልብ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ይሆናል፤ አለፍ ሲልም ለከፋ ሕመም እና ሞት ሊዳርግ እንደሚችል ይገለጻል፡፡
♧ የጀርባ ሕመምን በሚመለከት የአከርካሪ አጥንት ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሰላም አክሊሉ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
♧ ለዚህ ሕመም መንስዔ በዋናነት የአኗኗር ዘይቤያችን መሆኑን የሚያነሱት ዶ/ር ሰላም፤አቀማመጣችን፣ አተኛኘታችን፣ስራ የምንሰራባቸው መንገዶች እንዲሁም የስልክ አጠቃቀማችን እንደሚጠቀሱ ይገለጻሉ፡፡
♧ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት ዶ/ር ሰላም፤ ለረዥም ሰዓት መቀመጥ እና የ8 ዓመት እድሜን ያህል እንደሚቀንስ ጥናቶች እንደሚያስረዱ አንስተው"ብዙ መቀመጥ ይገላል" ይላሉ፡፡
♧ ብዙ ሰዓት የሚቀመጡ ሰዎች በመታጠፍ ምክንያት ሳንባቸው እና የአከርካሪ አጥንታቸው ጉዳት እንደሚደርስበት ገልጸው፤ ከጀርባ የሚገኙ ነርቮች በሚደርስባቸው ጉዳት የነርቭ ስርዓቱ በትክክል ስለማይካሄድ ሕመም እንደሚያስከትል አብራርተዋል።
♧ ብዙ ሰዎች ከ7 ሰዓታት በላይ እንደሚቀመጡ ጠቅሰው፤ በአንድ ቦታላይ ከ 45 ደቂቃ በላይ መቀመጥ እንደማይገባ እና ቢንስ ለ2 ደቂቃ እረፍት ማድረግ እንደሚስፈልግ ተናግረዋል፡፡
♧ በመቀመጥ ምክንያት የስኳር፣ የደም ግፊት፣ የልብ ሕመም እንዲሁም የድብርት በሽታዎች እንደሚከሰቱም ዶ/ር ሰላም ገልጸዋል፡፡
♧ ተማሪዎች ከአቅማቸው በላይ በጀርባቸው የሚሸከሙት ቦርሳም ጉዳት ጉዳት እንደሚመጣ ገልጸው፤ ወላጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል፡፡
♧ በቸልተኝነት ሕመሙ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ሕክምና ማግኘት እንደሚገባ የአከርካሪ አጥንት ሕክምና ስፔሻሊስቷ ዶ/ር ሰላም ይናገራሉ።
♧ ያደጉ ሀገራትን ኢኮኖሚ እየጎዳ ያለው እና ለታዳጊ ሀገራትም ስጋት የሆነውን ይህን የጀርባ (የአጥንት አከርካሪ) ሕመምን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ጥቅምት 16 የአከርካሪ አጥንት ቀን ይከበራል፡፡
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#ክፉውን_ያርቀውና_ድንገት_የመሬት_መንቀጥቀጥ_ቢከሰት_ምን_ያደርጋሉ
♧ ከአስፈሪ የተፈጥሮ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ርዕደ መሬት ነው፡፡ በእርግጥ በመሬት ከመከዳት በላይ ምን ሊያስፈራ ይችላል፡፡
♧ ዓለማችን በርዕደ መሬት መለኪያ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦችን በየጊዜው ታስተናግዳለች፡፡
♧ በእኛም ሀገር ባሳለፍነው ሳምንት እሑድ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ አካባቢ፣ በዛሬው ዕለትም ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ገደማ በአዋሽ ፈንታሌ መካከለኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል፡፡
♧ የተከሰቱት ርዕደ መሬቶች ንዝረታቸው እስከ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱ ለመሰል ክስተቶች እንግዳ የሆነውን ህዝብ ያስደነገጠውም ይመስላል፡፡
♧ ምንም እንኳን በስምጥ ሸለቆ እና አካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ንዝረት የተለመደ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ቢናገሩም ፤ ክፉውን ያርቀው እንጂ አደጋው ቢያጋጥም ምን ማድረግ ይኖርብናል የሚሉ ጥያቄዎች ከብዙዎች ተነስተዋል፡፡
♧ የመሬት መንቀጥቀጥ ባለንበት ሥፍራ ቢከሰት ድንጋጤን ውጦ እኚህን ነገሮች ለማድረግ መሞከር የራስንም ሆነ የወዳጅን ህይወት ለመታደግ ያግዛል፡፡
♧ የመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ የሚሰጥ አደጋ ባለመሆኑ እራስን ለማዳን ከቦታ ቦታ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ባሉበት ቦታ ከታች ያሉትን የአደጋ መከላከያ ነጥቦች ይተግብሩ፡፡
♧ የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተሰማዎ አንገትዎን በሁለት እጅዎ አጥብቀው በመያዝ በጉልበትዎ ይንበርከኩ
♧ በቀላሉ የማይንቀሳቀሱ ጠንካራ ነገሮችን አጥብቀው ይያዙ
♧ እንደ ጠረጴዛ ያሉ ከላይ መከለያ ያላቸው ዕቃዎች ሥር መግባት በሚወድቅ ዕቃ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ይቀንሳል፡፡
♧ የሚይዙት ዕቃ እንዳይንቀሳቀስ ከጠንካራ ነገር ጋር በደምብ ያስጠጉት (ለምሳሌ ከቤት ምሰሶ ጋር)
♧ እንደ መስታውት ያሉ በቀላሉ ረግፈው ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ነገሮች ይራቁ
♧ ቤት ውስጥ ከሆኑ ሲሊንደር ጋዝ፣ የተለኮሰ ሻማ አሊያም ሌላ እሳት ሊፈጥር የሚችል ነገር ካለ ያጥፉ
♧ አሳንሰር ከመጠቀም ይቆጠቡ
♧ ወጪ ከሆኑ ኤሌክትሪክ የተሸከሙ ፖሎች፣ ዛፎች አሊያም ሌሎች የተተከሉ ነገሮች እንዳይወድቁብዎ መራቅ እና በተቻለ መጠን ሜዳማ በሆነ ግልጽ ቦታ ላይ መገኘት እራስን ከአደጋው ለመጠበቅ ያግዛሉ፡፡
©ebc
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#አስገራሚ_እውነታዎች_ስለ_ፅንስ_እና_እርግዝና
♧ ፅንስ በማህፀን ውስጥ እያለ ያለቅሳል፤ ፅንሱ ከሚለማመዳቸው ነገሮች ማለትም ከፊት እና ከአፍ እንቅስቃሴ ቀጥሎ አንዱ ማልቀስ ስለሆነ ነው፤ ሆኖም ግን የሽርት ውኃ ውስጥ ባሉ የቅባት እና የጡንቻ ፈሳሾች ምክንያት ድምፁን መስማት አይቻልም፡፡
♧ ፅንስ ከሰባተኛው ወር ጀምሮ ማሽተት የሚችል ሲሆን በተለይ መጥፎ ሽታን የመለየት አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡
♧ ከ18ኛው ሳምንት ጀምሮ ድምፅ መስማት የሚችሉ ሲሆን፤ ከተወለዱ በኋላ የእናታቸውን እና በተደጋጋሚ የሰሙትን ሰው ድምፅ በፍጥነት መለየት ይችላሉ፡፡
♧ ፅንስ በማህፀን ውስጥ በሚተኛበት ወቅት ህልም ሊያይ ይችላል፤ ህልሙም በማህፀን ውስጥ ስለሚያውቃቸው ነገሮች ነው፡፡
♧ ጨቅላ ህፃናት በተወለዱ ከ1 እስከ 2 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይፀዳዳሉ፤ ሆኖም ግን በማህፀን ውስጥ ሊፀዳዱም ይችላሉ፤ ይህም በተፈጥሮ እና የመውለጃ ግዜ በማለፍ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን የመፈጠር እድሉም እስከ 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡
♧ ቁመቷ 1.65 ሜትር እና ከዚያ በላይ የሆነች ሴት መንታ የመፀነስ እድሏ ከፍተኛ ነው፤ይህም ረዘም ያሉ ሴቶች ከጉበት የሚያገኙት የፕሮቲን መጠን ከፍ ያለ በመሆኑ የሚመረተውን ዕንቁላል መጠን ለመጨመር አስተዋፆ ስለሚያደርግ ነው፡፡
♧ የእርግዝና ጊዜ ከ 9ወር ሊበልጥ ይችላል፤ እስካሁን የተመዘገበው ትልቁ የእርግዝና ግዜ 1 ዓመት ከ15 ቀን ነው፡፡
♧ ነፍሰ ጡር ሴት የምትመገባቸውን ምግቦች ጣዕም ፅንሱ ከ16ኛው ሳምንት ጀምሮ መለየት ይችላል፤ በተለይ የማቃጠል ይዘት ያላቸውን ምግቦች የሚለይ ሲሆን ሲወለድ አዘውትራ የተመገበችውን ምግብም ይወዳል፡፡
♧ ከተመገበችም በኋላ የተጣራው ምግብ በቅድሚያ ለፅንሱ ነው የሚደርሰው፡፡
♧ እርግዝናው በሚያመርታቸው ሆርሞኖች ምክንያት የማይበሉ ነገሮችን መመገብ እንድትፈልግ ያደርጋታል፤ለምሳሌ ቀይ አፈር፣ አሸዋ፣ አመድ እና ሌሎችም
♧ በእርግዝና ወቅት የማቃር እና የማቃጠል ስሜት ካለ በዚያ ሳቢያ የሚመረቱ ሆርሞኖች የሚወለደው ልጅ ፀጉር ብዛት እና ወፍራም ዘለላ ያለው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
♧ ነፍሰ ጡር ሴት የኦክስጅን መጠኗን ከፅንሱ ጋር በመጋራቷ ምክንያት ወደ ጭንቅላቷ የሚሄደው የኦክስጅን መጠን ይቀንሳል፤ ይህም ለከፍተኛ የመርሳት ዕክል ያጋልጣታል።
♧ አንዲት ሴት በእርግዝናዋ ወቅት ሰውነቷ ተጨማሪ ደም ያስፈልገዋል፤በዚህም የደም መጠኗ ከ40 እስከ 50 በመቶ ይጨምራል፡፡
♧ የደም መጠኗ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ የልብ መጠኗ 50 በመቶ በመሆን ከፍ ይላል፡፡
♧ የጫማ ቁጥሯ እስከ አንድ ደረጃ ድረስ ያድጋል፡፡
♧ በተለየ መልኩ ሽታን የመለየት አቅሟ ይጨምራል፡፡
♧ በእርግዝና ወቅት የሚመረተው ፕሮጀስትሮን የተባለ ሆርሞን የድካም፣ የእንቅልፍ እና የአቅም ማነስ ስሜቶችን የሚያሳድርባት ሲሆን፤ይህም ከበድ ባሉ እንቅስቃሴዎች ልጁን እንዳትጫነው ይጠቅማል፡፡
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#ሊጎበኟቸው_የሚገቡ_ምርጥ_ሀገራት
♧ 🇹🇭🇮🇩 ታይላንድ በ2024 በህይወት ዘመን ሊጎበኟቸው የሚገቡ ምርጥ ሀገራት በአለም 1ኛ እና ኢንዶኔዥያ ቁጥር 3 ተብላለች።
♧ የCEOWORLD መጽሔት ድህረ ገጽ ከ295,000 በላይ አንባቢዎችን አስተያየት መሰረት በማድረግ በ2024 በብዛት የተጎበኙ ሀገራትን ደረጃ ሰጥቷል፣ይህም በመጽሔቱ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛው ተሳትፎ ነው።
♧ ታይላንድ በ72.15 ነጥብ ከአለም 67 ሀገራት 1ኛ ስትሆን ግሪክ በ67.22 ነጥብ ሁለተኛ ስትሆን ኢንዶኔዢያ 65.15 በማስመዝገብ 3ኛ ደረጃን ይዛለች።
♧ CEOWORLD መጽሄት ታይላንድ እንደ የምሽት ህይወት ቦታዎች፣ ጣፋጭ ምግቦች፣ ጥበባት እና ባህል፣ ምርጥ የገበያ ቦታዎች፣ የሚያማምሩ ጠመዝማዛ ቦዮች፣ ቤተመቅደሶች እና የምሽት ገበያዎች ባሉ ልዩነቶች የተሞላች መሆኗን ጠቅሷል።
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#የበዓል_ጥያቄዎችን_በሙሉ_የመለሱ_ተሸላሚዎች
1. ያሬድ አጥላው 8:29
2. ኢብሳ ሳዲቅ 8:47
3. አምዱ በርጋ 8:49
4. ጫላ ኢብሳ 8:50
5. ያሲን አባድር 9:13
6. ጂኔ ኑስ 9:13
✍የአዲስ ዓመት ጥያቄዎችን በመመለስ አሸንፈዋል እንኳን ደስ ያላችሁ👏👏
✍በውድድሩ ላይ #34ሰዎች ተሳትፈዋል።
➹ይመልሱ፤ይሸለሙ፤ይሸልሙ
👇🏾👇🏾👇🏾
☄ @ewentesfa
7 291
#የአዲስ_ዓመት_አሸላሚ_ጥያቄ_መልሶች
➊ የመጀመሪያዋና ጥንታዊ ነጻ አፍሪካዊ ሐገር ማነች?
☞ኢትዮጵያ 🇪🇹
➋ ብዙ ቅርሶችን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ በማስመዝገብ ቀዳሚ አፍሪካዊ ሐገር ማነች?
☞ኢትዮጵያ 🇪🇹
➌ በዓለም ላይ አብዝሀኛው ክፍሏ በደን የተሸፈነች ሐገር ማነች?
☞ሩሲያ 🇷🇺
➍ በኦሎምፒክ ወርቅ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሐገር ማነች?
☞ኢትዮጵያ 🇪🇹
➎ የአለማችን ረጅሙ ወንዝ መነሻው ሐገር ማነች?
☞ኢትዮጵያ 🇪🇹
➏ በዓለም ላይ በጣም የምትጎበኝ ቀዳሚ ሐገር ማነች?
☞ፈረንሳይ 🇫🇷
ጉርሻ:
➐ አዲስ ዐመትን ዘግይታ የምትቀበል ሐገር ማነች?
☞አሜሪካን ሳሞዐ 🇦🇸
🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌼
🗣➹ #ይመልሱ_ይሸለሙ!
@ewentesfa
7 291
#የአዲስ_ዓመት_አሸላሚ_ጥያቄዎች
➊ የመጀመሪያዋና ጥንታዊ ነጻ አፍሪካዊ ሐገር ማነች?
➋ ብዙ ቅርሶችን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ በማስመዝገብ ቀዳሚ አፍሪካዊ ሐገር ማነች?
➌ በዓለም ላይ አብዝሀኛው ክፍሏ በደን የተሸፈነች ሐገር ማነች?
➍ በኦሎምፒክ ወርቅ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሐገር ማነች?
➎ የአለማችን ረጅሙ ወንዝ መነሻው ሐገር ማነች?
➏ በዓለም ላይ በጣም የምትጎበኝ ቀዳሚ ሐገር ማነች?
ጉርሻ፡
➐ አዲስ ዐመትን ዘግይታ የምትቀበል ሐገር ማነች?
🚫 መልሳችሁን ስትልኩልን ሙሉ ስማችሁን እንዳትረሱ፤መልሱን እስከ ነገ ማታ2 ሰዐት (01/01/2017ዓ.ም) ድረስ ብቻ አድርሱን!
⭕️ መልሳችሁን @Bochemelaku ላይ ላኩልን!
✍ማስታወሻ፡
• መልሱን አንዴ ከላኩ በኋላ ማሥተካከል ከውድድሩ ውጪ ያደርጋል።
• ቀድመው ለሚመልሱ #አምሥት ተሳታፊዎች የ2⃣5⃣ ብር ካርድ ይደርሳቸዋል፡፡
🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌼
🗣➹ #ይመልሱ_ይሸለሙ!
@ewentesfa
7 291
ልዩ የአዲስ አመት(እንቁጣጣሽ) ጥያቄና መልስ ውድድር
📆 ቀን፡ ማክሰኞ ጷጉሜ 5 2016 ዓ.ም ምሽት 2 ሰዓት
☞ ለተጨማሪ 50 ሰዎች👨🦳👨🦳 ይህንን መልዕክት ሲያጋሩ ተጨማሪ 40 MB🎁
♣ ውድድሩን ለመደገፍ @Bochemelaku ላይ ያነጋግሩን፡፡
🗣➹#ይመልሱ_ይሸለሙ
🗣➹#መፅሐፍትን_ያውርዱ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?
♧ ብዙዎቻችን ውሀን የመጠጣት ባህላችን በጣም ዝቅ ያለ ነው። ይህ ልምድ ደሞ ብዙ መዘዝን ይዞብን ምጣቱ አይቀሬ ነው።
♧ አንድ ወንድማችን "ኩላሊቴ በጠጠር ምክንያት ፈሳሽን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ አልቻለም እና ሀኪሞቹ አሁን መውጣት አይችልም ፣ ገና ነው የሚል መልስ ነው የሰጡኝ ፣ እና ለምንድን ነው" የሚል ጥያቄ አንስቶልኝ ነበር።
♧ የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው ጊዜ 80% በውስጡ ካልሺየም ኦግዛሌት (calcium oxalete) የተቀሩት ደግሞ ከካልሺየም ፍስፌት (calcium phosphate) ፣ ዩሪክ አሲድ (uric acid) ፣ ሲስቲን (cystine) ሊሰሩ ይችላሉ።
♧ የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው በአንድ ኩላሊት በኩል ይታያል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሁለቱም ኩላሊት ሊኖር ይችላል።
ለኩላሊት ጠጠር የሚያጋልጡን ነገሮችስ?
♧ ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ እድላችን የሚወሰነው ሽንት በተሰራበት (composition) ለምሳሌ በካልሼየም ኦግዛሌት የተሰራ ጠጠር ከሆነ በሽንት ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛ መጠን ካልሺየም እና ኦግዛሌት ሲኖር እንዲሁም ዝቅተኛ ካልሽየም እና ፖታሺየም መውሰድ እና ፈሳሽ ነገር ያላቸው ምግቦች አለማዘውተር እንዲሁም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከስኳር የተሰሩ ጣፋጭ መጠጦች ተጋላጭነተን ይጨምረዋል ተብሎ ይታሰባል።
♧ ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች ለምሳሌ አንድ ሰው ከዚህ በፊት የኩላሊት ጠጠር ከነበረበት ድጋሚ የመመለስ እድል ሊኖረው ይችላል።
♧ ከዚህ በተጨማሪ በዘር (በቤተሰብ) ወስጥ ጠጠር ያለበት ካለ ፣ በተደጋጋሚ የላይኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተጠቂ መሆን ፣ መድሀኒቶች ለምሳሌ Idinavir, Acyclovir, Sulfadiazine፣ መድሀኒቶችን ከሚገባው መጠን በላይ መውሰድ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ከመጠን በላይ በፕሮቲን እና Vitamin C የበለፀጉ ምግቦች መመገብ ፣ ከከመጠን በላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ለምሳሌ የማራቶን ሯጮች ፣ ደም ግፊት ፣ ስኳር ፣ ሪህ ችግር ያለባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
ምልክቶቹስ?
♧ በአብዛኛው ከ20-60 ደቂቃ ሄድ መጣ የሚል ህመም በጎናችን አካባቢ ሊሰማን ይችላል። ህመሙ በጣም ሀይለኛ ውጋት ፣ ቁርጠት ስለሆነ ህመምተኛው የመንቆራጠጥ ነገር ሊያሳይ ይችላል።
♧ አንዳንዴም ህመሙ እስከ ሽንት ፌኛ አካባቢ ሊደርስ ይችላል። ይህም አንደ ጠጠሩ ያለበት ቦታ ይወሰናል። ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም ወደቀይነት (ደም) መቀላቀል ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ሽንት ማጥ ፣ ሽንት ማጣደፍ ሊኖር ይችላል።
ምርምራዎቹስ?
◇ ከላይ የጠቀስኳቸውን ምልክቶች በምናይበት ግዜ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብናል። የጤና ባለሙያውም እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ምርመራዎችን ለምሳሌ የሽንት ምርመራ ፣ የሆድ አልትራሳውንድ ፣ የሆድ x ray ፣ የሆድ ሲቲ ስካን ፣ ሊያዝልን ይችላል
♧ ነፍሰ ጡር እናት ላይ ምርመራዎችን ስናዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ከx-ray ፣ እና ሲቲ ስካን የሚወጣው ጨረር በተለይ ፅንሱን ሊጎዳው ስለሚችል ነው። ስለዚህ በዚህ ጊዜ አልትራሳውንድ ተመራጭ ይሆናል።
የሚያመጣውስ ችግር?
◇ የኩላሊት ጠጠር ካልታከመ ለኢንፌክሽን ፣ ደጋሚ ተመልሶ የመምጣት ችግር (recurrence) ፣ የሽንት ቱቦ መዘጋት ፣ ኩላሊትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እስከማድረስ ሊደርስ ይችላል።
ህክምናውስ?
◇ አመጋገባችንን ማስተካከል
◇ ጠጠሩን ያመጣብን ችግር ከታወቀ ማከም
◇ የህመም ስሜት ላላቸው ታካሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ የህመም ማስታገሻ ሊሰጥ ይችላል።
◇ ማንኛውም የኩላሊት ጠጠር በቀዶ ጥገና ይወጣል ማለት አይደለም። ይህም የሚወሰነው እነደ ጠጠሩ መጠን ሲሆን የጠጠሩ መጠን እስከ 10 ሚሊ ሜትር ከሆነ በሽንት እንዲወጣ ነው የሚመከረው። በዚህ ጊዜ ታካሚው ዉሀ በብዛት እንዲጠጣ ይመከራል መጠናቸው ከ10 ሚሊሜትር በላይ ከሆነ የመውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ሊጠበቅን ይችላል።
♧ ለምሳሌ በድምፅ እና በጨረር በመታገዝ ጠጠሩ እንዲሰባበር በማድረግ ከዛም ውሀ በመጠጠት በሽንት እንዲወጣ ይደረጋል አንዳንድ ጊዜም በቀዶ ጥገና መውጣት ሊያስፈልግ ይችላል።
♧ የህክምና አማራጮቹ የሚወሰኑት በባለሙያው ስለሆነ ከባለሙያ የሚሰጡንን ምክሮች ማክበር ተገቢ ነው።
ማስታወሻ: ንፁህ ውሀ በብዛት መጠጣት ተነገሮ ከማያልቁት ጥቅሞች አነዱ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ባሉበት ተቀምጠው ጉዳት እንዳያስከትሉ እና ለማስወገድ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ ውሀ የመጠጣት ልምዳችንን ብናዳብር መልካም ነው።
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#ቀነኒ_ኬኛ
ሰውየው ጀግና ብቻ አይደለም ተዐምረኛ ነው ‼️
🇪🇹 36 ጊዜ ሀገር ወክሎ በመሳተፍ የኢትዮጵያ ባለ ሪከርድ ነው።
🇪🇹 36 ጊዜ ሀገር ወክሎ 24 ወርቅ ለሀገሩ አምጥቷል - ይህም ሪከርድ ነው።
🇪🇹 አራት ኦሎምፒክ ተሳትፏል። አብዛኛውን በድል አጠናቋል‼️
🇪🇹 በ42 አመቱ ኦሎምፒክ በመወዳደሩም ሪከርድ ይዟል
🇪🇹 ከቀነኒሳ ቀጥሎ ለሀገር በመሰለፍ
🇪🇹 ቀነኒሳ በቀለ በ25 አመት የሩጫ ዘመኑ 173 ኢንተርናሽናል ውድድሮችን አድርጓል።
➢ 5000 ሜትርን 56 ጊዜ ሮጧል።
➢ 3000 ሜትርን 37 ጊዜ ሮጧል።
➢ ሀገር አቋራጭ 21 ጊዜ በተለያየ ርቀት
➢ 10000 ሜትርን 19 ጊዜ ሮጧል።
➢ ማራትን 13 ጊዜ ሮጧል።
➢ 10 ኪ ሜ ጎዳና 6 ጊዜ ሮጧል።
➢ 2000 ሜትር 5 ጊዜ ሮጧል።
➢ 1500 ሜትር 4 ጊዜ ሮጧል።
➢ 2 ማይል 4 ጊዜ ሮጧል።
➢15 ኪሎ ሜትር ጎዳና 3 ጊዜ ሮጧል።
➢ ግማሽ ማራቶን 2 ጊዜ ሮጧል።
➢ አንድ ማይልን 10 ማይልን እና 25 ኪሎ ሜትርን አንድ አንድ ጊዜ ሮጧቸዋል።
🇪🇹 ቀነኒሳ ካደረጋቸው ከ173 ውድድሮች ውስጥ
➢ 110 ውድድሮችን - ❶ኛ
➢ 21 ውድድሮችን - ❷ኛ
➢ 6 ውድድሮችን - ❸ኛ ሆኖ ጨርሷል።
ከ173 ውድድሮች ውስጥ 137 ውድድሮችን ሜዳሊያዎች ማለት ነው።
🇪🇹 36 ጊዜ ሀገሩን ወክሎ ያገኛቸው ድሎች
🥇 24 ወርቅ 🙏 👌
🥈 5 ብር 🙏 👌
🥉 1 ነሀስ 🙏 👌
➢ ❹ኛ ደረጃ በማግኘት ሁለት ዲፕሎማ
➢ ❶ ውድድር ❾ኛ ደረጃ በ1999
➢ ❷ ውድድሮችን አቋርጧል።
🇪🇹 ሜዳሊያዎቹ ሲዘረዘሩ
📌 በኦሎምፒክ
🥇 ❸ ወርቅ
🥈 ❶ ብር
👉 ❶ ዲፕሎማ ❹ኛ ደረጃ አግኝቶ
📌 በአለም አትሌትክስ ሻንፒዮና
🥇 ❺ ወርቅ
🥉 ❶ ነሀስ
📌 በአለም ሀገር አቋራጭ
🥇⓭ ወርቅ
🥈 ❶ ብር
📌 ወጣቶች ሻንፒዮና
🥈❷ ብር
📌 ኮንትኔታል
🥈 ❶ ብር
📌 በአፍሪካ ሻንፒዮና
🥇 ❸ ወርቅ
👉 ❶ ዲፕሎማ ❹ኛ ደረጃ አግኝቷል።
🇪🇹 ቀነኒሳ የምንጊዜም ጀግናችን ነው‼️
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#በዓለም_ላይ_ለቱሪስቶች_10_በጣም_አደገኛ_ከተሞች
♧ ለቱሪስቶች በጣም እና አነስተኛ ተጋላጭ ከተሞችን ለመወሰን በሰባት ቁልፍ መለኪያዎች ላይ በመመርኮዝ 60 ዓለም አቀፍ ከተሞችን ገምግሟል።
➊ ካራካስ፣ ቬንዙዌላ 🇻🇪
➋ ካራቺ፣ ፓኪስታን 🇵🇰
➌ ያንጎን፣ ቡርማ 🇲🇲
➍ ሌጎስ፣ ናይጄሪያ 🇳🇬
➎ ማኒላ፣ ፊሊፒንስ 🇵🇭
➏ ዳካ፣ ባንግላዴሽ 🇧🇩
➐ ቦጎታ፣ ኮሎምቢያ 🇨🇴
➑ ካይሮ፣ ግብፅ 🇪🇬
➒ ሜክሲኮ ሲቲ፣ ሜክሲኮ 🇲🇽
➓ ኮይቶ፣ ኢኳዶር 🇪🇨
© ፎርብስ አድቫይዘር
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#ለጥንቃቄ
#አልማዝ_ባለጭራ(AC MILAN)
♧ በክረምት ወቅት በብዛት የምትገኘውና ብዞቻችን ግንዛቤ የሌለን በአካባቢያችን የሚገኙ እጅግ ብዙ ዓይነት ነፍሳት አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም በተለምዶ ‹አልማዝ ባለጭራ› ተብላ የምትታወቀው ነፍሳት ትገኝበታለች፡፡
ለመሆኑ አልማዝ ባለጭራ ምንድር ናት? መገለጫዎቿስ ምንድር ናቸው ? እንዴት ልንለያት እና ራሳችንን ልንጠብቅስ እንችላለን?
♧ አልማዝ ባለጭራ በሳይንሳዊ ስሟ ፔይደሪኔ (Paederinae) በመባል ትታወቃለች፡፡ በቅጽል ስሟ ደግሞ ቶምካት (Tomcat) ይሏታል፡፡ ይህቺ ነፍሳት ከጉንዳን ጋር ከፍተኛ ተመሳሳይነት ያላት ሲሆን፤ መለያዋ ቀይ ክፍሎች በሰውነቷ ላይ መኖራቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ከተራ ጉንዳን በተለየ መልኩ ክንፍ አላት፤ ትበራለችም፡፡ የአልማዝ ባለጭራ አትናከስም፤ አትናደፍም፡፡ ሆኖም ግን በቆዳዋ ላይ እና በደሟ ውስጥ እጅግ መርዛማ የሆነ እና ፔደሪን የተባለ ንጥረ ነገር አላት፡፡ ይህ ፔደሪን የተባለ ንጥረ ነገር እጅግ መርዛማ ከመሆኑ የተነሳ ኮብራ በመባል ከሚታወቀው አደገኛ የእባብ ዝርያ መርዝ ጋር ሲነጻጸር በአሥራ ሁለት እጥፍ አደገኛ ነው፡፡
♧ አልማዝ ባለጭራ ባትናከስም ስንኳ ከቆዳችን ጋር ከተጋጨች፣ ከደፈጠጥናት፣ ከመታናት ወይንም በተለያየ መንገድ ከጨፈለቅናት በቆዳና በደሟ ያለው ፔደሪን የተባለው ንጥረ ነገር በቆዳችን ላይ ያርፋል፡፡ ይህ በቆዳዋ ላይ የሚገኝ መርዝ በልብሶች ላይ ካረፈና ቆዳችን ከልብሶቹ ጋር ንክኪ ከፈጠረም ልንመረዝ እንችላለን፡፡ ይህ ንጥረ-ነገር ወዲያው ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ከነካን ከአሥራ ሁለት ሰዓት እስከ ሠላሳ ስድስት ሰዓት ባለ ጊዜ ውስጥ ቆዳችን ሽፍ ማለት ይጀምራል፡፡ ቀስ በቀስም ሽፍታው ውሃ ይቋጥራል፤ ከፍተኛ ሕመምንም ይፈጥራል፡፡ ሕክምናን ካላገኘን በሕመም ሊያሰቃየን እና የማይድን ጠባሳን ቆዳችን ላይ ሊተው ይችላል፡፡
ይህቺ አልማዝ ባለጭራ እንዲህ መርዛማ ከሆነች በምን መንገድ እንከላከላት?
♧ የመጀመሪያው መንገድ ስንተኛ መስኮት ዘግተን መተኛት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በምሽት መብራት አብርቶ የመተኛት ልምድ ካለን ይህንን ማቆም አለብን፡፡ የዚህም ምክንያት አልማዝ ባለጭራ በጨለማ ውስጥ በሚታይ ብርሃን ስለምትሳብ ነው፡፡ በመቀጠል ደግሞ በአንድ አካባቢ ላይ ካየናት ከመርገጥ፣ ከመደፍጠጥ ወይም በማንኛውም መንገድ ከመንካት መቆጠብ አለብን፡፡ ለማስወገድ ከፈለግንም በትንፋሽ እፍ በማለት፣ በእንጨት ወይም በሌላ ግዑዝ ነገር ተጠቅመን በከፍተኛ ጥንቃቄ ወደ ውጪ አውጥቶ መጣል ይገባል፡፡ ልብሳችንን ከነካችም ሳይታጠብ ማድረግ የለብንም፡፡ ሆኖም ግን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከነካችን ወይም በቆዳችን ላይ ከተደፈጠጠች የመጀመሪያ እርምጃችን በፍጥነት በውሃና በሳሙና ሙልጭ አድርገን መታጠብ መሆን አለበት፡፡ በመቀጠልም በቀጥታ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት አለብን፡፡
♧ ከመርዙ ጋር በሚኖር ንክኪ ምክንያት ቆዳችን ቆስሎ ሕክምናውን እየተከታተልን ከሆነም እስኪድን ድረስ በፍጹም ቁስሉን ለፀሐይ ማጋለጥ የለብንም፤ የማይድን ጠባሳ እንዲፈጥር ልናደርግ እንችላለንና፡፡
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#የ21ኛው_ክፍለ_ዘመን_የአፍሪካ_ምርጥ_አስር_አትሌቶች
➊ ቀነኒሳ በቀለ፣ የረዥም ርቀት ሯጫ 🇪🇹
➋ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ፣የረዥም ርቀት ሯጫ 🇰🇪
➌ ሳሙኤል ኤቶ፣ እግር ኳስ 🇨🇲
➍ ክርስቲ ኮቨንትሪ፣ ዋና 🇿🇼
➎ ጥሩነሽ ዲባባ፣ የረጅም ርቀት ሩጫ 🇪🇹
➏ ዲዲየር ድሮግባ፣ እግር ኳስ 🇨🇮
➐ ፌዝ ኪፕዬጎን፣ የረጅም ርቀት ሩጫ 🇰🇪
➑ ዣክ ካሊስ፣ ክሪኬት 🇿🇦
➒ አሲስታ ኦሿላ፣ እግር ኳስ 🇳🇬
➓ ሞሃመድ ሳላህ፣ እግር ኳስ 🇪🇬
©ESPN
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#ሰባት_የማዲያት_ማጥፊያ_ተፈጥሮአዊ_መንገዶች
♧ ማዲያት በተለያዩ ምክንያቶች በፊታችን ላይ ሊከሰት ይችላል። ከምክንያቶች መካከል ለብርቱ የፀሀይ ብርሀን መጋለጥ፣የሆርሞን መለዋወጥ፣ የፊት ቅባት፣ የወሊድ መከላከያ፣ የተለያዩ የፊት መዋቢያዎች ከፍተኛ ሙቀት ወዘተ ይገኙበታል።
♧ በመሆኑም ተፈጥሮአዊ መላዎችን ማወቅና መጠቀም ተገቢ ይሆናል። ከዚህ በመቀጠል በተፈጥሮ ከሚገኙ ነገሮች እንዴት ማድያትን 0ማጥፋት እንደምንችል እንመለከታለን።
➊ የሎሚ ጭማቂ
♧ ሎሚ ማድያትን ለማጥፋት ምርጡ መንገድ ነው፡፡ የሎሚን ጭማቂ ፊትን ቀብቶ ለ2 ደቂቃ ማሸት ለትንሽ ለ20 ደቂቃ ካቆዩ በኋላ መታጠብ
♧ የሎሚ ጭማቂ እና ማርን በእኩል መጠን መቀላቀል እና ፊትን መቀባት ከዛም በሞቀ ፎጣ ለ 15 ደቂቃ ሸፍኖ ማቆየትና መታጠብ የሎሚን ጭማቂ ከእርድ ዱቄት ጋር በመደባለቅ መቀባት ጥሩ ውጤት ሊሰጥ ይችላል፡፡
➋ አጃ
♧ የተፈጨውን የአጃ ዱቄት ከማር ጋር መለወስ ከዛም በማድያቱ ላይ መቀባት እና ለግማሽ ሰአት አቆይቶ በሙቅ ውሀ መታጠብ፡፡ የሞቱትን ሴሎች ከቆዳችን ላይ ያነሳልናል፡፡
➌ የፖም ኮምጣጤ
♧ አንድ ማንኪያ የፖም ኮምጣጤ ከ አንድ ማንኪያ ውሀ ጋር በመደባለቅ በየቀኑ መቀባት
➍ እርድ
♧ አንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ እርድ ከ 2-3 የሻይ ማንኪያ ወተት ጋር በመደባልቅ ማዋሀድ እና 1 የሻይ ማንኪያ የባቄላ ወይም የሽንብራ ዱቄት ጋር ደባልቆ መቀባት ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ ይህን ውህድ በየቀኑ መቀባት ማዲያቱ እስኪጠፋ መቀባት
➎ የሽንኩርት ጭማቂ
♧ ከ 2-3 የሚሆኑ ሽንኩርትን በመፍጨት ወይም በመቀጥቀጥ የሽንኩርቱም ውሀ በጥጥ መቀባት እና ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሀ መታጥብ በየቀኑ ለተወሰኑ ሳምንታት መቀባት ይመከራል።
➏ እሬት
♧ አንድ የእሬት ቅጠል በመውሰድ እንደጄል ያለውን ፈሳሽ ተቀብቶ ለ 2 ደቂቃ ማሸት ከ 15-20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ ይህን ውህድ በየቀኑ መቀባት ማዲያቱ እስኪጠፋ
➐ ፓፓያ
♧ ግማሽ የሻይ ሲኒ የበሰለ ፓፓያ መፍጨት ከ 2 ማንኪያ ማር ጋር ደባልቆ መቀባት ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ።
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#በአፍሪካ_ውስጥ_ያሉ_10_ትላልቅ_የገበያ_ማዕከሎች(ሞሎች)
➊ ሞሮኮ የገበያ ማዕከል, ሞሮኮ 🇲🇦
➋ ቱ ሪቨርስ ሞል, ኬንያ 🇰🇪
➌ ሞል ኦፍ አፍሪካ, ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦
➍ ሞል ኦፍ አረቢያ, ግብፅ 🇪🇬
➎ ሣንድተን ሲቲ, ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦
➏ ጌትዌይ ቲያትር, ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦
➐ ካናል ዎክ, ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦
➑ ደምበል ሲቲ ሴንተር, ኢትዮጵያ 🇪🇹
➒ ኖቫር ለኪ ሞል, ናይጄሪያ 🇳🇬
➓ ጌም ሲቲ ሞል፣ ቦትስዋና 🇧🇼
📷 ደምበል ሲቲ ሴንተር, ኢትዮጵያ 🇪🇹
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
Airplane Control Surfaces:
Ailerons✈️
- Purpose: Control roll.
- Location: Outer edges of the wings.
- Function: Move in opposite directions to tilt the plane's wings.
Rudder✈️
- Purpose: Control yaw.
- Location: Vertical stabilizer (tail fin).
- Function: Moves left or right to steer the plane left or right.
Elevators✈️
- Purpose: Control pitch.
- Location: Horizontal stabilizer (tailplane).
- Function: Move up or down to make the nose of the plane go up or down.
Spoilers✈️
- Purpose: Reduce lift and increase drag.
- Location: Top surface of the wings.
- Function: Deploy upwards to disrupt airflow over the wing.
Flaps✈️
- Purpose: Increase lift at lower speeds.
- Location: Trailing edge of the wings.
- Function: Extend downwards to increase wing area and curvature.
Slats✈️
- Purpose: Increase lift at lower speeds.
- Location: Leading edge of the wings.
- Function: Extend forward to smooth airflow over the wing at high angles of attack.
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
7 291
#የጡት_ካንሰር
♧ የካንሰር በሽታ ዝምተኛ ገዳይ የሚባል በሽታ ነው። በሽታው በጊዜ ከተደረሰበት የመዳን ዕድል ያለው ቢሆንም፣ በጊዜ ካልታወቀ የመዳን ዕድሉ እየቀነሰ ይሄዳል።
♧ የተለያዩ የካንሰር በሽታ ዓይነተቶች ያሉ ሲሆን፣ ከነዚህም አንዱ የሆነው የጡት ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገራችን የብዙ እናቶችን ሞት እያፋጠኑ ካሉ በሽታዎች ተጠቃሹ ነው።
♧ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በ2020 ይፋ የሆነው መረጃ በኢትዮጵያ ከተከሰቱ ከ77 ሺህ በላይ የካንሰር ሕመሞች መካከል 50 ሺዎቹ በሴቶች ላይ የተከሰቱ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 16 ሺዎቹ የጡት ካንሰር መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።
♧ የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት አድገው እና ተከፋፍለው ዕጢ ሲፈጥሩ የሚከሰት ሕመም ነው።
♧ የማንኛውም ጤናማ ሰው ሴሎች በየጊዜው ያድጋሉ ይለዋወጣሉ። ይህ የሴሎች እድገት ጤናማ ባልሆነ መልኩ እየጨመረ ሲሄድ እብጠትን (ዕጢ) ያስከትላል። እነዚህ ጤናማ ያልሆኑ እብጠቶች በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰርነት ይለወጣሉ። የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በአብዛኛው ይከሰት እንጂ ወንዶች ላይም ይከሰታል።
♧ የጡት ካንሰር ምልክቶች በጡት ውስጥ ያሉ መጓጎሎች፣ እብጠቶች እና የጡት ቀለም መቀየርን ያካትታሉ። የጡት ካንሰር በጊዜ ከታወቀ የመዳን ዕድል ስላለው ሴቶች ሁሉ ቢያንስ በወር አንዴ ጡታቸውን መፈተሽ እንዳለባቸው የህክምና ባለሞያዎች ይመክራሉ።
ምልክቶ
◇ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከጡት መውጣት፣
◇ በጡት ላይ የሚከሰት እብጠት፣
◇ የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባት፣
◇ የጡት ቆዳ ወደ ውስጥ መሰርጎድ፣
◇ የጡት ቆዳ መሻከር፣
◇ የጡት ወይም የጡት ጫፍ ህመም፣
◇ የጡት ቆዳ ቀለም ወደ ቀይነት ማድላት ናቸው።
♧ እናቶች እነዚህን ምልቶች ካስተዋሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ እንዳለባቸው የሕክምና ባለሞያዎች ይመክራሉ።
የጡት ካንሰር በሽታ መንስኤዎች
◇ የዕድሜ መጨመር
◇ ከወለዱ በኋላ ጡት አለማጥባት
◇ የጡት ካንሰር ታሪክ ያለበት ቤተሰብ ካለ
◇ አልኮል መጠጣት እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ መንስኤዎቹ ናቸው።
♧ አንድ ሰው በጡት ካንሰር እንደተጠቃ ለማወቅ የህክምና ባለሙያዎች ከሚያደርጓቸው የምርመራ ሂደቶች ውስጥ የማሞግራፊ እና አልትራሳውንድ ምርመራዎች ተጠቃሾች ናቸው።
♧ የጡት ካንሰርን ለማከም የተለያዩ እርምጃዎች የሚወሰዱ ሲሆን፣ እነዚህ እርምጃዎችም ካንሰሩ እንደ ደረሰበት ደረጃ እና እንደህመምተኛው ሁኔታ ሊለያዩ ይችላሉ። በዚህ መሰረትም የቀዶ ጥገና፣ ኬሞቴራፒ፣ ሆርሞናዊ ቴራፒ እና ራዲዮቴራፒን የመሳሰሉ ክምናዎች ሊሰጡ ይችላሉ።
♧ የቀዶ ጥገና ህክምና ካንሰሩን ሙሉ በሙሉ ማውጣትን ወይም ሙሉ ጡትን መቆረጥን ሊያካትት ይችላል። ከዚያ በኋላ አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ ኬሞ እና ራዲዮቴራፒ ያስፈልጋቸዋል።
♧ ካንሰርን ለመከላከል በየጊዜው ምርመራ ማድረግ፣ ከወሊድ በኋላ ጡት ማጥባት አና የአልኮል መጠጥ መቀነስ የህክምና ባለሞያዎች የዘወትር ምክሮች ናቸው።
መልካም ጤንነት!!
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
