ch
Feedback
ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ

ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ 

前往频道在 Telegram

ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH

显示更多

📈 Telegram 频道 ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  的分析概览

频道 ᴛᴇᴄʜ🌍ᴢᴏɴᴇᴱᵗʰ  (@computer_android_tricks) 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 983 名订阅者,在 教育 类别中位列第 17 269,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 838 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 983 名订阅者。

根据 04 三月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -107,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 0%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 0 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡ 🕳Professional Hack Tips and tricks 💡Cracked Softwares 🌎 ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ YouTube channel https://youtube.com/c/MkTechZoneETH”

凭借高频更新(最新数据采集于 05 三月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 教育 类别中的关键影响点。

11 983
订阅者
无数据24 小时
-337 夊
-10730 夊
帖子存档
መጋቢት 21 ቀን 2012 ዓ.ም አሜሪካ የፀረ ወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል ፈቃድ ሰጠች። የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀዉ ሁለት የፀረ ወባ መድሃኒቶችን ለኮቪድ 19 መፈወሻ ይዉል ዘንድ የአገሪቱ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ፍቃድ እንደሰጠዉ ታዉቋል፡፡ የአሜሪካዉ የጤና እና የሰዉ ሃይል ዲፓርትመንት ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ክሎሮኪን እና ሃይድሮክሲክሎሮኪን የተሰኙት የጸረ ወባ መድሃኒቶች ለኮቪድ 19ን እንደሚፈዉሱ ተረጋግጧል ብሏል፡፡ ባለስልጣኑ እንዳለዉ ሁለቱ የመድሃኒት አይነቶች በህክምና ባለሙያዎች ለህመምተኞች እንዲታዘዙ እና በተለያዩ ሆስፒታሎች እንዲሰራጩ እየተደረገ ይገኛል ነዉ ያለዉ፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ ሳምንት እነዚህን ሁለት መድሃኒቶች ከፈጣሪ የተሰጡን ሲሉ መግለፃቸዉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡ በርካታ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ኤክስፐርቶች ግን በመድሃኒቶች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ የምርምር ማእከላት በመድሃኒቶቹ ላይ ምርመራ እያደረጉ እንደሚገኙ ዘገባዉ አስታዉቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ከ140 ሺ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ የተያዙባት ሲሆን ከ2 ሺኅ 500 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks

የኮቪድ19 በሽታ የየቀኑ ምልክቶች *=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*= ፨ ከ1-3 ቀን . በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን መሰል ሆኖ ቀለል ያለ ትኩሳት እና የጉሮሮ ህመም ብቻ ሲኖር የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ጥሩ ነው ። . የሰውነት መከላከያ ደከም ያለባቸው ስዎች ቀለል ያለ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽ ሊኖራቸው ይችላል ። ፨ በ 4 ኛው ቀን . የጉሮው ህመም ይጨምራል እንደዚሁም የድምፅ መወፈር ይኖራል ። . ብዙ ጊዜ ትኩሳት አይኖርም 36.5 degree ብቻ ይሆናል . ቀለል ያለ እራስ ምታት እና የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ሊስተገዋጎል ይችላል ። ፨ በ 5 ኛው ቀን . ስሜቶች የበለጠ ይጨምራሉ ፦ የጉሮሮ ህመም ይጨምራል ፣ ድምፅ የበለጠ ይጎረንናል ። . በእንቅስቃሴ ወቅት የስውነት ህመምና ቁርጥማት ይኖራል ፤ የሰውነት ድካም ይኖራል ። ፨ በ 6 ኛው ቀን . ትኩሳት ይጀምራል . ደረቅ ሳል ከጉሮሮ ህመም ጋር ይበረታል . ምግብ በመመገብ ፣ የሚጠጣ ነገር ሲወስድ እንደዚሁም በንግግር ጊዜ የጉሮሮ ህመም ይኖራል ። ተቅማጥና ማቅለሽለሽ የበለጠ ይጨምራል ። ፨ በ 7 ኛው ቀን . ትኩሳት ከ 38 ድግሪ በላይ ይሆናል . ደረቅ ሳል ይኖራል ፣ ይጨምራል . የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ፣ ተቅማጥና ማቅለሽለሽ ይጨምራል ። ፨ በ 8 ኛው ቀን . መተንፈስ መቸገር . የደረት መክበድና ህመም . ደረቅ ሳል ይኖራልም ይጨምራልም . የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ይቀጥላልም በጣም ይጨምራል ። . ትኩሳት ይቀጥላል ፣ ይጨምራል ፨ በ 9 ኛው ቀን እና በሚቀጥሉት ቀናት . ሁልም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በጣም ይጨምራሉ ። ⚠️ማንኛው ስው የሚከተሉት አደገኛ ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቁአም መሄድ ያስፈልጋል ። ፧ የተራዘመ ድረቅ ሳል ፧ የትንፋሽ ማጠር ፧ የደረት ህመም ፧ ከፍተኛ ትኩሳት እነዚህን ምልክቶች በሚያዩበት ወቅት ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደውል ያመልክቱ መጠንቀቅ ለራስ ነው የጤና ባለሙያዎች የሚያስተላልፉትን መልክቶች በአግባቡ መስማትና ስራ ላይ በማዋል ራሶትንና የቤተሰቦትን ጤና ይጠብቁ !!! 📌 “Discipline saved China. Indiscipline drowned Europe. Ignorance will kill Africa.” ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!

#Ethiopia : በኦሮሚያ ክልል የተወሰዱ እርምጃዎች ❗️ 1. የመንግስትም ሆነ ፓርቲ የትኛውም አይነት ስብሰባ እንዳይካሄድ የተወሰነ ሲሆን ስብሰባ የጠራም ሆነ የተሳተፈ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል። 2. ህብረተሰቡም በየአካባቢው እንዲቆይ፤ ከገጠር ወደ ከተማ ከሚደረጉ ጉዞዎች እንዲቆጠብም መልዕክት ተላልፏል። 3 በኦሮሚያ ክልል ያሉ ህዝብ የሚበዛባቸው ገበያዎች ለጊዜው ታግደዋል። 4. የሀይማኖተት ተቋማት በርካታ ቁጥር ላላቸው ምዕመናን አገልሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል። የሀይማኖት አባቶችም የተቀመጠውን አቅጣጫ እንዲያስፈፅሙ ጥሪ ቀርቧል። 5. ጭፈራ ቤቶች፣ ጫት ቤቶች እና ሺሻ ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ተወስኗል። 6. ትልልቅ ከተሞች መግቢያ እና መውጫ ላይ የሰውነት ሙቀት ልኬት እንደሚካሄድ እና ተጠርጣሪዎች ክትትል እንዲደረግላቸው። 7. ጡረታ ለወጡ የህክምና ባለሙያዎች እና የህክምና ትምህርት እየተማሩ ለሚገኙ ተማሪዎች ጥሪ ሊደረግ ስለሚችል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ። 8. በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆች፣ የወጣቶች ማዕከላት እና ትምህርት ቤቶችም ለማቆያነት እንዲያገለግሉ ዝግጁ እንዲሆኑ። 9. የመንግስት ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚቀጥሉ ቢሆንም በቅርብ አለቆች አማካኝነት ወሳኝ የስራ ሂደቶችን በማሳተፍ ሌሎች ፍቃድ እንዲወጡ። 10. ቫይረሱን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ። 11. በዚህ ወሳኝ ወቅት የመንግስት አቅም ውስን መሆኑ ታውቆ ህብረሰተቡ፣ ባለሀብቱ እና ሌሎችም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል። ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks

#የታማሚዎች ሁኔታ ፦ - አንደኛዋ ታማሚ መጋቢት 10 ከዱባይ እንዲሁም ሁለተኛው ታማሚ መጋቢት 12 ከአሜሪካ የገቡ ናቸው። - ሁለቱም ታማሚዎች የበሽታው ምልክት በማሳየታቸው በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። - ከታማሚዎቹ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎችን የመለየትና ክትትል ሂደት እየተከናወነ ይገኛል። - ሁለቱም ታማሚዎች በአማራ ክልል የለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks

#UPDATE ሁለቱ (2) የቫይረሱ ተጠቂዎች፦ - በአማራ ክልል ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑ የ37 ዓመት ሴትና የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የሆኑ የ32 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያውያን
#UPDATE ሁለቱ (2) የቫይረሱ ተጠቂዎች፦ - በአማራ ክልል ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑ የ37 ዓመት ሴትና የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የሆኑ የ32 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያውያን ናቸው። #DrLiaTadesse ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks

⚠️Ethiopia has now confirmed 2 cases of CoVid19. Now the total number is 23.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፦ - 23 ሰው ገደማ በቫይረሱ መጠቃቱ ተረጋግጧል - ከተጠቂዎች ውስጥ 2 ሰው አገግሟል - በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምንም ሰው አልሞተም - በከተሞች ያለው ከንክኪ መረራቅ እና የሚሰጠውን መመሪያ መቀበል በሚያረካ ደረጃ ላይ አይደለም። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks

አልኮል መጠጥ መጠጣት የኮቪድ-19 በሽታን አይከላከልም - የዓለም የጤና ድርጅት **** አልኮል መጠጥ መጠጣት የኮቪድ-19 በሽታን አይከላከልም ሲል የዓለም የጤና ድርጅት አስጠንቅቋል፡፡ ይልቁንም አ
አልኮል መጠጥ መጠጣት የኮቪድ-19 በሽታን አይከላከልም - የዓለም የጤና ድርጅት **** አልኮል መጠጥ መጠጣት የኮቪድ-19 በሽታን አይከላከልም ሲል የዓለም የጤና ድርጅት አስጠንቅቋል፡፡ ይልቁንም አልኮል መጠጥ መጠጣት አደገኛ ሊሆን ይችላል ነው ያለው ድርጅቱ፡፡ አልኮል መጠጥን አብዝቶ ወይም አዘውትሮ መጠጣት የጤና ችግር ስጋትን ሊጨምር እንደሚችል ድርጅቱ ጠቁሟል፡፡ (የዓለም የጤና ድርጅት/EBC)

#Coronavirus : በኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁት 11 የዓለማችን አገራት እነማን ናቸው? 1. በመላው ዓለም 722,289 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል። ከእነዚህም መካከል 151,901 ያህሉ ሙሉ በሙሉ መዳናቸው ታውቋል። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተደራጀውን መረጃ እናካፍላችሁ:: 2. በአሜሪካ 142,106 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 4,767 ደግሞ ድነዋል:: 3. በጣሊያን ደግሞ 97,689 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፣ 13,030 ደግሞ መዳናቸው ታውቋል። 4. ቻይና 82,122 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 75,583 ደግሞ ድነዋል 5. ስፔን 80,110 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 14,709 ደግሞ ድነዋል 6. ጀርመን 62,095 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 9,211 ደግሞ ድነዋል 7. ፈረንሳይ 40,723 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 7,226 ደግሞ ድነዋል 8. ኢራን38,309 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 12,391 ደግሞ ድነዋል 9. ዩናይትድ ኪንግደም ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 19,784 151 ደግሞ ድነዋል 10. ስዊዘርላንድ 14,829 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 1,595 ደግሞ ድነዋል 11. ኔዘርላንድስ 10,930 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 253 ደግሞ ድነዋል

#ከአገሪቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አማራ ክልል የሚገቡ ማንኛውም አይነት የህዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት የማይችሉ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት የኮረና ወረርሽኝ መከላከል ኮማንድ
#ከአገሪቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አማራ ክልል የሚገቡ ማንኛውም አይነት የህዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት የማይችሉ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት የኮረና ወረርሽኝ መከላከል ኮማንድ ፖስት አስታውቋል። ከዩኒቪርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸውው እየመጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ግን በልዩ ሁኔታ የሚገቡ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!

#BREAKING የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 21 ደረሱ! ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!
#BREAKING የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 21 ደረሱ! ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!

#በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦ ❖ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው - 884 ❖ ዛሬ 20/07/2012 በበሽታው የተያዙ - 3 ❖ በአሁን ሰዓት በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 16 ❖ ፅ
#በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦ ❖ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው - 884 ❖ ዛሬ 20/07/2012 በበሽታው የተያዙ - 3 ❖ በአሁን ሰዓት በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 16 ❖ ፅኑ ህሙማን - 1 ❖ ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 1 ❖ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ድምር - 19 ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!

የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ #ጥቆማ ለመስጠት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ ተከታዮቻችን የሚከተሉን ነፃ የስልክ መስመሮች ይጠቀሙ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_
የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ #ጥቆማ ለመስጠት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ ተከታዮቻችን የሚከተሉን ነፃ የስልክ መስመሮች ይጠቀሙ። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

በርካታ ሰራተኞች የሚገኙበት የአበባ እርሻ... "ዝዋይ ከትማ ላይ ግዙፍ የአበባ እርሻ እንዳለ የታወቀ ነው...አናም ይህ የአበባ አርሻ ከ30,000 (ሰላሳ ሺ) በላይ ሰሪትኞች የሉት ሲሆን ፥ ይህ
በርካታ ሰራተኞች የሚገኙበት የአበባ እርሻ... "ዝዋይ ከትማ ላይ ግዙፍ የአበባ እርሻ እንዳለ የታወቀ ነው...አናም ይህ የአበባ አርሻ ከ30,000 (ሰላሳ ሺ) በላይ ሰሪትኞች የሉት ሲሆን ፥ ይህ ቦታ እጅግ በጣም የታፈነ ቦታ ነው:: የኮቪድ 19 ( ኮሮና ) ቫይረስ ሊስፋፋ ከሚችሉበት ቦታ በዋንኝነት ሊጠቅስ ይችላል፡፡ የከተማው ህዘብ ቫይረሱን ለመከላከል እንዲዘጋ ተቋውሞውን ቢያሰማም አሁን እስካለንበት ስአት የከተማው ድርጅቱ መንም ምላሽ አልሰጠም፡፡ በአሁኑ ስአት ይህ ሁሉ ሀዝብ ስሪ ላይ ነው የሚመለከተው አካል መፍተሄ እንዲሰጠን እንጠይቃለን።" ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

#Eritrea በእንግሊዝ ሀገር ሁለት ኤርትራዊያን በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሞታቸው ሲታወቅ 10 ኤርትራዊያን ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ተገኝቶ የህክምና ክትትል እይደረጉ መሆኑ ተነግሯል:: ሟቾቹ ኤር
#Eritrea በእንግሊዝ ሀገር ሁለት ኤርትራዊያን በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሞታቸው ሲታወቅ 10 ኤርትራዊያን ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ተገኝቶ የህክምና ክትትል እይደረጉ መሆኑ ተነግሯል:: ሟቾቹ ኤርትራዊያን የ 65 አመት እና የ 75 አመት አዛውንት መሆንቸው ተረጋግጧል:: ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━

#NewsAlert ‼️ #Chole #Gololcha #zeway ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ ከቤት አትውጡ መረጃውን አጣርተን እናቀርባለን!! ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!

Its Either #RestInHome or #RestInPeace I CHOOSE TO #REST_IN_HOME How about YOU !? #Staysafe #SocialDistance #CoronaAwarness #
Its Either #RestInHome or #RestInPeace I CHOOSE TO #REST_IN_HOME How about YOU !? #Staysafe #SocialDistance #CoronaAwarness #StayHome ⚠️ጮሌ እና ዘዋይ አከባቢ የምትኖሩ ከቤት ባትወጡ መልካም ነው የተለያዩ መረጃዎች እየደረሱን ነው። ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!

#ADAMA በአዳማ ከተማ ባሉ ጎዳናዎች ላይ "ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በከተማው ውስጥ አንገብጋቢ ካልሆነ በስተቀር እንቅስቃሴ ማድረግ ተከልክሏል" የሚሉ ማስታወቂያዎች እየተነገረ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ
#ADAMA በአዳማ ከተማ ባሉ ጎዳናዎች ላይ "ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በከተማው ውስጥ አንገብጋቢ ካልሆነ በስተቀር እንቅስቃሴ ማድረግ ተከልክሏል" የሚሉ ማስታወቂያዎች እየተነገረ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግሩ። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ትልልቅ የድምጽ ማጉያዎችን በጫኑ መኪኖች በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በዋና ዋና ጎዳናዎች ማስታወቂያውን እያሰራጨ መሆኑን ነው ነዋሪዎች የገለፁት። ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!

የታማሚዎች ሁኔታ፦ #የመጀመሪያዋ ታማሚ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8፣ 2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10፣ 2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ
የታማሚዎች ሁኔታ፦ #የመጀመሪያዋ ታማሚ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8፣ 2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10፣ 2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ አድርጋለች፡፡ ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በመጋቢት 19፣2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል፡፡ #ሁለተኛ እና #ሶስተኛ ታማሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡ ግለሰቦቹ በመጋቢት 19፣ 2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

#በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 19 ደረሰ! #በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 87 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት ተጨማሪ
#በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 19 ደረሰ! #በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 87 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ #MoH ━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @Computer_Android_tricks ━━━━━━━━━━━━━━━ ☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!