ch
Feedback
የጥበብ እመቤት 📜

የጥበብ እመቤት 📜

前往频道在 Telegram

╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️‍🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady

显示更多
未指定国家未指定类别
272
订阅者
-124 小时
+77
+15230
帖子存档
አባ ይፍቱኝ 😢.. ሲኦል አለ ሲሉኝ የለም ብየ ክጄ የሰው ተረት ነው በማለት ቀልጄ። አውቄ በድፍረት በድያለሁና ያንፁኝ በንስሀ ያንሱኝ በቀኖና። ሲኦል ከነ ጭፍራው በጉም ተሸፍኖ እንዴት ሳላየው ኖ
አባ ይፍቱኝ 😢.. ሲኦል አለ ሲሉኝ የለም ብየ ክጄ የሰው ተረት ነው በማለት ቀልጄ። አውቄ በድፍረት በድያለሁና ያንፁኝ በንስሀ ያንሱኝ በቀኖና። ሲኦል ከነ ጭፍራው በጉም ተሸፍኖ እንዴት ሳላየው ኖርኩ ካጠገቤ ሁኖ። አባ ይፍቱኝ..... ሰይጣን ብሎ ነገር ተጭበረበረ ዋዛ ነው ቧልት ነው ብየ አስቤ ነበረ። የሄው እውነት ሁኖ ዋዛና ተረቱ ባይኔ በብረቱ። ዲያብሎስ አየሁት በሸሚዝ ዘንጦ እልፍ ገዳይ ጥሎ ቸብችቦ ጨብጦ። አባ............ ልክ እንደ ብርሌ አጥንት ሲከሰክስ አባይን አዋሽን የሚያስንቅ ደም ሲፈስ ለምለም ፍጥረት ሁሉ ወደ አመድ ሲመለስ ልክ እንደ ጧፍ ሀወልት ሚስኪኖች ሲሰቃዩ ምድጃው ዳር ሁነው የሄን እያዩ ገሀንም ከላይ ነው ብለው መሳትዎ እርሱዎ እንደ ፈቱኝ እግዛብሄር ይፍታው ። በስደት ያለነው እህት ወንድም ለንስሀ ያብቃን። https://t.me/mekuytrrwxnc

𝚠𝚑𝚎𝚗𝚎𝚟𝚎𝚛 𝚢𝚘𝚞 𝚜𝚎𝚎 𝚊 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜𝚏𝚞𝚕 𝚙𝚎𝚜𝚘𝚗 𝚢𝚘𝚞 𝚘𝚗𝚕𝚢 𝚜𝚎𝚎 𝚝𝚑𝚎 𝚙𝚞𝚋𝚕𝚒𝚌 𝚐𝚕𝚘𝚛𝚒𝚎𝚜,�
𝚠𝚑𝚎𝚗𝚎𝚟𝚎𝚛 𝚢𝚘𝚞 𝚜𝚎𝚎 𝚊 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜𝚏𝚞𝚕 𝚙𝚎𝚜𝚘𝚗 𝚢𝚘𝚞 𝚘𝚗𝚕𝚢 𝚜𝚎𝚎 𝚝𝚑𝚎 𝚙𝚞𝚋𝚕𝚒𝚌 𝚐𝚕𝚘𝚛𝚒𝚎𝚜,𝚗𝚎𝚟𝚎𝚛 𝚝𝚑𝚎 𝚙𝚛𝚒𝚟𝚊𝚝𝚎 𝚜𝚊𝚌𝚛𝚒𝚏𝚒𝚌𝚎𝚜 𝚝𝚘 𝚛𝚎𝚊𝚌𝚑 𝚝𝚑𝚎𝚖, 🥀🍿☕️🫖🥀🍿☕️🫖 https://t.me/mekuytrrwxnc

በፈገግታ መመላለስ ፈገግታችን ከሌሎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት መልካም ለማድረግ በጣም ወሳኝ ነው። ከፍትፍቱ ፊቱ አይደል የሚባለው። ፈገግታ ብርሃን ነው። ፈገግ ስንል የእኛም፣ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችም
በፈገግታ መመላለስ ፈገግታችን ከሌሎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት መልካም ለማድረግ በጣም ወሳኝ ነው። ከፍትፍቱ ፊቱ አይደል የሚባለው። ፈገግታ ብርሃን ነው። ፈገግ ስንል የእኛም፣ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችም መንፈስ እንደ ብርሃን እንዲያበራ ያደርጋል፤ ፈገግ እንበል። በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር መግባባት በመፍጠር የመረጋጋትና በራስ የመተማመን ስሜታችንን ማጎልበት አለብን። አሁን እያወራን ያለነው የለበጣ ፈገግታን አይደለም። እያወራን ያለው ከልብ ስለሚመነጨው ፈገግታ ነው። በሀዘናችን ፣ በድካማችንና በብስጭታችን ጊዜ በራስ መተማመናችን ይቀንሳል። ከልባችን ፈገግ ስንል ከሀዘንችን እንጽናናለን፣ ከድካማችን እንበረታለን፣ ከብስጭታችን እንረጋጋለን። ስለዚህ በየትኛውም ሁኔታ እንሁን ከልባችን ፈገግ ማለትን አንርሳ።   🥀🍿☕️🫖✨ https://t.me/mekuytrrwxnc

⌛ ጊዜ አለሽ ሂዋኔ 🥰 ህይወት አጭር ናት’ የሚል ወሬ ሰምተሽ ታውቅያለሽ? ያ ትልቁ ውሸት ነው! "እውነት ለመናገር ከሆነ ፣ አብዛኛው የህይወትሽ ክፍል ገና አልተጀመረም። የምትኖሪው እድሜ፣ ካለፈ
⌛ ጊዜ አለሽ ሂዋኔ 🥰 ህይወት አጭር ናት’ የሚል ወሬ ሰምተሽ ታውቅያለሽ? ያ ትልቁ ውሸት ነው! "እውነት ለመናገር ከሆነ ፣ አብዛኛው የህይወትሽ ክፍል ገና አልተጀመረም። የምትኖሪው እድሜ፣ ካለፈው እድሜሽ በብዙ እጥፍ ይበልጣል። ራስሺን ላይ መወሰን የጀመርሺው ገና በ18 ወይም በ20 አመትሽ ነው። ማለትም፣ በትክክል መኖር የጀመርሺበት እድሜ ገና ሁለት ወይም ሶስት አመት ብቻ ነው! ስለዚህ 40፣ 50፣ አልፎም 60 አመት ገና ከፊትሽ አለ። ስለዚህ መዘግየቴ፣ መክሰሬ ብለሽ አትጨነቂ። ጨዋታው ገና ተጀምሯል። አሁንም ጊዜው አለሽ፣ ተስፋ አትቁረጪ ይሄንን ፅሁፍ የምታነበው አንተ ነገሮች ከባድ ሆነውብህ ከሆነ፣ ይሄ መልእክት ላንተ ላንቺ ነው ፤ ተስፋ አትቁረጥ 🙏 🥀🍿🫖☕️🥀🍿🫖☕️ https://t.me/mekuytrrwxnc

Repost from N/a
HDMONA_ተወራሪድካለይ_ብ_ዳናይት_a.mp34.86 MB

በምሽቱ ጀንበር ​ኑሮን ስናባርር፣ መኖር እየራቀን፣ ​ከራሳችን ጋራ፣ ስንቴ ተራራቅን። ​ከፀሐይ መጥለቂያ፣ በምሽቱ ጀንበር፣ ​ጥላችን ሲጠፋ፣ ለመኖር ሲለን ግር፤ ​ድንገት ብንጠይቅ፣ ብቻችንን ቆመን
በምሽቱ ጀንበር ​ኑሮን ስናባርር፣ መኖር እየራቀን፣ ​ከራሳችን ጋራ፣ ስንቴ ተራራቅን። ​ከፀሐይ መጥለቂያ፣ በምሽቱ ጀንበር፣ ​ጥላችን ሲጠፋ፣ ለመኖር ሲለን ግር፤ ​ድንገት ብንጠይቅ፣ ብቻችንን ቆመን፣ ​ለእውነት የኖርነው ቀን፣ ከቶ ይኖር ይሆን? ​ዕጣችን ካልመረጥን፣ በገዛ እጆቻችን፣ ​ያልኖርንበት ህይወት፣ ይሆናል ዕዳችን!። 🥀🍿🫖☕️🥀🍿🫖☕️ https://t.me/mekuytrrwxnc

የኔ ልዩ ሴት ድክመት ውድቀት አይደለም ይልቁንስ ተስፋ መቁረጥ ነው ውድቀት የሚሆነው እናማ ሁሌም የማትሰበሪ ጠንካራ ስትወድቂ የምትነሺ ስትታመሚ የምታገግሚ ስታለቅሽ የምስቂ በራስሽ መቆም የምትችይ
የኔ ልዩ ሴት ድክመት ውድቀት አይደለም ይልቁንስ ተስፋ መቁረጥ ነው ውድቀት የሚሆነው እናማ ሁሌም የማትሰበሪ ጠንካራ ስትወድቂ የምትነሺ ስትታመሚ የምታገግሚ ስታለቅሽ የምስቂ በራስሽ መቆም የምትችይ ጠንካራ ሴት ሁኚ ምክንያቱም አለም በአሁን ስአት በአስመሳዬችነወ የተሞላች ነች። 🥀🍿🫖☕️ https://t.me/mekuytrrwxnc

ከራስ ጋር አዎንታዊ ንግግር ስለራሳችን የምናስበው እያንዳንዱ ሀሳብ ለእራሳችን የምንሰጠው ግምት ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተፅእኖ አለው። ለእራሳችን የምንነግረው ሀሳብ አሉታዊ ከሆነ ቀስ በቀስ ለ
ከራስ ጋር አዎንታዊ ንግግር ስለራሳችን የምናስበው እያንዳንዱ ሀሳብ ለእራሳችን የምንሰጠው ግምት ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተፅእኖ አለው። ለእራሳችን የምንነግረው ሀሳብ አሉታዊ ከሆነ ቀስ በቀስ ለእራሳችን የምንሰጠው ግምት እየወረደ ይመጣል። ስለዚህ እነዚህን አሉታዊ ሀሳቦች በአዎንታዊ ሀሳቦች የምንተካበት መንገድ መፈለግ አለብን። አዎንታዊ ሀሳቦችን ማሰብ ስለእራሳችን ያለን ግምት በጣም ጥሩ እንዲሆን ያደርጋል። የእራስ መተማመናችንም እንዲያደግ ያግዘናል። 🥀🍿☕️🫖🥀

𝚙𝚊𝚒𝚗.𝚒𝚜 𝚏𝚞𝚎𝚕. ህይወታችን የሚሻሻለዉ በሚደግፉንና በሚያበረቱን ሰዎች ብቻ ሳይሆን በሚገፉንና በሚንቁንም ሰዎች ነዉ። በደንብ ካሰባችሁት ክፉም ሆነ በጎ ሀሳብ ወደፊት እንድትጓዙ
𝚙𝚊𝚒𝚗.𝚒𝚜 𝚏𝚞𝚎𝚕. ህይወታችን የሚሻሻለዉ በሚደግፉንና በሚያበረቱን ሰዎች ብቻ ሳይሆን በሚገፉንና በሚንቁንም ሰዎች ነዉ። በደንብ ካሰባችሁት ክፉም ሆነ በጎ ሀሳብ ወደፊት እንድትጓዙ የሚያደርግ ጉልበት ነዉ። 🥀🍿☕️🫖

Repost from N/a
Alex_Hirpo_–_Man_Ayelign_ዓለማየሁ_ሂርጶ_ማን_አየልኝ128k.m4a5.50 MB

" ተስፋ መቁረጥ ተስፋ ይቁረጥ " በህይወት ግብግብ በመርታት መረታት ወድቆ በመዛል ውስጥ ደግሞ በመነሳት በመኖር ጉጉት ስንቅ በፈጣሪ ቸርነት ተስፋ መቁረጥ ሲገዝፍ በዚህች ዓለም ክፋት አዲስ ህልም
" ተስፋ መቁረጥ ተስፋ ይቁረጥ " በህይወት ግብግብ በመርታት መረታት ወድቆ በመዛል ውስጥ ደግሞ በመነሳት በመኖር ጉጉት ስንቅ በፈጣሪ ቸርነት ተስፋ መቁረጥ ሲገዝፍ በዚህች ዓለም ክፋት አዲስ ህልም ይኑርሽ ሌላ ብርታት ታጠቂ በተስፋ መቁረጥ ህግ ተስፋን አትነጠቂ ሄዋኔ እጅ አትስጪ ደጋግመሽ ሞክሪ ወድቆ መነሳትን ተጋፈጭ አትፍሪ በተስፋ መነፀር በመኖር ስልተ ምት በዛሬሽ ሙከራ በነገሽ መስተዋት አይክፋሽ ቀና በይ ዓለምን ሳቂባት ማንም ምንም ይበል ከውስጥሽ ካለ እውነት። 🥀🍿☕️🫖

ሰዎች ስለ እኛ ምን ያስባሉ ብለን አንጨነቅ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ሌሎች ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል አጉል ተፅእኖ ስር እንዳንገባ እንጠንቀቅ። አብዛኛው ሰው ለእኛ የግል ውሳኔና የአኗኗር ግድ የለውም
ሰዎች ስለ እኛ ምን ያስባሉ ብለን አንጨነቅ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ሌሎች ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል አጉል ተፅእኖ ስር እንዳንገባ እንጠንቀቅ። አብዛኛው ሰው ለእኛ የግል ውሳኔና የአኗኗር ግድ የለውም። መኖራችን እንኳን ትዝ የሚላቸው ስንገናኝ ነው። ታዲያ እኛ ለምንድነው ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል አስተሳሰብ የምንጠመደው? ማንም የእኛን ኑሮ አይኖርልንም። አረረም መረረም የእኛ ኑሮ የእኛ እንጂ የማንም አይደለም። የማንንም መብት እስካልተጋፋን ድረስ በነፃነት ያሻንን ማድረግ አለብን። ተስፋ እንዳንቆርጥ በመልካም ከሚቀርቡን እንኳን ብዙ አንጠብቅ። ወዳጅ መስለው ጠላቶች፣ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች አሉ። ለእኛ ግድ የሌላቸው ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ ከአላማችን እንዳንስት እንጠንቀቅ። https://t.me/mekuytrrwxnc

ሰው ያላወቀውን፣ ያልተረዳውን ወይም በቂ መረጃ የሌለውን ነገር ከመማርና ከመጠየቅ ይልቅ በፍጥነት ለመንቀፍ ሲሞክር፣ ይህ ብዙ ጊዜ ከጥልቅ እውቀት ሳይሆን ከአስተሳሰብ ዝግነት፣ ከኩራት ወይም ከአለማ
ሰው ያላወቀውን፣ ያልተረዳውን ወይም በቂ መረጃ የሌለውን ነገር ከመማርና ከመጠየቅ ይልቅ በፍጥነት ለመንቀፍ ሲሞክር፣ ይህ ብዙ ጊዜ ከጥልቅ እውቀት ሳይሆን ከአስተሳሰብ ዝግነት፣ ከኩራት ወይም ከአለማወቅ ይመነጫል። ምክንያቱም እውቀት ጥያቄ ይፈጥራል፤ አለማወቅ ግን ያለ ማስረጃ ፍርድ ይሰጣል። ጥበበኛ ሰው ያልገባውን ለመረዳት ይጥራል፤ ኩሩ ሰው ግን ያልገባውን ለማጣጣል ይቸኩላል። ስለዚህ ያልተረዳነውን ነገር መንቀፍ ከእውቀት በላይ የአስተሳሰብ ውስንነትን ያሳያል። "ያልተረዳኸውን ነገር መንቀፍ የእውቀት ምልክት አይደለም፤ የኩራት፣ የአስተሳሰብ ዝግነት እና የአለማወቅ መገለጫ ነው። ጠያቂ ሰው ይማራል፤ ፈራጅ ሰው ግን በአለማወቁ ይቀጥላል።" https://t.me/mekuytrrwxnc

የሳቅ ጀርባው በጥርስሽ ፈገግታ፣ የደላሽ ቢመስል፣ እኔ መች አጣሁት፣ የውስጥሽን ቁስል፤ ከፊትሽ ላይ ያለው፣ የመስመሩ ብዛት፣ የውስጥሽ ህመም ነው፣ የልብሽ ትኩሳት። እስቲ ወገኖቼ፣ ከልብ ምትወዱትን
የሳቅ ጀርባው በጥርስሽ ፈገግታ፣ የደላሽ ቢመስል፣ እኔ መች አጣሁት፣ የውስጥሽን ቁስል፤ ከፊትሽ ላይ ያለው፣ የመስመሩ ብዛት፣ የውስጥሽ ህመም ነው፣ የልብሽ ትኩሳት። እስቲ ወገኖቼ፣ ከልብ ምትወዱትን፣ በትኩረት አጢኑት፣ ተረዱት ሕይወቱን፤ እንደ ፅጌረዳ፣ እንደ አበባ ቅጠል፣ ፍቅር ከተለየው፣ ሰው ይጠወልጋል። የውስጡ ትኩሳት፣ ፊት ላይ ሲንበለበል፣ ያዛዝናል አይደል፣ እንዲህ አይነት በደል፤ በሳቅ አይሸፈን፣ ለሰው ለማስመሰል፣ ከውስጥ ሲሞላ ነው፣ ፊት የሚታይ ቁስል። ማንስ ያስተውላል፣ የሳቅ ጀርባን ሸክም፣ ከፈገግታ ጀርባ፣ ያለን የውስጥ ሕመም፤ በውጩ ፈገግታ፣ እየተገመተ፣ ስንቱን ሳንረዳው፣ሰው እንዳጣ ሞተ። 🥀🍿🫖☕️🥀🍿🫖☕️ https://t.me/mekuytrrwxnc

መልካም አሳቢ( Positive Thinking) መሆን መልካም አስተሳሰብ ወይም አዎንታዊ አስተሳሰብ በራስ መተማመናችንን የሚያጎለበት ነገር ነው። በራስ መተማመን ማለት ደግም ስለራሳችን የሚናስበው የሚ
መልካም አሳቢ( Positive Thinking) መሆን መልካም አስተሳሰብ ወይም አዎንታዊ አስተሳሰብ በራስ መተማመናችንን የሚያጎለበት ነገር ነው። በራስ መተማመን ማለት ደግም ስለራሳችን የሚናስበው የሚሰማን ስሜት ነው። አዕምሮአችን ውስጥ ርካሽ የማይረቡ ዝቅ ያሉ ሀሳቦች እንዲመላለሱ ካደረግን የራስ መተማመናችንን በገዛ ፈቃዳችን ሸርሽረን ለሽንፈት እጅ እንሰጣለን። የማይረቡ ዝቅ ያሉ ሀሳቦች ወደ አዕምሮአችን ሲመጡ ፈጥነን በመልካም እና ገንቢ ሀሳብ ልንተካቸው ይገባል። መልካም አስተሳሰብ ወይም አዎንታዊ አስተሳሰብ ወደ ራስ መተማመን የሚያሸጋግረን መወጣጫ መሰላል ነው። ደግ ደጉን ማሰብ ወደ መልካም ነገር ይምራናል። 🥀🍿☕️🫖🥀🍿☕️🫖🥀☕️🫖

ለምን ጠፋህ አዳሜ ? ግን አልናፍቅህም? እውነቱን ስነግርህ አኔ ናፍቀሀኛል፣ ብቻየን ቁጭ ስል ሳቅና ጨዋታህ ውል ውል ይለኛል፣ እንደውም ልንገርህ ሱስ ሁነህብኛል፣ በምግብ መጠጡ አንተን ያሳየኛል፣
ለምን ጠፋህ አዳሜ ? ግን አልናፍቅህም? እውነቱን ስነግርህ አኔ ናፍቀሀኛል፣ ብቻየን ቁጭ ስል ሳቅና ጨዋታህ ውል ውል ይለኛል፣ እንደውም ልንገርህ ሱስ ሁነህብኛል፣ በምግብ መጠጡ አንተን ያሳየኛል፣ ከሰው ተለይቸ ብቻየን መቀመጥ እጅጉን ያምረኛል፣ ለምን አትለኝም አዳሜ!? ብቻየን ስቀመጥ ባይነ ህሊናየ አንተን ያሳየኛል፣ የናፍቆትህ ነገር እንድህ እያረገ ያንቀዋልለኛል፣ ግን የኔውድ... አንተም ከናፈኩህ እንዴኔ ካረገህ፣ ና ከጎኔ ሁነህ እንደ ልጅ ልቀፍህ ፣ ከአለም ሁካታ ትንሽ ላሳርፍህ፣ የልቤን ትርታ ዜማውን ላሰማህ፣ ባንተ እንደተረታ ሚስጥሩን ይንገርህ፣ የአፌ ቅላጤ የልቤ ላይ መዝሙር፣ አለምን ማየቻ የአይኔ መነፀር፣ ደግሞም እስትንፋሴ የደሜ ዝውውር፣ የመላ አካላቱ አዛዡ እንዳረከህ፣ ይሄ ነው ሚስጥሩ ልቤ የሚነግርህ። 🥀🥀❤️🥀🥀❤️🥀🥀❤️🥀🥀🥀 https://t.me/mekuytrrwxnc

የምናውቀውን ብቻ እንናገር በእለት ተእለት ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት የምናውቀውን እና እቅጩን እንናገር። ይህን ማድረጋችን በሰዎች ዘንድ ተአማኒነት እንዲኖረን ያደርጋል። ፍሬ ቢስ እና የማይረባ
የምናውቀውን ብቻ እንናገር በእለት ተእለት ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት የምናውቀውን እና እቅጩን እንናገር። ይህን ማድረጋችን በሰዎች ዘንድ ተአማኒነት እንዲኖረን ያደርጋል። ፍሬ ቢስ እና የማይረባ ወሬ ላለማውራት በእያንዳንዱ ግንኙነታችን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ሰዎች ከአፋችን በሚወጣው እኛነታችንን በደንብ ይገመግሙናል። እኛ ተራ አሉባልታ መስማት እንደማንፈልገው ሁሉ እኛም የሌሎችን ጊዜ በማይጠቅም ከንቱ ወሬ ማባከን የለብንም። የመናገር ክህሎት የሚለካው የሚያስፈልገውን፣ እውነቱን እና ቁምነገሩን በማውራት ሲሆን በተጨማሪም የማያስፈልገውን ባለመናገርም ጭምር ነው። ሰዎችን በውሸት ለማስደነቅ በፍፁም መሞከር የለብንም። ይዘገያል እንጂ እውነቱ መውጣቱ ሀሰተኛ ምላስም መጋለጧ አይቀርም። ስለዚህ እውነቱን ብቻ በተገቢው ቦታ አስፋላጊ ሲሆን መናገር ይገባል። 🥀🍿☕️🫖🥀🍿☕️🫖 https://t.me/mekuytrrwxnc

ነፃና ግልፅ አስተሳሰብ ነፃና ግልፅ አስተሳሰብ ማለት ከውጫዊ ተፅእኖ የፀዳ፣ በስሜት ሳይሆን በምክንያት፣ በነባራዊ ሁኔታና በመረጃ የተደገፈ ቀና ሀሳብና ዉሳኔ ማሰብ ማለት ነው። አመለካከታችንን እና
ነፃና ግልፅ አስተሳሰብ ነፃና ግልፅ አስተሳሰብ ማለት ከውጫዊ ተፅእኖ የፀዳ፣ በስሜት ሳይሆን በምክንያት፣ በነባራዊ ሁኔታና በመረጃ የተደገፈ ቀና ሀሳብና ዉሳኔ ማሰብ ማለት ነው። አመለካከታችንን እና ውሳኔያችን ሚዛናዊና በምክንያትና በሀቅ የተመሰረተ ማድረግ አለብን። ነፃና ግልፅ አስተሳሰብ ለህይወታችን በጣም ጠቃሚ ነው። ግልፁ አስተሳሰብ በዙሪያችን ያለውን ነገር ለመረዳት በጣም ጠቃሚ ነው። የተሳሳተ አስተሳሰብ፣ ስሜታዊነት እና ሌሎች ከእኛ የሚጠብቁት ነገር ሳናምንበት ማድረግ መጨረሻው ፀፀት ነው። ሁሌም አዎንታዊ አስተሳስብና ሚዛናዊነት ከእኛ አይለየን። የተለያዩ ሀሳቦችን ለማስተናገድ የተዘጋጀ ነጻ ህሊና ይኑረን። ከውጫዊ ተፅእኖ የፀዳ ንፁህ አስተሳሰብ ይኑረን። 🥀🍿🫖☕️✨🍿🫖☕️🥀 https://t.me/mekuytrrwxnc

𝚒 𝚠𝚘𝚛𝚕𝚍 𝚛𝚊𝚝𝚑𝚎𝚛 𝚋𝚎 𝚌𝚘𝚖𝚙𝚕𝚎𝚝𝚎𝚕𝚢 𝚎𝚡𝚑𝚊𝚞𝚜𝚝𝚎𝚍 𝚏𝚛𝚘𝚖 𝚝𝚑𝚎 𝚑𝚊𝚛𝚍 𝚝𝚒𝚖𝚎𝚜 𝚠𝚑𝚒𝚌𝚑 𝚋𝚛𝚎
𝚒 𝚠𝚘𝚛𝚕𝚍 𝚛𝚊𝚝𝚑𝚎𝚛 𝚋𝚎 𝚌𝚘𝚖𝚙𝚕𝚎𝚝𝚎𝚕𝚢 𝚎𝚡𝚑𝚊𝚞𝚜𝚝𝚎𝚍 𝚏𝚛𝚘𝚖 𝚝𝚑𝚎 𝚑𝚊𝚛𝚍 𝚝𝚒𝚖𝚎𝚜 𝚠𝚑𝚒𝚌𝚑 𝚋𝚛𝚎𝚎𝚍 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 𝚝𝚑𝚊𝚗 𝚠𝚎𝚕𝚕 𝚛𝚎𝚜𝚝𝚎𝚍 𝚏𝚛𝚘𝚖 𝚊𝚌𝚑𝚒𝚟𝚕𝚗𝚐 𝚗𝚘𝚝𝚑𝚒𝚗𝚐, 🥀🍿🫖☕️🥀🍿🫖☕️🥀

እንግሊዘኛ ፅሁፍ ሲፖሰት left የምትሉ ሰዎች ግን ደና ናቹ 😏🫣😁