ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

前往频道在 Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

显示更多
未指定国家未指定类别
899
订阅者
-224 小时
-167 天
+2730 天
帖子存档
[ حفظ الله  مشايخنا ]   ‏قَالَ الْبُخَارِيُّ -رَحِمَهُ اللهُ تَعَالَى-: "سَمِعْتُ أَحْمَدَ بْنَ حَنْبَلٍ يَقُولُ: "إنَّمَا النَّاسُ بِشُيُوخِهِمْ، فَإِذَا ذَهَبَ الشُّيُوخُ؛ فَمَعَ مَنْ الْعَيْشُ؟!". ["طبقات الحنابلة" (٢٧٤/١)]

የሰለፊዮች መለያየት ምክንያትና የድንበር አላፊዎች አይነት፦ 👉 የሰለፊዮች መለያየት እንደ ማንኛውም አይነት ሰው መለያየት ነው። ምክንያቱም እነሱም ሰዎች ናቸው። ሰለፊዮች እንደነብያቸው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፍፁምና ጥቡቅ ጀመዓዎች ናቸው ያለ ማንም የለም። እንደ አጠቃላይ የሰለፊዮች ደዕዋ ጥቡቅና ፍፁም ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን #የተናጥል የዳዕዋ ሂደታቸው ፍፁም አይደለችም። የተናጠል የደዕዋ ሂደት ላይ ልዩነት ይፈጠራል። ነብያችንም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የዚህ ኡማ መለያየት እንደሚያስጋቸው ጠቅሰዋል። ይህ ልዩነት ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ያስጠነቀቁን ነገር ነው። እውነታውም ይህን መለያየት የሚወደው የለም። ምክንያቱም وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ (የዋለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ የምትለዋን ትልቁ የሙስሊሞች መርህና መሰረት ስለምታጠፋና ስለምትንድ ነው። የሚያሳዝነው ግን፦ አንዳንዶች መሀይማን ብቻ ሳይሆን አውቀው #የመኸየሙ ወንድሞቻችን ብቅ ብለው አብዛኛው ሃሳብና ጭንቀታቸው በአህለል ሱና ወንድማቸው ላይ ረድ ማድረግ ሆነ። ሸይጧንም ትልቁ በአሏህ መንገድ ላይ የሚደረግ ትግል አድርጎም ሳለላቸው። ➜ ከተለያዩ ግልፅና ጥርት ካሉ የቢዳዓ አንጃዎች የተለያዩ ማምታቻዎችን እያዩ ምንም አይመስላቸውም። በሱናና በዓቂዳህ ከሚመሳሰለው ወንድሙ ዘንድ ግን አንድ #የኢጅቲሃድ ( ልዩነትን የሚያስተናግድ) ነጥብ ካየ እጅጉን ይቃወማል፣ጉዳዩንም ያተልቀዋል እንዲሁም ይህን መታገል ትልቁ #ጂሀድ ያስመስለዋል። ይህ ሚስኪን በዚህ በር በመግባት ሰለፊዮችን ይበታትናል።ያለበት መንገድ ጥርት ያለች ሰለፊይነትም ትመስለዋለች። እውነታው ግን የሰለፊዎችን አንድ መስመር እየሰነጠቀ ነው። ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስለ መለያየት በተናገሩ ጊዜ ያሉትን አስተውሉ። መለያየትን "የ ም ት ላ ጭ" ብለው ሰየሟት። "ፀጉር የምትላጭ ማለቴ አይደለም። ነገር ግን ዲንን ነው የምትላጨው " ብለዋል። ➜ ወደ አኼራ የሄዱ የዘመናችን ዑለማኦች እንደ እነ ሸይኽ አልባኒ፣ ሸይኽ ኢብን ባዝ፣ሸይኽ ኢብኑ ኡስይሚን እና ሸይኽ ሙቅቢል አላህ ይዘንላቸውና ይህንን ኡማ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ብዙ ጥረት አድርገዋል። አላህ ምስጋና ይገባውና ሱናም ይፋ ሆነች።ወዳጅ ይቅርና ተቀዋሚ እንኳን ራሱን ወደዚህ መንሃጅ ሲያስጠጋ ይደሰት ይኮራም ነበር። ........ በጣም በሚያሳዝን መልኩ ግን አንዳንድ ወንድሞች መጥተው ( ይህንን መንገድ ) ጥፍሩን ቆረጡት ክንፋንም ሰበሩት አፈር ውስጥም መቅበር ፈለጉ።በማያውቁት ሁኔታ #የሐቅ ጀመዓዎችን መቅበር ጀመሩ። እነሱ ጋር ያለው የእጅቲሓድ ነጥብ በሙሉ ስሙን ቀይረው ቀዋዒድ ( መርህ) ብለው ይጠሩትም ጀመሩ። እነ እንትና የቢዳዓ ሰዎችን መርህ ወይም ቃዒዳ አለው ይላሉ። ነገር ግን እነ እንትና ጋር ያለው የቢዳዓ ሰዎች መርሕ ምንድን ነው??? ሲባል ዝም ይላሉ። ወንድሞች እውነታው ግን እኛ የሚያስተሳስረን የሰለፎች፣ የአንሷሮችና የሙሃጅሮች ዓቂዳህ ነው።እዚሁ ላይ ነው ውዴታና ጥላቻ የሚገነባው። እነዚህ ሰዎች ግን ጥላቻና ውዴታቸውን መሰረት የሚያደርጉት ➜#የኢጅቲሀድ ነጥብ ላይ ነው። ከእነሱ መካከል አንዱ ሌላ ሰው ላይ ከተናገረ ከእሱ ጋር ካልተስማማህ ከተናገረበት ሰው ጋር ይለጥፍሀል። ➜ እንዲህ አይነቱን አካሄድ የትኛው ዲን ላይ ነው ያገኛችሁት??? ➜ የአንተ ንግግር ራሱ እኮ ኢጅቲሀድ ነው።ምን አልባትም አላህ ዘንድ ተሳሳች ነህ በጣም የሚገርም ነዉ?! ያም ሆነ ይህ እነዚህ በዘመናችን ብቅ ያሉ ሰዎች በጣም በሚያዝነው መልኩ እነዚያ ጥርሳቸው የሚሰብሩላቸውና ጥፍራቸውን ሊቆርጡላቸው የሚችሉ ዑለማዖዎች በነበሩበት ዘመን አልነበሩም።ዛሬ ብቅ አሉ እንጂ። እነዚህ ሰዎች ሶስት አይነት ሰዎች ናቸው። 1ኛ፦ ያልተማሩ ተራ ሰለፊዮች፦እነዚህ ደግሞ በፊት ያልነበሩ አዲስ ትውልዶች ናቸው።አህለል ሱናዎች ላይ ካልዘመቱ አህለል ሱና የማይሆኑ መሰሏቸዋል። እነሱ ብቻ አህለል ሱና ሌላው በአጠቃላይ የቢዳዓ ባለቤት በሚል ሰይመዋል። በጣም የሚያሳዝኑ ሚስኪን፣ መሰረት የሌላቸውና ጭፍን ተከታዮች ናቸው። 2ኛ፦መካከል ላይ ያሉ ራሳቸውን ወደ ሽይኽነት የሚያስጠጉ ዱዓቶች ናቸው። ይህንን መንገድ የሚከተሉት የመጣልና ዋጋ የማሳጣት ዘመቻ እንዳይደረግባቸው ፈርተው ነው። ካረፈች ገዳይ የሆነች ጨካኝ መዶሻ እንዳታርባቸው ፈርተህ ታዘዝ ሰላም ትሆናለህ አሉ። ለሚተቸው ሁሉ ታዛዥ ሁን " የሚል ነው። 3ኛ፦አደገኛው ነው። እነሱም፦ የዳዕዋ እንቅስቃሴ ነበራቸው። ነገር ግን ዳዕዋቸው ብዙም ተቀባይነትና እውቅናን አላገኘችም። እንደ መፍትሄ የውስዱት ሰዎችን የመተቸት ፣የማዋረድ ፣ ያለአግባብ የመናገር ማዕበል መከተል ነው። ያኔ እላይ ይሰቀላሉ።ተሰቀሉም። ኡለማኦች ያለፉበት የትግል፣ የሂፍዝ፣ የመማር፣የዒባዳህ መንገዶች ሳያልፉ በአንዴ ኡለማዕ ሆነው ተሰቀሉ። እነዚህ ግለሰቦች አካባቢያቸው ላይ ብቸኛ የጀርህ ወተዕድል መመለሻ ይሆናሉ። ➜ የጀርህና ተዕድል ኡለማዕ በሰለፎች ዘመን ጥቂቶች ነበሩ። ምክንያቱም ዘሀቢ እንደ ገለፁት "ሙሉ እውቀትና ሙሉዕ ጥንቃቄ ( ➜ ወረዕ) " ስለሚፈልግ ነበር።እነዚህ የዘመናችን ግን ብዙ ሆነው አረፋ። ይህ የሰለፎች እውቀትና ጥንቃቄ እነዚህ ዘንድ የት አለ??? ይህ ሶስተኛው አይነት ችግር ከአላህ እንጂ መፍትሄ  የለውም።ምክንያቱም በሽታው ያለው ልቡ ውስጥ ስለሆነ። የታይታና የይስሙልኝ ሰዎች ናቸው። ➜ቫይረስ ልብ ካጠቃ ዱዐ ከማድረግ ውጪ መፍትሄ የለውም። ወንድም እህቶች ሆይ! ከእነዚህ ሶስት አይነት ሰዎች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። 🎙️ ከሽይኽ አብዱል-መሊክ ረመዷኒ ንግግር የተወሰደ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ مَن قال في مؤمنٍ ما ليس فيهِ؛ أسكنَهُ اللهُ رَدغةَ الخَبالِ، حتى يخرُجَ ممَّا قالَ "በሙዕሚን ላይ የሌለበትን የ
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ مَن قال في مؤمنٍ ما ليس فيهِ؛ أسكنَهُ اللهُ رَدغةَ الخَبالِ، حتى يخرُجَ ممَّا قالَ "በሙዕሚን ላይ የሌለበትን የተናገረበት ሰው፤ ከተናገረው ነገር እስካልወጣ ድረስ አላህ ከጀሃነም ሰዎች አካል በሚወጣ የእዥና የመ^ግል አረንቋ ውስጥ ያኖረዋል።" [ሶሒሑ ተርጊብ፡ 2845] = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

"ሳታስመስሉ ለምትጠሉን ትልቅ ክብር አለን" የሚል የዓረበኛ ጥቅስ አነበብኩና እውነትም ክብር ይገባቸዋል አልኩኝ። አለሁልህ እያሉ ከጀርባ መውጋት ፣ እያሳሳቁ መንከስና በማር የተቀባ ፍቅር መሳይ በሽታን ከሚሰጡን ይልቅ፤ በግልጽ የሚገድለን ጠላት በስንት ጣዕሙ!። ለዚህ ይመስለኛል አል-ሙተነቢ የሚከተለውን ግጥም የቋጠረው ፦ ​ومن العداوة ما ينالك نفعه .. ومن الصداقة ما يضر ويؤلم t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

«አንተ አቡል ዐስ ሆይ፤ ለመሆኑ የእኛ መለያየት እንዲህ ቀለለህ?» አለችው... ይህች ቃል የነብዩ(ﷺ) ውድ ልጅ ዘይነብ፣ ለትዳር አጋሯ ለአቡል ዐስ ኢብኑ ረቢዕ የሰነዘረችው የናፍቆት ቃል ናት። የ
«አንተ አቡል ዐስ ሆይ፤ ለመሆኑ የእኛ መለያየት እንዲህ ቀለለህ?» አለችው... ይህች ቃል የነብዩ(ﷺ) ውድ ልጅ ዘይነብ፣ ለትዳር አጋሯ ለአቡል ዐስ ኢብኑ ረቢዕ የሰነዘረችው የናፍቆት ቃል ናት። የዘይነብ የሞት ሰዓት ሲቃረብ፣የአቡል ዐስ ዓለም በድቅድቅ ጨለማ ተዋጠ። የምድር ሕይወት ትርጉም አጥታ ታየችው። ሞቷን ሲሰማ የመነጨው ከባድ ለቅሶና ጩኸት፣ ልቡ ውስጥ የነበረውን ጥልቅ ፍቅርና የደረሰበትን የውስጥ ስብራት የሚያሳይ ነበር። ያዩትን ሁሉ የሚያዝኑት ታላቁ ነብይ (ﷺ) በአማቻቸው ከባድ ስቃይ ልባቸው ተነክቶ፣ በሩህሩህ እጃቸው እየዳበሱ ሊያፅናኑት ሞከሩ። እርሱ ግን እንባው እየጎረፈ፣ በሀዘን በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለ፦«ወላሂ አንተ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ያለ ዘይነብ ይህችን ዱንያ መኖር አልችልባትም!» አላቸው። በእርግጥም ያለ እርሷ መኖር አልቻለም። የልብ ስብራት፣ የናፍቆት እሳትና የፍቅር ቁስል ሰውነቱን ቀስ በቀስ አደከመው። ዘይነብ በሞተች በዓመቱ፣ እርሱም ይህችን ዓለም ተሰናብቶ ተከተላት። ◈ምን ማለት ፈልጌ መሰላችሁ...በፍቅር መጎዳትንና የመለያየትን ስቃይ መቼም ቢሆን ቀላል አድርገን ልንመለከተው አይገባም።ቀስ በቀስ ሰውን የሚያደክም፣ አልፎ ተርፎም ለህልፈት የሚዳርግ ኃይል አለው። አላህ በሃላሉ ያብቃቃችሁ! -- t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

ዛሬ ሰኔ 21 የሺ ደበሌ ሁዘይፍ መሰጅድ የተደረገ ሙሀደራ ርዕስ:ሱናን አጥብቆ መከተል በተለይ በሰሞኑ ቁርአንዮች ነን እያሉ ነገር ግን ከቁርአን ጋ የተራራቁ ሰለመሆናቸው የተዳሰሰበት ወሳኝ ደዕዋ በኡስታዝ ኢብኑ ምነወር አላህ ይጠብቀው ።

መልካም ሚስት.......! ብዙ አይነት እድለኛ ሰዎች ቢኖሩም ለኔ ግን መልካም ሚስት እንዳለችው ሰው የታደለ የለም ። ከላይ ከአሏህ የተፃፈች መልካም ሚስት ካለችህ  በየትኛውም  ሁኔታ ላይ  ሁነህ እንኳ ሙሉ ሰው ነህ ። የህይዎት  ውጣ ውረድ  እና ጉድለት ላንተ ምንም ናቸው ። ወጥተህ እስክትገባ በናፍቆት የምትጠብቅህ  ከውጭ ስትመጣ ደሞ በስስት እያየች ስቃ የምትቀበልህ  ስትናገር የምትረዳህ መልካም ሚስት ስትኖርህ  ችግርህ ድሎት ፣መድከምህ እረፍት፣ መክሰርህ ትርፍ ፣ ማጣትህ ማግኛት፣ ብሶትህ ደሞ  ደስታ ነው። ▸ በቃ መልካም ሚስት ጎንህ ካለች  ከቤት ውጭ ስቱል እንኳ የሚያጋጥሙህን ጥሩ ያልሆኑ አጋጣሚዎችን በቅፅበት ረስተህ  ወደ አዲስ የእፎይታ ስሜት ውስጥ ለመግባት  ፊቷን ማየት ብቻ በቂህ ነው። ▸መልካም ሚስት ማለት በህይዎትህ  ትልቅ ዋጋ ከምሰጣቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነውን ልጅ  ትወልድልህና  አይንህን ባይንህ ታሳይሀለች።  አለፍ ሲል ደሞ የወለደችልህን ልጆች በመልካም ባህሪዎቿ  እየኮተኮተች በፍቅር አሳድጋ ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰቡን  የሚያከብሩ ከመሆንም በላይ ለእስልምናቸው፣ ለተውሒዳቸው ፣ለሱናቸው የስምህ_መጠሪያ  የሚሆኑ ጥሩ ልጆች ባለቤት  ታደርግሀለች። መልካመሰ ሚስት ቤተሰቦችህን እና ጓደኞችህን ስለምትወድልህ  ከነሱ ጋር በቂ የሆነ ሰአት  ለመስጠትም ሆነ  ማደረግ ያለብህን ለማድረግ ስለማትቸገር  የቤተሰብህን ሀቅ_በመጠበቅ በኩል አትዘናጋም። መልካም ሚስት ማህበራዊ ህይዎት ላይ ያለህ ተሳትፎም አይቆረፍድብህም  እሷ ከምሰጥህ ፍቅር እና ደስታ በመነሳት በምትኩ አንተ የልጆችህን እና የሷን ሀቅ ለመጠበቅ ብለህ በምታደርጋቸው  የመልካም ነገር_ሩጫዎች ከፈጣሪህ ዘንድ  ትልቅ ደረጃ ታሰጥሀለች። መልካም ሚስት የእናት፣የአባትህን፣የእህት፣ወንድምህን  ቦታ ሳይቀር ተክታ በመያዝ ብቻዋን ሁና  ነገር ግን  ባለ ሙሉ ቤተሰብ እንደሆንክ እንዲሰማህ ታደርግሀለች። መልካም ሚስት ካለችህ ሁሉም ነገር አለህ  የመልካም ሚስት ደረጃዋ በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚወራ እና ተቆንጥሮ  የሚያልቅ  ነገር  አይደለም።   ለዛም ነውኮ.... መልካም ሚስት ከፈጣሪ የምትሰጥ  ልዩ ሰው ናት የሚባለው ።  ወንዶች መልካም "ባል" አድርጎን  መልካም ሚስት ይሰጠን ዘንድ እንማፀን። ሴቶች ደሞ  "ሚስት" ብቻ ሳይሆን መልካም_ሚስት  ሁናችሁ  "መልካም ባል" ታገኙ  ዘንድ ምኞቴ ነው። አለ አንዱ ✋

እኛ ሐሞታችን ፈሰሰ እንጂ የነብዩ ﷺ ዳዕዋ እንዲህ ነበር بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ، مِنْ مُحَمَّدٍ عَبْدِ اللَّهِ وَرَسُولِهِ، إِلَى هِرَقْلَ عَظِيمِ الرُّومِ: سَلَامٌ عَلَى مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَى، أَمَّا بَعْدُ، فَإِنِّي أَدْعُوكَ بِدِعَايَةِ الإِسْلَامِ، أَسْلِمْ تَسْلَمْ، يُؤْتِكَ اللَّهُ أَجْرَكَ مَرَّتَيْنِ، فَإِنْ تَوَلَّيْتَ فَإِنَّ عَلَيْكَ إِثْمَ الأَرِيسِيِّينَ. وَيَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَى كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَنْ لَا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئاً وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضاً أَرْبَاباً مِنْ دُونِ اللَّهِ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ. የነቢዩ ﷺ ደብዳቤ «በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። ከአላህ ባሪያና መልክተኛ ከሆኑት ሙሐመድ፥ ወደ ሮማውያን ታላቅ መሪ ወደ ሒረቅል። ቅኑን መንገድ (ሂዳያን) በተከተለ ሰው ላይ ሰላም ይሁን። ከዚህ በመቀጠል፦ እኔ በኢስላም ጥሪ ጥሪ አደርግልሃለሁ፤ እጅህን ስጥ (ሙስሊም ሁን) ሰላም ታገኛለህ፣ አላህም ምንዳህን (አጅርህን) ሁለት እጥፍ አድርጎ ይሰጥሃል። እምቢ ካልክና ፊትህን ካዞርክ ግን የገበሬዎችህና የሕዝቦችህ (የተከታዮችህ) ኃጢአት በአንተ ላይ ይሆናል። "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በኛና በእናንተ መካከል እኩል ወደሆነች ቃል ኑ፤ (እርሷም) አላህን እንጂ ሌላን እንዳናመልክ፣ በርሱም ምንንም እንዳናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ ጌቶች አድርጎ እንዳይዝ ናት" (በላቸው)። እምቢ ካሉም "እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ" በሏቸው።»

~ከ ሁለት ዓመት በፊት በ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ(AASTU) ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የተደረገ ምክር ቢጤ! ወንድም አቡ ሱፍያን t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/Sle_qelbachn1

‎وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنْتَ }أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ} " አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ »ሲል በተጣራ ጊዜ አስታውስ [አንቢያእ 83] ‎{وَزَكَرِيَّا إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا وَأَنْتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ} " ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ ሲል» ጌታውን በተጣራ ጊዜ አስታውስ [አንቢያእ 89] ‎{وَنُوحًا إِذْ نَادَىٰ مِنْ قَبْلُ فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ} " ኑሕንም ከዚያ በፊት ጌታውን በጠራ ጊዜ አስታውስ ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው!! እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን [አንቢያእ 76] ☞ አንተስ ወደ ማነው የምጮኸው!? ቴሌግራም👇

والله في عون العبد، ما كان العبد في عون أخيه -
الشيخ أ.د سليمان الرحيلي حفظه الله.

በነገራችን ላይ ለተሞ የሚመጥነው ከሙስጠፉ ጋር ሲጠዛጠዙ ነው ። የለተሞ አቻ ተሳዳቢ ሙስጠፋ መሆኑን አድምጡ ።

ሁሉም ሙአዚን ቢላልን አይሆንም። ደግሞ ሁሏም አፍቃሪ ዙለይኻን አይደለችም። ከአመታት በኋላ ወዳጁን አስታውሶ የእንባ ዘለላውን እያራገፈ ቃላት የሚያንቀውን ቢላል አውቀዋለሁ። ስራ ሆኖበት አዛን የሚለውንም አውቃለሁ። ዙለይኻንም አውቃታለሁ አላህ እንደገለፀው "ቀድ ሸጘፈሃ ሁበን" እብድ በሆነ ፍቅር ተለክፋ ለአመታት ያልተለወጠ ውዴታዋን።  እናም ብዙ ሰው እንደሚወድህ ቢነግርህም ሁሉም ሙአዚን ቢላል አይደለም። ቢላልን ፈልገው። ዙለይኻንም አትርሳት። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

ሸይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን ቢን ዐብዲላህ አል-ፈውዛን ልጅ የላቸውም ነገር ግን እውነተኛ ውርስ ልጅ መውለድ ብቻ አይደለምና ለዓለም የሚተርፍ እውቀትን ትተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን አስተምረዋል። በጣም በርካታ ሸይኽነት ደረጃ ላይ የደረሱ ምሁራኖችንም አፍርተዋል። * ሸይኹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪታቦችን ከትበዋል። መጽሀፍቶቻቸው በዐለም ጫፍ ድረስ ተሰራጭተው የሚሊዬኖችን ዐቂዳ አሳምረዋል። ሸይኽ ፈውዛን ሲታወሱ ኢርሻድን ማስታወስ የተለመደ ነው። * ከሸይኽ ሙሀሐድ ቢን ዐብዱልወሀብ የዐቂዳ ኪታቦች ቀጥሎ እንደርሳቸው ኪታቦች ለዐቂዳ  መስተካከልና ማማር አስተዋፅኦ ያደረጉ ኪታቦች የማን ይሆኑ!? * ሸይኹ እጥር ምጥን ያሉ ቃላቶችን በመጠቀም ቁምነገሮችን ማስጨበጥ እጁግ ይችሉበታል። * ብቻ ሸይኹ በ አጭሩ…በኢስላሙ ዐለም  በመሪዎች፣ በተማሪዎችና በተራው ማህበረሰብ ዘንድ እንደ እርሳቸው ተቀባይነትን ያተረፈ ዓሊም የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። لا أجد غضاضة أن قلت بأن الشيخ العلامة صالح الفوزان - حفظه الله - مفتى عام المملكة العربية السعودية ، هو شيخ الإسلام في زماننا . وإمام الدنيا في وقته، وهو الجبل الشامخ الذي تكسرت فيه قرون أهل البدع والأهواء ومحارب الفرق المنحرفة حفظه الله ورعاه من كل مكروه وسوء. በሱና ያሸበረቀ ረዘም ያለ እድሜና ጤና አላህ ይስጣቸው🤲