የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 327
订阅者
+2824 小时
+307 天
-4230 天
帖子存档
4 330
🇵🇰🇮🇷🇺🇸⚡️ - "ፓኪስታን፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ውይይት ላይ፣ ባለቀ ሰዓትም ቢሆን እንድትሳተፍ ማድረግ እንደምትችል እርግጠኛ ነች" ሲል ሮይተርስ የፓኪስታን መንግስትን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
"ከኢራን አዎንታዊ ምልክት ደርሶናል። ነገሮች በመስመራቸው እየሄዱ ናቸው፣ ነገ ወይም ከአንድ ቀን በኋላ ውይይቱን ስንጀምር እዚህ እንዲገኙ እየሞከርን ነው" ማለቱን ሮይተርስ ጨምሮ ተናግሯል።
4 330
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 — Wall Street Journal እንደዘገበው፡ ወታደራዊ አማካሪዎች፣ የተከሰከሰውን የአሜሪካ ፖይለት ለማዳን በተወሰደው ነፍስ-አድን ዘመቻ ወቅት፣ ተገማች ያልሆነውን የትራምፕን ቁጣ በመፍራት ሆን ብለው ትራምፕን Situation Room ውስጥ እንዳይገባ አድርገው ነበር።
4 330
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 የኢራን ተደራዳሪ ልዑካን አባል የፓርላማ አባል ማህሙድ ናባቪያን - "በዛቻ፣ በጥቃት እና በተኩስ አቁም ጥሰት ጥላ ሥር፣ ከክፉ የአሜሪካ አገዛዝ ጋር መደራደር ትርጉም የለሽ ብቻ ሳይሆን ጎጂም ነው እናም ጠላት የበለጠ ስግብግብ እንዲሆን ያበረታታል።"
ለነገው የኢስላማባድ ድርድር አሜሪካ ልዑካኗን የላከች ቢሆንም፣ እስካሁን ኢራን ለመደራደር ፈቃደኛ ባለመሆኗ፣ ልዑካኖቿን እስካሁን አላከችም።
4 330
🇺🇸 አሜሪካ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት (The Supreme Court) ውሳኔ በኋላ፣ $166 ቢሊዮን ዶላር የትራምፕ ዘመን ታሪፍን ልትመልስ ነው።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት በዶናልድ ትራምፕ ስር የተሰበሰበውን $166 ቢሊዮን ዶላር ታሪፍ ለንግድ ድርጅቶች መመለስ ይጀምራል።
➡ ይህም፣ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ፣ ለንግድ ድርጅቶች ከተደረጉ ትልልቅ ክፍያዎች አንዱ ሆኖ በታሪክ እንዲመዘገብ አድርጎታል።
ከጥቂት ወራት በፊት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትራምፕ በገቢ ምርቶች ላይ የጫነው ታሪፍ ሕገ-ወጥ እንደሆነና በዚህ ጊዜ ውስጥ ድርጅቶች ለመንግስት ያለ አግባብ የከፈሉት ጭማሪ ክፍያ እንዲመለስ ወስኖ ነበር።
4 330
🇺🇸 PBS Reporter: "ኢራን በኢስላማባድ ድርድር ትሳተፋለች?"
ትራምፕ "አላውቅም፣ ግን እዚያ መገኘት አለባቸው።"
ጋዜጠኛ "ባይሆኑስ?
ትራምፕ "ያ ጥሩ ነው። ከተሳተፉ በጣም ጥሩ ነው፣ ካልተሳተፉም በጣም ጥሩ ነው።"
4 330
🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ NewYork Post - "በድርድሩ 'ይሄ ነው' የሚባል ለውጥ የሚመጣ ከሆነ፣ ከኢራን ከፍተኛ መሪዎች ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነኝ።"
4 330
- 🇮🇷 / 🇻🇦 አዲስ፡ በ'ሚናብ' እልቂት የተገደሉት የኢራን ትምህርት ቤት ሕፃናት ወላጆች፣ ለጳጳስ ሊዮ አሥራ አራተኛ በጻፉት ደብዳቤ ጳጳሱ በሰብአዊ መብቶች ላይ ላሳዩት አቋም አመስግነዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ 'ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ' ሆነው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
4 330
🇵🇱🇮🇱⚡️ - "የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራዶስላው ሲኮርስኪ የ IDF ወታደሮች ራሳቸው የጦር ወንጀል ፈጽመዋል። ሲቪል ፍልስጤማውያንን ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ታጋቾችም ገድለዋል።"
4 330
🇦🇪🫴🇺🇸💰- UAE ጦርነቱ ወራቶችን የሚፈጅ ከሆነ ለጦርነት ማለፊያ ትንሽ ገንዘብም ቢሆን አሜሪካ እንድትለቅላት ተማፀነች። ኤሜሬት ጥያቄዋን ለአሜሪካ የግምጃ ቤት ሃላፊ፣ Scott Bessent አቅርባለች።
የኢሚሬት የገንዘብ ፍሰት፣ ወደ ውጭ ነዳጅ መላክ ባለመቻሏ፣ ደርቋል።
4 330
🇺🇸🇮🇷⚡ - "አሜሪካ በሚቀጥሉት ቀናት ማዕቀብ የተጣለባቸውን የኢራን ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን፣ በዓለም ዙሪያ፣ በተለያዩ አካባቢዎች፣ በዓለም አቀፍ የውሃ መተላለፊያ መስመሮች ውስጥ ለመያዝ በዝግጅት ላይ ትገኛለች። በዚህም በመካከለኛው ምስራቅ አሁን ካለው እገዳ ባሻገር፣ እየተካሄደ ያለውን የባህር ኃይል እርምጃ ለማስፋፋት እቅድ አላት" - The Wall Street Journal.
4 330
🇺🇸 🇮🇷 የቀድሞ የዋይት ሀውስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ John Bolton - JD Vance ን ከኢራን ጋር ለመደራደር መላክ፣ ትራምፕ ከጦርነቱ መውጫ መንገድ እየፈለጉ ለመሆኑ ምልክት ነው። ኢራናውያን ደግሞ ይህንን ተረድተዋል። ኢራናውያን በዋይት ሀውስ ውስጥ ፍርሃት እንደነገሰ አሽትተዋል።
4 330
🇮🇷❗️የኢራን የዜና ወኪል Tasnim፡ በአሜሪካ ጦር ጥቃት የደረሰበት የኢራን መርከብ ከቻይና መጥቶ ወደ ኢራን እያመራ ነበር። የአሜሪካን ጥቃት ተከትሎ፣ የኢራን ጦር ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በርካታ የአሜሪካ ወታደራዊ መርከቦችን አጥቅቷል።
4 330
🇮🇱❌🇮🇷 የእስራኤል ምንጮች፡
ከኢራን ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለማደስ በጣም እየተቃረበን ነው። የእስራኤል ዋና አዛዥ ከኢራን ጋር ወደ ጦርነት ለመመለስ ጦሩ እንዲዘጋጅ መመሪያ ሰጥቷል።
4 330
🇮🇷❌🇺🇸🇮🇱የኢራን የዜና ወኪል Tasnim ኤጀንሲ፡ "ኢራን ለዳግም ጦርነት ተዘጋጅታለች፣ እና ባብ አል-ማንዳብ (ቀይ ባሕር የመን) አራምኮ (ሳዑዲ ዓረቢያ)፣ ያንቡ እና ፉጃይራ (ገልፍ አገሮች) ወደ ግጭት ቀጠና ይገባሉ።
4 330
- 🇰🇼 / 🇮🇷 አዲስ፡ በዓለም ላይ በጣም ዝነኛ እና በሰፊው የታወቀው የቁርዓን አንባቢ፣ ሚሻሪ ራሺድ አል-አፋሲ፣ 'የኢራን እና ከኢራን ጋር ያሉት እጆች ይጥፉ! እኛ የተውሂድ ሕዝብ ነን' በሚል ርዕስ ነሽዲ (ዝማሬ) አውጥቷል።
ነሺዳው፣ እንደ መሀመድ ቢን ሰልማን፣ መሀመድ ቢን ዛይድ እና ሃማድ አል ካሊፋ ላሉ የአረብ መሪዎች አድናቆትን ያቀርባል። ኢራን በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የምታደርገውን የበቀል ጥቃትም ይረግማል።
አል-አፋሲ ኩዌታዊ ሲሆን፣ የአረብ መሪዎችን፣ የአሜሪካንን እና የእስራኤልን ወንጀሎች ያለማቋረጥ የሚያሳንሰው አክራሪ ወሃቢ/መድኸሊ የእስልምና ቅርንጫፍ ተከታይ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙስሊም ባልንጀሮቹን በመተቸት እና በማውገዝ ላይ ጠንካራ ሆኗል።
በዩቲዩብ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች አንዱ አስተያየት ሰጪ እንዲህ ብሏል - 'በጋዛ በእነዚህ ሁለት ዓመታት ግድያ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ውስጥ 'የእስራኤልን እጅ ጥፋ' ስትል አንድም ጊዜ እንኳን አልሰማንም።'
አል-አፋሲ በሁሉም የእስልምና መተግበሪያ እና ድረ-ገጾች ላይ ፎቶው እንደ 'Default' የሚጠቀሙበት ታዋቂ ሰው ነው።
የቁርዓን ድህረ-ገጾች እና መድረኮች ይህንን ማጭበርበር ወዲያውኑ አውቀው ድምፁን ከመተግበሪያዎቻቸው ላይ ማስወገድ አለባቸው፣ ምንም አይነት ገቢም እንዳያገኝ ወይም ለአጠቃቀሙ ሽልማት እንዳያገኝ ሊደረግ ይገባዋል፣ ብለዋል አብዛኞቹ አስተያየት ሰጪዎች።
4 330
🇮🇱 🇱🇧 IDF አንድ ወታደሩ የክርስቶስን ሐውልት ማፍረሱን አምኖ፣ ይህ ተግባር ጦሩን እንደማይወክል እና የሲቪሊያን እና የሃይማኖት ተቋማትን ኢላማ ማድረግ መርሁ እንዳልሆነ አስታወቀ።
