ch
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

前往频道在 Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

显示更多
未指定国家未指定类别
4 316
订阅者
-824 小时
-117 天
-8230 天
帖子存档
🇮🇷 በጦርነቱ ምክኒያት ዘግይቶ የነበረው የታላቁ አያቶላህ ዐሊ ኻመኒይ የቀብር ሥነ-ስርዓት፣ በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረግ ይሆናል። ለዚህም ኢራን ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ ተዘግቧል። ተወ
+4
🇮🇷 በጦርነቱ ምክኒያት ዘግይቶ የነበረው የታላቁ አያቶላህ ዐሊ ኻመኒይ የቀብር ሥነ-ስርዓት፣ በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረግ ይሆናል። ለዚህም ኢራን ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ ተዘግቧል። ተወካዮቻቸውን ለቀብር ሥነ- ስርዓቱ የሚልኩ ሀገሮችም ታውቀዋል። ሥነ-ስርዓቱ በሳምንቱ መጨረሻ በቴህራን የሚደረግ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ፣ በቆም (የሺዓ ቅዱስ ከተማ)፣ በመሽሃድ እና በኢራቅ ይደረጋል ተብሏል። እንደ ፈረንጆች በ1989 በተደረገው የቀድሞ አያቶላህ ኮመኒይ የቀብር ሥነ-ስርዓት የወጣው የሕዝብ ብዛት በዓለም ታሪክ እስካሁን ሪከርድ የያዘ ነው። ያን ጊዜ 10.2 ሚሊዮን ሕዝብ ወጥቶ ነበር። ​
Russia China Türkiye India Pakistan Turkmenistan. Tajikistan. Iraq. Georgia. Armenia. Afghanistan. Oman. Qatar. Azerbaijan. Kyrgyzstan. Uzbekistan. Bangladesh. Egypt. Kazakhstan. Ghana. Nicaragua Congo. Serbia. Tunisia. Lebanon. Namibia. Malaysia. Cuba. Sri Lanka. Myanmar. Gambia. Thailand. ​
ኢትዮጵያን እንወክላት እንዴ ሄደን? ከአውቶቡስ ተራ ሦስት ባስ ነው፣ ከዛ በሆርሙዝ በኩል ቴህራን ዶሮ ማነቂያ።

🇷🇺🇺🇦⚡️ - የዩክሬን ኪየቭ ከንቲባ ትናንት ማታ ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ በከተማዋ ላይ ትልቁን ጥቃት እንዳደረገች ዘግቧል። የሟቾች ቁጥር እስካሁን በውል ገልታወቀም፣ ሁሉምም የከተማው
🇷🇺🇺🇦⚡️ - የዩክሬን ኪየቭ ከንቲባ ትናንት ማታ ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ በከተማዋ ላይ ትልቁን ጥቃት እንዳደረገች ዘግቧል። የሟቾች ቁጥር እስካሁን በውል ገልታወቀም፣ ሁሉምም የከተማው ወረዳዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል ብሏል። የዩክሬን አየር ሃይል እንደዘገበው፣ ሩሲያ ትናንት ማታ በዩክሬን ላይ 94 ሚሳኤሎችን እና 646 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ተጠቅማለች።

🇷🇺 የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር፡ የሩሲያ ጦር ኃይሎች፣ የኪየቭ አገዛዝ በሩሲያ ውስጥ በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ላደረሰው እና እያደረሰ ላለው የሽብር ጥቃት ምላሽ በመስጠት፣ ሌሊቱን እና አሁንም
+6
🇷🇺 የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር፡  የሩሲያ ጦር ኃይሎች፣ የኪየቭ አገዛዝ በሩሲያ ውስጥ በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ላደረሰው እና እያደረሰ ላለው የሽብር ጥቃት ምላሽ በመስጠት፣ ሌሊቱን እና አሁንም ድረስ ንጋቱን በቀጠለ፣ ከአየር፣ ከመሬት እና ከባህር ላይ፣ በጥምረት እና በተቀዳጀ መልኩ፣ በዩክሬን ዘርፈ ብዙ ኢላማዎች ላይ እርምጃ ወስዷል። በጥቃቱ ምክንያት በኪየቭ ከተማ እና በኪየቭ ክልል ውስጥ ያሉ ወታደራዊ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዞች፣ የኤሌክትሪክ ሰብ ስቴሽኖች፣ የነዳጅ እና የኢነርጂ ውስብስብ መገልገያዎች፣ እንዲሁም በዲኔፕሮፔትሮቭስክ, ፖልታቫ, ቼርካሲ, ቼርኒጎቭ እና ኪየቭ ክልሎች ውስጥ ያሉ ወታደራዊ አየር ማረፊያዎችና እና የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ተመትተዋል።

+1
🇷🇺⚡️🇺🇦 ኪየቭ፣ ሊነጋጋ ሲል በቀጠለው የሩሲያ ጥቃት፣ እየተቃጠለች ነው።

🇸🇩 - ያበደ ቀረጻ - በሰሜን ሱዳን ኮርዶፋን ግዛት፣ በኤል-ኦቤይድ ከተማ ዙሪያ፣ በጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ አብይ አሕመድ ዓሊ እና በኤሜሬት ሼክ የሚደገፈው የRSF ቡድን አማፂያኖች፣ በከተማው ዙሪያ በተኮለኮሉበት፣ አንዱ ተዋጊ፣ እራሱንና ጓደኞቹን በመቅረፅ ላይ እያለ በሱዳን መንግሥት ድሮን በተሰነዘረባቸው ጥቃት፣ ዶግ አመድ ሲሆኑ ታይተዋል። ቀራጭ፣ የመጨረሻ 'ሸሃዳውን' እየሳበ ሞቱንም ቀርጿል። ባሁኑ ሰዓትም፣ የሱዳን መንግሥት ጦር፣ የRSF አማፂያኖችን ከከተማው ዙሪያ እያባረራቸው ይገኛል።

🇸🇩 - ያበደ ቀረጻ - በሰሜን ሱዳን ኮርዶፋን ግዛት፣ በኤል-ኦቤይድ ከተማ ዙሪያ፣ በጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ አብይ አሕመድ ዓሊ እና በኤሜሬት ሼክ የሚደገፈው የRSF ቡድን አማፂያኖች፣ በከተማው ዙሪያ በተኮለኮሉበት፣ አንዱ ተዋጊ፣ እራሱንና ጓደኞቹን በመቅረፅ ላይ እያለ በሱዳን መንግሥት ድሮን በተሰነዘረባቸው ጥቃት፣ ዶግ አመድ ሲሆኑ ታይተዋል። ቀራጭ፣ የመጨረሻ 'ሸሃዳውን' እየሳበ ሞቱንም ቀርጿል። የሱዳን መንግሥት ጦር፣ የRSF አማፂያኖችን ከከተማው ዙሪያ እያባረራቸው ይገኛል።

🇵🇱🇺🇦⚡️ - የፖላንድ መከላከያ ሚኒስትር፣ ዩክሬን የድሮን ቴክኖሎጂዋን ለማካፈል ፈቃደኛ ባለመሆኗ የተነሳ፣ ቀደም ሲል በፖላንድ ፕሬዝዳንት ቃል ተገብቶላት የነበረውን MIG-29 የጦር ጀቶችን ከፖላንድ እንደማታገኝ አስታወቀ። "ለዩክሬን፣ በአጋርነት ላይ የተመሰረተ አካሄድ ነው ብዬ የማምነውን ሐሳብ አቅርቤ ነበር፣ በድሮኖች ምትክ ሚግ ጀቶችን። ዩክሬናውያን መጀመሪያ ላይ ተስማምተው ነበር፣ ነገር ግን በኋላ ላይ እያወላወሉ የሚጠበቅባቸውን ሳያሟሉ ቀርተዋል። ስለዚህ ለዩክሬን ሚግ አይኖርም" - የፖላንድ መከላከያ ሚኒስትር Władysław Kosiniak-Kamysz.

🇵🇸 የፍልስጤም ግብ ጠባቂ፣ ሳሊም አል-አሽካር፣ በጋዛ በእስራኤል ጦር ተገድሏል። ⚫ የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር አል-አሽካር በእስራኤል ተኩስ መገደሉን ገልጿል። ከጥቅምት 2024 ጀምሮ ከ100
🇵🇸 የፍልስጤም ግብ ጠባቂ፣ ሳሊም አል-አሽካር፣ በጋዛ በእስራኤል ጦር ተገድሏል። ⚫ የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር አል-አሽካር በእስራኤል ተኩስ መገደሉን ገልጿል። ከጥቅምት 2024 ጀምሮ ከ1000 በላይ የፍልስጤም አትሌቶች በእስራኤል ተገድለዋል።

+5
🇷🇺⚡️🇺🇦 ኪየቭ ከከፍተኛ ጥቃት በኋላ በእሳት ተቃጥላለች። አዳዲስ ተጨማሪ ሚሳኤሎችም ወደ ዒላማቸው እያመሩ ነው። ▪️75 ድሮኖች በኪየቭ ላይ እየበረሩ ናቸው። ▪️ቢያንስ 30 ባለስቲክ ሚሳኤሎች የዩክሬን ዋና ከተማ ላይ ወድቀዋል። ▪️በተጨማሪም ወደ 20 የሚጠጉ የክሩዝ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ ባሁኑ ሰዓት እየተቃረቡ ናቸው። ▪️የመጀመሪያዎቹ "ካሊበርስ" እና X101 የተባሉ ሚሳኤሎች ቀድሞውኑ በሀገሪቱ መሃል ላይ ይገኛሉ። የከተማው ነዋሪዎች በምድር ባቡር ጣቢያዎች፣ እንዲሁም በአደጋ ጊዜ መጠለያዎች ተጠልሏል።

+4
🇷🇺⚡️🇺🇦 ኪየቭ ከከፍተኛ ጥቃት በኋላ በእሳት ተቃጥላለች። አዳዲስ ተጨማሪ ሚሳኤሎችም ወደ ዒላማቸው እያመሩ ነው። ▪️75 ድሮኖች በኪየቭ ላይ እየበረሩ ናቸው። ▪️ቢያንስ 30 ባለስቲክ ሚሳኤሎች የዩክሬን ዋና ከተማ ላይ ወድቀዋል። ▪️በተጨማሪም ወደ 20 የሚጠጉ የክሩዝ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ ባሁኑ ሰዓት እየተቃረቡ ናቸው። ▪️የመጀመሪያዎቹ "ካሊበርስ" እና X101 የተባሉ ሚሳኤሎች ቀድሞውኑ በሀገሪቱ መሃል ላይ ይገኛሉ።

🇷🇺⚡️🇺🇦 ዩክሬን በበኩሏ፣ ወደ ሩሲያ ግዛት 450 የድሮን መንጋዎችን በአሁኑ ሰዓት ልካለች ተብሏል።
🇷🇺⚡️🇺🇦 ዩክሬን በበኩሏ፣ ወደ ሩሲያ ግዛት 450 የድሮን መንጋዎችን በአሁኑ ሰዓት ልካለች ተብሏል።

🇹🇷❌🇮🇱 - የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን፡
እስራኤል አሁን ባላት አስተዳደር፣ ጥሬ እቃዋ ደም እና እንባ ብቻ የሆነ የአፍራሽ ፋብሪካ ሆናለች፣ አለመረጋጋት እና ትርምስ ካልሆነ በስተቀር ምንም አታመርትም። ደም እንዳሸተቱ ሻርኮች ቀጠናችንን  የሚያጠቁ፣ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ላፈሰሱት ደም ተጠያቂ ይሆናሉ። ሰማያትን የሚያናውጠው የጭቁኖች ጩኸት፣ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ጨቋኞችን ይይዛል። ዛሬ የሂትለርን ፈለግ የሚከተሉ ሰዎች በዚህ መንገድ ከቀጠሉ እጣ ፈንታቸው በታሪክ ውስጥ ከሌሎች አምባገነኖች ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆን መዘንጋት የለባቸውም።
በሁለቱ ሀገሮች መካከል፣ የቃላት ጦርነቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ኤርዶጋንን "በጣም ተብተሃል፣ አርፈህ ብትቀመጥ ይሻለሃል" ብሎት እንደነበር ይታወቃል።

🇹🇷❌🇮🇱 - የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን፡
እስራኤል አሁን ባላት አስተዳደር፣ ጥሬ እቃዋ ደም እና እንባ ብቻ የሆነ የአፍራሽ ፋብሪካ ሆናለች፣ አለመረጋጋት እና ትርምስ ካልሆነ በስተቀር ምንም አታመርትም። ደም እንዳሸተቱ ሻርኮችቀጠናችንን  የሚያጠቁ፣ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ላፈሰሱት ደም ተጠያቂ ይሆናሉ። ሰማያትን የሚያናውጠው የጭቁኖች ጩኸት፣ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ጨቋኞችን ይይዛል። ዛሬ የሂትለርን ፈለግ የሚከተሉ ሰዎች በዚህ መንገድ ከቀጠሉ እጣ ፈንታቸው በታሪክ ውስጥ ከሌሎች አምባገነኖች ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆን መዘንጋት የለባቸውም።
በሁለቱ ሀገሮች መካከል፣ የቃላት ጦርነቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ኤርዶጋንን "በጣም ተብተሃል፣ አርፈህ ብትቀመጥ ይሻለሃል" ብሎት እንደነበር ይታወቃል።

🇷🇺⚡️ሩሲያ፣ ከተለያየ አቅጣጫ ወደ 13 የሚጠጉ ረጅም ርቀት ቦንብ ጣይ አይሮፕላኖች በዚህ ሰዓት ወደ ዩክሬን መላኳ ታውቋል። አይሮፕላኖቹ፣ ዩክሬን ግዛት ከ 1ሰዓት ተኩል በኋላ ይደርሳሉ ተብሎ
🇷🇺⚡️ሩሲያ፣ ከተለያየ አቅጣጫ ወደ 13 የሚጠጉ ረጅም ርቀት ቦንብ ጣይ አይሮፕላኖች በዚህ ሰዓት ወደ ዩክሬን መላኳ ታውቋል። አይሮፕላኖቹ፣ ዩክሬን ግዛት ከ 1ሰዓት ተኩል በኋላ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

🇮🇳🇷🇺 ሩሲያ፣ በኃይል መሠረተ ልማቶቿ ላይ፣ በዩክሬን ጥቃቶች በደረሰባት ውድመት ምክኒያት የተፈጠረውን የነዳጅ እና የጋዝ እጥረት ለማካካስ፣ ከሕንድ 60 ሺ ሜትሪክ ቶን ዘይት ማስገባቷ ታወቀ
+1
🇮🇳🇷🇺 ሩሲያ፣ በኃይል መሠረተ ልማቶቿ ላይ፣ በዩክሬን ጥቃቶች በደረሰባት ውድመት ምክኒያት የተፈጠረውን የነዳጅ እና የጋዝ እጥረት ለማካካስ፣ ከሕንድ 60 ሺ ሜትሪክ ቶን ዘይት ማስገባቷ ታወቀ። እንደ ሮይተርስ ዘገባ፣ ሩሲያ በጋዝ እና በነዳጅ ኢንድስትሪዎቿ ላይ እየደረሰባት ባለው ውድመት የተነሳ፣ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቷ ተገልጿል። እስከ ትናንት ድረስ በርካሽ ዋጋ ለሕንድ ነዳጅ ትሸጥ የነበረችው ሩሲያ፣ ዛሬ ላይ መልሳ ከሕንድ ለማስገባት ተገድዳለች፣ ሲል አክሏል። ሩሲያ፣ ከበርካታ ሀገሮች በወር እስከ 400 ሺ  ቶን ዘይት ለማስገባት እየተነጋገረች ነው።

❗️🇺🇦 ዘሌንስኪ፣ በሩሲያ ፌዴሬሽን የዛሬ ምሽት ከፍተኛ የጥቃት ስጋት ምክንያት፣ የአየርላንድ ጉብኝቱን አቋርጦ ወደ ዩክሬን ተመልሷል። ፕሬዚዳንቱ፣ ከአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በጋራ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ከዩክሬን የደህንነት አካላት መረጃ ከተቀበለ በኋላ፣ እሱና ቡድኑ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ ዩክሬን ሊመለሱ መሆናቸውን ተናግሯል።

🇺🇸🇵🇦⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ AI ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልትን "የፓናማ መተላለፊያ ቦይን እንደ ታላቅ ስኬትዎ ይቆጥሩታልን?" በማለት በሰሜን ዳኮታ በሚገኘው የቴዎዶር ሩሰቬል ቤተ መፃህፍት በመገኘት ጠይቆታል። ሩሰቬልትም፣ "የተከበሩ ፕሬዝዳንት፣ ነርቭዎን ይጠብቁ እና ሀገራችን እንደምትቀድም ያስታውሱ" ብሎታል በመልሱ።

🇺🇸 ጥያቄ፡ የፋይናንስ ዶክሜንትዎ ባለፈው ዓመት በጣም ትርፋማ ዓመት እንዳሳለፉ ያሳያል። ይህ ለአማካይ አሜሪካውያን ምን መልእክት ያስተላልፋል? ትራምፕ፡ ምኑን ከምኑ ለማገናኘት ነው የምትሞክሪው? አሳምረሽ ታውቂያለሽ በእዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ ጣልቃ እንደማልገባ። ገንዘቤን የሚያስተዳድር የራሴ ፈንድ ያሉኝ ሰው ነኝ። ጥያቄ፡ ግን ተጠቃሚ ነህ። እየተነጋገርን ያለነው በቢሊዮን ስለ ሚቆጠር ዶላር ነው። ትራምፕ፡ ፕሬዝዳንት ከመሆኔ በፊት ብዙ ገንዘብ አግኝቻለሁ።ገንዘቡን አይተሻል? እኔኮ ሀብታም ሰው ነኝ።

+2
🇿🇦⚡️በደቡብ አፍሪካ፣በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ፀረ ስደተኛ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች በመደረግ ላይ ናቸው። ሰልፈኞቹ፣ ሰነድ-አልባ እና ሕገ ወጥ ስደተኞች በአፋጣኝ ደቡብ አፍሪካን ለቅቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል። ፖሊስ፣ እስካሁን 900 ሰልፈኞችን በቁጥጥር ሥር ማድረጉን እና ከእንግዲህ ወዲያ እንዲህ ያሉ ሕገ-ወጥ ሰልፎችን እንደማይታገስ ተናግሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ፣ በብዛት ቂጣቸውን የጣሉ፣ በነጮችና በመንግሥታቸው የተናቁ እና በገዛ ሀገራቸው በሥራ እና በኑሮ በተለወጡ አፍሪካዊያን ስደተኞች የሚቀኑ፣ በብዛት የዙሉ ጎሳ አባላት የሆኑ ደቡብ አፍሪካዊያን፣ ላሉበት ችግር እነዚህን ስደተኞች እንደ ምክኒያት በመጥቀስ፣ በተለያየ ጊዜ ጥላቻዊ ጥቃቶችን ሲያደርሱ ይስተዋላሉ። በአንዳንድ ቦታዎች፣ ጥቃቶችን እና ዛቻዎችን በመፍራት፣ ብዛት ያላቸው ሀገሩን ለቅቀው ለመውጣት የፈለጉ አፍሪካዊያን ስደተኞች ጓዛቸውን ይዘው በየመንገዱ ታይተዋል።

+1
🇿🇦⚡️በደቡብ አፍሪካ፣በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ፀረ ስደተኛ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች በመደረግ ላይ ናቸው። ሰልፈኞቹ፣ ሰነድ-አልባ እና ሕገ ወጥ ስደተኞች በአፋጣኝ ደቡብ አፍሪካን ለቅቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል። ፖሊስ፣ እስካሁን 900 ሰልፈኞችን በቁጥጥር ሥር ማድረጉን እና ከእንግዲህ ወዲያ እንዲህ ያሉ ሕገ-ወጥ ሰልፎችን እንደማይታገስ ተናግሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ፣ በብዛት ቂጣቸውን የጣሉ፣ በነጮችና በመንግሥታቸው የተናቁ እና በገዛ ሀገራቸው በሥራ እና በኑሮ በተለወጡ አፍሪካዊያን ስደተኞች የሚቀኑ፣ በብዛት የዙሉ ጎሳ አባላት የሆኑ ደቡብ አፍሪካዊያን፣ ላሉበት ችግር እነዚህን ስደተኞች እንደ ምክኒያት በመጥቀስ፣ በተለያየ ጊዜ ጥላቻዊ ጥቃቶችን ሲያደርሱ ይስተዋላሉ። በአንዳንድ ቦታዎች፣ ጥቃቶችን እና ዛቻዎችን በመፍራት፣ ብዛት ያላቸው ሀገሩን ለቅቀው ለመውጣት የፈለጉ አፍሪካዊያን ስደተኞች ጓዛቸውን ይዘው በየመንገዱ ታይተዋል።