ch
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

前往频道在 Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

显示更多
未指定国家未指定类别
4 303
订阅者
+824 小时
-47 天
-7130 天
帖子存档
⚡🇮🇱🇱🇧 በኢንተርኔት ላይ እየተሰራጨ ያለው ምስል፡ አንድ እስራኤላዊ ወታደር በዴቤል ሊባኖስ የክርስቲያን መንደር ውስጥ በሃውልቱ አፍ ሲጋራ በማስገባት የድንግል ማርያምን ሃውልት ሲያረክስ የሚ
⚡🇮🇱🇱🇧 በኢንተርኔት ላይ እየተሰራጨ ያለው ምስል፡  አንድ እስራኤላዊ ወታደር በዴቤል ሊባኖስ የክርስቲያን መንደር ውስጥ በሃውልቱ አፍ ሲጋራ በማስገባት የድንግል ማርያምን ሃውልት ሲያረክስ የሚያሳይ ነው። IDF የፎቶውን ስርጭት ተከትሎ ክስተቱን እየመረመረ መሆኑን ገልጿል። ጉዳዩ የመጣው በዚያው መንደር ውስጥ አንድ የእስራኤል ወታደር የኢየሱስ ክርስቶስን ሐውልት በመዶሻ ሲያፈርስ ከተቀረጸና እስራኤል ዓለም አቀፍ ውግዘትን ካስተናገደች ከሳምንታት በኋላ ነው። ለዚያኛው ክስተት የእስራኤል መንግሥት ለመላው ሕዝበ-ክርስቲያን በይፋ ይቅርታ ጠይቆ ወታደሩን በሕግ እንደሚጠይቅ ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል።

⚡️🇺🇸🇮🇷 U.S. ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ስምምነት ላይ ትደርስ ዘንድ የአንድ ሳምንት የጊዜ ገደብ መስጠቱ ታወቀ Fox News. ትራምፕ እንዳለው፣ ይሄ፣ ወደ ሆነ ተጨባጭ ነገር እንደሚያመራው እና በዘላቂነት አንድ ነገር እንደሚያመጣ ያምናል።

 🇺🇸 /🇮🇷/ 🇮🇱 ትኩስ፡ የእስራኤል ምንጭ ለCNN፡ አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ ለማንሳት በቁም ነገር እያሰበችበት ነው፣ እና እስራኤል ስለ ጉዳዩ 'አሳስቧታል።'

🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለPBS 'የኢራን የበለፀገ ዩራኒየም ወደ አሜሪካ ይመጣል። ኢራን ከእኛ ጋር ከተስማማች ነገሩ ያበቃል ካልተስማማች በአናቷ ላይ ቦምብ ማፈንዳታችንን እንቀጥላለን።'

🚜 🚢 🌾 የኢነርጂ ቀውሱ በፍጥነት ወደ ምግብ ቀውስ እየተቀየረ ነው። - 30% የዓለም የማዳበሪያ ምርት ጠፍቷል። - 20% የአለም LNG (Gas) ምርት ጠፍቷል። - ማዳበሪያ በተፈጥሮ ጋዝ ላይ
🚜 🚢 🌾 የኢነርጂ ቀውሱ በፍጥነት ወደ ምግብ ቀውስ እየተቀየረ ነው። - 30% የዓለም የማዳበሪያ ምርት ጠፍቷል። - 20% የአለም LNG (Gas) ምርት ጠፍቷል። - ማዳበሪያ በተፈጥሮ ጋዝ ላይ የተመሰረተ ነው። - ~ አሁን ላይ 50% የሚሆነው የዓለም የምግብ ምርት፣ በማዳበሪያ ላይ የተመሰረተ ነው። ~ 40% የጋዝ ፍላጎት ውድቀት የሚከሰተው፣ ከማዳበሪያ ኢንዱስትሪዎች መዘጋት ጋር ነው። ስለዚህ፣ የኃይል ገበያውን ሚዛናዊ ለማድረግ፣ በግልፅ እንደሚታየው፣ የምግብ ምርትን እያጠፋን ነው። በየቀኑ ሆርሙዝ ተዘግቶ በቆየ ቁጥር፣ ወደ ክልላዊ ረሃብ አንድ እርምጃ እንቀርባለን! 📎 Haaretz

📢 🇺🇸 🇮🇷 ኢራን "የተስማማንበትን "አሳልፋ ለመስጠት" ፈቃደኛ ካልሆነች፣ የአሜሪካ ድብደባ ከባለፈው ጊዜ በላይ ተጧጡፎ የሚቀጥል ይሆናል፣ ትራምፕ። 📎 Faytuks News
📢 🇺🇸 🇮🇷 ኢራን "የተስማማንበትን "አሳልፋ ለመስጠት" ፈቃደኛ ካልሆነች፣ የአሜሪካ ድብደባ ከባለፈው ጊዜ በላይ ተጧጡፎ የሚቀጥል ይሆናል፣ ትራምፕ። 📎 Faytuks News

🇮🇷 | የ IRGC የባሕር ኃይል በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ማለፍን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል
- በፋርስ ባሕረ ሰላጤ እና በኦማን ባሕረ ሰላጤ የሚገኙ ካፒቴኖችን እና የመርከብ ባለቤቶችን፣ የኢራንን የሆርሙዝ ባሕር ደንቦችን በማክበራቸው እና ለክልላዊ የባሕር ደህንነት አስተዋፅዖ በማድረጋቸው እናመሰግናለን። የወራሪዎች ዛቻ ተመትቶ ሲወገድ እና አዲስ ፕሮቶኮሎች ሲኖሩ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተረጋጋ ማለፊያ በሆርሙዝ በኩል ይረጋገጣል።

🇮🇷 🇺🇸⚡️ — Tasnim የኢራን መገናኛ ብዙሃን፡
"Freedom Project" የተባለው የትራምፕ ዘመቻ ያሳካቸው፡ — የ US የጦር መርከብ በበርካታ ሚሳዬሎች መመታት። — ካልታወቀ አካል የ UAE ፋጁራ ወደብ መጠቃት። — በአሜሪካ የነዳጅ ዋጋ መናር።

🇺🇸🇮🇷⚡️- ሰበር: ፕሬዝዳንት ትራምፕ እሁድ ዕለት አውጆት የነበረውን እና “Project Freedom” ብሎ የሰየመውን፣ መርከቦችን አጅቦ የማለፉን መርሃ-ግብር፣ ለጊዜው፣ "ለዘላቂ ሰላም ዕድ
🇺🇸🇮🇷⚡️- ሰበር: ፕሬዝዳንት ትራምፕ እሁድ ዕለት አውጆት የነበረውን እና “Project Freedom” ብሎ የሰየመውን፣ መርከቦችን አጅቦ የማለፉን መርሃ-ግብር፣ ለጊዜው፣ "ለዘላቂ ሰላም ዕድል ለመስጠት ሲባል" በሚል እንደተወው ተናገረ። ከኢራን ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግጭቱን በሰላም ለመቋጨት የሚቻልበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፣ ብሏል።

🇸🇩🇪🇹🇦🇪⚡ - ሱዳን ኢትዮጵያን እና UEA ን በካርቱም አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል ስትል ከሰሰች "ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ያደረጉት ነገር በሱዳን ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ነው፣ እናም ዝም ተብሎ የሚታለፍ አይሆንም!" - የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ‹"ኃይላችን ማንኛውንም አደጋ ለመቋቋም ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነው›"

🇸🇩🇪🇹🇦🇪⚡ - Rapid Support Forces በደቡብ ሱዳን ራባክ አቅጣጫ በኮስቲ ከተማ በሚገኝ የነዳጅ መጋዘን ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቶችን ሰንዝረዋል። የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ከኢትዮጵያ የመጡ ናቸው ብለዋል። በጥቃቱ ሦስት ሰዎች ተገድለዋል።

—❗️🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ: ካርጎ መርከብ አሁን በዚህ ሰዓት በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ባልታወቀ መሳሪያ ተመትቶ በእሳት ተያይዟል– UKMTO
—❗️🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ: ካርጎ መርከብ አሁን በዚህ ሰዓት በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ባልታወቀ መሳሪያ ተመትቶ በእሳት ተያይዟል– UKMTO

🇸🇦🇸🇩⚡️🇪🇹 የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሱዳን ላይ ጥቃት የሚያደርሱት ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) መነሻቸው ከኢትዮጵያ መሆኑ ይታወቅልኝ፣ ብሏል። - ከሱዳን ጋር አጎራባች ሀገራት ግዛቶቻቸውን በሱዳን ላይ ለጥቃት ማስጀመሪያ እንዳይጠቀሙ ራሳቸውን ይፈትሹ፣ ስትል አስጠንቅቃለች።

🇮🇷⚡️- ሰበር: ኢራን የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥን በተመለከተ አዲስ አስተዳደራዊ አሠራርን መዘርጋቷን አስታወቀች። መርከቦች ከማለፋቸው በፊት የኢሜል መልዕክት እና ትእዛዝ ከኢራን የሚደርሳቸው ይሆና
🇮🇷⚡️- ሰበር: ኢራን የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥን በተመለከተ አዲስ አስተዳደራዊ አሠራርን መዘርጋቷን አስታወቀች። መርከቦች ከማለፋቸው በፊት የኢሜል መልዕክት እና ትእዛዝ ከኢራን የሚደርሳቸው ይሆናል፣ ያንን ተከትለው ለማለፍ የሚችሉበት አሠራር እውን ሆኗል ስትል ተናግራለች በመግለጫዋ ይህን ኢራን "የፋርስ ባሕረ-ሰላጤ የባሕር አስተዳደር" የሚል ስያሜ ሰጥተዋለች።

🇮🇷⚡️የኢራን ወታደራዊ ኮማንድ (ካቲመል አንቢያ)፣ በትናንቱ የኤሜሬት ድብደባ እጁ እንደሌለበት ተናገረ። "ያጠቃነው እኛ ቢሆን፣ ችግር የለብንም፣ ወጥተን እንናገራለን። በትናንትናው ዕለት ኤሜሬት
🇮🇷⚡️የኢራን ወታደራዊ ኮማንድ (ካቲመል አንቢያ)፣ በትናንቱ የኤሜሬት ድብደባ እጁ እንደሌለበት ተናገረ።
"ያጠቃነው እኛ ቢሆን፣ ችግር የለብንም፣ ወጥተን እንናገራለን። በትናንትናው ዕለት ኤሜሬትን ኢራን አላጠቃችም
ብሏል።

🇦🇪🇺🇳 - የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን አስመልክቶ ዝግ የምክክር ስብሰባ ያካሂዳል። ኢራን ትናንት በኤሜሬት ለደረሰው ጥቃት፣ ዛሬ ዘግይታ ባወጣችው መግለጫ፣ ኃላፊነት እንደማትወስድ እና ጦሯ ምንም ዓይነት ጥቃት እንዳልፈፀመ ተናግራለች። ኤሜሬትንም  ያለ ምንም ማስረጃ ለጥቃቱ ኢራንን በመክሰሷ አውግዛለች። የተባበሩት አረብ ኤሜሬትን በሚሳዬሎች የደበደበው ማን እንደሆነ አልታወቀም።

- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን የባለስቲክ ሚሳኤል መርሃ ግብር ስለመገደብ በተመለከተ፣ አቋሙን ላላ አድርጓል - 'አዎ፣ ሚሳኤሎች መጥፎ ናቸው፣ ቢሆንም ግን እሱ አሁን አያሳስበንም
- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን የባለስቲክ ሚሳኤል መርሃ ግብር ስለመገደብ በተመለከተ፣ አቋሙን ላላ አድርጓል -
'አዎ፣ ሚሳኤሎች መጥፎ ናቸው፣ ቢሆንም ግን እሱ አሁን አያሳስበንም። የእኛ ዋና ጉዳይ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሊኖራት እንዳይችል ማድረግ ነው።' 

- 🇺🇸 / 🇮🇷 የአሜሪካ የጦር ሚኒስትር ፒት ሄግሴት - አሜሪካ ለዓለም ስጦታ ይሆን ዘንድ በሆርሙዝ ባሕር ላይ ኃይለኛ እና የማይሰበር ቀይ፣ ነጭ እና ሰማያዊ ጥላ ዘርግታለች። በመቶዎች በሚቆጠሩ ተዋጊ ጀቶች፣ ሄሊኮፕተሮች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች የሚደገፉ የአሜሪካ መርከቦች ለሰላማዊ የባሕር ትልልፍ የ24 ሰአት ሽፋን እየሰጡ ናቸው።

🇮🇱🇺🇸🚫🇮🇷 አልጀዚራ አሜሪካ የሆርሙዝ ባህርን ለምን መክፈት እንደማትችል ገልጿል። 'የኢራን የወባ ትንኝ' መርከቦች በመቶዎች የሚቆጠሩ፣ ከዚያም በላይ ፈጣን ጥቃት ጀልባዎች ለሆርሙዝ ባሕር ስጋት  እና አስፈሪ መሆናቸውን ቀጥለዋል። ማንኛውንም ዓይነት መርከብ በወረራ መያዝ ይችላሉ። እነዚህ ትናንሽ መርከቦች የሚሠማሩት ከመሬት በታች ካሉ ጥልቅ ዋሻዎች ነው። ታይተው በቶሎ ይሰወራሉ። የአሜሪካን የጦር መርከቦች አጨናንቀው መስበር ይችላሉ። እነዚህ 'የወባ ትንኞች' የኢራን 'ከባድ ሚዛን ደፊ መሳሪያዋ' ሆነው ብቅ ብለዋል። ኢራን ጀልባዎቹን ግዙፍ የኮንቴይነር መርከቦችን ለመያዝ ተጠቅማበታለች።

🇮🇱🇺🇸🚫🇮🇷 የእስራኤል ሚዲያ Maariv i24News፡ ኢራን እስካሁን ጦርነቱን አሸንፋለች። ኢራናውያን አሁን ባለው ሁኔታ ነጭ ባንዲራ ያውለበልባሉ ብሎ የሚጠብቅ ማሰብ የማይችል ነው፣ የማይሆን ነው።