የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 337
订阅者
+124 小时
+307 天
-3930 天
帖子存档
4 340
🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️ — ሰበር ዜና፦ በኢራን የዜና ኤጀንሲ Tasnim መረጃ መሠረት፣ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እና በሊባኖስ የምታካሂደውን ቀጣይ ወታደራዊ ተግባራት ምክንያት በማድረግ፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ያላትን ድርድር አግዳለች።
እስራኤል የምታካሂደውን ወታደራዊ ተግባር ካላቆመች እና ከተያዙ የሊባኖስ አካባቢዎች ወታደሮቿን ካላስወጣች፣ ድርድሩ አይቀጥልም። ኢራን እና አጋር ቡድኖች የሆርሙዝ ወሽመጥን እና በቀይ ባሕር የባብ አል-ማንደብን ጨምሮ፣ ቁልፍ የባሕር መተላለፊያ መንገዶችን ሊያደናቅፉ በመቻል ጫናውን ለመጨመር እያሰቡ ናቸው።
4 340
🇮🇷⚡️🇺🇸 CENTCOM ከዛሬው የኢራን ማጥቃት ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ፣ የአሜሪካ ኃይሎች በኢራን ጎሮክ እና በቀሻም ደሴቶች ላይ የሚገኙትን የኢራን ራዳር እና የድሮን ትዕዛዝና ቁጥጥር ተቋማትን ዒላማ በማድረግ ራስን በመከላከል ሂደት ጥቃቶችን እንዳካሄደ ተናግሮ ነበር።
4 340
🇮🇷❌🇺🇸🇰🇼— ሰበር ዜና፡ ኢራን ዛሬ ጠዋት በኩዌት በሚገኘው የአሊ አል-ሳሌም አየር ኃይል ማዕከል ላይ Fateh-110 በተባለ የአጭር ርቀት ባሊስቲክ ሚሳይል አስወንጭፋለች። ይህንም የሚያሳይ ቪዲዮ ለቃለች።
የኩዌት ምንጮች፣ ኢራን ሚሳዬሎቹን ወደ አሜሪካ ጦር ሠፈር እንደተኮሰች አምነው የደረሰ ጉዳት ካለ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
4 340
+1
🇺🇸🇮🇱🗽⚡️- የኒው ዮርክ ሲቲ 'የእስራኤል ቀን' ፌስቲቫል ሰልፍ ዛሬ የተካሄደ ሲሆን፣ የኒው ዮርክ ገዥ ሆቹል እና አብዛኛዎቹ የግዛቱ አመራሮች ከቀድሞ ከንቲባዎች ኤሪክ አዳምስ እና ማይክ ብሉምበርግ ጋር ተገኝተዋል።
ከንቲባ ማምዳኒ አልተገኘም።
4 340
🇺🇸🇺🇦⚡️— የአሜሪካ የጦር አለቃ ፒት ሄግሴት፦
በፕሬዝዳንት ትራምፕ የ2027 በጀት ውስጥ በግልፅ የሚታይ፣ በድሮን የበላይነት ለመያዝ የሚደረግ $56 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት አለ። ዩክሬን በጦር ሜዳ ላይ ካደረገችው ነገር መማራችንን እንቀጥላለን። ከዩክሬን እንዴት እንደሚሠሩ ብዙ ተምረናል። እኩል ለመሆን ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ምርጥ ለመሆን አስበናል። ይፍጠኑ አለቃ ፒት ሄግሲት! ኢራን፣ ዩክሬን እና ሩሲያ በድሮን ቴክኖሎጂዎች እና ትግበራዎች ይበልጥዎታል።
4 340
🇪🇹⚡️ዕውራኖች፣ እመጫቶች፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ አካለ ስንኩላኖች፣ ሌቦች (ታራሚዎች)፣ ወያላዎች፣ ኩሊዎች እና ወታደሮች … በታሪካዊው የኢትዮጵያ ምርጫ ድምፃቸውን እየሰጡ ናቸው' Etv
4 340
🇪🇹⚡️'ኖቤል ተሸለመ ፣ የእርስ በርስ ጦርነት አቀጣጠለ፣ አሁን ደግሞ (ብቻውን) ምርጫ ለመወዳደር ሽርጉድ እያለ ነው' CNN
'ዓለም እየመሰከረልኝ ነው' ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ።
4 340
— 🇺🇸/🇮🇷📱| የኢራን ሃከሮች፣ ከዚህም በተጨማሪ፣ የኦባማን ዋይት ሃውስ የInstagram ገጽ ጠልፈዋል፣ በቃሲም ሱለይማኒ ምስሎች ሞልተውታል፦
በሳይበር ጥቃቱ ወቅት፣ የቀድሞው የኢራን የቁድስ ኃይል አዛዥ 'የሰማዕት' ቃሴም ሶሌማኒ ምስሎች ወደ ገጹ ተጭነዋል።
“ዋይት ሃውስ በሺዓውያን ቁጥጥር ሥር ነው፣ ዋይት ሃውስ የለም፣ የሺዓ ሃውስ ብቻ!” የሚል መልእክትም ታትሟል።
የ Instagram ባለቤት የሆነው Meta፣ ፔጁ መጠለፉን አረጋግጦ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደህንነቱ መጠበቁን ገልጿል።
ኩባንያው በጠላፊዎቹ የተለጠፈው ሁሉም ይዘት መወገዱን አክሏል።
4 340
— 🇺🇸/🇮🇷 የኢራን ሃከሮች የዩኤስ የጠፈር ኃይል አዛዥ የሆኑት የቺፍ ማስተር ሰርጄንት ጆን ኤፍ. ቤንቲቬኛ የInstagram ፔጅን መቆጣጠር ችለዋል።
የኢማም ዐሊ ኤዲት ፎቶንም ለጥፈዋል።
ኢማም ዐሊ፣ በሺዓ እምነት መሠረት በመለኮታዊ ትዕዛዝ በሰው ልጆች ላይ ኢማም ተደርገው የተሾሙ የፈጣሪ አገልጋይ ናቸው።
4 340
🇫🇷🇮🇱 ፈረንሳይ፣ እስራኤል በሊባኖስ በሠራቻቸው ድርጊቶች ምክንያት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ እንዲቀመጥ ጠይቃለች። ይህን ያለው የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በሂዝቦላ እንቅስቃሴ ላይ የሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ እንዲስፋፋ እና በደቡብ ሊባኖስ ባሉት ግዛቶች ላይ ቁጥጥር እንዲጠናከር አዝዟል።
4 340
🇪🇹🇬🇧⚡️እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀች። ዋና ከተማው ሲቀር፣ መላው ሀገሩ ለደህንነት አስጊ እና አደገኛ ነው ብላለች።
ማስጠንቀቂያው፣ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል ለጉዞ አደገኛ አድርጎ በመጥቀስ፣ ዜጎቹ ወደ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎች ሙሉ በሙሉ እና ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በምትዋሰንባቸው የድንበር አካባቢዎች ከአሥር እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ እንዳይንቀሳቀስ አሳስቧል።
4 340
🇪🇹⚡️የዐማራ ፋኖ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ አስረስ ማረ ዳምጤ፡- 'ሠራዊቱ ከጅምሩ ስለ አገዛዙ ምርጫ ይዞት የነበረው አቋም ትክክለኛ እንደነበር በተግባር ተረጋግጧል።'
1️⃣ BBC 2️⃣ The Economist 3️⃣ Reuters 4️⃣ Foreign Affairs 5️⃣ Al Jazira 6️⃣ Bloomberg 7️⃣ Netherlands Medias 9️⃣ Africa Report 🔟 Democracy Journal 11. Africa News 12. The conversation 13. Ethiopian Insight 14.DW(Deutsche Welle) 15. France 24 16. Amnesty International 17. African Intelligence እና ሌሎችም፣ የአብይ አህመድን የምርጫ ድግስ ውድቅ አድርገውታል። በኢትዮጵያ ከምርጫ ጋር በተያያዘ በዚህ ልክ ዓለም አቀፋዊ እውቅና የተነፈገው እና ተቃውሞ የቀረበበት የፖለቲካ ክንውን ታይቶ አያታወቅም። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በዘንድሮው ምርጫ ጉዳይ የያዘው አቋም ትክክለኛ እንደነበር በተግባር ተረጋግጧል። በታንክ እና በድሮን ታግዞ እንኳን አንድ ሐሙስ የቀረውን ስልጣን በምርጫ ስም በተዘጋጀ የደም ድግስ ለማስቀጠል መሞከር የብልፅግናን የፖለቲካ ፆመኛነት ከማሳዬት ያለፈ ፋይዳ የለውም።
4 340
+2
🇸🇩🇨🇳🇦🇪⚡- የሱዳን መንግሥት ጦር ኃይሎች፣ ከኢትዮጵያ የተነሳ ነው የተባለ እና ባለቤትነቱ የኤሜሬት የሆነ ቻይና ሰራሽ CH-95 ድሮንን፣ መትቶ መጣሉን አስታወቀ።
***
የኤሜሬት ሼክ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር፣ ጃንጃዊድ (RSF) የተባለውን እና በዘር ማጥፋት በተደጋጋሚ የተከሰሰውን አማፂ ቡድን እንደሚደግፉ ይታወቃል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ የመንግሥት ኃይሎች በአማፂው ቡድን ላይ የበላይነት እየተቀዳጁ ናቸው።
4 340
🇱🇧🇱🇧❌🇮🇱 —ሂዝቦላ በሰሜን እስራኤል በሚገኘው የጋሊሊ ፎረስት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሁለት የIDF ወታደሮችን በቀጥታ ሲመታ የሚያሳይ የFPV ድሮን ቪዲዮ ዛሬ አውጥቷል።
4 340
— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'ኢራን በጣም መጥፎ አቋም ላይ ትገኛለች።
አየር ኃይል የላቸውም፣ የባሕር ኃይል የላቸውም፣ ምንም የላቸውም።
ያላቸው ንግግር እና የውሸት ዜና (fake news) ብቻ ነው።'
4 340
— 🇺🇸/🇮🇷 ትራምፕ ኢራን ለቅርብ ጊዜ ሀሳቡ ምላሽ ለመስጠት ሦስት ቀናት ያህል እንደሚወስድባት ተነግሮታል፤ አንድ ባለስልጣን 'ቃል በቃል በዋሻ ውስጥ ናቸው፣ ኢሜይል አይጠቀሙም' ብሏል – Axios
4 340
🇮🇷⚡️— የኢራን IRGC የባሕር ኃይል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በIRGC የባሕር ኃይሎች በተደረገ ቅንጅት እና ደህንነት የነዳጅ ታንከሮችን፣ የኮንቴይነር መርከቦችን እና ሌሎች የንግድ መርከቦችን ጨምሮ 28 መርከቦች በደህና ሁኔታ የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋርጠዋል ብሏል።
