ch
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

前往频道在 Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

显示更多
未指定国家未指定类别
4 308
订阅者
-324 小时
-237 天
-8630 天
帖子存档
🇸🇾 ተክፊር/ወሃቢ አክራሪ አንጃ የሆነው ISIS፣ በሶሪያ ራቃ ግዛት ውስጥ የደማስቆው መንግሥት የፀጥታ አካላት ላይ፣ ለተሰነዘረው ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል። በጥቃቱ በርካቶች፣ ሲቪሊያንን ጨምሮ፣
+1
🇸🇾 ተክፊር/ወሃቢ አክራሪ አንጃ የሆነው ISIS፣ በሶሪያ ራቃ ግዛት ውስጥ የደማስቆው መንግሥት የፀጥታ አካላት ላይ፣ ለተሰነዘረው ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል። በጥቃቱ በርካቶች፣ ሲቪሊያንን ጨምሮ፣ ሕይወታቸው አልፏል።

🇮🇷🇱🇧 "ምስጋና ለኢራን እና ለሂዝቦላ ይሁንልን። ኢራን ባትኖር ወደ ቤታችን አንመለስም ነበር፣ እናመሰግናለን" የደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች ወደ ቄያቸው በመመለስ ላይ። *-*-*- እንደ አረብ መንግሥታትማ ቢሆን፣ ቤታቸው እስከ ዘላለሙ ይናፍቃቸው ነበር። የአረብ መንግሥታት፣ ቀሚሳቸው እየጎተቱ አይሁድንና ፈረንጅን ከማገልገል ውጭ ለወገኖቻቸው የሚደርሱ አይደሉም።

🇺🇸🇮🇹 የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሚሎኒ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እየተውረገረገች ስትናገረው ታይታለች። ምን እያለችው እንደሆነ አልታወቀም።

🇫🇷 የG7 ቤተሰብ ፎቶ ሥነ ስርዓት፣ በስብሰባው ማጠቃለያ ተካሂዷል። በክብር እንግድነት የሕንድ፣ የግብፅ እና የኬኒያ መሪዎች ተገኝተዋል።

🇺🇸🇮🇷🇨🇭⚡️ — የአሜሪካ-ኢራን ስምምነት፣ በመጪው ዓርብ በስዊዘርላንድ በርገንስታክ ሐይቅ ሪዞርት፣ የሚካሄድ እንደሚሆን ተነግሯል። *-*-*- ጨበራ ጩርጩራ ሪዞርት እኮ መምጣት ይችሉ ነበ
🇺🇸🇮🇷🇨🇭⚡️የአሜሪካ-ኢራን ስምምነት፣ በመጪው ዓርብ በስዊዘርላንድ በርገንስታክ ሐይቅ ሪዞርት፣ የሚካሄድ እንደሚሆን ተነግሯል። *-*-*- ጨበራ ጩርጩራ ሪዞርት እኮ መምጣት ይችሉ ነበር፣ ዝሆን አለ እዚ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በመኪና ዞር ዞር ያደርጋቸው ነበር። የሚያሰጋው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ታጣቂዎች (ኦነግ) JD VANCEን እና አያቶላውን እንዳያግቷቸውና ሚሊዮን ብር እንዳይጠይቁባቸው ነው።

🇺🇸🇮🇷🇨🇭⚡️ — የአሜሪካ-ኢራን ስምምነት፣ በመጪው ዓርብ በስዊዘርላንድ በርገንስታክ ሐይቅ ሪዞርት፣ የሚካሄድ እንደሚሆን ተነግሯል። *-*-*- ጨበራ ጩርጩራ ሪዞርት እኮ መምጣት ይችሉ ነበ
🇺🇸🇮🇷🇨🇭⚡️የአሜሪካ-ኢራን ስምምነት፣ በመጪው ዓርብ በስዊዘርላንድ በርገንስታክ ሐይቅ ሪዞርት፣ የሚካሄድ እንደሚሆን ተነግሯል። *-*-*- ጨበራ ጩርጩራ ሪዞርት እኮ መምጣት ይችሉ ነበር፣ ዝሆን አለ እዚ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በመኪና ዞር ዞር ያደርጋቸው ነበር። የሚያሰጋው በመንግሥት ታጣቂዎች (ኦነግ) እንዳያግዷቸውና ሚሊዮን ብር እንዳይጠይቁባቸው ነው።

🇮🇱⚡️🇱🇧 ሰበር ዜና፡ የእስራኤል ድሮን በደቡብ ሊባኖስ ማይፋዱን የተባለ መንደርን አሁን ማጥቃቱ ታውቋል። *-*-* ኔታንያሁ በቀጠናው ሰላም እንደማይፈልግ ምልክት ነው። በግሉ ከሚመጡበት ብዙ ጫናዎች ማምለጥ የሚችለው፣ በትንኮሳና ጦርነት ነው። አሁን ኢራን የምትለውን መጠበቅ ነው።

+4
🇺🇦⚡️🇷🇺 ንጋት ላይ፣ የዩክሬን ድሮኖች በሞስኮ ዙሪያ የሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ ኢንዱስትሪን ማጥቃታቸው ታወቀ። በጥቃቱ ከፍተኛ ውድመት ሳይደርስ እንዳልቀረ ተሰምቷል። ሌሊቱን፣ ሩሲያ 86 የዩክሬን ድሮኖችን በሞስኮ ዙሪያ እና በአቅራቢያው መትታ መጣሏን አስታውቃለች።

+3
🇺🇦⚡️🇷🇺 ንጋት ላይ፣ የዩክሬን ድሮኖች በሞስኮ ዙሪያ የሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ ኢንዱስትሪን ማጥቃታቸው ታወቀ። በጥቃቱ ከፍተኛ ውድመት ሳይደርስ እንዳልቀረ ተሰምቷል። ሌሊቱን፣ ሩሲያ 86 የዩክሬን ድሮኖችን በሞስኮ ዙሪያ እና በአቅራቢያው መትታ መጣሏን አስታውቃለች።

🇺🇦🇫🇷 የፈረንሳዩ ማክሮን እና የዩክሬኑ ዘለንስኪ፣ በG7 ስብሰባ እረፍት ሰዓት ላይ፣ ማይኩን ሳይዘጉ በመቅረቱ ያወሩት ተሰምቷል።
ማክሮን፡ ሰላም ዘለንስኪ እንዴት ነህ? ዘለንስኪ፡ አለን፣ አመሰግናለሁ ለግብዣው። -- ኧረ ምን ችግር አለው፣ የሚካበድ አይደለም፣ ትቆያለህ አደል? -- አይመስለኝም፣ ነገ እሳፈራለሁ ብራሰልስ መሄድ አለብኝ። -- ምነው፣ ቆይ ትንሽ -- ኧረ ልሂድ -- ከትራምፕ ጋር ተገናኛችሁ? -- እንገናኛለን ብሏል በኋላ፣ እሱ ባንኩንም ታንኩንም ይዞ እኮ አስቸገረ -- አዎ፣ እኔ ጋር ተገናኝተናል፣ አስቸጋሪ ሰው ነው።
ማይኩ ያለመዘጋቱን በኋላ ሲያውቁ፣ ደንገጥ ብለው ነበር ተብሏል።

🇺🇸🇺🇦 ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በG7 ስብሰባ ላይ ጥቂት አውርተዋል። ከስብሰባው በኋላ ለብቻቸው ይገናኙ ይሆናል ተብሏል።
+2
🇺🇸🇺🇦 ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በG7 ስብሰባ ላይ ጥቂት አውርተዋል። ከስብሰባው በኋላ  ለብቻቸው ይገናኙ ይሆናል ተብሏል።

🇺🇸🇺🇦🇫🇷 ትራምፕ፣ ዘለንስኪ እና ማክሮን ለG7 ስብሰባ አንድ ላይ በፈረንሳይ ተገኝተዋል። ዘለንስኪ ፑቲንን በዚህ ስብሰባ ና እንገናኝ አትፍራ ብሎት ነበር። *-*-*- ደቃቃ ዘለንስኪ እንዲህ ተከብራ big boys ስብሰባ ላይ ስትገኝ … ፑቲን ከሞስኮ ለመውጣት መፍራቱ የሚገርም ነው።

🇷🇺⚡️🇺🇦ዩክሬን፣ ከ 30% እስከ 40% የሚሆነውን የሩሲያ የነዳጅ ማጣራት አቅምን፣ በታለመ የረጅም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተሳካ ሁኔታ እንዳሰናከለች ተነገረ። ይህ ቀጣይነት ያለው ዘመቻ፣ የሞስኮን የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን፣ ወደ ውጭ የምትልከውን የተጣራ ዘይትም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሽቆለቁል አድርጎታል። ዩክሬን፣ 1/3ኛ የሚሆነውን የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ኢንዱስትሪን ከጥቅም ውጭ ማድረጓ በተዘገበበት ሪፖርት ላይ፣ በግንቦት ወር ከ10 የሩሲያ ግዙፍ ማጣሪያዎች ውስጥ 8ቱ በዩክሬን ድሮኖች ተመትተው ከሥራ ውጭ መሆናቸው ተነግሯል። ሩሲያ፣ በኢራን ጦርነት ምክኒያት በዓለም ገበያ የተፈጠረውን የነዳጅ ክፍተት ለመሸፈን እና ቢሊዮኖችን በትርፍ ለማግኘት አልማ ስትንቀሳቀስ የነበረ ቢሆንም፣ በተወሰደባት የተጠና ተከታታይ ጥቃቶች ምክኒያት እና በዚህም በነዳጅ ኢንዱስትሪዋ ላይ በደረሰባት ውድመት፣ ዓላማዋ ሊጨናገፍባት ችሏል። ዛሬ በብዙ የሩሲያ ግዛቶች የነዳጅ እጥረት ይታያል። *-*-*- ፑቲን ስንት ተጠብቆ ሲያበቃ፣ ጦርነቱን  መጨረስ እና ማሸነፍ ሲችል፣ አቅሙ ሳያንሰው፣ ሲግደረደር …… ሀገሩን እና ጦሩን  ቀስ እያለ አስበላ። እመኑኝ፣ በዚሁ ከቀጠለ ይገለብጡታል። በጦሩ እና በናሽናሊስቶች ውስጥ ብዙ ቁጣ ፑቲን ላይ አለ። ካሁን በኋላ ብዙ የሚታገሱት አይሆኑም።

🇷🇺⚡️🇺🇦ዩክሬን፣ ከ 30% እስከ 40% የሚሆነውን የሩሲያ የነዳጅ ማጣራት አቅምን፣ በታለመ የረጅም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተሳካ ሁኔታ እንዳሰናከለች ተነገረ። ይህ ቀጣይነት ያለው ዘመቻ፣ የሞስኮን የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን፣ ወደ ውጭ የምትልከውን የተጣራ ዘይትም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሽቆለቁል አድርጎታል። ዩክሬን፣ 1/3ኛ የሚሆነውን የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ኢንዱስትሪን ከጥቅም ውጭ ማድረጓ በተዘገበበት ሪፖርት ላይ፣ በግንቦት ወር ከ10 የሩሲያ ግዙፍ ማጣሪያዎች ውስጥ 8ቱ በዩክሬን ድሮኖች ተመትተው ከሥራ ውጭ መሆናቸው ተነግሯል። ሩሲያ፣ በኢራን ጦርነት ምክኒያት በዓለም ገበያ የተፈጠረውን የነዳጅ ክፍተት ለመሸፈን እና ቢሊዮኖችን በትርፍ ለማግኘት አልማ ስትንቀሳቀስ የነበረ ቢሆንም፣ በተወሰደባት የተጠና ተከታታይ ጥቃቶች ምክኒያት እና በዚህም በነዳጅ ኢንዱስትሪዋ ላይ በደረሰባት ውድመት፣ ዓላማዋ ሊጨናገፍባት ችሏል። ዛሬ በብዙ የሩሲያ ግዛቶች የነዳጅ እጥረት ይታያል። *-*-*- ፑቲን ስንት ተጠብቆ ሲያበቃ፣ ጦርነቱን  መጨረስ እና ማሸነፍ ሲችል፣ አቅሙ ሳያንሰው፣ ሲግደረደር …… ሀገሩን እና ጦሩን ቀስ እያሉ እየቆረጠሙለት ነው።

🇷🇺⚡️🇺🇦ዩክሬን፣ ከ 30% እስከ 40% የሚሆነውን የሩሲያ የነዳጅ ማጣራት አቅምን፣ በታለመ የረጅም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተሳካ ሁኔታ እንዳሰናከለች ተነገረ። ይህ ቀጣይነት ያለው ዘመቻ፣ የሞስኮን የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን፣ ወደ ውጭ የምትልከውን የተጣራ ዘይትም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሽቆለቁል አድርጎታል። ዩክሬን፣ 1/3ኛ የሚሆነውን የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ኢንዱስትሪን ከጥቅም ውጭ ማድረጓ በተዘገበበት ሪፖርት ላይ፣ በግንቦት ወር ከ10 የሩሲያ ግዙፍ ማጣሪያዎች ውስጥ 8ቱ በዩክሬን ድሮኖች ተመትተው ከሥራ ውጭ መሆናቸው ተነግሯል። ሩሲያ፣ በኢራን ጦርነት ምክኒያት በዓለም ገበያ የተፈጠረውን የነዳጅ ክፍተት ለመሸፈን እና ቢሊዮኖችን በትርፍ ለማግኘት አልማ ስትንቀሳቀስ የነበረ ቢሆንም፣ በተወሰደባት የተጠና ተከታታይ ጥቃቶች ምክኒያት እና በዚህም በነዳጅ ኢንዱስትሪዋ ላይ በደረሰባት ውድመት፣ ዓላማዋ ሊጨናገፍባት ችሏል። ዛሬ በብዙ የሩሲያ ግዛቶች የነዳጅ እጥረት ይታያል። *-*-*- ፑቲን ስንት ተጠብቆ ሲያበቃ፣ ጦርነቱን  መጨረስ እና ማሸነፍ እየቻለ፣ አቅሙ ሳያንሰው፣ ሲግደረደር …… ቁርጭምጭም ቀስ እያሉ።

🇷🇺⚡️🇺🇦ዩክሬን፣ ከ 30% እስከ 40% የሚሆነውን የሩሲያ የነዳጅ ማጣራት አቅምን፣ በታለመ የረጅም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተሳካ ሁኔታ እንዳሰናከለች ተነገረ። ይህ ቀጣይነት ያለው ዘመቻ፣ የሞስኮን የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን፣ ወደ ውጭ የምትልከውን የተጣራ ዘይትም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሽቆለቁል አድርጎታል። ዩክሬን፣ 1/3ኛ የሚሆነውን የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ኢንዱስትሪን ከጥቅም ውጭ ማድረጓ በተዘገበበት ሪፖርት ላይ፣ በግንቦት ወር ከ10 የሩሲያ ግዙፍ ማጣሪያዎች ውስጥ 8ቱን በዩክሬን ድሮኖች ተመትተው ከሥራ ውጭ መሆናቸው ተነግሯል። ሩሲያ፣ በኢራን ጦርነት ምክኒያት በዓለም ገበያ የተፈጠረውን የነዳጅ ክፍተት ለመሸፈን እና ቢሊዮኖችን በትርፍ ለማግኘት አልማ ስትንቀሳቀስ የነበረ ቢሆንም፣ በተወሰደባት የተጠና ተከታታይ ጥቃቶች ምክኒያት እና በዚህም በነዳጅ ኢንዱስትሪዋ ላይ በደረሰባት ውድመት፣ ዓላማዋ ሊጨናገፍባት ችሏል። ዛሬ በብዙ የሩሲያ ግዛቶች የነዳጅ እጥረት ይታያል። *-*-*- ፑቲን ስንት ተጠብቆ ሲያበቃ፣ ጦርነቱን መጨረስ እና ማሸነፍ እየቻለ፣ አቅሙ ሳያንሰው፣ ሲግደረደር …… ቁርጭምጭም ቀስ እያሉ።

🇮🇷🤝🇺🇸 የአሜሪካ እና የኢራንን ስምምነት ተከትሎ፣ በተለያዩ ሀገሮች የሚገኙ መገበያያ አክሲዎኖች ትርፍ በትርፍ ሆነው አድረዋል። የኢራን ገበያ ከላይ እስከ ታች አረንጓዴ ለብሶ በትርፍ ያበበ
+2
🇮🇷🤝🇺🇸 የአሜሪካ እና የኢራንን ስምምነት ተከትሎ፣ በተለያዩ ሀገሮች የሚገኙ መገበያያ አክሲዎኖች ትርፍ በትርፍ ሆነው አድረዋል። የኢራን ገበያ ከላይ እስከ ታች አረንጓዴ ለብሶ በትርፍ ያበበ ሲሆን፣ በመላው እስያ የሚገኙ፣ በተለይ የዓለም ትኩረቱን የሚጣልበት የጃፓኑ ኒኪ ገበያ፣ ሸጋ ሆኖ መከፈቱ ተሰምቷል። የእስራኤል ብቻ ቀይ ለብሶ በሀዘን ላይ ነው።

+3
🇺🇸🇷🇺 የሩሲያ ረጅም ርቀት ቦንብ ጣይ አይሮፕላን፣ TUPOLEV TU -22M3፣ በስልጠና ላይ እያለ ኢርኩትስ ግዛት ውስጥ መከስከሱ ተነገረ። ሁለቱ ፖይለቶች ቀድመው በመውጣት መትረፋቸው ተሰምቷል። ይሄ፣ ከፈረንጆች 2024 ጀምሮ፣ የተከሰከሰ 4ኛ TUPOLEV ነው። በተመሳሳይ ቀን፣ ዛሬ፣ የአሜሪካው ረጅም ርቀት ስትራቴጂካል ቦንብ ጣይ አይሮፕላን፣ B52 Stratoforester, ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በካሊፎሪያ ሞጃቭ በረሃ እንደተከሰከሰና በውስጡ የነበሩ 8 የበረራ አባላት ወዲያው ሕይወታቸው እንዳለፈ ታውቋል።

🇮🇷🇺🇸 ኢራን የመታቻቸው አረቦች፣ መልሰው በገንዘባቸው ኢራንን ሊገነቡ ነው። New York Post ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት የመልሶ ግንባታ ካሳ ለማግኘት፣ በሩ ክፍት እንደሚሆንላት
🇮🇷🇺🇸 ኢራን የመታቻቸው አረቦች፣ መልሰው በገንዘባቸው ኢራንን ሊገነቡ ነው። New York Post ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት የመልሶ ግንባታ ካሳ ለማግኘት፣ በሩ ክፍት እንደሚሆንላት አሜሪካ ተናገረች። $300 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ለኢራን ሊለቀቅ ይችላል። አሜሪካ፣ ለዚህ ሥራ ወደ ሚቋቋመው አቁማዳ፣ የገልፍ አረብ ሀገራት ገንዘብ በማምጣት እንዲከቱ (በኢንቨስትመንት ስም) የምታመቻች እና ኢራን የስምምነቱን ነጥቦች እያንዳንዱን ያሟላች ጊዜ፣ ገንዘቡን በመቆጣጠር፣ በሂደት ለኢራን መልሶ ግንባታ የምትለቅ መሆኑ ተነግሯል። *-*-* አይ አረብ ይል ነበር ጋዳፊ፣ ነብሱን ይማረውና። አረቦች 'ስትመታው ይጠብቃል' አይደሉም፣ 'ስትመታው ይፈታል' ናቸው።