🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
前往频道在 Telegram
显示更多
未指定国家未指定类别
1 376
订阅者
+324 小时
+3607 天
+65030 天
帖子存档
ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ
ቁርአን ሲቀራ መላኢኮች ድምጹን ሰምተው ከሰማይ የወረዱለት ሰሀባ ማን ነው ?
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
بـــــســــم الله الرحـــــمــــن الرحــــيـــم
←اولا اصيكِ ونفسي بتقوى الله يا عزيزتي
📜አላህ ይዘንልሽ እና በመቀጠል የማስታውስሽ፦_ ....
1ኛ, ለምን እንደተፈጠርሽ እወቂ!
አንቺ ማለት በለውኸል መህፉዝ ላይ የተጻፍሽ/የምትታወቂ ከሩሁ በመንፋት ሰው የመሆንን፣ የባርነትን ቀንበር አሸክሞ በምድር ላይ ከዘራቸው አንዷ መሆንሽን አስታውሺ! ከሀላፊነትሽ የትም ማምለጥ አትችይም።
ይሄን ሀላፊነት ለመወጣት ደግሞ አላህን በትክክል ማወቅ ግድ ይላል።
قال ربي { إِنَّمَا یَخۡشَى ٱللَّهَ مِنۡ عِبَادِهِ ٱلۡعُلَمَـٰۤؤُا۟ۗ }
ትክክለኛ መፍራትን አላህን የሚፈሩት እኮ ከባሪያዎቹ አዋቂ የሆኑት ባሮቹ ናቸው ይላል።
☞ድንን ማወቅ አምላክ ጋር መዳረሻ ድልድይን መገንባት ነው። ድንን ማወቅ የስኬት መሰረት ነው የተፈጠርንበት ህግ፣ የነብያት አደራ ነው
ሰለፎች ያለፉበት ጎዳና እና ዋጋ በመክፈል ለእኛ ያስተላለፉልን (ርስት) ነው።
አምኛለው ያለ ሁሉ ሊያውቀው፣ ሊጠብቀው፣ ለቀጣይ ትውልድ ሊያስተላልፈው ግድ ነው
ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ ሢባል፦ ቤተሰብሽን ከማስተማር ይጀምራል ግደታ ትላልቅ መድረክ ላይ መገኘት ላይሆን ይችላል---
ድንን መገንዘብ ትክክለኛ ሰው የመሆን ትርጉም ነው።አላህን ለማወቅ ፣መልእክተኛውን ለመከተል ካልተማርን፣ ካልጣርን የመኖራችን ትርጉም ምንድን ነው!? ህይወትስ በውስጧስ ያሉት ነገሮች ምንድን ናቸው ??
قال امام الشافعي وَمَن فاتَهُ التَعليمُ وَقتَ شَبابِهِ فَكَبِّر عَلَيهِ أَربَعاً لِوَفاتِهِ
"በወጣትነቱ ዒልምን ሳይማር/ሣይፈልግ ያለፈው ሰው እንደሞተ ይቆጠራልና ለሞቱ አራት ተክቢራን ከብርበት" ብለዋሉ(ኢማሙ ሻፊዒይ)--
መእልክተኛውም እንዳሉት፦
صلى الله عليه وسلم
قال أبي هريرة: سمعت رسول الله ﷺ يقول: ألا إن الدنيا ملعونة، ملعون ما فيها إلا ذكرَ الله تعالى وما والاه، وعالماً ومتعلماً رواه الترمذي، وقال: حديث حسن.
☞አዋጅ! ዱንያ በውስጥም ያለው ሁሉ አላህን ማውሳት ወይም የሚማር እና የሚያስተምር{ወደ አላህ የሚያዳርሰውን እውቀት የሚፈልግ}ሢቀር የተረገመች ናት። ብለዋል።
2ኛ ራዕይ ይኑርሽ!
ራእይ ያለው ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት ጠንቅቆ ሥለሚያውቅ ግራ በመጋባት፣ በመደበር፣ ራሱን አያባክንምራእይ ከሌለሽ መኖር እጅጉን ያስፈራል፣ ያለ ራእይ የህይወትን ጎዳና ማቋረጥ እጅጉን አድካሚ ነው so የምትኖሪለትን ነገር እወቂ፣ መነሻሽን እና መድረሻሽን ለይ፣ልፋትሽም ድካም ብቻ ሆኖ አይቀርም እናም፦እኔ ማነኝ፣ የት ነው መድረስ የምፈልግ፣ በህይወቴ ላሳካው የምፈልገው ነገር ምንድን ነው!የህይወት መዝገቤ ላይ ምን ተብዬ ነው መሰየም የምፈልገው! ለምንድን ነው የምኖረው! ዛሬን የምሰራው፣ ነገን የማስበው ለምንድን ነው! እያልሽ ራስሽን ጠይቂ መልሱንም አግኚ!።
3ኛ የተመቻቸ ጊዜ እና ቦታ አለመጠበቅ።
በምድር ጀርባ ላይ እስካለሽ ድረሽ አንቺ የምትፈልጊውን ለማድረግ ራስሽ ጊዜውን ትፈጥሪዋለሽ እንጂ የተመቼ ጊዜ መቼም አይመጣም። ቆጥ ላይም ተንጠልጠይ፣ ተራራ ላይም ተሰቀይ የምድር ሢኦልም ላይ ሁኚ የትም ሁኚ የት በህይወትሽ መሆን የምትፈልጊውን ለመሆን፣ ማግኘት የምትፈልጊውን ለማግኘት ባለሽበት ሁኔታ ላይ ሁነሽ ታገይ እንጂ የተመቻቸን ጊዜ አትጠብቂ። ምክንያቱም የለም።
4ኛ ለስንፍናሽ፣ እና ለራስሽ ድክመት ምክንያተኛ አትሁኚ!
አንድትችይ አድርጎ ፈጥሮሽ ሣለ አስችለኝ እያል ስትጸልይ አትኑሪ ወይም የሆነ ተአምራይዊ ነገር እስከሚከሰት አትጠብቂ ምድር ላንቺ ብላ ገነት አትሆነም ጎበዝ ከሆንሽ በህመሞቿ መካከል ሁነሽ ተዋጊና ድል አድርጊ።እኔኮ ስላልተማርኩ ነው፣ የሚረዳኝ ስለሌለ ነው፣ ፈሪ ስለሆንኩ፣ ድሀ ስለሆንኩ፣ መልኬ ስለማያምር፣ ተወዳጅ ስላልሆንኩ፣ ጊዜ ስለሌለኝ፣ whatever...በህይወትሽ ለውጥ ከፈለግሽ ምክንያትን አስወግጂ።ምናልባት ምክንያትሽ ትክክል ሊሆን ይችላል ነገር ግን መንገድሽን፣ ሀይልሽን፣ ከማጠር ውጪ የትም አያደርስሽም።
5ኛ በቻልሽው መጠን ከራስሽ ጋ እውነተኛ ሁኝ!
ከህሊናው ጋ እውነተኛ ያልሆነ እና ራሱን የማይመራ ሰው ማንንም መምራት አይችልም።
ከራስሽጋ እውነተኛ ስትሆኚ መማር ያለብሽን፣ መስራት ያለብሽን ነገር ሣትዘናጊ ሰአቱን አክብረሽ ታደርጊያለሽ አደርጋለው ብለሽ ያልሽውን ነገር የራስሽን ህግ በማክበር አድርጊው ካልሆነ ከህሊናሽ ጋ ጦርነት ስለምትከፍቺ በራስሽ አለም ተቀባይነትን ታጫለሽ
6ኛ ጥሩ ጓደኛ መምረጥ!
ምንም ጠንካራ ብንሆን ሰው በዙሪያው ባሉ ሰዎች ቀስ እያለም ቢሆን ወደነርሱ ይሳባል
እናማ አላማ ከሌላቸው ሰዎች መራቅ ስብእናቸው ካልተገራ፣ ያልሆነ ቦታ ላይ ሢያዩሽ ተይ ከማይሉሽ ሰዎች በመራቅበአላህ መንገድ ላይ የሚያበረታቱሽን ሰዎች መወዳጀት።
7ኛ ጊዜን በፕሮ ግራም መጠቀም!
8ኛ ሰው መሆንሽን እና በቂ መሆንሽን እመኚ!
ሰው ማለት አምላክ ከስንት እና ስንት ፍጡሮች በላይ ያላቀው ከድንቅ ብቃት ጋ የተፈጠረ ግሩም ፍጥረት ነው
﴿ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَى كَثِيرٍ مِمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلا﴾
በመጨረሻም፦ እንደምትችይ በትንሹ ላስታውስሽ ከያዝነው ስልክ ጀምሮ ለእኛ ተአምር የሚመስሉን ነገሮች ሁሉ በሰው አዕምሮ የተቀመሩ የሀሳብ መዋቅሮች ናቸው እመኚኝ የእውነት በትክክለኛው መንገድ እስከጣርሽ ድረስ የምትፈልጊያትን ሴት ትሆኛለሽ አንቺ መሆን ለምትፈልጊው ነገር በቂ ነሽ። እንድትችይ አድርጎ ፈጥሮሻልና።
ከሚያነቡት
📜«እህታዊ ምክር ከ እህትሽ ሰልዋ»
جعلني الله وإياكِ من الذين يقرؤون فيتبعون أحسنه أقول قولي هذا وأستغفر الله لي ولكِ انه هو الغفور الرحيم በወንጀል ላይ እየኖሩ «አላህ መሐሪ ነው» በማለት ብቻ መሸወድ ጥፋት ነው፤ እውነተኛ ተስፋ ከመልካም ሥራ ጋር የተቆራኘ ነው። ...
አላህ መልካም ሰሪወች ያድርገን .....
#ብቻ_የቂን ይኑርህ
~
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
”إنك لَن تدَع شيئًا للهِ إلا بدَلك اللهُ به ما هو خيرٌ لكَ منه“
"አንተ አንድን ነገር ለአላህ ብለህ አትተውም፣ አላህ በሱ ፋንታ የተሻለን የሚተካህ ቢሆን እንጂ።"
[አሶሒሐህ: 2/734]
Repost from []سَكِينَةُ الْقُلُوبِ ሰኪነቱል-ቁሉብ[]
🌙 አል አፋቅ የኦንላይን የቁርአን መማሪያ ማዕከል 🌙
📢 ምዝገባ ተጀምሯል!
በማዕከላችን የሚሰጡ ኮርሶች፦
📖 ቁርአን ነዘር
📖 ቁርአን ሂፍዝ
📖 የሂፍዝ ሙራጀአ
📖 ቃዒዳ ኑራንያ
📖 የተጅዊድ ኮርስ
💻 በዘመናዊ የኦንላይን መማሪያ መንገዶች፦
🔹 Zoom
🔹 Telegram
🔹 WhatsApp
ከየትኛውም ቦታ ሆነው ቁርአንን በትክክል ይማሩ!
📞 ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ፦
0993808209
0929317462
مَنْ أَصْبَحَ مِنْكُمْ آمِنًا فِي سِرْبِهِ، مُعَافًى فِي جَسَدِهِ، عِنْدَهُ قُوتُ يَوْمِهِ، فَكَأَنَّمَا حِيزَتْ لَهُ الدُّنْيَا
"ከእናንተ መካከል በቤተሰቡ (በማህበረሰቡ) ውስጥ ተረጋግቶ፣ በሰውነቱ ጤነኛ ሆኖ፣ የዕለቱን ቀለብ (ምግብ) አግኝቶ ያነጋ (ጠዋቱን የጀመረ) ሰው፤ አለም በሙሉ እንደተሰጠችው (እንደተሟላችለት) ይቆጠራል። (ቲርሚዚ
የሴቶች ነፃነት...
ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን እንዲህ ብለዋል፦ «የሴት ልጅ ነፃነት የሚረጋገጠው ጌታዋን ስትታዘዝ ነው። ልጆቿን በጥሩ ተርቢያ ኮትኩታ ስታሳድግ፣ እንደአቅሟ አላህ የጣለባትን በቤቷ ውስጥ የጣለባትን ሀላፊነት ስትወጣ ነው። ሴት ልጅ ለባሏ ቤት ጠባቂ ስትሆን ስለ አጠባበቋም ተጠያቂ ናት።]
🖋ይችን ቀን ሁሌም አስታውሺ በዝች ዱንያ ላይ ለጊዜው እንጂ እንግዳ ነሺና እና ለነገ እሚጠቅምሺን ➷ስንቅ አዘጋጅ💦
