ch
Feedback
Amharic book store

Amharic book store

前往频道在 Telegram

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን መፅሀፎች ማግኘት ይችላሉ 🎯ተከታታይ ልቦለድ 🎯ግጥም 🎯ፍልስፍና 🎯ምክር የተለያዩ PDF መፅሐፍት ለማግኘት ይቀላቀሎ ቻናሉን ማጋራት አይዘንጋ 🙏 🙏 🙏

显示更多
未指定国家未指定类别
458
订阅者
无数据24 小时
+197
+20330
帖子存档
ምርጥ አባባሎች "ሌሎችን ሰዎች ለመምሰል ራሱን የሚቀይር ሰው ብዙም ሳይቆይ ራሱን ሸራርፍ ይጨርሰዋል።" (Roymnod hull) "እራሳችሁን ታማኝ አድርጉ። የዛኔ በአለም ላይ ያሉ የቀጣፊዎች ቁጥር በአንድ እንደቀነሰ እርግጠኛ ትሆናላችሁ።" (thomas carlyn) "አንድ ሰው ለሰው ዘር ሊያበረክተው የሚችለው ትልቁ ስጦታ ሩሱን መቀየር ነው።" ( frank herbert) "ክረምቱ መጥቶ በበጋው ወራት ምን ስታደርግ ከረምክ ብሎ ሚጠይቅህ ጊዜ ይመጣል።" (henry clay) "ለራሳችን ያለንን ክብር አሳልፈን ካልሰጠናቸው በቀር ሰዎች ሊወስዱብን አይችሉም።" (Gandii) "አንድን ነገር ለታይቶ መስራት ሞኞች የፈለሰፉት የመክበር ሙከራ ነው።" (Bruce lee) ምንጭ፦ google ማጋራት መተሳሰብ ነው! Join https://t.me/Amharic_Books_storee

1,ከማንም ምንም ነገር አትጠብቅ! 2,ትግልህን ቀጥልበት፤የተሻሉ ቀኖች እየመጡ ነውና! 3,ብቻህን መሆንን ተማር፤ሁሉም ሰው አይቆይምና! 4,አንዴ ችላ እንተባልክ ከተሰማህ ደግመህ ተመልሰህ እንዳትሄድ! 5,ታማኝ ሁን፤ብርቅ ሁን! 6,ሁኔታውን በፈገግታ ተቀበል፤እናም ቀጥል 7,ምንም ቋሚ ነገር የለም፤ሁኔታው ሁሉንም ነገር ይለወጣል For more : join join share share https://t.me/Amharic_Books_storee

. 📚ርዕስ፦ሮሚዮና ጁልየት ✍️ደራሲ፦ዊልያም ሼክስፒር ሮሚዮ እና ጁልዬት የመጀመሪያው አሳዛኝ ተውኔቱ ተደርጎ የሚቆጠር የዊልያም ሼክስፒር የፍቅር ተውኔት ነው። በዚህ ተውኔት ላይ የሼክስፒር ታሪክ ትኩረት ያደረገው ፍቅር ላይ ሲሆን ታሪኩን ከልቡ በመናገር ለዘመናት በተመልካቾች ዘንድ ይህን ስሜት መፍጠር ችሏል። https://t.me/Amharic_Books_storee

⚪️ውድድር ለተሸናፊዎች ነው (Competition is for Losers) እውነተኛ ስኬት የሚገኘው ከሌሎች ጋር በመፎካከር ሳይሆን፣ ማንም ሊወዳደረው የማይችል ልዩ የሆነ ሞኖፖሊ (monopoly) በመ
⚪️ውድድር ለተሸናፊዎች ነው (Competition is for Losers) እውነተኛ ስኬት የሚገኘው ከሌሎች ጋር በመፎካከር ሳይሆን፣ ማንም ሊወዳደረው የማይችል ልዩ የሆነ ሞኖፖሊ (monopoly) በመፍጠር ነው። ሞኖፖሊ ሲባል ገበያውን በህገ-ወጥ መንገድ መቆጣጠር ሳይሆን፣ በጣም የተለየና የተሻለ ነገር በመፍጠር ተወዳዳሪ አልባ መሆን ማለት ነው። እንዲህ አይነቱ ሞኖፖሊ ትርፋማነትንና ለረጅም ጊዜ ፈጠራን የማስቀጠል አቅምን ያሳድጋል። 📖 Zero to One ✍️ Peter Thiel https://t.me/Amharic_Books_storee

​አንድ ወጣት የደስታን ሚስጥር ለማወቅ ፈልጎ ወደ አንድ ታላቅ ጠቢብ ዘንድ ይሄዳል። ጠቢቡም ወጣቱን ቤተ መንግስቱን እንዲጎበኝ ይነግረውና፣ ነገር ግን ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ሁለት ጠብታ ዘይት ያ
​አንድ ወጣት የደስታን ሚስጥር ለማወቅ ፈልጎ ወደ አንድ ታላቅ ጠቢብ ዘንድ ይሄዳል። ጠቢቡም ወጣቱን ቤተ መንግስቱን እንዲጎበኝ ይነግረውና፣ ነገር ግን ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ሁለት ጠብታ ዘይት ያለበትን የሻይ ማንኪያ ይዞ ዘይቱ እንዳይፈስበት ተጠንቅቆ እንዲዞር ያዘዋል። ​ወጣቱም ዘይቱ እንዳይፈስበት አይኑን ማንኪያው ላይ ብቻ ተክሎ ቤተ መንግስቱን ዞሮ ተመለሰ። ጠቢቡም፣ "በቤተ መንግስቴ ውስጥ ያሉትን ድንቅ ስእሎች፣ ውብ አትክልቶች እና ያማሩ ንጣፎች አየሃቸውን?" ብሎ ጠየቀው። ወጣቱም ዘይቱ እንዳይፈስበት ሲጠነቀቅ ሌላ ምንም እንዳላየ ተናገረ። ​ጠቢቡም፣ "እንኪያስ ተመልሰህ ሂድና የቤቴን ድንቅ ነገሮች በደንብ አይተህ ና" አለው። በዚህኛው ዙር ወጣቱ ማንኪያውን እንደያዘ ዘይቱን ግን ረስቶ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሉትን አስገራሚ እና ውብ ነገሮች እያደነቀ ተመለሰ። ​ጠቢቡም መምጣቱን ሲያይ፣ "ለመሆኑ የሰጠሁህ የዘይት ጠብታዎች የት አሉ?" ሲል ጠየቀው። ወጣቱም ወደ ማንኪያው ሲመለከት ዘይቱ መፍሰሱን እና ባዶ መሆኑን ተረዳ። ​በዚህ ጊዜ ጠቢቡ ፈገግ ብሎ እንዲህ አለው፦ ​"የደስታ ብቸኛው ሚስጥር በዓለም ላይ ያሉትን ድንቅ እና ውብ ነገሮች ሁሉ ማየትና ማድነቅ መቻል ነው፤ ነገር ግን በማንኪያህ ላይ ያሉትን ሁለት ጠብታ ዘይቶች ሳትዘነጋ።" ምንጭ :- አልኬሚስቱ https://t.me/Amharic_Books_storee

በእውነታዎች እና በችግሮች መካከል ያለውን ልዩነት መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ እውነታዎች ተጨባጭ እና የማይለወጡ የሕይወት ገጽታዎች ናቸው፤ ልክ እንደ የአየር ሁኔታ ሁሉ ባንተ ፍላጎት የማይቀየሩ ናቸው
በእውነታዎች እና በችግሮች መካከል ያለውን ልዩነት መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ እውነታዎች ተጨባጭ እና የማይለወጡ የሕይወት ገጽታዎች ናቸው፤ ልክ እንደ የአየር ሁኔታ ሁሉ ባንተ ፍላጎት የማይቀየሩ ናቸው። እነሱን ከመቃወም ወይም ከመጠን በላይ ስለነሱ ከመጨነቅ ይልቅ፣ በእነሱ ላይ ተመስርተህ አንተን ሊጠቀም የሚችል ውሳኔን ማድረግ አለብህ፡፡ ለምሳሌ ዛሬ እንደሚዘንብ ካሰብክ ዣንጥላ ይዘህ ትወጣለህ እንጂ ዝናቡ ባልዘነበ እያልክ አታስብም። በሌላ በኩል ችግሮች በእውቀት እና በፈጠራ ሊፈቱ የሚችሉ ሁኔታዎች ናቸው። 📓 ቢዝነስ ማይንድ ✍ብሪያን ትሬሲ https://t.me/Amharic_Books_storee

* ፍርሀት ወደ ጨለማ ይመራል፣ ጨለማ ደግሞ ወደ ቁጣ ይመራል፣ ቁጣ ደግሞ ወደ ጥላቻ ይመራል፣ ጥላቻ ደግሞ ወደ መከራ ይመራል።" * "አድርግ ወይም አታድርግ መሞከር የሚባል ነገር የለም።" * "ብር
* ፍርሀት ወደ ጨለማ ይመራል፣ ጨለማ ደግሞ ወደ ቁጣ ይመራል፣ ቁጣ ደግሞ ወደ ጥላቻ ይመራል፣ ጥላቻ ደግሞ ወደ መከራ ይመራል።" * "አድርግ ወይም አታድርግ መሞከር የሚባል ነገር የለም።" * "ብርሃንን የምትፈልግ ከሆነ፣ ጨለማውን መታገስ አለብህ።" * መጠንህን ከቁም ነገር አትውሰድ።" * የማታውቀው ነገር ብዙ ነው፤ የምትማረውም ብዙ ነው።" * "የመንገዱ መጨረሻ ላይ ስትደርስ፣ የመንገዱ መጀመሪያ እንደሆነ ትገነዘባለህ።" - ዮዳ (ከስታር ዋርስ)- https://t.me/Amharic_Books_storee

አደገኛ የስለላ መጽሐፍ እባካችሁ ለስለላ እንዳትጠቀሙበት🙏 ይሄ መጽሐፍ የቀረበው አንብባችሁ እንድትዝናኑበት እንጂ እንድሰልሉበት አይደለም። ማጋራት መተሳሰብ ነው

🛑ቂም ተሸክመው እስከመቼ? ⏳አንድ ትልቅ መነኩሴ ገና አመክሮ ላይ ካለ ወጣት መነኩሴ ጋር ረጅም መንገድ እየተጓዙ ነበር። መንገድ ላይ አንድ ወንዝ ጋር ሲደርሱ፣ አንዲት ወጣት ሴት ወንዙን መሻገር አቅቷት ቆማ አገኟት። 🛑 ከመነኮሳቱ አንደኛው ያለምንም ማመንታት ሴቲቱን አቅፎ ወንዙን አሻገራት፤ ከዚያም መሬት ላይ አውርዶ ጉዞውን ቀጠሉ። ሁለተኛው መነኩሴ ግን በዚህ ድርጊት በጣም ተበሳጩ። ለሰዓታት በዝምታ ከተጓዙ በኋላ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው "እንዴት ሴት ትነካለህ? እኛ እኮ መነኮሳት ነን፤ ህጋችንን ጥሰሃል!" አሉት። ወጣቱ መነኩሴም ፈገግ ብሎ እንዲህ ሲል መለሰ፦ "ወዳጄ ሆይ! እኔ ያቺን ሴት ወንዙ ዳር አውርጃት መጣሁ፤ አንተ ግን አሁንም በሃሳብህ ተሸክመሃት እየተጓዝክ ነው!" ሲል መለሰላቸው። ✍️በዚህ ታሪክ ስለ ሴቷ አይደለም ያወራነው። በልባችን ተሸክመን ስለያዝነው ቂም (ሀጢያት) ነው። 👉በህይወት ጉዟችን ላይ ሰዎች ይበድሉናል፣ ያሳዝኑናል ወይም መጥፎ ነገር ያደርጉብናል። ያኔ ሁለት ምርጫ ይኖረናል። ድርጊቱን በዚያው ትተን ጉዟችንን መቀጠል። የደረሰብንን በደል በሃሳብ ተሸክመን (ቂም ይዘን) ራሳችንን እያሰቃየን መጓዝ። 👉ይቅርታ ማድረግ ማለት የበደሉንን ሰዎች ነፃ ማውጣት ሳይሆን፣ እኛን ከቂም "ሸክም" ነፃ ማውጣት ነው። ቂም መያዝ ማለት ሌላው ሰው እንዲሞት መርዝ ጠጥቶ የመጠበቅ ያህል ነው። ዛሬ ወንዙ ዳር መጣል ያለባችሁን የጥላቻና የቂም ሸክም አውርዱና በሰላም ተጓዙ። https://t.me/Amharic_Books_storee

የተመረጠ መጽሐፍ 📕ርዕስ፦ የልማድ አስደናቂ ኃይል ✍ደራሲ፦ጄምስ ክሌር "መጥፎ ልማዳችንን ለማቆም በየቀኑ በ1% ከጣርን በዓመቱ መጨረሻ የሚታይ 37% ለውጥ ይኖረናል።" 🔥እንደዚህ አይነት ምርጥ ምርጥ መጽሐፎች እንዲለቀቁ ሪያክት👍 አድርጉ ማጋራት መተሳሰብ ነው! https://t.me/Amharic_Books_storee

ሾተላዩ ሰላይ.pdf14.10 MB

ይሄን መጽሐፍ ብዙዎቻችሁ ስጠይቁ ነበር፤ወቅታዊ ጉዳይ ስለሆነ አቅርበንላችኋል። 📕ርዕስ፦የዐረቦችና እስራልኤል የ6ቱ ቀን ጦርነት ✍ደራሲ - ራንዶልፍ እና ዊንስቶን ቸርችል በተርጓሚ ማሞ ውድነህ የቀረበ ማጋራት መተሳሰብ ነው https://t.me/Amharic_Books_storee

የገንዘብ እውቀት ያለው ሰው አንድን ነገር ለመግዛት 1,000 ብር ሲያወጣ፣ የሚያየው የሚገዛውን እቃ ብቻ ሳይሆን ያ 1,000 ብር ኢንቨስት ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ወደፊት ሊያመጣው የሚችለውን ትርፍ ጭም
የገንዘብ እውቀት ያለው ሰው አንድን ነገር ለመግዛት 1,000 ብር ሲያወጣ፣ የሚያየው የሚገዛውን እቃ ብቻ ሳይሆን ያ 1,000 ብር ኢንቨስት ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ወደፊት ሊያመጣው የሚችለውን ትርፍ ጭምር ነው። ለምሳሌ ዛሬ ለማያስፈልግህ ጌጥ የምታወጣው ገንዘብ፣ ከ10 ዓመት በኋላ ሊኖርህ የሚችለውን ትልቅ ሀብት የመሰዋት ያህል ነው። ማንኛውንም ብር ስታወጣ "ይህ ብር ኢንቨስት ቢደረግ ኖሮ ምን ሊያመጣ ይችል ነበር?" ብለህ ጠይቅ። 📕 ርዕስ፦ የገንዘብ ሳይኮሎጂ ✍️ ደራሲ፦ ሞርጋን ሃውሰል https://t.me/Amharic_Books_storee

ዴርቶጋዳ .pdf6.23 MB

ባንክ ቤት መበደር ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም። ልዩነቱ ያለው ብድሩ በሚገዛው ነገር ላይ ነው። አብዛኛው ሰው ከባንክ ተበድሮ ልብስ፣ መኪና ወይም የቤት እቃ ይገዛል፤ ይህ "መጥፎ እዳ"ይባላል ምክንያቱም
ባንክ ቤት መበደር ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም። ልዩነቱ ያለው ብድሩ በሚገዛው ነገር ላይ ነው። አብዛኛው ሰው ከባንክ ተበድሮ ልብስ፣ መኪና ወይም የቤት እቃ ይገዛል፤ ይህ "መጥፎ እዳ"ይባላል ምክንያቱም ከኪስህ ገንዘብ ያወጣል።"ሀብታሞች ግን ከባንክ ተበድረው ገቢ የሚያስገኝ ንብረት ይገዙበታል። የባንኩን ወለድና ዋናውን ክፍያ ከንብረቱ በሚገኘው ትርፍ ይሸፍኑታል። በዚህ ሲስተም የሌላውን ሰው ገንዘብ (Other People's Money - OPM) በመጠቀም ያለ ምንም የራስ ካፒታል ይበለፅጋሉ። 📕 ርዕስ፦ ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት ✍️ ደራሲ፦ ሮበርት ኪዮሳኪ https://t.me/Amharic_Books_storee

ባንክ ቤት መበደር ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም። ልዩነቱ ያለው ብድሩ በሚገዛው ነገር ላይ ነው። አብዛኛው ሰው ከባንክ ተበድሮ ልብስ፣ መኪና ወይም የቤት እቃ ይገዛል፤ ይህ "መጥፎ እዳ"ይባላል ምክንያቱም
ባንክ ቤት መበደር ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም። ልዩነቱ ያለው ብድሩ በሚገዛው ነገር ላይ ነው። አብዛኛው ሰው ከባንክ ተበድሮ ልብስ፣ መኪና ወይም የቤት እቃ ይገዛል፤ ይህ "መጥፎ እዳ"ይባላል ምክንያቱም ከኪስህ ገንዘብ ያወጣል።"ሀብታሞች ግን ከባንክ ተበድረው ገቢ የሚያስገኝ ንብረት ይገዙበታል። የባንኩን ወለድና ዋናውን ክፍያ ከንብረቱ በሚገኘው ትርፍ ይሸፍኑታል። በዚህ ሲስተም የሌላውን ሰው ገንዘብ (Other People's Money - OPM) በመጠቀም ያለ ምንም የራስ ካፒታል ይበለፅጋሉ። 📕 ርዕስ፦ ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት ✍️ ደራሲ፦ ሮበርት ኪዮሳኪ https://t.me/Amharic_Books_storee

+9
Leaders_Eat_Last_Why_Some_Teams_Pull_Together_and_Others_Don’t_PDFDrive.pdf2.59 MB

+3
Limitless.pdf4.47 MB

ሳይንሳዊ ግምት.pdf5.48 MB

አፄ_ዮሐንስ_እና_የኢትዮጵያ_አንድነት_ተክለጻድቅ_መኩሪያ_@Yemesahft_Alem.pdf6.66 MB