(( مركز نور الإسلام للتعلم والتعليم ))Nur Al-Islam Center for Teaching and Learning
前往频道在 Telegram
التعلم والتعليم
显示更多未指定国家未指定类别
223
订阅者
-124 小时
无数据7 天
+830 天
帖子存档
هل تعلم من يمكنه أن يوسوسك في الصلاة أكثر من "خنزب"*؟
عندما تعلم أن صاحب البيت الذي تتجنب الرد على مكالماته بسب تأخرك في دفع الإيجار واقف بجنبك يصلي تمامًا!!
ሰላት ውስጥ ከኺንዘብ በበለጠ ማን ሊወሰውስህ እንደሚችል ታውቃለህ??…………
ቀን አልፎብህ ስልክ አላነሳ ያልከው አከራይህ እሶላት ውስጥ ከጎንህ እንደቆመ ስታውቅ ነው!!
ملاحظة: "خنزب" هو اسم الشيطان الموكل بالوسوسة للمصلي في الصلاة كما جاء في الحديث النبوي الشريف.
ማስታወሻ ኺንዘብ ማለት እሶላት ውስጥ የሚወሰውስ የሰይጣን ስም ነው.
https://t.me/merkeznurilislam
⚠️️ ለተጋቢዎች የተሰጠ ማሳሰቢያ፡
🔸 በመካከላችሁና በችግሮቻችሁ ውስጥ ማንንም አታስገቡ።
🛑 እናት፣ እህት፣ ጓደኛ ወይም ቤተሰብ አይግባ።
❗ ምክንያቱም የሌሎች ሰዎች ጣልቃ ገብነት አብዛኛውን ጊዜ አይጠቅምም፤ የሕይወታችሁን ሙሉ ዝርዝር፣ የችግሩን መንስኤና ሥር፣ እንዲሁም የሁለታችሁን ባህሪ ማንም ሊያውቅ አይችልም።
👌🏻 ስለዚህ የእናት፣ የጓደኛ ወይም የእህት ምክር ለሁሉም ባለትዳሮች ላይስማማ ይችላል፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ባለትዳር ማንም የማያውቀው የራሱ የሆነ ባህሪ፣ ሁኔታና ችግር አለው።
💥 ነገር ግን ችግሩ ትልቅና ውብስብ ከሆነ፣ ችግሩ በሁለት ቤተሰቦች መካከል ወደሚፈጠር አለመግባባት ከመቀየሩ በፊት፣ ዓላማው በፍትህ ማስታረቅ የሆነን አስተዋይና ታማኝ የቤተሰብ ሰው እርዳታ ጠይቁ።
💍 ስኬታማ ጋብቻ ማለት የቤታቸውን ምስጢርና ችግር የሚጠብቁ፣ የሌሎችን ጣልቃ ገብነት የማይፈቅዱ፣ መቼ መናገር እንዳለባቸው እንዲሁም መቼ ይቅር ተባብለው ማለፍ እንዳለባቸው የሚያውቁ ባለትዳሮች ናቸው።
https://t.me/merkeznurilislam
الْمَوْتُ لَيْسَ مَوْعِظَةً؛ فَالْمُؤْمِنُ وَالْكَافِرُ كُلُّهُمْ يُؤْمِنُونَ بِالْمَوْتِ، وَإِنَّمَا الْعِبْرَةُ بِمَا بَعْدَ الْمَوْتِ، مِمَّا يَتَعَلَّقُ بِالسُّؤَالِ، وَالضَّمَّةِ، وَحَيَاةِ الْبَرْزَخِ ـ وَفِيهَا عَذَابٌ وَنَعِيمٌ ـ ثُمَّ هُنَاكَ جَنَّةٌ وَنَارٌ.
الشيخ عَبْدِ السَّلَامِ بْنِ مُحَمَّدٍ الشُّوَيْعِرِ
የጁሙዓ ኹጥባ
📖ርዕስ: የጎረቤት ሀቅ እና የአከራይና ተከራይ ሥነ-ምግባር በኢስላም.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📍ቦታ፦አ/አ
🌇መስጂድ፦ሂጅራ መስጅድ
🎙 በሸይኽ ሰዒድ አቡ አህመድ
ለራስህ እፎይታን ስጥ፤
ነገሮች ሁሉ የሚሄዱት በአላህ (ﷻ) ውሳኔና ድልድል (ቀደር) ነውና። የአላህ ውሳኔዎች በሙሉ — ምንም እንኳን ቢጎዱህም — መጨረሻቸው ኸይር (መልካም) ነው።
አንድን ነገር ከአላህ ዘንድ በጽኑ ተማጽነህ ሳይሰጥህ ሲቀር ታዝናለህ። ነገር ግን አንተ ያንን ያሸበረቀ ከረሜላ መስሎት ለመውሰድ እንደሚያለቅስና እናቱ ደግሞ ጥፋቱ እንደሆነ አውቃ እንደምትከለክለው ህፃን መሆንህን አታውቅም። ለአላህ ላቅ ያለ ምሳሌ አለው፤ በአላህ ክልከላ ውስጥ አብሮ የተሸሸገ ታላቅ ስጦታ አለ!
እንዲሁም አንድን ውድ ነገር አጥተህ ታዝናለህ፤ አላህ ደግሞ የተሻለ ሊሰጥህ እንጂ እንደማይወስድብህ አታውቅም።
በእርግጥ አላህ ነገሮችን ሁሉ በእኛ ህሊና ውስጥ ሊመጣ በማይችል ጥበቡና እዝነቱ ያመቻቻል::
https://t.me/merkeznurilislam
የባልና ሚስት ቀልድ🤩
አንድ ባል ሚስቱን ማሞገስ ፈልጎ፡
እንዲህ አላት፡ ዛሬ እንዴት እንደምታምሪ!
እሷም አለች፡ ማለት ትናንት አስቀያሚ ነበርኩ ማለት ነው‼️
እሱ፡ አሳቤ አልገባሽም!
እሷም መለሰች፡ ማለት እኔ ደደብ ነኝ?!
እሱ፡ አይደለም፣ ንግግሬን ልጨርስ ፍቀጅልኝ...
እሷ፡ ማለት በእንተ አስተያየት የውይይት ጥበብ የለኝም ማለት ነው?!
እሱ፡ እባክሽን እስከ መጨረሻው ስሚኝ!
እሷ፡ ደግሞ ደንቆሮም አደረግከኝ እንዴ?!
أبو_أحمدـ_خطبة_الجمعة_٠٩٢٥_١٢٥٤١٤.mp323.65 MB
ሙስሊም የሆነ ሰው ህይወትን ሊጠላ ወይም ከአላህ ዘንድ ካለው እፎይታና መልካም ነገር ተስፋ ሊቆርጥ አይፈቀድለትም።
ይልቁንም አላህ በወሰነበት ነገር ላይ መታገስ፣ በጌታው መልካም ማሰብ (ጥሩ መጠራጠር)፣ እንዲሁም ችሮታውንና እዝነቱን መመኘት ግዴታው ነው።
መከራዎች ምንም ያህል ቢበረቱ አይዘልቁም፤ ምእመንም ከትዕግስት በኋላ አላህ ምን አይነት እፎይታና መልካም ነገር እንደደበቀለት አያውቅም።
https://t.me/merkeznurilislam
የዘወትር ምክር:
ትልቅም ሆነ ትንሽ፣ ያሳሰበህንና ያጨነቀህን፣ የምትመኘውንና የምትፈራውን — ጉዳይህን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ለአላህ (ሱ.ወ) አደራ ስጥ (አስረክብ)።
በአላህ ካዝና ውስጥ ያንተን ፍላጎት የሚያጠበብ ነገር የለም፤ በችሮታውና በበጎነቱ ዘንድም ያንተን ምኞት ከመፈጸም የሚያግደውና የሚያስቸግረው ነገር የለም። ሰዎች እጅግ የራቀ አድርገው ያዩት ስንት ነገር አለ—እሱ ግን በአላህ ዘንድ እጅግ ቅርብ ነው! በባሮች ፊት የተዘጋም ስንት በር አለ—አላህ በእውነተኛና ከልብ በሆነ ዱዓ (ጸሎት) የከፈተው!
ስለዚህ ማንኛውንም ዱዓ አታንስሰው (አታቀልለው)፤ ማንኛውንም ጥያቄና ምኞትም ከአላህ እቅም በላይ አድርገህ አታግዝፈው፤ እጅግ ቸር የሆነው አላህ (ሱ.ወ) ችሮታውን የሚያስቀር ነገር የለም፤ መስጠቱ ስለበዛም ካዝናው አይጎድልም።
ስለሆነም በዱዓህ ላይ ጽና (ተደጋግመህ ለምን)፤ በጌታህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑርህ (መልካሙን አስብ)፤ እርግጠኛ በሆነ ልብም ወደ እሱ ተመለስ። የአላህን እዝነት ስፋት ያወቀ ሰው ከሚፈልገው ነገር አይቆርጥምና (ተስፋ አይቆርጥም)።
https://t.me/merkeznurilislam
أبو أحمدـ خطبة الجمعة - الجوال.mp326.66 MB
﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا}
{አላህና መላኢካዎቹ በነቢዩ ላይ ሰለዋት (የአክብሮት ውዳሴና ዱዐ) ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት ዱዐን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡}
💫ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦
«أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا »
«ጁሙዐ ቀንና ጁሙዐ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ ዐስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል።»
«من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات»
«በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት ዐስር ምንዳ ይፅፍለታል።»
« من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات »
«ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት ዐስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ ዐስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ ዐስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ ዐስር ወንጀልም ያብስለታል።»
« من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا »
«በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ ዐስር ያወርድበታል።»
🤲اللهم صل على محمد وعلى آل محمد
كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد،
🤲اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد
كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
ወደ መልካም ያመላከተ የሰሪው ምንዳ ያገኛል!!
የጁሙዓ ኹጥባ
📖ርዕስ:
እውነተኛነት እና የውሸት አደጋ
!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📍ቦታ፦አ/አ
🌇መስጅድ፦ሂጅራ መስጅድ
🎙 በሸይኽ ሰዒድ አቡ አህመድ
أبو_أحمدـ_خطبة_الجمعة_٠٩١١_١٢٤٧٠٠.mp315.43 MB
أبو أحمد_٠٩٠٤_١٢٤٣٥٥.mp310.33 MB
اللهم في يوم الجمعة نسألك نفحة من نفحات رحمتِك تلك التي لا تُبقي بؤسًا ، و لا حزنًا ، و لا ضيقًا ، و لا يأسًا أتت عليه إلا جعلته فرجًا و فرحًا يا الله ... يارب بك تطيبُ الخواطر و من عندك تتحقّق الأمنيات استودعناك شيئاً في خواطرنا ؛ فحققه لنا يا رب العالمين
أبو أحمد_٠٨٢٨_١٣٠٤٥٤.mp323.09 MB
🎀
🫧🌸 *يُنْدب للرَّجل إِذَا أَعْطَى لِذرِّيته شيئًا أنْ يَبْدأ بأُنْثَاه* .🎀
*قال العلامة الألوسي :* 🌹
💍🌸 " *المعهود من ذوي المروءة جبر قلوب النساءِ لضعفهن؛ ولذا يندب للرجل إذا أعطى شيئا لولده أن يبدأ بأنثاهم".*
🌸🪞
*[روح المعاني ٣٦/٨📚].*🌹
ለወንድ ልጅ ለልጆቹ አንድን ነገር (ስጦታ) በሚሰጥበት ጊዜ በሴት ልጁ መጀመሩ የተወደደ (ሱና) ነው።
ዐላማቱ አል-አሉሲ እንዲህ ብለዋል፦
"ለጋስና የሞራል ባለቤት ከሆኑ ሰዎች የሚጠበቀው ነገር የሴቶችን ልብ መጠገን/ማስደሰት ነው፤ ምክንያቱም ድካም (ስስነት) ስላላቸው። ስለዚህም አንድ ሰው ለልጆቹ አንድን ነገር በሚሰጥበት ጊዜ በሴት ልጁ መጀመሩ የተወደደ ነው।"
[ሩሑል-መዓኒ፣ 8/36]
https://t.me/merkeznurilislam
📜 اليقين بالله ‼
በተዘጋ መንገድ ፊት ለፊት ቆመሃል፤ በዙሪያህ ያሉት ቁሳዊ ምክንያቶች በሙሉ ነገሩ እንደበቃና ከዚህ ቀውስ የመውጫ መንገድ እንደሌለ ያረጋግጣሉ።
ነገር ግን በውስጥህ ዘንድ እንግዳ የሆነ ሰላም ይሰማሃል፤ በሰው ልጅ እይታ የማይቻል ቢመስልም አላህ የሚከፍትልህ አንድ በር እንዳለ በሙሉ ልብህ ትተማመናለህ።
ይህ ጥልቅ ሰላም ከየቂን (ከጽኑ እምነት) እጅግ ውብ ከሆኑ ገጻቶች አንዱ ነው፤ የምክንያቶችን አስቸጋሪነት በዓይኖችህ እያየህ፣ ልብህ ግን በአላህ አቅምና ችሎታ ላይ ተማምኖ ይኖራል፤ እርሱም በአእምሮህ በጭራሽ ያላሰብካቸውን በሮች ሊከፍትልህ እንደሚችል ታምናለህ።
ይህ በትክክል የሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) የቂን (ጽኑ እምነት) ዓይነት ነው፤ ባህሩ ከፊታቸው፣ ፈርዖንና ሰራዊቱ ደግሞ ከኋላቸው በነበሩበት ወቅት፣ ባልደረቦቻቸው፡ «እኛ እኮ ተያዝን!» ባሉ ጊዜ፣ እርሳቸው ሙሉ በሆነ የቂንና በአላህ ላይ በነበራቸው ጽኑ እምነት፡ «ከቶ አይሆንም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነውና በእርግጥ ይመራኛል» ብለው መለሱላቸው።
https://t.me/merkeznurilislam
የመርፌው ሹልነት ያለ ፈትል ዋጋ የለውም...
የፈትሉም ደካማነት ያለ መርፌ ዋጋ የለውም።
በሚያምም ሹልነትና በሚችል ደካማነት መካከል፣
የሕይወት ልብስ በስፌት ላይ ስፌት እየተጨመረ ይሰፋል።
ሕይወት ያለ አላህ ሒክማ — በመስጠትና በመቀበል — አትሞላም፤
ማንኛውም ግንኙነትም ያለ ትግስት እና ሚዛናዊነት አይቀጥልም🍂
