✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
前往频道在 Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
显示更多未指定国家未指定类别
195
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-730 天
帖子存档
የአራቱ አዒማዎች ሱናን መከተልና ንግግሮቻቸው ያን የሚቃረን ከሆነ መተው እንደሚገባ ከራሳቸው አንደበት!
አል‐ኢማም አቡ ሐኒፋ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿إذا صح الحديث فهو مذهبي﴾
“ትክክለኛ የሆነ ሐዲስ፤ እርሱ የኔ መዝሀቤ (አቋሜ) ነው።”
📙 ኢብን አብደይን ፊይ አልኻሺይ: 1/23
አል‐ኢማሙ ማሊክ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿ليس أحد بعد النبي (ﷺ) إلا ويؤخذ من قوله
ويترك إلا النبي (ﷺ)﴾
“ከነብዩ (ﷺ) በኋላ አንድም ሠው የለም ንግግሩ (ታይቶ ትክክል ከሆነ) የሚያዝለት፤ (ትክክል ካልሆነ) የሚተው ቢሆን እንጂ ነቢዩ (ﷺ) ሲቀሩ”
📙 ኢብኑ አብዱልበር በጃሚዕ ውስጥ ዘግበውታል፡ 2/91
አል‐ኢማሙ አህመድ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿لا تقلدني ولا تقلد مالكا ولا الشافعي ولا الأوزاعي ولا الثوري وخذ من حيث أخذوا﴾
“እኔን በጭፍን አትከተሉኝ፡፡ ኢማሙ ማሊኪን፣ ሻፊዒይን፣ አውዛዒንም ሆነ ሰውሪ በጭፍን አትከተሉ፡፡ እኛ ከያዝንበት (ከተማርንበት) ያዙ።”
📙 አል‐ፉላኒይ፡ 113
አል‐ኢማሙ ሻፊዒይ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿أجمع المسلمون على أن من استبان له سنة (ﷺ)
لم يحل له أن يدعها لقول أحد﴾
“ከአላህ መልእክተኛ (ﷺ) የተረጋገጠ ሱና እርሱ ዘንድ የደረሰው ሰው በሙሉ፤ ለየትኛውም የሰው ንግግር ብሎ (ሱናን) መተው እንደሌለበት ዑለማዎች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።”
📙አል‐ፉላኒይ: 68
ከሰለፎች አንደበት!
አል‐ኢማሙ ዘሀቢ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿إذا وَقَعَت الفتن لمستك بالسنة ، وألزم الصمت ولا تخض فيما لا يَعْنيك وما أشكل عَلَيْكَ فَرُدَّهُ إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ، وَقِف وَقُل: اللهُ أَعْلَمُ﴾
“ፊትና በሚከሰት (በሚሆን) ግዜ፤ ሱናን አጥበቅህ ያዝ፣ ዝምታን አዘውትር፣ በማይመለከትህ ጉዳይ አትግባ፣ ግራ የገባህን ነገር ወደ አላህና መልዕክተኛው (ወደ ቁርአንና ሀዲስ) መልሰው፣ አላሁ አዕለም (አላህ የበለጠ አዋቂ ነው) ብለህ ቁም።”
📙ሲየር አዕላሙ ኑበላ፡ 20/142
መቅራት ከማዳመጥ ይበልጣል
~
ቁርኣን መቅራትም ሆነ ማዳመጡ የተደነገገ እና አጅር ያለው ተግባር ነው። ነገር ግን መቅራት ከማዳመጥ ይበልጣል። በማስተዋልና በመገንዘብ መቅራት ያለ ማስተዋልና ያለ መገንዘብ ከመቅራት ይበልጣል።"
[ፈታዋ አለጅነቲ ዳኢማህ፣ ሁለተኛ ስብሰብ፡ 3/ 90 ]
=
IbnuMunewor
🌿🌿🌿 ጥቆማ🌿🌿🌿
🔻ደሀው ሰውዬ ለትዳር ሲጠይቃት;
"ደሀ ነው" ብለው መለሱት።
🔻 ሀብታም ሁኖ ፋሲቅ የሆነው ሰውዬ ሲጠይቅ ግን;
"አላህ ይመራዋል" ብለው ዳሩት።
🌿 ለፋሲቁ "አላህ ይመራዋል" እንዳሉት; ለደሀው "አላህ ይከፍትለታል" ሊሉ ምን ከለከላቸው??
ኢስላም
•ከሰዎች ቤት ለመግባት ፍቃድ እንድትጠይቅ የሚደነግግ
•ፈቃድ ስትጠይቅ ዐይኖችህን ወደ ቤት ውስጥ እንዳትልክ
•በመጀመሪያው የፈቃድ ጥያቄ ምላሽ ካላገኘህ ሁለት ጊዜ ደጋግመህ እንድታስፈቅድ
•መግባት አይፈቀድም ከተባልክ ያለምንም ቅሬታ እንድትመለስ
•መመለስህም ለአንተ ንፅህና እና የክብር ደረጃ እንደሚሆንልህ የሚደነግግ ውብ ሀይማኖት ነው።
የተቀማጭ ወይም የንግድ ገንዘብ ዘካ ሂሳብ አሰራር
~
🌿የሚወጣው የአጠቃላይ ገንዘቡን 2•5% ነው። ስለዚህ:
ጠቅላላ ገንዘቡ x በ 2.5%= የዘካ መጠን ይሰጣል።
ወይም ዘካ የሚወጣለትን ጠቅላላ ገንዘብ ለ 40 ስናካፍል የዘካውን መጠን ይሰጠናል።
ሁለት ምሳሌ እንመልከት፡
🔻 ምሳሌ አንድ:- 500,000 ብር ያለው ሰው የሚያወጣው የዘካ መጠን ስንት ነው?
500,000 × 2.5%=12,500 ብር
ወይም
500,000 ፥ 40=12,500 ብር
🔻 ምሳሌ ሁለት 1,000,000 ብር ያለው ሰው የሚያወጣው የዘካ መጠን ምን ያህል ነው?
1,000,000 × 2.5%=25,000 ብር
ወይም
1,000,000 ፥ 40=25,000 ብር
ይቀጥላል
🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿
የዘካ ፋይዳዎችና ዘካን ያለመስጠት አደጋዎች!
~~~~
ዘካ ለሰጪው የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች፡-
① ዘካ ከአምስቱ የኢስላም ምሰሶዎች አንዱ እንደመሆኑ በትክክል የሚሰጥ ሰው ይህን የኢስላሙን ምሰሶ ነው ያፀናው። ባይሰጥ ደግሞ ይህን ምሰሶውን ነው ያናጋው።
② ዘካ በኢኽላስ እስከተወጣ ድረስ ኢማንን ይጨምራል፤ የአላህን ውዴታ ያጎናፅፋል።
③ ዘካ ወንጀልን ያብሳል። ነብዩ ﷺ "ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሶደቃ ሃጢአትን ያጠፋል" ብለዋል።
④ ዘካ ፈተናን መከራን ይመክታል።
⑤ ዘካ ማውጣት የአዛኝነት፣ የርህሩህነት፣ የተቆርቋሪነት ባህሪን ያላብሳል። ዛሬ ራስ ወዳድነት በነገሰበት ዘመን ለሙስሊም ወገን ከምላስ ባለፈ ከልብ መቆርቆርና ማዘን የእውነት ትልቅ መታደል ነው።
⑥ ዘካ የቀልብ መለዘብና በሞራል መገራትን ያጎናፅፋል። ከክፋት፣ ከስስት፣ ከድንበር ዘለል የዱንያ ፍቅር እንዲወጡ ሰዎችን ያግዛል።
⑦ ዘካ የህሊና እርካታን ፣ መንፈሳዊ ሰላምን፣ ስነ ልቦናዊ መረጋጋትን ያጎናፅፋል።
⑧ ዘካ ገንዘብን ያፋፋል፣ በረካ ይጨምርበታል።
⑨ ዘካ ለችግር ጊዜ ደራሽ ወገን እንዲኖረንም ይጠቅማል። መቼም ሁሌ ድሎት፣ ሁሌ ምቾት የለም። ዱንያ ተገለባባጭ ናት።
ለተቀባዩ ያሉት ፋይዳዎች:–
~
① በዘካ ድሃዎች ይደጎማሉ ወይም ይቋቋማሉ።
② ሃብታሙን በቅናትና በክፋት ከማየት እንዲታቀቡ ያግዛቸዋል።
③ ይህን የሚደጎሙበትን ህግ ለዘረጋው ጌታ ውዴታ ለሃይማኖታቸውም ቀናኢነትን እንዲያሳድሩ ይጠቅማቸዋል። ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ከፊሉ ጌታውን ሊያማርር፣ ኢማኑ ሊሸረሸር ይችላል።
④ ለገንዘብ ሲሉ እምነታቸውን ከመሸጥ፣ በጥፋት ላይ ከመሰማራት ያቅባቸዋል።
የዘካ ማህበራዊ ፋይዳዎች
~~~
① በሰጭና በተቀባይ መካከል ትስስር እንዲጠነክር ያደርጋል። ዝምድናን ይቀጥላል። የሰመረ ጉርብትና እንዲኖር ያግዛል። ምክንያቱም ነፍስ በጎ ለዋለላት አካል ተዘንባይ ነችና።
② ዘካ በአግባቡ ከተወጣ በሀብታሙና በደሃው መካከል ያለውን የሃብት ርቀት ስለሚያጠብ ለጤናማ ኢኮኖሚ የማይናቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
③ ዘካ ከድህነት ወለል በታች ያሉ ወገኖች ተስፋ በመቁረጥ ወደ ስርቆትና ዝርፊያ በማምራት ማህበራዊ ቀውስ እንዳይፈጥሩ ይታደጋል።
④ ዘካ ሀብታሙን ሃላፊነት እንዲሰማው ስለሚያደርግ ከስግብግብ የካፒታሊዝም አስተሳሰብ በማቀብ የሃገር ሐብት በጥቂቶች እጅ ብቻ እንዳይሆን ያግዛል።
ዘካ አለመስጠት ያለው አደጋ
~
ባጭሩ እስካሁን የተዘረዘሩትን ፋይዳዎች ያሳጣል። የዱንያም የአኺራም ኪሳራን ያስከትላል። ሰጪንም፣ ተቀባይንም፣ ማህበረሰብንም አገርንም ይጎዳል።
ወገኔ ሆይ! ዘካ ወጅቦብሀል? እንግዲያውስ ውለታ ቢስ አትሁን። ላንተ የሰጠህ ጌታ ነው "ስጥ" ብሎ ያዘዘህ። በሰፊው ከሰጠህ ነው ጢኒጥየ ቆንጥረህ ስጥ ያለህ። ልብህ ፈታ ብሎ፣ ደስ ብሎህ ስጥ። ደስ እያለህ ጀነትን ትወርሳለህ።
ደግሞ አትሸወድ! ዘካ ገንዘብህን ያፋፋዋል እንጂ አይቀንሰውም። ነብዩ ﷺ "የአንድን ባሪያ ገንዘብ ሶደቃ አይቀንሰውም" ብለዋል።
በነገርህ ላይ የዘካው መጠን ያንተ ድርሻ፣ ያንተ ገንዘብ አይደለም። ዘካውን ባስቀረህ ጊዜ የሰው ሐቅ እየበላህ እንደሆነ ይታወቅህ። አይሰቀጥጥም? "ላቤን ጠፍ አድርጌ ያመጣሁት ነው" እያልክ የምትጎረር ከሆንክ ግን የነ ቃሩን ባቡር ላይ ተሳፍረሀል። ወዴት እንደሚወስድህ አልነግርህም።
ወንድሜ! ያገኘኸሁ ባንተ ብልጠትም ብቃትም አይደለም። ስንት የበቁ የነቁ በድህነት እየማቀቁ መሰለህ?! ስንት መንቻካ ዶክተሮች ፕሮፌሰሮች እንዳሉ ሁሉ ስንት ቁልቁል መደመር የማይችሉ ቱጃሮች አሉ?!
ይልቅ ልንገርህ! ሌሎችን በድህነት የሚፈትነው ጌታ አንተን በሃብት እየፈተነህ ነው። እራስህ በምታዝበት ገንዘብ ፈተናውን ከወደቅክ አሳዛኝ ክሽፈት ነው። ገንዘብህ ተከትሎህ ቀብር አይገባም። ወራሽ ወገኖችህ የቀብር ጥያቄን፣ የአላህን ምርመራ አይታደጉህም። ዛሬ ነገ አትበል! ሞት አለቅጥ የበዛበት ዘመን ላይ ነን። እንደ ወጣ የሚቀረውን ብዛት እያየን ነው። ነብዩ ﷺ ዘካ የማያወጣ ሰው ነገ በቂያማ ቀን የገዛ ገንዘቡ እባብ ሆኖ እንደሚያሰቃየው የተናገሩትን አስብ።
ደግሞም ዙሪያ ገባህን አስተውል። እድለኛ ማለት ሌላው ላይ ከደረሰው የተመከረ ነው። አላህ ሃብት ከሰጣቸው በኋላ ዘካ ሳያወጡ፣ ሐጅ ሳይፈፅሙ አልፈው በቁጭት ወላፈን እየተለበለቡ ያሉ ስንት አግኝተው ያጡ ወገኖች አሉ?!
ባጭሩ ገንዘብህ ወይ ጀነትህ ወይ እሳትህ ነው። ያሻህን መምረጥ ያንተ ድርሻ ነው።
ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው?
~~~
የዘካ ባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:–
(إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ)
"ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱ፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አተውባ: 60]
መጠነኛ ማብራሪያ
① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም።
③ ዘካ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑ እንኳ ዘካ ይሰጣቸዋል።
ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም።
④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ ማለት ሁለት አይነት ናቸው።
አንደኛ፡- ሙስሊም ያልሆነ ሰው ነው። ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው።
– ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣
– የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ
ሁለተኛ፡- ሰለምቴ ነው።
– በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ
– በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290]
⑤ እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው።
የተጠለፉ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል።
⑥ ባለ እዳ:– የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አስቦ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል።
⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል።
⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል።
ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
"ሰዎች ጋር ከተቀላቀልክ መልካም ስነ ምግባር ያላቸው ሰዎች ጋር ተቀላቀል፤ ምክንያቱም እነሱ ወደ መልካም እንጅ አይጠሩምና"
[مكارم الأخلاق للخرائطي (٣٣)]
ሶሐብዩ ዓሚር ኢብኑ ረቢዐ ረዲየላሁ ዐንሁ “ነብዩን ﷺ ፆመኛ ሆነው እጅግ ብዙ ጊዜ ሲዋክ ሲጠቀሙ አይቻለሁ” ብለዋል፡፡
(ቲርሚዚ ዘግበውታል፡፡)
ከሰለፎች አንደበት!
ኢብኑልቀዪም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿الكسَالى أكثر النَّاس همًّا وغمًّا وحزنًا ، ليس لهم فرح ولا سرور ؛ بخلاف أرباب النَّشَاط والجد في العمل﴾
“ከሰው ሁሉ በላይ ሃሳብ፣ ጭንቀትና ትካዜ የሚበዛባቸው ሰነፍ ሰዎች ናቸው። ስራቸው ላይ ንቃትና ትጋት ያላቸው ግን ይለያሉ።”
📙 ረውደቱል ሙሒቢን፡ 168
ከሰለፎች አንደበት!
ኢብኑልቀዪም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿كتمان المصائب والأوجاع من شيم النبلاء﴾
“መከራና ህመሞችን መደበቅ የታላላቆች ባህሪ ነው።”
📙አል‐ፈዋዒድ: 36
ከሰለፎች አንደበት!
ለአላህ ብለህ መልካም ለምትውልለት ድሃ ምስጋናም ሆነ ዱዓእ አትጠይቅ!
የላቀው አላህ (ﷻ) እንዲህ ይላል፦
{وَيُطْعِمُونَ الطَّعَامَ عَلَى حُبِّهِ مِسْكِينًا وَيَتِيمًا وَأَسِيرًا إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنْكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا}
“ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ። የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው። ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም።”
📗 [ምዕራፍ አል‐ዒንሳን፡ 8‐9]
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿ومَن طَلَبَ مِنَ الفُقَراء الدعاء أو الثناء خرج مِنْ هذه الآية﴾
“ድጎማ (ድጋፍ) ከሚያደርግላቸው ድሃዎች ዱዓእ እንዲያደርጉለት ወይም እንዲያሞግሱት የፈለገ ከዚህ አያት (አንቀፅ) ይወጣል።”
📙 መጅሙዓ አል‐ፈታዋ፡ 11/111
فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
(الأنبياء22)
የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
أَمْ خُلِقُوا مِنْ غَيْرِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ الْخَالِقُونَ
(الطور35)
ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?
ለ ተፈኩር
هَذَا خَلْقُ اللَّهِ فَأَرُونِي مَاذَا خَلَقَ الَّذِينَ مِن دُونِهِ
(لقمان11)
ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡
አላሁ አክበር!
~
እስከሚነጋ ወይም እስከሚመሽ ድረስ ዱዐ እንዲደረግልህ ትፈልጋለህ?
ያውም በመልአክ?!
ያውም በ 70 ሺህ መልአክ?
እንግዲያውስ ተከተለኝ።
ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ "የአላህ መልእክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ:–
( مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَعُودُ مُسْلِمًا غُدْوَةً إلا صَلَّى عَلَيْهِ سَبْعُونَ أَلْفَ مَلَكٍ حَتَّى يُمْسِيَ , وَإِنْ عَادَهُ عَشِيَّةً إلا صَلَّى عَلَيْهِ سَبْعُونَ أَلْفَ مَلَكٍ حَتَّى يُصْبِحَ ، وَكَانَ لَهُ خَرِيفٌ فِي الْجَنَّةِ ).
"አንድ ሙስሊም ጧት ላይ የታመመን ሙስሊም አይጠይቅም በሱ ላይ እስከሚመሽ ድረስ ሰባ ሺ መልአክ ሶለዋት የሚያወርድበት ቢሆን እንጂ። በማታ ከጠየቀውም እስከሚነጋ ድረስ ሰባ ሺ መልአክ ሶላት ቢያወርድበት እንጂ።
አልባኒይ "ሶሒሕ" ብለውታል።
=
IbnuMunewor
«ጤናማው ከዓፊያ ውጪ የህይወትን ጣፋጭ ነገሮች ሁሉ ይመኛል። ህመምተኛው ግን ከዓፊያ ውጪ ሌላ ምኞት የለውም!»
አላህ ሆይ! ካንተ ውጪ ህመሙን ማንም የማያውቅለትን በሽተኛ ሁሉ ዓፊያ ለግሰው!
☀የጠዋት ዚክር
_اَلْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِيْ أَحْيَانَا بَعْدَ مَا أَمَاتَنَا وَإِلَيْهِ النُّشُوْر
ትርጉሙ
ሕይወታችንን በከፊል ከገደለ በኋላ ነፍስ ለዘራብን አላህ ምስጋና ይገባው መመለሻም ወደርሱ ነው።
_اَلْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِيْ عَافَانِيْ فِيْ جَسَدِيْ، وَرَدَّ عَلَيَّ رُوْحِيْ، وَأَذِنَ لِيْ بِذِكْرِه_ِ
ትርጉሙ
አካላዊ ጤንነት ለለገሠኝ ነፍሴንም ለመለሰልኝ እንዳወሳውም ለፈቀደልኝ አላህ ምስጋና ይገባው።
وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَتَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا
(إبراهيم34)
የአላህንም ጻጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡
