✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
前往频道在 Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
显示更多未指定国家未指定类别
193
订阅者
无数据24 小时
-27 天
-530 天
帖子存档
#የሬት_ቅጠል_ፈሳስ (#ጀል) #የጤና_ጥቅሞች
መረጃዎች እንደሚያስረዱት በዓለማችን ቁጥራቸው 500 የሚደርስ የሬት አይነቶች ሲኖሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ 46 የሚደርሱ የሬት አይነቶች ይገኛሉ። ከነዚህም ውስጥ 30 የሚደርሱት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው።
እሬት በጣም ብዙ የህክምና ባህርያቶች ያሉት ሲሆን የጥንት ግብፃውያን ህያው ተክል ብለው ይጠሩታል፡፡
ዛሬም እንኳን ቢሆን በውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ በጣም በሰፊው እና በተስፋፋ ሁኔታ እሬት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
በሀገራችንም ለተለያዩ የጤና ችግር እንደመፍትሄ እና ለውበት ማሳመሪያ ይጠቀሙበታል።
#ለምሳሌ ፤ፎሮፎር ፤ለፀጉር ማሳደጊያ፤ለቆዳ ውበት
በእሬት ቅጠል ውስጥ ያለው ጄል ለቆዳ እና ለፀጉር ጥሩ በሆኑት ንጥረ ነገሮች፣ ማዕድናት፣ እና ቫይታሚኖች የተሞላ ነው፡፡
1. #ያለ_ዕድሜ_የማርጀት_ምልክቶችን_ይከላከላል
የማርጀት ምልክቶች እንደ መሸብሸብ፣ ቀጭን መስመሮች እና የቆዳ መርገብ ከዕድሜ ጋር የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ነገር ግን በሆነ ወቅት እነዚህ ምልክቶች ያለ እድሜ ቀድመው ይከሰታሉ፡፡ እሬቶች በከፍተኛ የፀረ ኦክሲዳንት ይዘቶቹ ምክንያት በውበት መጠበቂያ መስፈርት ውስጥ በማካተት ያለዕድሜ የማርጀት ምልክቶች
የቆዳ መሸብሸብ፣ ቀጭን መስመሮች ፤ የቆዳ መርገብ እና የፀጉር መነቃቀል በተጨማሪም የፊት ቆዳ ወዝን ያመጣጥናል የፀጉር እድገት ላይ ትልቅ አስተዋዕጽኦ አለው።
እሬት ወደ ፀጉር ቆዳ ውስጥ በመዝለቅ እርጥበቱን ይጠብቃል(የራስቅል ድርቀትን ይከላከላል)፡፡
በራስ ቅል ድርቀት ምክንያት ሊከሰቱ ከሚችሉት እንደ ፎሮፎር የፀጉር መነቃቀልን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ ነው።
እንደ ቫይታሚን ኤ፣ ቢ፣ ሲ እና ኢ የሆኑ ንጥረ ነገሮች የተሟላ ምንጭ ስለሆነ ቆዳዎን ይመግባል፡፡ የቆዳ ድጋሚ ማደግን የሚያነቃቃውን ፖሊሳካራይድን የያዘ ነው፡፡
Repost from MuhammedSirage M.Noor
ዱዓእ እና ኢስቲቓሳን በተመለከተ ከጥንት ጀምሮ የጥፋት ሰዎች የሚያቀርቧቸውን ማደናገሪያዎች ከበቂ መልሶች ጋር ማወቅ ለምትፈልጉና የዓረብኛ ኪታቦችን የምታነቡ ወገኖች እነዚህን ኪታቦች በማንበብ ብቻ ሳይሆን በማጥናትም አደራ፦
الإستغاثة / الرد على البكري - الإمام ابن تيمية
الصارم المنكي في الرد على السبكي - الحافظ ابن عبدالهادي
صيانة الإنسان عن وسوسة الشيخ دحلان - السهسواني
هذه مفاهيمنا - الشيخ صالح آل الشيخ
የሺርክ ሰዎች ማደናገሪያዎች በነዚህ አስደናቂ ኪታቦች አፈር በልተዋል
በድጋሚ የተለጠፈ
https://t.me/msirage4
የአራቱ አዒማዎች ሱናን መከተልና ንግግሮቻቸው ያን የሚቃረን ከሆነ መተው እንደሚገባ ከራሳቸው አንደበት!
አል‐ኢማም አቡ ሐኒፋ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿إذا صح الحديث فهو مذهبي﴾
“ትክክለኛ የሆነ ሐዲስ፤ እርሱ የኔ መዝሀቤ (አቋሜ) ነው።”
📙 ኢብን አብደይን ፊይ አልኻሺይ: 1/23
አል‐ኢማሙ ማሊክ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿ليس أحد بعد النبي (ﷺ) إلا ويؤخذ من قوله
ويترك إلا النبي (ﷺ)﴾
“ከነብዩ (ﷺ) በኋላ አንድም ሠው የለም ንግግሩ (ታይቶ ትክክል ከሆነ) የሚያዝለት፤ (ትክክል ካልሆነ) የሚተው ቢሆን እንጂ ነቢዩ (ﷺ) ሲቀሩ”
📙 ኢብኑ አብዱልበር በጃሚዕ ውስጥ ዘግበውታል፡ 2/91
አል‐ኢማሙ አህመድ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿لا تقلدني ولا تقلد مالكا ولا الشافعي ولا الأوزاعي ولا الثوري وخذ من حيث أخذوا﴾
“እኔን በጭፍን አትከተሉኝ፡፡ ኢማሙ ማሊኪን፣ ሻፊዒይን፣ አውዛዒንም ሆነ ሰውሪ በጭፍን አትከተሉ፡፡ እኛ ከያዝንበት (ከተማርንበት) ያዙ።”
📙 አል‐ፉላኒይ፡ 113
አል‐ኢማሙ ሻፊዒይ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿أجمع المسلمون على أن من استبان له سنة (ﷺ)
لم يحل له أن يدعها لقول أحد﴾
“ከአላህ መልእክተኛ (ﷺ) የተረጋገጠ ሱና እርሱ ዘንድ የደረሰው ሰው በሙሉ፤ ለየትኛውም የሰው ንግግር ብሎ (ሱናን) መተው እንደሌለበት ዑለማዎች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።”
📙አል‐ፉላኒይ: 68
በህብረት መመገብ ያለው ትሩፋት!
ከወህሺይ ቢን ሐርብ ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦ የረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች አሉ፡
﴿يا رسولَ اللَّهِ إنّا نأكلُ ولا نَشبعُ قالَ: فلعلَّكُم تأكُلونَ متفرِّقينَ؟ قالوا: نعَم، قالَ: فاجتَمعوا على طعامِكُم، واذكُروا اسمَ اللَّهِ علَيهِ، يبارَكْ لَكُم فيهِ﴾
“አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እኛ ምግብን እንመገባለን ግና አንጠግብም (አንረካም)። እንዲህ አሉ፡ ‘ተለያይታችሁ (ለየብቻ) ነው እንዴ የምትመገቡት?’ አዎ! አሉ። ከዛም እንዲህ አሉ፦ ምግባችሁን በህብረት ተመገቡ። በሱ ላይ የአላህን ስምም አውሱ። ለናንተ በረካ ያደርግላችኋል።”
ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል፡ 2674
Repost from Abu_Oubeida~channel
መልከም ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች፦
በሸይኻችን ሸይኽ አወል ቢን አሕመድ ሲሰጥ የነበረው የ"ሱነኑ አት'ቲርሚዚይ"ኪታብ በመጠናቀቁ በቦታ የ"ሱነኑ ነሳኢ"ኪታብ ነገ ከፈጅር በኋላ ስለሚጀመር መከታተል የምትፈልጉ ካላችሁ በጊዜ እንድትገኙ አስታወስናችሁ።
የስርጭት ሊንክ፦
t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed
Repost from SadatKemal Abu Meryem
CBE: 1000680622543
HIJRA: 1000034780001
ZEMZEM: 0054754710301
AWASH: 01437999853200
+251 911 678 186
ባሎችዬ ግን ለሚስቶቻችሁ እንዴት ናችሁ??
👉አንድ ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ (ሰለሏህ አለይሂ ወአላ አሊሂ ወሰለም ) ዘንድ በመምጣት እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፦
﴿ما حقُّ زَوجةِ أحدِنا علَيهِ؟، قالَ: أن تُطْعِمَها إذا طَعِمتَ، وتَكْسوها إذا اكتسَيتَ، أوِ اكتسَبتَ، ولا تضربِ الوَجهَ، ولا تُقَبِّح، ولا تَهْجُرْ إلّا في البَيتِ﴾
“ሚስቶቻችን በእኛ ላይ ያላቸው ሐቅ (መብት) ምንድነው? እንዲህ አሉት፦ ከምትበላው ልታበላት፣ ከምትለብሰው ልታለብሳት፣ ፊቷን ላትመታት፣ የምትሰራውን ላታጣጥልባትና ኮርፊያም ካለህ ቤት ውስጥ እንጂ ላታኮርፋት ነው።”
አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 2142
አላህ ከአርሽ በላይ ነው!!!
ከሙዓዊያ ቢኑል ሐከም አሱለሚ (አላህ ስራውን ይውደድለትና) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦
﴿جَارِيَةٌ لِي كَانَتْ تَرْعَى غُنَيْمَاتٍ قِبَلَ أُحُدٍ وَالْجَوَّانِيَّةِ إِذِ اطَّلَعْتُ عَلَيْهَا اطِّلَاعَةً، فَإِذَا الذِّئْبُ قَدْ ذَهَبَ بِشَاةٍ مِنْهَا، وَأَنَا مِنْ بَنِي آدَمَ آسَفُ كَمَا يَأْسَفُونَ، لَكِنِّي صَكَكْتُهَا صَكَّةً، فَعَظَّمَ ذَاكَ عَلَىَّ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقُلْتُ : أَفَلَا أُعْتِقُهَا ؟ قَالَ : ائْتِنِي بِهَا . قَالَ : فَجِئْتُهُ بِهَا، فَقَالَ : أَيْنَ اللَّهُ ؟ . قَالَتْ : فِي السَّمَاءِ. قَالَ : مَنْ أَنَا ؟ . قَالَتْ : أَنْتَ رَسُولُ اللَّهِ . قَالَ : أَعْتِقْهَا فَإِنَّهَا مُؤْمِنَةٌ﴾
“አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በግ የምትጠብቅ ባሪያ ነበረችኝ፤ አንድ ቀን ጎራ ስል አንዷን በግ ተኩላ ሲበላት ተመለከትኩኝ፤ ሰውነኝና በብስጭት በጥፊ አልኳት። ነቢዩ (ﷺ) እንዴት እንዲህ ታደርጋለህ በማለት ነገሩን አጠባበቁብኝ። ይሄን ግዜ ለምን ነፃ አላወጣትም? አልኳቸው። ይዘሃት ና አሉኝ። አመጣኃት። ከዚያም፦ አላህ የት ነው? ብለው ጠየቋት ‘ሰማይ ላይ’ አለች። እኔስ ማነኝ አሏት ‘አንተ የአላህ መልዕክተኛ ነህ’ አለቻቸው። ይህን ግዜ ‘ነፃ አውጣት! ምክንያቱም እሷ አማኝ ነችና’ አሉኝ።”
አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል:
የዘመናችን ትልቁ ፈተና
እዳን አለመክፈል
የግል ጉዳዮቻችንን ከሟማላት በፊት እዳችንን መክፈል ልናስቀድም የተገባ አሳሳቢ ጉዳይ ነው!
ረሱል (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿والذي نفسي بيدِه، لو أن رجلًا قُتِلَ في سبيلِ اللهِ، ثم أُحْيِىَ، ثم قُتِلَ، ثم أُحْيِىَ، ثم قُتِلَ، وعليه دَيْنٌ، ما دخَلَ الجنةَ حتى يُقْضى عنه دَيْنُه.﴾
“ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለለሁ፣ ሰውዬው በአላህ መንገድ ላይ ሆኖ ተገድሎ። እንደገና ህያው ሆኖ ከዛም ቢገደል። አሁንም ህያው ሆኖ ከዛም ቢገደል። በሱ ላይ እዳ ካለበት እዳው እስኪከፈል ድረስ ጀነት አይገባም።”
ነሳዒ ሶሂህ ብለውታል:
