ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

前往频道在 Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

显示更多
未指定国家未指定类别
195
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-730 天
帖子存档
ዛሬም ገንዘባቸውን ለጫት የሚያወጡ ሰዎች አሉ! ~ የኑሮ ውድነቱ እጅግ ከባድ ደረጃ ላይ ደርሷል። የቤተሰቡን ጉሮሮ ለመዝጋት እየተንገዳገደ ያለ ሰው ጫትና ሲጋራ ሲገዛ ማየት የእውነት ሱስ ምን ያህል ህሊናን የሚጋርድ ክፉ በሽታ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው። ልጆች አገር አቋርጠው በሰው ሃገር፣ በሰው ቤት ነጭ ላብ አፈስሰው የሚልኩትን ገንዘብ ለጫት ማዋል የጭካኔ ጥግ ነው። አላህ ማስተዋሉን ያድለን። = IbnuMunewor

السلام عليكم ورحمت الله وبركاته

ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። አንድ ሰው በነብዩ ላይ ሰለዋት በማውረዱ ከሚያገኛቸው ጥቅሞች ወስጥ፦ *ባስጨነቀው ጉዳይ ላይ አላህ ይበቃዋል *ድህነት ለማንሳት አንዱ ምክንያት ነው *አላህ ሀጃውን እንዲሳካ ያደርግለታል [جلاء الْأَفْهَام (٤٤٦)] اللهم صلِّ على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد وبارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم  إنك حميد مجيد

በኢማን ላይ መጠራጠር እና ወስዋስ (ጉትጎታ ) የተለያዩ ነገሮች ናቸው Muhammedsirage

የአንድን ሰው የግንዛቤ ብስለት እንዴት ማወቅ ይቻላል? ታላቁ የአልጀሪያ (ጀዛኢር) ዓሊም ኢብኑ ባዲስ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ "እኛ የአንድን ሰው የግንዛቤ ብስለት ከሚያነባቸው መፃህፍት በመነሳት እናውቃለን። ለሱንናህ መፃህፍት ትኩረት ያላየንበትን ሰው በሃይማኖታዊ እውቀቱ ላይ እምነት አንጥልበትም።" (ኣሣሩ ኢብኑ ባዲስ: 4/244) እስኪ አንዴ ቆም ብለን እናስተውል የኛስ የግንዛቤ ብስለት ምን ያክል ነው? የንባብ ትኩረታቸን ወዴት ነው? ቀድሞ ነገር እናነባለን?  IbnuMunewor

ሸይኽ ፈውዛን ሀፊዘሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ አሁን በኡማው ላይ ከባዱ አደጋ ፣ የነዛ አላዋቂ መሃይም የሆኑ ሰዎች ጥሪ ነው ፣ ሰዎችን በአላዋቂነት ፣ በጥመት ጥሪ ያደርጋሉ።

🔴 ሊጀመር  ነው!!!!!! 🎉🎉🎉🎉🎉🎉 ✨አዲስ የሶርፍ ኮርስ✨ 📣 📣📣📣📣📣📣 ​•┈•┈•⊰✿◇✿⊱•┈•┈•       ገባ🚪              ገባ🚪                   ገባ🚪                           ገባ🚪በሉ 👇ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት👇  ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ https://t.me/Jud_Acadamy?livestream=bef3a52b06b1f53c6b

 🎙  የመጀመሪያ ፕሮግራም በኡስታዝ ሙሐመድ ዘይን      ተ                     ጀ                                    መ                                            ረ      ገባ ገባ በሉ  ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘ 📱⇘⇘⇘⇘⇘ https://t.me/+yxwTU-Sx-7szZGVk

ሲመጣ ይህ መልክት ምን ላርገው ዝም ማት ነው መደለት

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካተሁ

ከተልባ ከፍተኛ ጥቅም ለማግኘት በዚ መልኩ ተጠቀሙት! ⋄ መጀመሪያ መፍጨት ተልባን በሙሉ ፍሬው መመገብ ጥቅሙ አነስተኛ ነው። የሰውነታችን የምግብ መፈጫ ሥርዓት ጠንካራውን የፍሬውን ሽፋን ሰብሮ በውስጡ ያለውን ንጥረ-ነገር ማግኘት ስለማይችል፣ ከመመገብ በፊት መፍጨት ያስፈልጋል ⋄ እንደተፈጨ በትኩሱ መጠቀም ተልባ ከተፈጨ በኋላ አየር ካገኘ በቀላሉ ይበላሻል። ስለዚህ በአንድ ጊዜ ብዙ ፈጭቶ ከማስቀመጥ ይልቅ፣ ለቀኑ የሚፈለገውን ያህል ብቻ መፍጨት ይመረጣል ⋄ አለመቀቀል ተልባ ውስጥ ያለው ኦሜጋ-3 በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ሲቆይ ጥቅሙ ይጠፋል። ስለዚህ ተልባን በምግብ ውስጥ ስንጨምር፣ ምግቡ ከበሰለና ከጋለ እሳት ላይ ከወረደ በኋላ መሆን አለበት ⋄ ምግቦች እና ጭማቂ ውስጥ ሽሮ፣ ስልስ፣ ወጥ፣ ገንፎ እንዲሁም ሾርባ ላይ ከበሰለ በኋላ ጨምሮ መመገብ ይቻላል። እርጎ ወይም አጃ ላይ 1-2 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ተልባ በመነስነስ መጠቀም ኋይል ይሰጠናል፤ እንዲሁም በማንኛውም አይነት የፍራፍሬ ጭማቂ ላይ ጨምሮ መጠጣት፣ የምግቡን የንጥረ-ነገር ይዘት በአንድ ጊዜ ከፍ ያደርገዋል ⋄ በእንጀራ ወይም በዳቦ እንጀራ ወይም ዳቦ ሲጋገር ጥቂት የተፈጨ ተልባ ከዱቄቱ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም ለጤና ተመራጭ መንገድ ነው፤ እንዲሁም እንጀራው እጅግ ለስላሳ እንዲሆንና አይን የሚስብ ወዝ እንዲኖረው ያደርጋል ⋄ ለጨጓራ ጠዋት ጠዋት ቁርስ ከመብላት ወይም ቡና ከመጠጣት በፊት፣ አንድ ማንኪያ የተፈጨ ተልባ በግማሽ ብርጭቆ ለብ ባለ ውሃ ዘፍዝፎ መጠጣት። ይህም ለጨጓራ ግድግዳ እንደ መከላከያ ሽፋን ሆኖ ያገለግላል ⋄ ለጾም ወቅት በጾም ወቅት የሰውነት አቅም እንዳይቀንስ በተልባ ፍትፍት ወይም በሽሮ ወጥ ላይ (ወጡ ከበሰለ በኋላ) ተልባን ጨምሮ መመገብ። ይህም ሆድ እንዳይራብና የጠፋውን ፕሮቲን በቀላሉ ለመተካት ይረዳል ⋄ ለአራስ እና ለሚያጠቡ እናቶች በባህላችን ተልባ ለአራስ እናቶች እጅግ አስፈላጊ ነው። አጥሚት ወይም ገንፎ ላይ የተፈጨ ተልባን መጨመር ሰውነት በፍጥነት እንዲያገግም እና ለህጻኑም በቂ ወተት እንዲኖር እገዛ ያደርጋል ⋄ በቂ ውሃ መጠጣት ተልባ ከፍተኛ የሆነ የፋይበር ይዘት አለው። ይሄ ፋይበር በሰውነታችን ውስጥ ስራውን በአግባቡ እንዲሰራና የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ተልባ ከተመገቡ በኋላ ውሃ በደምብ መጠጣት የተሻለ ነው ⋄ ለፀጉርና ለቆዳ ተልባን በውሃ አፍልቶ የሚወጣውን "ጄል" ለፀጉር ጄል ወይም ለፊት ማስክነት መጠቀም ይቻላል

ሳይታወቀን የሸር መክፈቻ እንዳንሆን ~ የሆነ ጊዜ አንድ ጎረቤት ከሌላ ጎረቤቱ ቤት እየተጫወተ ይቆያል። ምግብ ቀረበ። ጎረቤት ከምግቡ ጋር የተያያዘ የቀልድ አስተያየት ጣል አደረገ፣ እንዲሁ እየሳቀ ነበር። አንዳንድ እየተባለ በባልና ሚስት መሃል ያልታሰበ ከባድ ጥል ተከሰተ። ሲመስለኝ የቀደመ ክፍተት ኖሮ ጎረቤት ሳያስበው ሰበብ ሆኗል። የልጅነት ትዝታ ስለሆነ ዝርዝሩ ትዝ አይለኝም። ትዝ ቢለኝም የሚጠቅም አይደለም። ቀጥዬ ለማነሳው ነጥብ ማሳያ ምሳሌ እንዲሆነኝ ነው ያነሳሁት። ሚስትን ከባል፣ ልጅን ከወላጅ፣ ሰራተኛን ከአሰሪ፣ ጓደኛን ከጓደኛ፣ ሸይኽን ከሸይኽ፣ ማጋጨትና ማለያየት የከፋ ሸር እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው። ነገር ግን አንዳንዴ እንዲህ አይነት ጥፋቶችን ክፋትን ሳናስብ ልንፈፅመማቸው እንደምንችል እንዘነጋለን። * ታመህ ሊጠይቅህ የመጣ ሰው ምንም ክፋትን ሳያስብበት እንደዋዛ "እንትና ይጠይቅሃል?" ብሎ የጣለው ቃል ውስጥህን ሊያደፈርሰው ይችላል። * "ባልሽ ለጥሎሽ ያደረገው ይሄው ነው? የወለድሽ ጊዜስ? የኔኮ እንዲህ እንዲህ አድርጎልኛል?" የሚል ቃል ምናልባት ሚስትን በባሏ ላይ ቅሬታ ውስጥ ሊከት፣ እሱንም "አቅሜን እያወቀች ለምን ታጨናንቀኛለች? እንዴት አትረዳኝም?" እያለ ነገር ተጓጉኖ ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስከትል ይችላል። * "ጓደኛህ እገሌ ግን ምን ሆኖ ነው ሰርግህ ላይ ያልተገኘው?"፣ "ሰራተኛሽ ምግብ ከናንተው ጋር ነው የምትቀርበው? ይሄማ ማቅበጥ ነው!"፣ "ልጅህ ምን ሆኖ ነው ለዒድ መጥቶ ያልዘየረህ?"፣ ... የመሳሰሉ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች እንደዋዛ ጥለናቸው አልፈን ውጤታቸው የከፋ ሊሆን ይችላል። እና ባላሰብነው አቅጣጫ ሰዎችን ማቀያየም፣ ትዳርን ማደፍረስ፣ አሰሪና ሰራተኛን ማለያየት፣ ጓደኛና ጓደኛን ማራራቅ ውስጥ እንዳንገባ እላፊ ቃላትን ከመሰንዘር መጠንቀቅ አይከፋም። የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦ "إِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلْخَيْرِ مَغَالِيقَ لِلشَّرِّ، وَإِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلشَّرِّ مَغَالِيقَ لِلْخَيْرِ، فَطُوبَى لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الْخَيْرِ عَلَى يَدَيْهِ، وَوَيْلٌ لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الشَّرِّ عَلَى يَدَيْهِ" "ከሰዎች ውስጥ የኸይር መክፈቻዎች እና የሸር መዝጊያዎች የሆኑ አሉ። ሌሎች ደግሞ የሸር መክፈቻዎች እና የኸይር መዝጊያዎች የሆኑ አሉ። አላህ የኸይር መክፈቻዎችን እጁ ላይ ያደረገለት ሰው ምንኛ የታደለ ነው!! አላህ የሸር መክፈቻዎችን እጁ ላይ ያደረገበት ሰው ወዮለት!!" [አስሶሒሐህ፣ አልባኒይ፡ 1332] = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

ያለ ቦታው ነገር አናጥብቅ! ~ ወዳጅ ቤተሰብ የሞተባቸውን ሰዎች ተዕዚያ ማለት የፈለገ ሰው የግድ ቤታቸው ሄዶ መሰባሰብ አይጠበቅም። በቤት፣ በቀብር ቦታ፣ መንገድ ላይ፣ በስራ ቦታ፣ በመስጂድ ፣ ... ባገኛቸው ቦታ ተዕዚያ ማለት ይችላል ፣ በቂም ነው። [አሕካሙል ጀናኢዝ ፡ 320፣ 210] በስልክም ሊሆን ይችላል። እቤቴ አልመጡ ብለን ሰዎችን ልንቀየም አይገባም። ይሄ አጉል ነገር ማጥበቅ ነው። ሰዎች ጋር እንዳንቀያየም ካልፈራን በስተቀር ለዚህ ጉዳይ ተብሎ አገር አቆራርጦ መሄድም አያስፈልግም። የኛ እንግልት ለሟች የሚያተርፈው ነገር የለም። ሞቱ የኛ ከሆነም ሰዎች አገር አቋርጠው እንዳይመጡ እንንገራቸው። ከሰዎች እንግልት የሚደርሰን ነገር የለም። = Ibnu Munewor የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor

ኢብኑል ጀውዚ ረሒመሁሏህ፦ "ሰዎች ጊዜን በማባከን ላይ ባህሉ አሸንፏቸው ታዘብኩኝ፤ እርስ በርሳቸው ሲጎበኛኙ በማይረባ ንግግር እና ሀሜት ላይ ከመሆን አይወገዱም፤ በትንሹ ጊዜን ያጠፋሉ፤ ያለፉት ቀደምቶች ከዚህ ያስጠነቅቁ ነበር" ይላሉ። [አልአዳብ ሸርዒያህ– ኢብኑል ሙፍሊሕ: (3/474)]