✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
前往频道在 Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
显示更多未指定国家未指定类别
194
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-730 天
帖子存档
ዳዕዋ
وَلْتَكُن مِّنكُمْ أُمَّةٌ يَدْعُونَ إِلَى الْخَيْرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡
ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ وَجَادِلْهُم بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡
عَن عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ: «بَلِّغُوا عَنِّي وَلَوْ آيَةً»
ትርጉም፦ ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፦ "ከእኔ ዘንድ አንዲት አንቀፅም እንኳ ብትሆን አድርሱ።" (ቡኻሪ ዘግበውታል)
🌿 የጫት ጉዳቶች እና የሽሪዓ ብይኑ🌿
🚨 ዋና ዋና ጉዳቶች
አካላዊ ተፅዕኖ:-
*የልብ ምት እና የደም ግፊት መጨመር (ለልብ ድካም እና ስትሮክ ያጋልጣል)።
* የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና የጨጓራ ህመም።
* የአፍ ጤና መታወክ እና ለካንሰር ተጋላጭነት።
* የስንፈተ-ወሲብ ችግር።
አእምሯዊ ተፅዕኖ:-
* ከባድ እንቅልፍ ማጣት፣ ጭንቀት እና ቅዠት።
* ጠንካራ ስነ-ልቦናዊ ሱስ እና የአእምሮ ህመም ስጋት።
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ:-
* ውድ ጊዜንና ገንዘብን ማባከን።
* ምርታማነት መቀነስ እና ለድህነት መዳረግ።
⚖️ የሽሪዓ ብይኑ (በኢስላም ያለው እይታ)
አቋም:አብዛኛዎቹ የዘመናችን የኢስላም ሊቃውንት ሀራም (ክልክል) እንደሆነ ይስማማሉ።
ዋና ዋና ምክንያቶች
1. ጤናን መጉዳቱ:ኢስላም ራስን መጉዳትን ይከለክላል።
2. አእምሮን ማደብዘዙ:እንደ አስካሪ መጠጥ (ኸምር) ይቆጠራል።
3. ገንዘብን ማባከኑ: ኢስላም ብክነትን (ኢስራፍን) ይከለክላል።
4. ከአምልኮ ማዘናጋቱ: ከሰላት እና ሌሎች ዒባዳዎች እንቅፋት ይሆናል።
ማጠቃለያ:ጫት በጤና፣ በአእምሮ እና በኢኮኖሚ ላይ በሚያደርሰው ከባድ ጉዳት ምክንያት መተው ያለበት ጎጂ ልማድ ነው።
ሰለፊያነት የደላላ መጫረቻ አይደለም!
በዘመናችን፣ "ሰለፊያ" የሚለው ታላቅ ስም፣ በየሰፈሩና በየጎጡ በተደራጁ "የመንሐጅ ደላሎች" እጅ የወደቀ ይመስላል። ሁሉም በየራሱ ጠባብ አጥር ውስጥ ሆኖ፣ "ንፁሕ ሰለፊያነት ያለው እኛ ጋ ብቻ ነው! ና ወደ እኛ ሰፈር!" እያለ ይጣራል። ይህ ሁኔታ፣ ሰለፊያነትን በጨረታ እንደተያዘ ሸቀጥ፣ ደላሎች የሚሻሙበት አስመስሎታል።
ወንድሜ ሆይ፣ እነዚህን የሰለፊያን ስም የሚያጠለሹ ደላሎችን ችላ በላቸው!
ሰለፊያነት በደላላ የሚከፋፈል የቡድን አባልነት አይደለም። ሰለፊያነት ማለት፦
በዐቂዳህ፣
በመንሐጅ፣
በተግባርህ፣
በንግግርህ፣
በስነ-ምግባርህ፣
ያንን የጠራውንና ንፁሁን የእስልምና መንገድ፣ የጥንት ብርቅዬ ሰለፎችን (ደጋግ ቀደምቶችን) መከተል ነው።
ሰለፊያነት የጎጥ ስብስቦችንና የእድርተኞችን ሸንጎ ማጀብ አይደለም።
እነዚህ ቡድኖች፣ በየስብሰቡ ታጉረው፣ ከራሳቸው "ክለብ" ውጪ ያለውን ሁሉ "ጠላት" እና "ሙብተዲዕ" እያሉ ይፈርጃሉ። ከዚያም፣ በራሳቸው ስብሰብ ውስጥ ትንሽ ወጣ ያለ አስተሳሰብ ሲፈጠርና የውስጥ ክፍፍል ሲመጣ፣ ድንገት "ወይኔ ሰለፊዮች ተጣሉ!"፣ "የሰለፊዮች አንድነት!" የሚል የይስሙላ ዲስኩር ያዥጎደጉዳሉ። ያኔ "ያዙኝ ልቀቁኝ" ማለቱ ፋይዳው ቢስ ነው ።
ወንድሜ ሆይ፣ ልብ በል!
ሰለፊያነት የመንደር እድር ወይም እቁብ አይደለም። ሰለፊያነት ማለት ያ የጠራው እስልምና ነው። "ሰለፊይ" ለመሆን ፍቃድ የሚሰጥህ የእድር ስብሰባ ወይም የአንድ ሸይኽ የግል ማህተም አይደለም።
"ሰለፊይ" ለመሆን ከፈለግክ፣ በሁሉም ነገርህ እነዚያን ምርጥ ትውልዶች ተከተል! አለቀ።
በደላሎች ጩኸትና በቡድንተኝነት ግርግር ግራ አትጋባ። መንገድህ ግልጽ ይሁን፤ መመዘኛህ ቁርኣንና ሱና በሰለፎች ግንዛቤ ብቻ ይሁን።
ስማ!!!
በዚህ በተከበረ በረመዳን ወር ምክነያት ከነበርክበት አፀያፊ ሁኔታ እና ወንጀል ውጣ!! የኔና የአንተ አምላክ አላህ ለተመለሰ ሰው መሐሪ ጌታ ነው::
እራስህን እንደገና እደስ!!!!
በአላህ ላይ መመካት
ወደ እሱው መጠጋት
ያለ አንተ ምን ዋጋ አለኝ ማለት
ለስኬት መብቂያ እና ከመከራ መጠበቂያ አዋጩ መንገድ ነው። ሺንቂጢይ
{ وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ }
{ فَوَقَاهُ اللَّهُ سَيِّئَاتِ مَا مَكَرُوا }. [سُورَةُ غَافِرٍ: ٤٤-٤٥]
እኛና ዱንያ..
የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ሀሳቡና ጭንቁ ዱንያ ሆኖ ያነጋ፦ የተሰበሰበውን ይበታትንበታል፣ድህነቱን በዓይኑ መሀል ያደረግበታል፣ከዱንያም የተቀደረለት እንጂ አይመጣለትም።
ሀሳቡና ጭንቀቱ አኼራ ሆኖ ያነጋ፦ መብቃቃትን(ሀብትን) በቀልቡ ያደርግለታል፣የተበታተነውን ይሰበስብለታል፣ዱንያ የግዷን ወደሱ ትመጣለች።"
[ቲርሚዚይ ዘግበውታል]
የዘመናችን ትልቁ ፈተና!!!
የሩቃ ቤት ንግድ!!!
ባለ ሩቃ ቤቶች አላህን ፍሩ
በህክምና ስም ብዙ ኪሳችሁን አታድልቡ።
ተመጣጣኝ ዋጋ ተምኑ።
የአላህ መልክተኛ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)
ከዕለታት አንድ ቀን
ከባለደረቦቻቸው
ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ ﺃَﻥَّ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠّﻪَ ﻗَﺎﻝَ :
ﺃَﺗَﺪْﺭُﻭﻥَ ﻣَﺎ ﺍﻟْﻤُﻔْﻠِﺲُ ؟ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ : ﺍﻟْﻤُﻔْﻠِﺲُ ﻓِﻴﻨَﺎ
ﻣَﻦْ ﻻَ ﺩِﺭْﻫَﻢَ ﻟَﻪُ ﻭَﻻَ ﻣَﺘَﺎﻉَ . ﻓَﻘَﺎﻝَ : ﺇِﻥَّ
ﺍﻟْﻤُﻔْﻠِﺲَ ﻣِﻦْ ﺃُﻣَّﺘِﻲ، ﻳَﺄْﺗِﻲ ﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔِ
ﺑِﺼَﻼَﺓٍ ﻭَﺻِﻴَﺎﻡٍ ﻭَﺯَﻛَﺎﺓٍ، ﻭَﻳَﺄْﺗِﻲ ﻗَﺪْ ﺷَﺘَﻢَ ﻫَـﺬَﺍ،
ﻭَﻗَﺬَﻑَ ﻫَـﺬَﺍ، ﻭَﺃَﻛَﻞَ ﻣَﺎﻝَ ﻫَـﺬَﺍ،
ﻭَﺳَﻔَﻚَ ﺩَﻡَ ﻫَـﺬَﺍ، ﻭَﺿَﺮَﺏَ ﻫَـﺬَﺍ . ﻓَﻴُﻌْﻄَﻰ ﻫَـﺬَﺍ
ﻣِﻦْ ﺣَﺴَﻨَﺎﺗِﻪِ ﻭَﻫَـﺬَﺍ ﻣِﻦْ ﺣَﺴَﻨَﺎﺗِﻪِ .
ﻓَﺈِﻥْ ﻓَﻨِﻴَﺖْ ﺣَﺴَﻨَﺎﺗُﻪُ، ﻗَﺒْﻞَ ﺃَﻥْ ﻳُﻘْﻀَﻰ ﻣَﺎ ﻋَﻠَﻴْﻪِ
. ﺃُﺧِﺬَ ﻣِﻦْ ﺧَﻄَﺎﻳَﺎﻫُﻢْ ﻓَﻄُﺮِﺣَﺖْ
ﻋَﻠَﻴْﻪِ . ﺛُﻢَّ ﻃُﺮِﺡَ ﻓِﻲ ﺍﻟﻨَّﺎﺭِ . ( ﻣﺴﻠﻢ 6531 (
“ድሐ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?” በማለት ይጠይቃሉ። ሰሀቦችም “እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው” በማለት ይመልሳሉ። የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ግን“ከኡመቴ (ህዝቤ) ድሃ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው። ግና ይህ ሰው አንድ ወንድሙን ሰድቧል፤ ሌላው ላይ ዋሽቷል፤ የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፤ የሌላውን ደም አፍስሷል፤ አንዱን መትቷል፤ በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፤ ያኔም(የትንሳኤ ቀን ምርመራ) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፤ጥሩ ሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ኃጢያት ይሸከማል። ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል።” በማለት መለሱላቸው። (ሙስሊም ሀዲሰ ቁ.6531)
የሙስሊሙ አለም አሁናዊ ገጽታ
🔥● በጥጋብ ተጣሉ; ትግል ተያያዙ; ያላቸውን ሀይል ተጠቀሙ; በመጨረሻም ተጠላልፈው ወደቁ; ፍፃሜያቸው ደግሞ የባሰ ነው:: ያላቸው እጣ ሁለት ነው::
👉1️⃣አንድም እንዲሁ እንደተጠላለፉ #አያ_ጅቦ መጥቶ ያለምንም አደን እና ድካም ከወፍራም አጋዘን እተዘጋጀው ማዕድ ቀርቦ መብላት:: የወንድሙን መኖር የጠላም መቋጫው ይሄው ነው::
👉2️⃣ ሁለተኛ እንደተያያዙ ለገላጋይ ሳይመቹ በውሃ ጥም; በረሀብ አለንጋ ተገርፈው ሁለቱም በስቃይ መሞት ነው::
🔶️ ሁለቱም የከፋ መጨረሻ ነው::
+4
ጥንቃቄ!!!!!!!!
ገበያ ላይ ወይም በየከተማው
ማርን
የተፈጨ ዱቄትን
ቅቤን
ጥሬ ስጋን እንዲሁም ምግብ ቤት ላይም ቢሆን
ማንኛውንም ለምግብነት የምንጠቀማቸውን ነገራቶች ስንገዛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
ታማኝ የሆኑ ሰዎች ላይ ቢሆን የተሻለ ነወ።
መረጃውን ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት
ይህ ኮምቦልቻ ከተማ ቦርከና ክፍለ ከተማ ቁጠባ ቀበሌ አዲስ አለም ሰፈር በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተገኘ ነው።
በባእድ ነገር የተመረተ ማር መሰል ምርት እና ለማዘጋጀት የሚጠቀሙበት
📌ስኳር ፤
📌ጀሶ፤
📌ፕላስቲክ ፤
📌በርሚልና
📌ብረት ድስት ከነተጠርጣሪው ግለሰብ ፖሊስ ይዞ ምርመራ እያጣራመሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ክፍል ኃላፊ የሆኑት ም/ኢንስፔክተር አንዋር ሰይድ አሳውቀዋል።
መረጃው ከኮምቦልቻ ፖሊስ መምሪያ የተገኘ ነው።
መኪና ካልገዛሁ
ከኮሌጅ ካልወጣሁ
ቤት ካልሠራሁ
እያልክ/ሽ አስከ 30 አመት ለቆየህ/ሽ ወንደላጤ/ሴተ ላጤዎች ልብ በሉና አዳምጡት!!!!
