✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
前往频道在 Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
显示更多未指定国家未指定类别
195
订阅者
无数据24 小时
-37 天
-730 天
帖子存档
የኛ ሰዎች አለህ እድሜ ሰጥቷቸው ወደ አላህ መመለስ ሲገባቸው ቁመ ቀር ሁነው ዛሬም እዛው ናቸው።
ለመውለድ እየተደገሱ ነው
🔴 የጫት ሱሰኝነት እና የወጣቶቻችን መጭ እድል ወዴት እያመራ ነው!????
ስለ ሰው ልጅ ባህሪ ስናነሳ ሰዎች ሁሉ ተመሳሳይ አይደሉም። ይልቁንም በተለያዩ ባህሪያትና ስብእናዎች የተቃኙ ናቸው። አንዳንዶቹ በደግነት፣ በለስላሳነት፣ በእውነተኝነት፣ በድፍረትና በጀግንነት ባህሪያቸው ይመሳሰላሉ፤ በአንጻሩ ደግሞ ሌሎች በክፋት፣ በመጥፎ ስነ-ምግባር፣ በውሸት፣ በጥማምነት፣ በግልጽ አደመኝነትና በመጥፎ ድርጊቶች የተሳሰሩ ናቸው።
ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ተሻለ መንገድ በመምራት ወይም ትተው ወደ እንቆቅልሽና ጥፋት በመልቀቅ ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው፤ ይህንን ሃላፊነት ማጎደል ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል።
ዛሬ የቃላት እና የተግባር ስነ-ምግባራቸው እጅግ የወረደ ወጣቶቻችንን ስናይ (አላህ የጠበቃቸው ጥቂቶች እንደተጠበቁ ሆነው) እውነታው አሳዛኝ ነው። በእርግጥ በጨለማ ውስጥ እንደ ደመቀ ብርሃን የሆኑ፣ ከፍተኛ ስነ-ምግባር ያላቸው ደጋግ ወጣቶችም አሉን።
በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩትን፣ ማህበረሰባችንን የማይወክሉ እና የእፍረት ድንበር የሚጥሱ አጸያፊ ቪዲዮዎችን ከተመለከትን፣ ነገሩ ግራ መጋባትንና ቁጭትን ይፈጥራል። ለዚህ ደግሞ የቤት ውስጥ አስተዳደግ ክፍተት፣ ሃይማኖታዊ እሴት ማጣት እና ወጣቶች ከመልካም ነገርና ከትክክለኛ አስተዳደግ መራቃቸው ትልቅ ሚና መጫወቱ አይቀሬ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ገና በወጣትነት እድሜ (ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት ያልበለጠ እና ከዚያም በታች ያሉ ህጻናት) በጫት ማስቃሚያ ቦታዎች ውስጥ ተቀምጠው መመልከት በእጅጉ ያሳዝናል።
ከሁሉም በላይ የሚያዝነው የወላጆች ቸልተኝነት ነው፤ ልጆች ቀኑን ሙሉ ከቤት ጠፍተው እኩለ ሌሊት ላይ ይመጣሉ፣ ወላጆች ግን ምንም እንደልተፈጠረ ዝም ይላሉ። "የት ነበርክ? ለምን ዘገየህ? በየቀኑ ለምን ይሄ ይሆናል? ከየት ነው የመጣኸው?" ብለው እንኳን አይጠይቁም። ወላጆች ልጆቻቸውን የመከታተልና የመጠየቅ ሃላፊነታቸውን እስከዚህ ድረስ የዘነጉት ለምንድነው?
ጫት፣ ትምባሆ እና ሲጋራ ማጨስ ለወጣቶችና በተለያዩ የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ጥፋትና መጥፎ መንገድ መያዝ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው።
ከዚህ ድንቅ መድረክ በመሆን ለወላጆች የማስተላልፈው መልእክት፦
👉 የወላጅነት ሃላፊነታችሁን ተወጡ፤
👉ልጆቻችሁን በጥብቅ ሁኔታ ተከታተሉ፣
👉በመልካም ስነ-ምግባርም ኮትኩታችሁ አሳድጉ። ካልሆነ ግን ለልጆቻችሁ ጥፋትና በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብ ላይ ለሚደርሰው ችግር ትልቁን ዋጋ የምትከፍሉት እና መራራውን ፍሬ የምትቀምሱት እናንተው ናችሁ።
👌በመጨረሻም
ማህበረሰብም ሆነ ሀገር ሊቆሙ የሚችሉት በወጣቶች ትጋትና ጥረት ነው፤ ወጣቶች የሀገር መሰረት፣ የእድገቷ ምስጢር፣ የክብሯና የልዕልናዋ ሰሪዎች ናቸው። እነዚህ ወጣቶች መስመራቸውን ስተው አደገኛ፣ ጠፊ እና ከስነ-ምግባር ውጪ ወደ ሆኑ መንገዶች ሲያመሩ ማየት በእጅጉ ያመማል።
ስለዚህ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን፣ የመስጂድ ኸጢቦች እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ወጣቶችን ከአደንዛዥ እጾችና መጥፎ መንገዶች አስተምረው የመመለስ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። በተለይም ከጫት፣ ሲጋራ፣ ትምባሆ፣ ህገ-ወጥ እጾች እና ከመጥፎ ጓደኞች በመራቅ በመከባበርና በመረዳዳት ላይ የተመሰረተ መልካም ማህበረሰብ እንዲገነባ መረባረብ አለብን። አላህ ይረዳን።
✍ ወንድማችሁ ሙሃመድ ሰኢድ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በትዳር አበላሾች (በሱና) ላይ ባሉ ሰዎች ዘንድም ሳይቀር የትዳር ችግሮች እና ፍቺ ልማድ እየሆነ መጥቶ ነገሩ ምስቅልቅሉ እስኪወጣ ድረስ ደርሷል፤ ለባልና ሚስቶች የሚለግሱት ምክር አለዎት?
መልስ
ለባልና ሚስቶች የምንመክረው በበጎ ነገርና በአላህ ፍርሃት (መልካም ስራ) ላይ እንዲተጋገዙ ነው፤ እንዲሁም ከሁለቱም ወገን በመልካም ሥነ-ምግባር እንዲታነፁ እንመክራቸዋለን።
ሰይጣን በባልና ሚስት መካከል ልዩነትን ለመፍጠር በጣም ጉጉ ነው። እንዲያውም በአንድ ሶሂህ (ትክክለኛ) ሐዲስ ላይ እንደተወሳው ሰይጣን በሰዎች መካከል ጥልን እንዲለኩሱ ልጆቹን ይልካል። ከእነርሱም አንዱ መጥቶ «ሚስቱን እስኪፈታ ድረስ አልተውኩትም» ይላል፤ እርሱም (ሰይጣኑ) «አንተ እንጂ! (ትልቅ ስራ ሰራህ)» ይለዋል።
በሌላ ሐዲስ ደግሞ፦ «ሰው እስኪገድል ድረስ አልተወሁትም» ይላል፤ እርሱም «አንተ እንጂ!» ይለዋል።
ስለዚህ ሰውየው በተሰሙት ሐዲሶች መሠረት ለሴቷ መልካም ሊውልላት ይገባል፦ «በሴቶች ላይ መልካምን ነገር አደራ ተባባሉ፤ በእናንተ ዘንድ እንደ ምርኮኞች ናቸውና»። የክብረት ባለቤት የሆነው አላህም በቅዱስ ቁርዓኑ እንዲህ ብሏል፦ (በመካከላችሁም መተሳሰብን አትርሱ)።
ሴት ልጅ ደካማ ናት፤ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰልም) ግመሎች በፍጥነት እንዲጓዙ ግመል ነጂው ግጥም በሚልበት ጊዜ ለነጂው እንዲህ ብለውታል፦ «በብርጭቆዎቹ ላይ ቀስ በል (በየዋህነት ያዛቸው)»፤ ማለታቸውም በግመሎቹ ላይ የተቀመጡትን ሴቶች ናቸው፤ ምናልባት ጉዞውን ያፋጥንና ከግመሉ ላይ ሊወድቁ ይችላሉና።
ሴት ልጅ እንደ ብርጭቆ ናት፤ መልካም ሊደረግላት ይገባል። የክብረት ባለቤት የሆነው አላህም በቁርዓኑ እንዲህ ብሏል፦ (ከነፍሶቻችሁ ለእናንተ ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ ሚስቶችን መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም መዋደድና እዝነትን ማድረጉ ከምልክቶቹ (አስደናቂ ተአምራቶቹ) ነው) [አል-ሩም: 21]።
ሴት ልጅም ቢሆን በባልዋ ላይ አላህን ልትፈራ ይገባታል፤ እርሱ ወደ ሥራው ይሄዳል፣ ቀኑን ሙሉ ይደክማል፤ ስለዚህ ወደ እርሷ ሲመለስ በትንሹም በትልቁም ልትጠይቀውና ልትከሰው አይገባም።
ይልቁንም መልካም ረዳቱ ልትሆን ይገባል፤ እመቤታችን ኸዲጃ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጂብሪልን አይተውና አቅፎአቸው በመፍራትና በመደንገጥ ወደ እርሷ በመጡ ጊዜ፦ «ምናልባት ሰይጣን ወይም ሌላ ነገር ይሆን?» ብለው በሰጉ ጊዜ፦ «በጭራሽ! በአላህ ይሁንብኝ አላህ አይጥልህም፤ አንተ ዝምድናን ትቀጥላለህ፣ የሌለውንም ታግዛለህ (ለደሆች ትረዳለህ)...» እንዳለችው ሁሉ።
ስለዚህ ለሴት ልጅ የሚገባት በባልዋ ጉዳይ አላህን ልትፈራና በትዕግሥት ልታልፈው ነው፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ልጅ ወልደው በልጆቻቸው ይበልጥ ይጠመዳሉ።
ነገር ግን አንድ ሱናን የሚከተል ሙስሊም የሚያገባና የሚፈታ፣ ደግሞ የሚያገባና የሚፈታ ከሆነ፣ ይህ ነገር ብዙ ሴቶች ከሱና (ከሃይማኖት መንገድ) እንዲሸሹ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ጌታችን እንደተናገረው በባልና ሚስት መካከል ፍቅርን ያሳደረው እርሱ ነውና ራሳቸውን በአላህ ኢባዳ (አምልኮት) እና በእውቀት (ዒልም) ሊያጠምዱ ይገባል። አላህም ረዳታችን ነው።
ምንጭ፦ «አስኢለቱ እም ያሲር አል-ፈረንሲያ» ከተሰኘው የካሴት ትምህርት
ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ)
ዲን ያላትን አግባ የተባልከው በምክንያት ነው፤ ለራስህም የኑሮህ ማጣፈጫ ቅመም ነች። ልጆችህንም በስነ ምግባር እና በዲን አንጻ ጥሩ ደረጃ ታደርሳቸዋለች።
እናት!!
እናት!!
እናት!!
⭕️ አል-ቡኻሪን ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ አሽ-ሻፊዒይን ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ አህመድ ኢብኑ ሀንበልን ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ ሙሐመድ አል-ፋቲህ የቁስጥንጥንያ (ኮንስታንቲኖፕል) ፈታሂ ይሆን ዘንድ ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ አል-ሀፊዝ ኢብኑ ሀጀርን ያሳደገችው እህቱ ናት።
⭕️ የኢብኑ ተይሚያ እናት "ተይሚያ" ትባል ስለነበር በሷ ስም ተጠራ፣ በሱም ታወቀ።
⭕️ የኢማም ማሊክ እናት የዑለሞችን (የሊቃውንትን) አልባሳት ታለብሰውና “ወደ ረቢዓ ሂድ፤ ከእውቀቱ በፊት ከሥነ-ምግባሩ ተማር” ትለው ነበር።
⭕️ የሱፍያን አሥ-ሠውሪ እናት፡ “እውቀትን ፈልግ፤ እኔ በእንዝርት ሥራዬ እመግብሃለሁ/እረዳሃለሁ” ትለው ነበር።
⭕️ ኢማም አል-ኦዛዒይን እናቱ የቲም (የላመደችበት/አባት የሌለው) ሆኖ ሳለ የሻም ህዝቦች ኢማም እስኪሆን ድረስ አሳደገችው።
⭕️ አብደላህ ኢብኑ አዝ-ዙበይርን ያሳደገችው እናቱ አስማእ ቢንት አቢ በክር ስትሆን፣ በጀግንነትና በጽናት ላይ ኮትኩታ አሳደገችው።
🌿 ሴቶች የወንዶች ማፍሪያ/መቅረጫ ናቸው፤ ሴት ልጅ ከተስተካከለች/ካመረች ቤቱ ያምራል፣ ቤቱም ከተስተካከለ ማህበረሰቡ ያምራል።
🌿 እናት የአمة (የህዝብ) እኩሌታ ናት፤ ሌላኛውን እኩሌታ ደግሞ የምታሳድገው እሷው ናት፤ ስለዚህ አمة (ህዝብ) የሚነሳው/የሚበለፅገው በሷ መልካምነትና ጥንካሬ ነው።
Repost from عبد الصمد محمد نور الجبرتي
የዲን ትምህርት መማር
ዓብዱሶመድ ሙሐመድ ኑር
Telegram : https://t.me/AbdusomedMNur_Channel/5475
YouTube: https://youtu.be/Us5gsXMdnKo?si=7aXoyYt9_WBHPcEZ
🌋በራያ ህዝብ ላይ የጦርነት ዳመና ዳምኗልና
በመላው አለም ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችን በዱኣ አትርሱን!!!!!!
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
🔘አጭር እና ቆንጆ የጁሙዓ ኹጥባ
👤 ኹጥባውን ያደረጉት፡ ሸይኽ አህመድ (ከሳዑዲ ኤምባሲ)
📍 ቦታ፡ አዲስ አበባ — ቦሌ ጀዕፈር መስጂድ
🗣 ቋንቋ፡ በአረብኛ ቋንቋ የተደረገ
📖 በኹጥባው ላይ የተዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች
① ተውሂዱል ኡሉሂያ (የአላህን ብቸኛ ተመላኪነት)
🔘 የኢባዳ ዓይነቶች በሙሉ ለአላህ ብቻ እንደሚገቡ በሰፊው ተዳሷል።
② የተውሂድ አሳሳቢነትና ታላቅነት
🔘የሰው ልጅ የተፈጠረበት ዋና ዓላማና የእስልምና መሠረት መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል።
③ የሽርክ አስከፊነት
🔘አላህ ዘንድ የማይማር ትልቅ ወንጀልና የሥራዎችን ዋጋ የሚያሳጣ መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል።
④ ስለ ቢድዓ ምንነት
🔘ቢድዓ በዲን ላይ የሚያስከትለው አደጋና ትክክለኛው መንገድ ምን እንደሆነ በሰፊው ተወስቷል።
⑤ ኢኽላስ እና ሙታባዓ በዒባዳ ላይ ያላቸው አስፈላጊነት
🔘ማንኛውም መልካም ሥራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ለአላህ ተብሎ ጥራት ተደርጎ የተሰራ(ኢኽላስ) እና የነቢዩን ሱና መከተል (ኢትባዕ) ግዴታ መሆናቸው ተብራርቷል።
⑥ ስለ ተቅዋ (አላህን መፍራት)
🔘የአላህን ትእዛዝ ማክበር፣ ክልከላዎቹን መራቅና የልብ መረጋጋትን ስለሚያስገኘው ተቅዋ ምክር ተለግሷል።
አላህ የሰማነውን ሰምተው ከሚተገብሩትና የተውሂድ ባለቤቶች ከሆኑት ባሮቹ ያድርገን!
ሼር ይደረግ🔗🔗🔗https://t.me/ansuar_muhammed_0088
አህባሽ ማን ነው?
አህባሽ የሚባለው አንጃ ከውጪ ሲታይ የሚከተሉት ገጽታዎች አለት፡፡
1. “አህባሽ” የኢትዮጵያ ተወላጅ በነበሩት ሼኽ አብደላሂ ሙሀመድ ዩሱፍ
(ወይም ሼኽ አብደላህ አል-ሀረሪ አል-ሀበሺ) ጠንሳሽነት በሊባኖስ ዋና
ከተማ ቤይሩት ውስጥ በ1983 አ.ል. የተመሰረተ ፖለቲካና ሀይማኖትን
አንድ ላይ አጣምሮ የሚራመድ አንጃ (ጀመአ) ነው፡፡
2. አንጃው በአረብኛ አጠራር “ጀምኢየቱል መሻሪኢል ኸይሪየቱል
ኢስላሚያ” ይባላል ፡፡ የእንግሊዝኛ ስሙ “Association of Islamic
Charitable Projects” የሚል ነው፡፡
3. “አህባሽ” የአንጃው ተከታዮች በጋራ የሚጠሩበት የቡድን ስማቸው ነው፡፡
እያንዳንዱ የጀመአው አባል “ሀበሺይ” ይባላል (ሴት ከሆነች “ሀበሺያ”
ትባላለች )፡፡ በሀገራችን ውስጥ ያሉት የአንጃው ተከታዮች ግን “አህባሽ”
ከሚለው ስም ይልቅ “የሼኽ ጀመዐ ነኝ” ማለትን ይመርጣሉ ፡፡
4. “አህባሽ” የሚውለው ቃል ምንጩ “ሐበሻ” ከሚውለው የሀገራችን የአረብኛ
ስም ነው፡፡ ይህም የአንጃው መስራች የተወለደበትን ሀገር (ኢትዮጵያን)
ያመለክታል፡፡ የጀመኣው አባላት ይህንን ስም ይወዱታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ ስለዚህ እኛ የአህባሽ ተቃዋሚዎች ያወጣንላቸው ስም አድርጋችሁ እንዳታዩት ያስፈልጋል ፡፡ (እውነቱን ለማወቅ አህባሾችን ራሳቸውን ጠይቋቸው፡፡ ዌብሳይቶቻቸውንና የፋስቡክ ቡዴኖቻቸውን የሚጠሩበትንም ስም ተመልከቱ )፡፡
5. አንጃው በሄደበት ሀገር ሁለ “መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር” ተብሎ ነው
የተመዘገበው፡፡ በመሆኑም ማህበራዊ አገልግልት የሚሰጡ አንዳንድ
ተቋማትን (እንደ መድረሳና የጤና ክሊኒክ የመሳሰሉትን ) ከፍቷል ፡፡
በሀገራችን ውስጥ ግን እንድህ አይነት ፕሮጀክቶችን የሰራ
አይመስለኝም፡፡
6. አህባሽን የመሰረቱት “ሼይኽ አብደላህ አል-ሀረሪ” ከአስራ ሰባት አመታት
በፉት ቢሞቱም እስካሁን ድረስ የአንጃው ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ
ተደርገው ይታያሉ ፡፡ በመሆኑም የጀመአው አባላት “ሼይኹና” ወይም
“ሰይዱና” ይሏቸዋል ፡፡ በቤታቸው ግድግዳና በሌሎችም ቦታዎች
(በሞባይል ስልካቸውም ጭምር) የመሪያቸውን ፎቶ ያስቀምጣሉ ፡፡
7. የአንጃው ዋና ማዕከል (Head Quarter) ነሆው በሊባኖስ ዋና ከተማ
ቤይሩት ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም በሶሪያ፣ ዮርዲኖስ፣ ግብጽ
ጫት በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የአደንዛዥ እጾች ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ባለሙያዎች ለ9 ዓመታት ያህል በጫት ላይ ሳይንሳዊ ጥናት ካደረጉ በኋላ፤ ጫት በአእምሮና በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ አደንዛዥ ንጥረ ነገሮች ያሉት መሆኑን አረጋግጠዋል። እንዲሁም በዩኔስኮ (UNESCO) እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደረጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለና ጎጂ እንደሆነ ተመዝግቧል።
ጫት መቃምን እንከላከል!!!
የጫት እርምነት (ሕገ-ወጥነት) ላይ የተሰጠ ፈትዋ
ጥያቄ፡
ጫት ሀላል ነው ወይስ ሀራም? እንዲሁም እርምናውን (ሀራምነቱን) የሚያስረዳ ግልጽ የሆነ ማስረጃ አለን? ምክንያቱም ብዙ ሰዎች «በጫት እርምና ላይ የመጣ ግልጽ ማስረጃ የለም» ይላሉና። እባክዎን አብራሩልን፤ አላህ መልካም ምንዳዎን ይክፈልዎት!
መልስ፡
ምንም ጥርጥር የለውም፤ ሃይማኖታችን እስልምና ምንም ዓይነት ጎደሎና ጉድለት የሌለበት ሙሉ ሃይማኖት ነው። ታላላቅ አንቀጾቹና መመሪያዎቹ በየዘመናቱ አዳዲስ ኩነቶች ጋር የሚሄዱ፣ ለሁሉም ጊዜና ቦታ የሚበጁ ናቸው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ብሏል፡
﴿وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا طَائِرٍ يَطِيرُ بِجَنَاحَيْهِ إِلَّا أُمَمٌ أَمْثَالُكُم ۚ مَّا فَرَّطْنَا فِي الْكِتَابِ مِن شَيْءٍ ۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يُحْشَرُونَ﴾ [الأنعام: 38] "በምድር ላይ የሚንቀሳቀስ እንስሳም ሆነ በሁለት ክንፎቹ የሚበር በራሪ የለም፤ እናንተን የመሰሉ ህዝቦች ቢሆኑ እንጂ። በመጽሐፉ ውስጥ ምንም ነገር አልተውንም፤ ከዚያም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ።" [ አል-አንዓም፡ 38]አላህ ጥራት ይግባውና እንዲህም ብሏል፡
﴿الْيَوْمَ يَئِسَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن دِينِكُمْ فَلَا تَخْشَوْهُمْ وَاخْشَوْنِ ۚ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا﴾ [المائدة: 3] "ዛሬ እነዚያ የካዱት ከሃይማኖታችሁ ተስፋ ቆረጡ፤ ስለዚህ አትፍሯቸው፤ እኔንም ፍሩኝ። ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ጸጋዬንም በእንተ ላይ ፈጸምኩ፤ እስልምናንም ለእናንተ ሃይማኖት አድርጌ ወደድኩ።" [ አል-ማኢዳህ፡ 3]ስለዚህ፤ የጫት ጉዳይ በአላህ መጽሐፍ (ቁርአን) እና በነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሱና ውስጥ በጠቅላይ መመሪያ የተካተተና የተገለጸ ነው። አላህ ስለ ነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላል፡
﴿يَأْمُرُهُم بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ﴾ [الأعراف: 157] "በመልካም ነገር ያዟቸዋል፤ ከጥፉ ነገርም ይከለክላቸዋል፤ መልካም የሆኑትን ነገሮች ለእነሱ ይፈቅድላቸዋል፤ መጥፎ (ጎጂ) የሆኑትን ነገሮች ደግሞ በእነሱ ላይ እርም (ሀራም) ያደርግባቸዋል።" [ አል-አዕራፍ፡ 157]ጫት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ሀራም ነው ብለው የፈረዱ የአብዛኞቹ ዘመናዊ ኡለማዎች (ሊቃውንት) አቋም፡ "ጫት ከመጥፎ/ጎጂ ነገሮች (ኸባኢስ) ወገን ነው" የሚል ነው። በቀደመው አንቀጽ መሠረት ደግሞ ጎጂና መጥፎ ነገሮች በሙሉ እርም (ሀራም) ናቸው። እንዲሁም አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا (29) وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا (30)﴾ [النساء: 29-30] "ነፍሶቻችሁንም አትግደሉ፤ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና። ይህንንም ወሰን በማለፍና በመበደል የሚያደርግ ሰውን፤ እሳት እናስገባዋለን፤ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው።" [ አል-ኒሳእ፡ 29-30] ጫት በሰው ልጅ ነፍስ፣ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና በኡማው ላይ ትልቅ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ ነው፤ ነፍስን፣ ጊዜን፣ ገንዘብንና ዲንን ያጠፋል!
﴿فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ﴾ [يونس: 32] "ከእውነት በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ? ታዲያ ወዴት ትመለሳላችሁ?" [ ዩኑስ፡ 32]ጫት የሚቅምን ሰው ጤና በቅርብም ሆነ በሩቅ ጊዜ ይጎዳል። የኡለማዎች ስምምነት (እጅማዕ) እንደሚያስረዳው ማንኛውም ሰውን የሚጎዳ ነገር ሁሉ በእሱ ላይ መጠቀም ሀራም ነው። ሐኪም "ይህ ነገር ይጎዳል" ካለ፤ የሸሪዓ ሊቅ (ፈቂህ) "ይህ ነገር ሀራም ነው" ማለት አለበት። እንዴት አይሆንም! የታላቋ ሸሪዓችን መሠረታዊ ዓላማ አምስቱን ዋና ዋና ሕጎች (አል-ኩልያት አል-ኻምስ) መጠበቅ ነው፤ ከእነሱም አንዱ "ነፍስን መጠበቅ" ነው። ስለዚህ ወደ ነፍስ ጥፋት ወይም ወደ ውድመት የሚያመራ ማንኛውም ነገር ማድረግ በቁርጥ ሀራም ነው። አላህም እንዲህ ብሏል፡
﴿وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ﴾ [البقرة: 195] "በአላህ መንገድ ላይ ለግሱ፤ ነፍሶቻችሁንም በእጆቻችሁ ወደ ጥፋት አትጣሉ፤ መልካምንም ሠሩ፤ አላህ መልካም ሠሪዎችን ይወዳልና።" [ አል-በቀራህ፡ 195]በጫት ምክንያት ራሱን ለበሽታ ወይም ለጥፋት ያጋለጠ ሰው፣ በአቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) ተተርኮ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት የነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሐዲስ ፡
«مَنْ تَرَدَّى مِنْ جَبَلٍ فَقَتَلَ نَفْسَهُ فَهُوَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ يَتَرَدَّى فِيهِ خَالِدًا مُخَلَّدًا فِيهَا أَبَدًا، وَمَنْ تَحَسَّى سُمًّا فَقَتَلَ نَفْسَهُ فَسُمُّهُ فِي يَدِهِ يَتَحَسَّاهُ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدًا مُخَلَّدًا فِيهَا أَبَدًا...» (رواه البخاري ومسلم) "ከተራራ ላይ ራሱን ጥሎ የገደለ ሰው፤ በጀሀነም እሳት ውስጥ ዘውታሪ ሆኖ ሁልጊዜ ይወድቃል። መርዝ ጠጥቶ ራሱን የገደለም ሰው፤ መርዙ በእጁ ላይ ሆኖ በጀሀነም እሳት ውስጥ ዘውታሪ ሆኖ ይጎነጨዋል።" (ቡኻሪና ሙስሊም)ከሱና የመጡ ማስረጃዎች፡ ከሱና ደግሞ ይህ ሶሂህ (ትክክለኛ) ሐዲስ በቂ ነው፤ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡
«كُلُّ مُسْكِرٍ خَمْرٌ وَكُلُّ خَمْرٍ حَرَامٌ» (رواه مسلم) "ማንኛውም አሰካሪ ነገር ኸምር (አልኮል/አደንዛዥ) ነው፤ ማንኛውም ኸምር ደግሞ ሀራም ነው።" (ሙስሊም ዘግበውታል)በሶሂህ ዘገባ ላይ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንደተረኩትም፡
«مَا أَسْكَرَ كَثِيرُهُ فَقَلِيلُهُ حَرَامٌ» > "ብዙው የሚያስክር ነገር፤ ጥቂቱም ሀራም ነው።"እንዲሁም እሙ ሰለማህ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ዘገባ፡
«نَهَى عَنْ كُلِّ مُسْكِرٍ وَمُفَتِّرٍ» > "ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ከማንኛውም አሰካሪና (አእምሮን ከሚያደነዝዝ) እንዲሁም አካልን ከሚያፈዝ/ከሚያደክም ነገር ከልክለዋል።"የጫት አነስተኛው ጉዳት አካልንና መንፈስን ማድከም (ሙፈቲር) መሆኑ ይታወቃል። የሳይንስና ሕክምና እይታ የታመኑ ባለሙያ ዶክተሮች እንደሚያረጋገጡት፤ በጫት ውስጥ ልክ እንደ አልኮልና ሌሎች አደንዛዥ ነገሮች ሁሉ አእምሮ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ንጥረ ነገሮች ይገኛሉ።
Repost from دروس وفوائد أبي حزام عبدالرحمن بن سعيد
ዕድሜያችን ሊመለሱ የማይችሉ እስትንፋሾች ናቸው፤ ሽበት ደግሞ ዱንያን የመልቀቂያችን ወቅት መቃረቡን የሚያሳስብ መልእክተኛ ነው።
የጊዜያት ማለፍና መተካካት፣ የእድሜያችን መጨመር ለጉዞ መሰናዳትን እንጂ የልብ ድንዛዜን እንዳያወርሰን።
በራሳችን ላይ የምትበቅለውን እያንዳንዷን ሽበት ለዒባዳ የምንነቃቃበት ቀብርን ማስታወሻ እናድርገው፣ የምናነበውንም እያንዳንዱን የቁርኣን አንቀጽ ካለንበት ጥፋት ነውር የሚመልሰን ተግሣጽ እናድርገው።
ጊዜያችን ከማለቁ በፊትም ለነፍሳችን ልንደርስላት ወደ ተውባ ለመምጣት ፈጥነን ልንነሳ ይገባል።»
ኢብኑ ረጀብ (رحمه الله ) ለጣኢፊል መዓሪፍ በተሰኘው ኪታባቸው ላይ
" يا من أنذره الشيب بالموت و هو مقيم على الآثام ، أما كفاك واعظ الشيب مع واعظ القرآن ؟! ".
الحافظ ابن رجب ،
: لطائف المعارف (٢٥٩).
«ሽበት በሞት እያስጠነቀቀህ፣ አንተ ግን አሁንም በወንጀልና በኃጢአት ላይ የጸናኸው ሰው ሆይ! ከቁርኣን ተግሣጽ ጋር የሽበትህ ተግሣጽ አልበቃህምንም?!» ሲሉ መክረዋል
https://t.me/durusuabihizam
https://t.me/durusuabihizam
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
ማነው መጤው?
~
ሙስሊሙ መብቱን በጠየቀ፣ ጭቆናን በተቃወመ፣ እምነቱን ባስተማረ ቁጥር "እናንተ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ስትገቡ አክብረን በተቀበልን እንዴት ውለታችን ይረሳል?" እያሉ በቅጥፈት ለሚመፃደቁ አካላት "እንዴ! እኛ እኮ ኢትዮጵያውያን እንጂ መጤዎች አይደለንም" እያሉ በከንቱ መድከም አያስፈልግም ብዬ በፅኑ አምናለሁ። ሰዎቹ እንዲህ አይነት አመክንዮ የሚገባቸው አይደሉም። ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው። መፍትሔው ማጥቃት እንጂ መከላከል አይመስለኝም። በራሱ ቋንቋ አናግረው።
በዚህ ድንቁ ^ ርና ላይ በሰፊው የሚታወቁት በዋናነት የአንድ እምነት ተከታዮች ናቸው። እነሱ ናቸው "የእስላም አገሩ መካ፣ የአሞራ አገሩ ዋርካ" የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ፈጥረው ድንቁርናቸውን ከትውልድ ትውልድ የሚያሻግሩት። እንዴት አድርገው እንደሚጠርቧቸው እንጃ በዚህ ዘመን እንኳ አልተቀየሩም። የለውጥ ተስፋ የሚታይባቸውም አይደሉም።
አስቂኙ ነገር ደግሞ ራሳቸውን የአይ^ሁድ ዘር አድርገው መኮፈሳቸው ነው። ሃገሪቱን ለሰባት መቶ ዓመታት በላይ የቦጠቦጠው ራሱን "ሰለሞናዊ መንግስት" ብሎ የሚጠራው መዥገር ስርአትኮ ባህር ተሻግሮ የሰሎሞን ዘር ነኝ የሚል ነው። መጤ ነኝ ማለት አይደል ይሄ? አፄ ምኒልክ "ዳግማዊ" ምኒልክ የተባለው ጥንት ከንጉስ ሰለሞን የተገኘ "ቀዳማዊ" ምኒልክ ነበር ብለው ስለሚያምኑ ነው። "የናዝሬቱ እየሱስ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ቃና ዘገሊላ፣ ቤተልሄም፣ እየሩሳሌም፣ ... " እያለ እምነቱን ከባህር ማዶ ጋር የሚያይዝ አካል እንዴት ሙስሊሞችን መጤ ሊያደርግ ይዳፈራል?!
የሙስሊሙን ኢትዮጵያዊነት መቀበል የከበዳቸው ጭንቅላቶች "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" የሚል ያረጀ ያፈጀ ተረት ዛሬም ይተርታሉ። ለመሆኑ እነሱ ዘንድ ኢትዮጵያ ማለት የቷ ናት? ለመሆኑ ኢትዮጵያ ሲሉ አፋርን፣ ሶማሊን፣ ሀረርን፣ ስልጤን፣ ከፊል ጉራጌን፣ ሰፊውን ኦሮሚያን፣ ሀላባን፣ አብዛኛው ወሎን፣ አብዛኛውን በኒሻንጉልን፣ ድሬዳዋን፣ አርጎባን፣ ... ይጨምራል ወይ? እስኪ እነዚህን አካባቢዎች ቆርጠው ያውጡና የደሴቷን ካርታ ይመልከቱ። ካርታው ላይ የሚታየው ቀዩ ክፍል ነው የሚቀራቸው። ከዚያ የቀራችሁን የክርስቲያን ደሴት ተመልከቷት! የምትዘምሩላት ኢትዮጵያ ይቺ ናት?
ለማንኛውም "በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል የሰለሞን ዘር ነን"፣ "ነገደ ይሁዳ ነን"፣ "የይሁዳ አንበሳ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት የምታምኑበት ከሆነ መጤዎች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ መስክራችኋል። እኛ ሙስሊሞች ዐረቦች ነን አላልንም። ኢትዮጵያውያን ነን። እናንተ "የሁ^ዶች ነን" ካላችሁ እኛ ነን የተቀበልናችሁ።
"አይ" ካላችሁ "አይ^ሁድ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት ውሸት እንደሆነ አስረግጣችሁ ወርውራችሁ ጣሉ። ከዚያ በኋላ ራሳችሁን የኢትዮጵያዊነት አከፋፋይና ድርጎ ሰፋሪ አድርጋችሁ ማየታችሁን አቁሙ። የነውረኝነታችሁ ዳፋ ለደካሞች ይተርፋልና ጥፍራችሁን ሰብስቡ። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የከረፋ ሃሳብ ስታንፀባርቁ ታንኩም ባንኩም በእጃችሁ በነበረበት የቀደመው ዘመን ያደረሳችሁትን ማሰብም ይሰቀጥጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
