ch
Feedback
قناة أبي عبدالله السلفي

قناة أبي عبدالله السلفي

前往频道在 Telegram

منهجنا منهج السلف الصالح هو المنهج الذي سار عليه الصحابة والتابعون نحارب البدع والخرافات

显示更多
未指定国家未指定类别
197
订阅者
无数据24 小时
-57 天
-530 天
帖子存档
ገነህ ለመታየትና ለመታወቅ አትዋሽ قال رجل لصاحبه : هل ذكرني الخطيب في تاريخ بغداد في الثقات أو مع الكذابين ؟ فقال صاحبه : ماذكرك أصلا ! فقال : ليته ذكرني ولو مع الكذابين السير: 381/18  “አንድ ሰው ለጓደኛው "ኸጢቡል በግዳዲ" የበግዳድ ታሪክ ላይ ከእውነተኞች ነው ያወሳኝ ወይስ ከውሸታሞች ብሎ ጠየቀው! ሲጀመር ከየትኞቹም አልተወሳህም ሲለው! ምናለ ነበር ከውሸታሞችኳ ስሜን አውስቶት ቢሆን ብሎ ቁጭቱን ገለፀለት።” ለታዋቂነት ከመጠማት አላህ ይጠብቀን! ዛሬም ቢሆን ሚዲያ ትክክለኛውን ነገርና ትክክለኛውን አካሄድ ሰዎች ጋር የምታስተዋወቅበት ብቻ መሆን አለበት። ከአላህ ዘንድ መታወቅ የስኬት ሁሉ ጥግ ሲሆን፤ ከሰዎች ዘንድ መታወቅ የማይዳሰስ የህልም ደስታ ነው።   #አንድ አባባል አለ! ቴሌቪዥን ላይ መጥቶ ታዋቂ ለመሆን፤ ትልቅ ከተማ ላይ በአደባባይ ባንክ ቤት መስረቅ በቂ ነው ሲባል እሰማ ነበር። ሆኖም ይሄን በተግባር አየሁት። ላይክ ፎሎ የቻናል ሚንበር ከፍ ለማድረግ እርኩስ ስራ በአደባባይ መስራት በሚዲያ ማሰራጨት ጥሩ ሠዎችን መወረፍ ትልልቅ መሻይኾችን በተለይ ሸይኽ አብዱል ሓሚድ ያሲንን ማንቋሸሽ ተደርጎ ተይዟል።     ስለሆነም የሰይጣን ስራ በተሰራ ቁጥር በርካታ ሠዎች የሚሰበሰቡት ሰይጣን በሰው ልጆች ላይ ምን ያህል ሥራውን እንደሠራ ያመለክታል። ሠዎች መልካም ነገር ጋዝ ጋዝ ብሏቸው ቅጥፈትና እኩይ ተግባር ማር ማር ካላቸው አደጋ ላይ ናቸውና ሁሉም ራሱን ሊፈትሽ ይገባል።    የአላህ ባሮች ሆይ ይሄ ዲናችን መጫዎቻ መበሻሸቂያ አይደለም። ቂልነትንና ቅጥፈትን በመላበስ ለመታወቂያ የሚጠቀሙበት አይደለምና ከዚህ ሁሉ እኩይ ተግባር የራቁ አላህ በደረጃቸው ከፍ ያደረጋቸው ሠዎች ለመሆን እንሞክር። وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا {{እነዚያም እብለትን የማይመሰክሩ፤ በውድቅ ቃልም (ተናጋሪ አጠገብ) ባለፉ ጊዜ የከበሩ ኾነው የሚያልፉት ናቸው፡፡}} [ ሱረቱ አል-ፉርቃን፣ - 72 ] የአላህ ባሮች በዲኑ ላይ የሚደርሰውን ነገር ሁሉ እንደመጠኑ ይታገላሉ። ዲኑን ለመጠበቅ ዲንን እያጠፉ ያሉ ሙሽሪክ ሙብተዲዕ የሆኑ አካላቶችን በሰዎች መካከል የሚሰራጭ ፈሳድን ይፋለማሉ። ከዛ ውጭ ለማነም ብድር ለመመለስ ብለው እኩይ ተግባር ውስጥ አይገቡም። የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abdurhman_oumer/7395

ተጀምሯል በሸይኽ መሀመድ ሲራጅ ሀሮ ግቡ https://t.me/haroselefi

ሊጀመር ነው በሸይኽ መሀመድ ሲራጅ ሀሮ ግቡ https://t.me/haroselefi

ኢትዮጵያ 👉ያቺ የድሮችን ◌◌◌◌◌◌◌◌◌ እንደዛሬው ሳይሆን ያኔ በድሮው ስምሽን የማውቀው በሰላምሽ ነው ሙስሊሞች ሲሸሹ በጠላት ተከበው  ➪ ሁለቴ ጎበኙሽ ሰላምን ፈልገው 💬 እምዬ ኢትዮጵያ ያቺ የድሮችን ዛሬም ተመለሺ ውቢት ሀገራችን ➰ እስኪ ልመርቅሽ አሚን በይኝማ አላህ ይቀበለኝ ዱዓዬንም ይስማ ◈ ከፍ ይበል ባንድራሽ መታወቂያሽ ይላቅ ጋራ ሸንተረርሽ በፍቅር ይጥለቅለቅ @ እንኳን የሰዉ ልጅ ማሰቢያ ያለው አፈሩም ቅጠሉም ክፉ አያግኘው ○ ጭቆና እና በደል ይጥፉ ከጉያሽ  👉 በፍትህ ይደሰት የተከፋብሽ ◊ ትንሹም ትልቁም ጠቅላላ የሰው ዘር ልቡን ሀሴት ይሙላው ተጠልሎሽ ሲኖር ▪ በቅን የሚመራ ይስጥሽ መልካም መሪ ጀግና ህዝብ ይፍራብሽ ፈጣሪውን ፈሪ Ⓞ ሰላም ውሎ ይደር ተፈጥሮሽ በሙሉ ⁼ አላህ እውን ያርገው ምኞትሽን ሁሉ 🌐 የሰቆቃ ኑሮ አይታይ በምድርሽ ፍቅር ብቻ ይግባ በአራቱም በርሽ ኢትዮጲያ ሀገሬ ሰላምሽ ይብዛልኝ በየትኛውም መስክ ሳይከፋሽ ኑሪልኝ ✅ የኢስላም አስተምሮ ተውሂድ ይዘራብሽ ሀገሬ ኢትዮጲያ ሱና ይዝነብብሽ የሱና ሰው ያፍራ መላው አፈርሽ ○ላምላኩ ሚሰግድ ወጣት ይውጣብሽ ▦ ሰልጥነሽ ታወቂ ስምሽ ይሁን ቀና ሽርክ የሚያገሳውን ይዞት ስይጥንና ➝በስምሽ ይታፈር አስደንግጪውና ▢ ማጭድሽ ስል ይሁን የከፋ ከሳት ሽርክና ቢድዓን እንድትቆርጭበት ↪️ አንቺን ያየ ሁሉ ዝናሽን የሰማ በታማኝነትሽ በቶሎ እንዲስማማ ህዝብሽ ይኑርልሽ በተውሂድ ከተማ 📏 በመጥፎ ያሰበሽ አንቺን ሊያጠፋሽ ክፋት ሲያሰላስል ይጠረው ትንፋሽ መልካምሽን አይቶ ኸይር ይመኝልሽ ☔️ ሀገሬ ኑሪልኝ ሳይከፋሽ ላንድፍታ ሁሌም ይጠብቅሽ ያ ሀያሉ ጌታ 💧          ➝ አላህ ያጎናፅፍሽ የሰላምን ፀጋ ህዝብሽ ንቁ ይሁን ከእምነቱ አይዘንጋ ➰ ኑሪ ተደላድለሽ በደስታ ክነፊ ማየት አልፈልግም አንቺ ስትከፊ ◆ ሀገሬ ሁኚልኝ የሰላም መስፈሪያ የደግነት አምባ የፍቅር ማደሪያ ◆ ብቁ ህዝብ ይፍራብሽ አእምሮው የነቃ ፍጡር  የማይለምን  ከሰው  የተብቃቃ ○ ለእምነቱ ሲታገል የሌለው ይሉኝታ ታማኝ ዘር ይውጣልሽ የማታ የማታ 📝 ኡሙ ማሂር [ገጣሚዋ።] 💬◈💬◈💬 👇👇👇👇 https://t.me/AbuImranAselefy/11278

📢አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ 📢አስደሳች ዜና በሀሮ ሰለፍዮች ግሩፕ ልዩ የዳአዋ ፕሮግራም ጥሪ↩️ ⚙ የፕሮግራሙ አዘጋጆች፦ ✅ በ
📢አዋጅ             አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ           አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ አዋጅ 📢አስደሳች ዜና በሀሮ ሰለፍዮች ግሩፕ ልዩ የዳአዋ ፕሮግራም ጥሪ↩️ ⚙ የፕሮግራሙ አዘጋጆች፦      ✅ በሀሮ  ሰለፍያ  ጀምዓዎች 🪑 የእለቱ ተጋባዣ እንግዶቻችን ፦↩️ 🎙በሸይኽ መሀመድ ሲራጅ አቡ አብዱረህማን (ሀፊዘሁሙሏህ) 🟢 ኢንሻአላህ ሌላም ተጋባዥ እንግዳ ይኖራል 🗓 ፕሮግራሙ የፊታችን ነገ ማክሰኞ ከምሸቱ 3፡00 ሰአት ቡሀላ ይጀመራል ቀደማችሁ በመገኘት የፕሮግራሙ ተካፋይ ይሁኑ!!! ♻️ ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ። ✍በቻናል እና በግሩፓች ሼር በማድረግ ሀላፍትናችንን እንወጣ ➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/haroselefi https://t.me/haroselefi 🌐 ሸር በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ኢንሻአሏህ ዛሬ በዚሁ ግሩፕ ያማረና ያሸበረቀ የዳዕዋ ና የንያ🎙 ፕሮግራም ይኖረናል ሸር 🌟 በማድረግ ወርቃማ ምሽቱን ሌሎችንም ተጠቃሚ እናርግ ሸ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ኢንሻአሏህ ዛሬ በዚሁ ግሩፕ ያማረና ያሸበረቀ የዳዕዋ ና የንያ🎙 ፕሮግራም ይኖረናል ሸር 🌟 በማድረግ ወርቃማ ምሽቱን ሌሎችንም ተጠቃሚ እናርግ ሸር              ሸር                ሸር https://t.me/bilalmesji https://t.me/bilalmesji

▶️ ሊጀመር 1:00 ሰአት ቀርቷል ግን ሸር እያረግን አደለም እንንቃ ይሰበር ዝምታዉ https://t.me/bilalmesji https://t.me/bilalmesji
▶️ ሊጀመር 1:00 ሰአት ቀርቷል ግን ሸር እያረግን አደለም  እንንቃ ይሰበር ዝምታዉ https://t.me/bilalmesji https://t.me/bilalmesji

🔴 ግቡ ግቡ ሰበር ላይቭ! 🎙 ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት አል-ወለዊይ 📚 ርእስ፦ “📚ሰቢሉ አል-ረሻድ ፊ ሀድይ ኸይሪ አል-ዒባድ !! ገብትዋል ሼር ሼር አድርጉ https://t.me/SheikMohmme
🔴 ግቡ ግቡ ሰበር ላይቭ! 🎙 ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት አል-ወለዊይ 📚 ርእስ፦ “📚ሰቢሉ አል-ረሻድ ፊ ሀድይ ኸይሪ አል-ዒባድ !! ገብትዋል ሼር ሼር አድርጉ https://t.me/SheikMohmmedHyatHara?livestream=43318a19438ec812ff

የጁመአ ሱናወች ሻወር 🚿 ፀዴ ልብስ 👕 ሲዋክ 🪥 ሽቶ (ለወንድ) 🌹 በጊዜ ወደ መሥጂድ 🕌 ሱረቱል ከህፍ መቅራት 📖 በነብያችንም ላይ ሰለዋት ማዉረድ እንዳይረሳ اللهم صل وسلم وبار
የጁመአ ሱናወች ሻወር 🚿 ፀዴ  ልብስ 👕 ሲዋክ     🪥 ሽቶ (ለወንድ) 🌹 በጊዜ ወደ መሥጂድ  🕌 ሱረቱል ከህፍ መቅራት 📖 በነብያችንም ላይ ሰለዋት ማዉረድ እንዳይረሳ اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد وعلى اله وصحبه اجمعين

﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾. «اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَاتَكَ وَسَلَامَكَ وَبَرَكَتَكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ أكْرَمِ الخَلْقِ وَإمَامِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ».

አዲስና ወሳኝ የሆነ ዳዕዋ! ======> ✅ محاضرة جديدة ✅ አዲስ ሙሐደራ      ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ 💎 ርዕስ፦ ↪️ «ወደ አላህ መመለስ (ተውበት)!» በሚል ርዕስ የተደረገ ወሳኝ እና አንገብጋቢ የሆነ ዳዕዋ! 📢 በደንብ ትደመጥ! 🎙الأستاذ الفاضل أبي أنس أبي جعفر محمد أمين السلفي «حفظه الله» 🎙በውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ አቡ አነስ [አቡ ጀዕፈር] ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና                         🏠ቦታ፦ 🕌 በሰለፍዮች ፉርቃን መስጂድ [ሸዋሮቢት ከተማ] የተሰጠ ወቅታዊ እና ወሳኝ የሆነ ምክር!         •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈• 👇👇👇 ጆይን ብለው ይከታተሉ https://t.me/+w-uAkEZwibVlNzM8 📱⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣⇣ @Durusu_Abu_Anes @Durusu_Abu_Anes @Durusu_Abu_Anes

የደዕዋ ፕሮግራማችን              ተጀምሯል                   ተጀምሯል                                          ተጀምሯል                        በሸይኽ  አሁን  ሸይኽ አቡዘር ሀሰን አቡ ጦልሀ (ሀፊዞሏሁ ተአላ )           ↘️ሼር       ↘️ሼር   ✅አድርጉት   ✅የስርጭት   ሊንክ👇👇 https://t.me/mesjidelfethii

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته       👉አስደሳች ዜና          ሰበር ዜና ↪️ታላቅ አኽባር በኸይር በር በስተኩል ↪️ታድማችኋል 👉 በ(online) 📢በአይነቱ ለየት ያለ ታላቅ የዳዕዋና የንያ ፕሮግራም ዝግጅት  የደመቀና ያሸበረቀ ምሽት ስላለን ታዳ የኸይር ባልተቤቶች በሙሉ ሁላችሁም ታድማችኋል በተባለው ሰአትና ወቅት በመገኛት ተሳትፈው የአኼራ ቤታችነን በመሰነቅ አሻራችነን እንጣል      ♻️የምስራች ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራም 👉እነሆ ◉◉ የፊታችን እሁድ ማለትም 🗓 መስከረም ቀን 04/01/2018 🕓ከምሽቱ  3:30 ሰአት በመገኘት ሁሉም ወንድም እህቶች ተጋብዘዋል 👁‍🗨 በኮምቦልቻ የቱሉ አዳሚ መስጅደል ፈትህ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የቴሌግራም ግሩፕ ላይ በተባለው ቀንና ሰአት ጎራ በማለት ይሳተፉ ሌሎችንም ያሳትፉ    የንያያ ዘመቻ በየአላችሁበት ሁላቹም ተጋብዛችዋል 📢📢📢📢📢📢 አሏህ በሰላም ያድርሰን 🪑በአሏህ ፍቃድ የእለቱ ተጋባዠ እንግዳቻችን 🎙በታላቁ ሸይኽ በሸይኽ  አቡ ዘር ሀሰን አቡ (አቡ ጦልሀ )ሀፊዞሁላህ 🎙በሸይሀችን ሸይህ ሙሀመድ ጀማል ኮምቦልቻ (ሀፊዘሁሏህ)      🎙ሸይኻችን አቡ መንሱር ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት አል-ወሎውይ አላህ ይጠብቃቸው! 🎙ኢንሻ አላህ ሌሎች ተጋባዥ እንግዳ ይኖራሉ! 🌐 👉ሼር      👉 ሼር   👉ሼር  👍በመነየት  👍አድ  👍 አድ 👍 አድ በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ  ለአኼራችን አሻራ እናሳርፍ !! ⬇️⬇️⬇️⬇️‎📡 ፕሮግራ📲ሙ የሚካሄድበት ቦታ;-             በቴሌግራም ቻናላችን!!! https://t.me/mesjidelfethii

ኢኽዋኖችና አባይ ግድብ ◌◌◌◌◌◌◌▿ ◈ የግብፅ ፍብርክ የሆነው የኢኽዋነል-ሙስሊሚን (ሙስሊም ወንድማማቾች) የተሰኘው የፖለቲካ ድርጅት በኢስላም ስም እየነገዴ የስልጣን ጥማቱን የሚያረካ ድርጅት ነው። በሀገራችንም እንቅስቃሴ ከጀመረ አመታት ተቀጥረዋል። ➪ የሀገራችን ኢኽዋኖች ከዚህ በፊት ከጠማማው የአህባሽ ጥርቅም ጋር ግርግር በፈጠሩ ጊዜ አብዛኛው ህዝብ የዲን ጉዳይ መስሎት በርካታ መስዋዕትነት ከፍሏል። ◊ በዛ ጊዜ ከዚህ ስብስብ አስተባባሪዎች አንዱ «አህባሽን የምንቃወመው በፖለቲካዊ ርዕሶች ብቻ ነው» በማለት ከአህባሽ ያላቸው ግብግብ የመጅሊስ ስልጣን ጉዳይ እንጂ የዲን አለመሆኑን የአደባባይ ነጥብ አድርገው ነበር። ➪ በዚያን ጊዜ ትግል ከሚያንዘባርቋቸው አቋሞች መካከል “አባይ ይገደባል አህባሽ ይወገዳል” የሚል ይገኝበት ነበር። ይች መፈክር ፖለቲካዊ አካሄዳቸውን ለማሳመሪያ እንጂ ከልባቸው የአህባሾች አቂዳ አሳስቧቸው አልነበረም። ◌ ሰሞኑን የህዳሴውን ግድብ ምርቃት አስመልክቶ ንግግር ካደረጉ ኢኽዋኖች መካከል ከፊሎቹ ❝አባይም ተገድቧል አህባሽም ከመጅሊሱ ተወግዷል❞ በማለት በደስታ ሲናገሩ አስተውለናል። ◈ አህባሽ ተወግዷልን? ❴ተወግዷል የሚሉት ከስልጣን ከሆነ ምናልባት በከፊል ልክ ነው። የናንተ ድካምና ግብ ስልጣን ስለሆነ ግባችን ተሳካ በማለት የስልጣን ጥማቸውን እየገለፁ ለዲኑ ደግሞ ደንታ ቢስ መሆናቸውን እያስመሰከሩ ነው።❵ ◆ የአህባሽ ስብስቦች ከዚህ በፊት ከሚንቀሳቀሱበት የሙስሊሙን አቂዳ የመሸርሸር ተግባር ባልተናነሰ አጠናክረው በቀጠሉበት ተጨባጭ አህባሽ ቸወግዷል እያሉ መሸልል ድርብርብ ጥፋት ነው https://t.me/AbuImranAselefy/11248

⁉️ የምን አዲስ አመት? =============> እረ ለመሆኑ ምን ጠፍቶ ከኛጋ፣ ከኩፋሮች በአል የምንለው ጠጋ፣ ◌ ጊዜው ሲቀያየር አመት ሲተካካ፣ ተሸቡህ ቢልኩፋር ወርሰነዋል ለካ፣ 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 መስከረም ሲጠባ ጷጉሜ ተጠናቆ፣ ለቅዱስ ዮሀንስ ፍየሏንም አንቆ፣ ◊ በገብስማ ዶሮ በእንቁላል በዳቦ፣ ከቤተሰቡጋ ሽርኩንም ተመግቦ፣ ◆ ➪ ከከሀድያኖች በይፋ ተመሳስሎ፣ ያከብራል ይህን ቀን አዲስ አመት ብሎ፣ 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 በሽርክ ውስጥ መዘፈቅ ከተውሂድ ርቆ፣ ከአሏህጋ መጣላት ከፍጡራን ታርቆ፣ ቆይ ግን እስከመቼ አመፅና ትእቢት፣ መሸንገል በዱንያ በዚህ አጭር ህይወት። 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 እንቁጣጣሽኮ የነርሱ በአል ነው፣ የኛ መቀላወጥ ሚስጥሩ ምንድነው? . ◌ ○ ለዘመናት ኖረን ነፃነት ተነፍገን፣ በአፄው ስርአት ተፅእኖ ውስጥ ወድቀን፣ ▪ ስንቋደስ ኖረን ከባህላቸው ቋት፣ ቀንበር ተጭኖብን የሚኒሊክ ስሌት፣ 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 በአንድ ሀገር አንድ እምነት ሙስሊም ተጨፍልቆ፣ ከሰው ሳይቆጠር አንሶና ተንቆ፣ ◉ ዛሬ ፀሀይ ወጥቷል ይበቃል ወገኔ፣ እምነታችን ይስፋን ተሸቡህ ለምኔ፣ 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 ◆ በቃ ይበቃናል ታሪኩም ይቀየር፣ በተውሂድ በሱና በመንሀጅ እንጠንክር፣ ⁰ የምን አዲስ አመት እረ የምን ጳጉሜ፣ ለኢስላም ብቻ ነው አጥንትና ደሜ፣ ◊ የሙስሊም ስም ለብሰህ ፍፁም አትልከስከስ፣ በረከሰ ቦታ በል እንዳትል ድርስ። 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 〰〰〰〰〰//〰〰〰〰〰 📝በወንድም አቡ ሳራህ ኸድር አደም https://t.me/AbuImranAselefy/11253

👆👆👆 #የመውሊድን ቢድዓነት እና በውስጡም ትልቁ ሺርክ እንደሚከሰትበት የተብራራበት ተከታታይ ክፍል፣ ክፍል 3 የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/shakirsultan/1494 🔶በአዲስ አበባ ከተማ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተሰጠ ኮርስ። 🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ) 🌐 https://t.me/shakirsultan

🟢ከሙመይዓዎች መገለጫዎች صفات المميعة ✏️وضع القواعد والتأصيلات المنهجية ✏️مسلك اللينة والسكوت عن أهل الضلا ✏️الرمي لأهل المنهج السلفي بالغلو في التجريح ✏️الرمي لأهل المنهج السلفي بتمزيق الصف ✏️መጤ መንሀጃዊ መርሆችና መሰረቶች ማስቀመጣቸው ✏️ከጥመት ባልተቤቶች ጋር ለዘብተኛ እና ጥፋታቸውን አይቶ የማለፈ አካሄዳቸው ✏️የሰለፊይ መንሃጅ ተከታዮችን "በትችት ወሰን አላፊ " ብለው መወረፋቸው ✏️የሰለፊይ መንሃጅ ተከታዮችን  አንድነትን አፍራሽ ብለው መወረፋቸው 📜البراهين المرصعة في كشف حال الحدادية والمميعة ከተሰኘው ኪታብ የተወሰደ 🛜በሀገራችን እነ ኢሊያስ አህመድ ፣ ኢብኑ ሙነወር እና መሰሎቻቸው ያሳራጩት መርዛማ አካሄድ ነው ተጠንቀቁ። https://t.me/Abuhemewiya

🚫   እውነትም እንቁ – ጣጣሽ      እንቁ የሚለው ቃል እኔ የማውቀው የከበረ ማእድን መሆኑን ነው ። እኛ ሀገር ግን ዘመን መለወጫ ላይ የሚወጣን አበባ ለመግለፅ ይጠቀሙበታል ። በእነርሱ እይታ አበባዋና ጣጣዋ ምን እንደሆነ ባላውቅም በኔ እይታ ግን የዘመን መለወጫን ተክትላ የምትመጣው እንቁ ብዙ ጣጣ አላት ። በሌላ አባባል ዘመን መለወጫው ብዙ ጣጣ አለው ።      ከሁሉም በፊት ይህ ባአል ከክርስትና እምነት ጋራ የተገናኘ ስለሆነ ሙስሊሞችን አይመለከትም ። ሙስሊሞች በአመት ሁለት ዒድ ( ባአል አላቸው) እነርሱም ዒደል አድሓና ዒደል ፊጥር ናቸው ። የዘመን አቆጣጠራቸውም የአላህ መልእክተኛ ወደ መዲና ሂጅራ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ በሂጅሪያ አቆጣጠር ነው የሚቆጥሩት ። በዚህ አቆጣጠር መሰረት አመቱ አልቆ አዲሱ የሚጀምርበት ወር ሙሐረም ይባላል ። ይሁን እንጂ ይህን የዘመን መለወጫ ቀን  እንደ ባአል አያከብሩትም ።     እንቁጣጣሽ የሚባለው ግን ከክርስትና እምነት ጋር የተገናኘ ባአል ነው ። ዘመኑንም ዘመነ ዮሐንስ,  ማቲዮሰ,  ሉቃስና ዻውሎስ ብለው ይሰይሙታል ።‼ ታዲያ ይህንን እንዴት ሙስሊሞች ያከብሩታል ? በጣም የሚገርመው የኢኽዋን መሪዎች አብሮነት በሚል ይህን ባአል የጋራ ለማድረግ ሲታትሩ ይታያል ። አልፎም በዚህና በጥምቀት ባአል ላይ በክብር እንግድነት ሲሳተፉና መግለጫ ሲሰጡም ሊታይ ይችላል ። ይህ የዲናቸውን ክብር ማስነካትና ራሳቸውንም ከማዋረድ ውጪ ጥቅም የለውም ።    የሀገረችን ሙስሊም በሱፍይ መሪዎች አማካይነት ታቦት ሲሸኙና ጥምቀት አብሮ እየጨፈረ ሲያከብር ኖራል ። ተራው የኢኽዋን ሆነና ጭራሽ እየሱስ ፍቅር ያስተማረ ጌታ ነው ‼ ብለው አረፉት ። ይህም ለሙስሊሙ ወላእና በራእ የሚለው የዐቂዳ ውድቀት ሰበብ ሆነ ። የአላህ መልእክተኛ ለኡመቴ የምፈራው አጥማሚ መሪዎችን ነው ያሉት ይህ ነው ።        ወደ ርእሴ ስመለስ እንቁ – ጣጣሽ እውነትም ብዙ ነው ጣጣሽ እላለሁ ። በመርህ ላይ ያልተመሰረተ ዐቂዳ ሁሌም ኮተት አያጣውም ። ዘመን መለወጫ ሲመጣ ሰዎች ካለፈው አመት ድክመታቸውና ስህተታቸው ታርመው የበለጠ ለመስራት ከመዘጋጀት ይልቅ የህይወታቸውን አቅጣጫ ለመቀየር ወደ መተትና ኮተት ያማትራሉ ። በመሆኑም ከምን ጊዜውም በላይ በዚህ የእንቁ–ጣጣሽ ባአል ላይ መተትና ድግምት ይሰራል ። ጠንቋዮች በጣም ቢዚ ይሆናሉ ። ይህ መተትና ድግምት የእነርሱ ህይወት ሊለውጥ የሌላው ህይወት ማጥፋት አለበት ብለው ነው የሚያስቡት ። በመሆኑም በአብዛኛው የሚሰሩ ድግምትና መተቶች በሰዎች ላይ ይሆናል ።    አላህ ከፈቀደው ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ። መጠንቀቁና ሰበብ ማስገኘቱ መልካም ነው ። በዘመን መለወጫው ማለዳ ( ጠዋት)  ላይ የተለያዩ ዶሮዎች በተለያየ መንገድ ተገለው በሰዎች መውጫና መግቢያ ላይ ወይም መንገድ ላይ ሊጣሉ ይችላሉ ። በሌላ መልኩ መሬት ተቆፍሮ ሊቀበሩም ይችላሉ  ። ሙስሊሞች በተለይ በዚህ ቀን ጠዋትም ሆነ ቀኑ ላይ ከቤታቸው ሲወጡ " ቢስሚላህ ተወከልቱ ዓለላሂ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢላህ " ብለው መውጣት ይኖርባቸዋል ። ለልጆቻቸው ይህን ዚክር ማስተማርና መንገድ ላይ የሚያገኙትን ነገር እንዳይረግጡ ፣ እንዳያነሱና እንዳይጫወቱበት መንገር ይኖርባቸዋል ። ይህን ዚክር አድርገው ሰበብ ካስገኙ በአላህ ይጠበቃሉ ። በእንቁጣጣሽ ጣጣ እንዳይገቡ ይረዳቸዋል ።     በመጨረሻም ይህን ኮተት ተሸክሞ የሚመጣውን ዘመን መለወጫ የሁሉም ነው ከማለት ተቆጥቦ ይዞት ከሚመጣው ጣጣና ኮተት በአላህ መጠበቅ ያስፈልጋል ። አላህ ሙስሊሞችን ከሸረኞች ተንኮል ይጠብቅልን ። https://t.me/bahruteka

👉 ነሲሓዎች ከኢኽዋን ጋር ተደምረው ወደ መጅሊስ በመምጣታቸው ሰለፍዮች ምን ተጠቀሙ ? አብዛኞች በየዋህነት ለእስልምናና ለሙስሊሞች ማሰብ በሚል መጅሊስ መግባት ግዴታ ነው የሚል እይታ አላቸው ። እነዚህ ወንድምና እህቶች በራሳቸው እይታ ጥሩ ነው የሚሉትን ነው የሚያንፀባርቁት ። ነገር ግን ለእስልምና ጥሩ ምን እንደሆነ ለሰዎች አስተሳሰብ አልተተወም ። ይልቁንም ንፁህ አእምሮዎች በቀላሉ የሚቀበሉት የሆነው መለኮታዊ መመሪያ ምንም ሳያስቀር አስቀምጦታል ። በመሆኑም ከሙስሊሞች የሚጠበቀው ሁለቱን ወሕዮች መከተል ነው ። አመለካከታችንና እይታችንን በሸሪዓ ሚዛን ላይ አድርገን ስሜታችንን በወሕይ ልጋም ለጉመን ነገሮችን ማየት የግድ ነው ። ሌላው መታየት ያለበት ብዙዎች የሱና ሰዎች የሚሏቸው ኢኽዋኖችና የእንጀራ ልጆቻቸው እንዲሁም እንባ ጠባቂዮቻቸው ወደ መጅሊስ በመምጣታቸው የሱና ዳዕዋ ምን አተረፈ የሚለውን ላፍታ ቆም ብለው ማየት ያለባቸው ይመስለኛል ። አሕባሽ ፣ ሱፍያ ፣ ኢኽዋንና የእንጀራ ልጆቻቸው ነሲሓዎች ተደምረው አንድ ነን በማለት ወደ መጅሊስ ከመጡ በኋላ የሰለፍያ ዳዕዋና የሰለፍይ መሻኢኽና ዱዓቶች ምን እንደደረሰባቸው በጥቂቱ እንመልከት : – በጥምሩ መጅሊስ አማካይነት በሰለፍዮች ላይ ከተፈፀሙ ግፎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል : – 1ኛ – በጉራጌ ዞን ጌቶ ወረዳ እስኩት ቀበሌ የሱና ኡስታዞች ከመስጂድ ተባረው ሌላ ቦታ ከወጡ በኋላ ቤት ተከራይተው ልጆች ሲያስቀሩ አከራዮች ላይ ከፍተኛ ማስፈራራትና ዛቻ ካደረሱ በኋላ ቤቱን በማሸግ ተማሪዮቹን በትነው ኡስታዞቹን አባረዋል ። 2ኛ – በዚሁ ዞን እዣ ወረዳ ሸህረሞ ቀበሌ የወሀንያ መንደር ላይ የሱና ዳዕዋ ሊደረግ ፕሮግራም ተይዞ ህዝብ ተሰብስቦ ፕሮግራሙ ከተጀመረ በኋላ በግብረሀይል እንዲበተን ተደርጓል ። 3 – በስልጤ ዞን በተለያዩ ቦታዎች የተዘጋጁ ፕሮግራሞች በግብረሀል የተበተኑ ሲሆን አልቾና ሌራ ላይ የነበሩት ፕሮግራሞች በወረዳ አስተዳደሮቻቸው ሀላፊነት አማካይነት ከመበተን ድነዋል ። የአልቾ ፕሮግራምን ለመበተን ትእዛዝ ተሰጥቷቸው ግብረሀይል ይዘው መጥተው የነበሩት የወረዳው ሴት አስተዳዳሪ ህዝቡን አይተው ሀላፊነቱን እወስዳለሁ አይበተንም ብለው የፕሮግራሙን ሰላም የሚያስጠብቅ የፀጥታ ሀይል መድበው ተመልሰዋል ። 4ኛ – በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ ከታማኝ ምንጭ እንደተገኘው በመጅሊሶች አማካሪነት ህዝብ አንድ እንዳይሆን የሚያደርገው የሰለፍዮች መሪ የሆነው ሸይኽ ሐሰን ገላው መታሰር አለበት በሚል እንዲታሰሩ ተደርጓል ። 5ኛ – በዚሁ ክልል በሀራ ከተማ ሶፋ መስጂድ በአሕባሽም ይሁን በሌላ ጊዜ ተደርጎ በማይታወቅ መልኩ በዚሁ ጥምር መጅሊስ አማካይነት ከ400 በላይ ተማሪዮች እየተገረፉ በጭነት መኪና ተጭነው ከሀራ እንዲወጡና የመስጂዱ ኢማምና ባልደረቦቻቸው እንዲታሰሩ በማድረግ መስጂዱ ለዳና ቀብር አምላኪዮች እንዲሰጥ አድርገው ድቤ መስጂድ ውስጥ አስደልቀዋል ። 6ኛ – በዚሁ ክልል ኮምቦልቻ ላይ የጥምሩ መጅሊስ እንምባ ጠባቂዮች ሰለፍዮች ከመስጂዳቸው እንዲባረሩ በማድረግ ሸይኽ ሙሐመድ ጀማልን በማባረር ደረሶችን በትነዋል ። 7ኛ – አ/አ ላይ ሰለፍዮች ሚሊኒየም አዳራሽ ላይ ፍቃድ በመውሰድ ሊያደርጉት ያዘጋጁትን ሀገር አቀፍ የተውሒድ ዳዕዋ እንዳይደረግ ለአዲስ አበባ ከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች በመደወል አሸባሪዮች ሊገቡ ይችላሉ በማለት የፀጥታ ስጋት የሚፈጠር እንዲመስላቸው በማድረግ በታሰበው ጊዜ እንዳይደረግ አድረገዋል ። እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ በጥምር መጅሊሱ አማካይነት በሱና ዳዕዋ ላይ የደረሰ በደል ነው ። ጥምሩ መጅሊስ ለሽርክና ቢዳዓ ምን አደረገ ? 1ኛ– መጅሊሱን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ የሽርክና ቢዳዓ መናኻሪያ የሆነውን መውሊድ ባጀት በመመደብ በከፍተኛ ድምቀት እንዲከበር ያደረገ መሆኑን መግለጫ በመስጠት አረጋግጧል ። 2ኛ– በቡታ ጀራ ላይ ለተደረገው አለም አቀፍ የቀብር አምላኪዮች ኮንፈረንስ የፋይናንስና የፀጥታ ድጋፍ በማድረግ ለፕሮግራሙ መሳካት ትልቅ አስተዋፆ አድርጓል ። 3ኛ– በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ከአላህ ውጪ ለሚመለኩ ቦታዎችን ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው እያደረጉ ይገኛሉ ። 4ኛ – በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ላሉ የባእድ አምልኮ ቦታዎች በአለም ቅርስነት በዩኒስኮ አንዲመዘገቡ አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ ። እነዚህ ከብዙ ተግባራቸው ውስጥ የተወሰኑት ናቸው ። ልብ ሊባል የሚገባው እያወራን ያለነው ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ስላለው የጥምር መጅሊስ ተግባር ነው ። እገሌ ለሰራው እኔ ምናገባኝ የሚል ማታለያ አይሰራም ። የዋህ ወንድምና እህቶች እነዚህን እውነታዎች ልብ በሉና የጥምር መጅሊሱን ምርጫ መቃወማችንን ከንደገና አጢኑት ። መከረኞቹ የነሲሓ ሙሪዶች ሆይ ሸይኻችሁ ኢልያስ አሕመድ በአ/አበባና በፌዴራል መጅሊስ የዑለማእ ም/ቤት አባል ሙሁራችሁ ኢልያስ አወል ደግሞ በአ/አ የኦዲት ኢኒስፔክሽን ሰብሳቢ ተደርገው የሚወሰነውንና የሚሰራውን ለማየት መመረጥ ምን የሚያመጣ ይመስላችኋል ? ወይስ አሁንም ለዳዕዋው መስላሓ ነው የተደመሩት ትላላችሁ ? በአባልነት የስልጣን ፍርፋሬ ምን ይፈይዱዋችኋል ? አለቆቻቸውን እየተማፀኑ ሰለፍዮችንና ማሳደድና የሰለፍያን ዳዕዋ ማሰናከል ካልሆነ በስተቀር ።!!! አሁንም አስረግጠን የምንነግራችሁ የሰለፍያ ዳዕዋ በአላህ ጥበቃ የበላይ እንደሚሆን ነው ። http://t.me/bahruteka