ጲንኤል
前往频道在 Telegram
ጲንኤል ...አንዳንድ ጦርነቶች በውስጣችን ይካሄዳሉ። ይህ ቻናል እነዚያ ጦርነቶች በቃላት የሚገለጹበት፣ ሰው ከራሱ ጋር የሚገናኝበት፣ ሀሳብ፣ ትዝታ እና ውስጣዊ ግጭቶች የሚጻፉበት ገጽ። ✍️ እስራኤል ሰይፉ
显示更多未指定国家未指定类别
194
订阅者
+124 小时
+17 天
-230 天
帖子存档
194
አሻጋሪዎቹ!
የጎጆ ቤት ጨዋታ።
እንዲህ ባለ የግንቦት ወር ነበር ያረፉት:- የቡታጅራ መንገድ: መንገድ መሆን እንደሚችል ሳይታሰብ ገና ድሮ እርሳቸው በባዶ እግር ሄደው: ለገዳሙ ቤተሰብ ቀለብ እህል፣ በርበሬ ጭነው በአህያ እየነዱ ይወስዳሉ።
ከአዲስ አበባ ሰባት ቤት ጉራጌ ምሁር ኢየሱስ ድረስ በእግር እየተጓዙ ጉዳይ ያስፈጽሙ ነበር:- አባ ፈቃደሥላሴ (አባ ፈቃደ፣ በሀገሬው አጠራር "አቦች") ዘምሁር ኢየሱስ ገዳም።
ይህንን በማደሪያቸው የሳር ጎጆ እሳት አቀጣጥለው ሻሂ እያፈሉ ያጫውታሉ።
በዚያ እርጅና በጎጆዋ ውስጥ ካለው ቆጥ የተፈለጠ እንጨት አውርደው፣ እሳት አቀጣጥለው የሀገሩን ቅዝቃዜ ሲረቱ ማየት ግር ሊል ይችላል። ለእርሳቸው ድንቅ አይደለም።
ያለፉትን ረዥም የምንኩስና፣ የአገልግሎት ሕይወት ሲነግሯችሁ ግን መደመማችሁን አታቆሙም።
አባ ሙሉ ለሙሉ አቅም አጥተው ቤት እስከሚውሉ ድረስ ከገዳሙ ወደ ሦስት ኪሎ ሜትር የሚርቀው የሃዋርያት ከተማ እየሄዱ የደብረ ታቦርን በዓል በሃዋርያት ቤተክርስቲያን ያከብሩ ነበር።
ከተማሪዎቹ እንጨት የሚፈልጥላቸው፣ የሚላካቸው እና ደግፎ ወደ ቤተመቅደሱ የሚወስዳቸው ተማሪ ይመደብላቸዋል።
አንድ ቀን ረዳታቸው ኃይለ ሚካኤል ሊያስመሰክር ከሄደበት ሀገር በአዲሳባ በኩል ወደ ገዳሙ ሲያልፍ አዲሳባ ላሉት የገዳሙ ቤተሰቦች በጨዋታ መሃል እንዲህ አላቸው:-
"ስለ አባቴ በስልክም አልጠይቅም፤ ለኢየሱስ ስዕለት ተስያለሁ፤ በሕይወት እንዳገኛቸው። እንደገና እግራቸውን እንዳጥብ፣ እንደገና እንጨት እንድፈልጥላቸው... እንዲባርኩኝ። አባቴ አሁንስ እየደከሙብኝ ነው"
አብ ይባርክ ኃይለሚካኤል ሊያስመሰክር ሲሄድ ተተካ። አንድ ሰው እጅጉን ውኃ ተጠምቶ ሲጠጣ እንደሚያረካው ያለ ነው የአባት እና የልጅ ፍቅራቸው!
እድሜአቸው ከ100 ዓመት ያልፋል። በእርጅና ድምጻቸው "አዪዪ ዛሬስ ቤተክርስቲያን አልሄድም። ልጄ ደክሞኛል ሰዓታት መቆም አልችልም" ይሉታል።
"እሺ አባ" ብሎ ቡራኬውን ተቀብሎ ይወጣል። አባም መደባቸው ላይ እግራቸውን ወደውጭ አድርገው ጋደም ይላሉ።
ትንሽ እንዳሸለቡ ይነቃሉ። "ዛሬ መነኮሳቱ ምን ሆነዋል! አይደውሉም እንዴ?! ሰዓታት ሳይቆም ሊነጋ እኮ ነው!" ይላሉ።
አለቃ* ይመልስላቸዋል። (*አለቃ የያኔው ሲራክ የአሁኑ የገዳሙ አበምኔት አባ ዘኢየሱስ።)
"ሰዓት ገና ነው አባ ፈቃደ ትንሽ አረፍ በሉ"
ሦስት አራቴ ለምን አይደወልም እያሉ ለመተኛት ሳይሆን ዓይናቸውን ትንሽ ለመጨፈን ብቻ መደባቸው ላይ ጋደም ብለው፣ እግራቸውን ከመደቡ ውጪ አድርገው ተዘጋጅተው ይጠብቃሉ።
ኃይለሚካኤልም ይሁን አብ ይባርክ ጸባያቸውን ስለሚያውቁ ሰዓታቸውን ጠብቀው ይመጣሉ።
አባም አልሄድም ማለታቸውን አያስታውሱም። "ጎሽ ልጄ መጣህ ቤተመቅደሱ ናፍቆኝ ነበር" ይላሉ። የሰርክ ጸሎት ሲያልቅ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ወደ ጎጆአቸው የመጡ አይመስሉም ሌሊት አምስት ወይም ስድስት ሰዓት ላይ "ናፈቀኝ" ሲሉ።
መቋሚያቸውን ተደግፈው እያንዳንዱን ንባብ ያደምጣሉ። ካልተሰማቸው "ጮክ ብለህ አንብብ!" ይላሉ። ማረፍ ሲፈልጉ "መነኮሳት: ትፈቅዱልኛላችሁ? ትንሽ ልቀመጥ?" ይላሉ በሚጣፍጥ የጉራጊኛ ቅላጼ።
ሲመለሱ በጎጆዋ ባለችው ክብ፣ በእበት የተለቀለቀች ባለ ሦስት ጉልቻ የእሳት ማንደጃ አጠገብ ይቀመጣሉ።
እማሆይ ወለተማርያም (የአሁኗ እማሆይ ማርያ) እራት ያቀርባሉ።
እርሳቸው ቆመው ይባርካሉ፤
በመዓድ መሀል ረስተው የቃል ጸሎታቸውን ሲቀጽሉ አለቃ "አባ ይብሉ እንጂ" ይላቸዋል፣ "የጨረስን መስሎኝ" ይሉና ደስ የምትል ሳቃቸውን ለአፍታ ብልጭ ያደርጋሉ፣ ምንም ደቂቃ ያለጸሎት መቀመጥ አይችሉም፣ መቁጠሪያቸውን መቼም አይለዩአትም 'ነፍሴ ናት' ይላሉ።
ጭስ ባወረዛት ጥንታዊት የሳር ጎጆ ውስጥ ጭስ በጠገበች የጥንት ማንቆርቆሪያ ሻሂ ይጣዳል። ምን ላምጣልዎት ለሚላቸው ሁሉ መልሳቸው አንድ ነው:- ስኳር። ሳጥናቸው ውስጥ ይቆለፋል :-) ለእንግዳ ሁሉ ይጋብዛሉ፤ ሰው ያመጣላቸውን መልሰው ያቀርባሉ።
ወፍራም ሻሂ በራሳቸው ኩባያ ይጠጣሉ።
ከስብሐት በኋላ ሊያሳርጉ ይቆማሉ። ሲነሱ እድሜ ያጎበጠውን ሰውነታቸውን ታግለው ያንሰራሩታል።
በመወዘቻው በሞቀ ውኃ ረዳቸው እግራቸውን ያጥባል።
ምርቃት ያወርዱለታል። ጉልበት ስሞ ወደ ማደሪያው ይሄዳል።.... እንደዛ እንደዛ.... ሁልጊዜ እንደዛ.....
ያን የዕርገት በዓል ምሽት ግን አብ ይባርክ ለመጀመሪያ እና ለመጨረሻ ጊዜ አረፈደ።
መነኮሳቱ ማኅሌት ቆመዋል። ደማቅ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል!
አባ ዓይናቸው በደንብ አያይም፤ ጉብጠታቸው ጭንቅላታቸው ከጉልበታቸው ሊደርስ ትንሽ ቀርቶታል፣ ምርኩዛቸውን የቱንም ያህል ቢያጠብቁት ሊደግፋቸው አይችልም ። ከማደሪያ ጎጆአቸው ቤተመቅደሱ ቅርብ ቢሆንም አድራሽ ያስፈልጋቸው ነበር።
የበዓል ልብስ የሚያለብሳቸው፣ እጃቸውን ያዝ፣ ጎናቸውን ደገፍ አድርጎ የሚያስገባቸው የሚመልሳቸው ሰው ያስፈልግ ነበር።
ጠበቁት፣ ጮክ ብለው ጠሩት፣ እርሱ መኖሪያው እዚያ የተማሪዎች ጊቢ።
"ልጄን ምን ነካብኝ?" አሉ ለብቻቸው "ይህን ቀን ናፍቄ ነበረ! ናፍቄ ነበረ! "
ወረቡን እየሰሙ፣ መሄድ እየፈለጉ፣
እያሉበት
እየኖሩበት የሚናፍቃቸውን ቤተመቅደስ ብድግ ብለው መሄድ እና መግባት ስላቃታቸው ሳግ እየተናነቃቸው።
"አባ እኔ ነጭ ልብስዎት የት እንዳለ አውቃለሁ። አልብሼ ልውሰድዎት ?" አለቻቸው እንግዳዋ። እንደሕጻን ልጅ ተፍለቀለቁ። እጃቸውን ይዛ ደረጃው ጋር አደረሰቻቸው እና ለአንዱ ተማሪ አቀበለቻቸው። የማያልቅ ምርቃት መረቋት። እናም "ልጄ አሞት እንዳይሆን እዩት" ብለዋት ገቡ።
አብ ይባርክ በዚያ መብራት በሌለው ድቅድቅ ጨለማ ጧፉን እያበራ ሲሮጥ መጣ። እርሱም እንዴት ሰዓት እንዳለፈበት አያውቅም።
አባ ፈቃደ ሥላሴ(አባ ፈቃደ) (አቦች) ኑሮአቸው እንደዚህ ነበር። የቤተክርስቲያናችን አባቶች ሁሉ እንጂ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኮሳት
ለማኅበረ መነኮሳቱ የሚያስፈልገውን ከሩቅ ቦታ ድረስ የቀናት፣ የሳምንታት፣ የወራት ጉዞ በእግር እየተጓዙ እየገዙ፣ በማኅበር እየሠሩ፣ በማኅበር እየጸለዩ፣
የቤተ መቅደስ አገልግሎት ሳያቋርጡ፣ ስብሐተ እግዚአብሔር ሳያቋርጡ፣ እየኖሩበትም እየናፈቃቸውም በቤተመቅደሱ ጸንተው አምላካቸው እግዚአብሔርን በገዳማት እስከሞት ታምነው አገለገሉት።
ለመንፈስ ልጆቻቸው ሃይማኖት ከምግባር፣ ሥራን ፣ ፍቅርን መከባበርን.... አስተምረው ኖረውት አወረሱ.. . ዘመንን አሻገሩ:- አሻጋሪዎቹ አባቶቻችን!
እንጨት ፈልጠው እሳት አቀጣጥለው ቀዝቃዛውን አየር እንዳሞቁት ፣ በወንጌል ብርሃን፣ በወንጌል ትምህርት ምድሪቷን አበሯት፣ አሞቋት! አሻጋሪዎቹ!
///***///
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ/ም
194
✍️ ቅማል በአስር ሺህ ብር!
"ቅማል በአስር ሺህ ብር እገዛለሁ" የሚል ጽሑፍ ከሩቅ አይቼ እየሮጥኩ መንገዱን ተሻገርኩ። አንድ ሽማግሌ በወረቀት ላይ የተጻፈውን መልዕክታቸውን ከፍ አድርገው ይዘው በሰዎች ተከበው ቆመዋል። አንዳንዱ "እብድ ናቸው" እያለ ሲሳለቅባቸው፣ ሌላው ደግሞ የልብሱን ኮሌታ እያገላበጠ ቅማል ይፈልጋል። እኔም ገና መጀመሪያ ሳያቸው እየቀለዱ መስሎኝ ነበር፤ በኋላ ግን እግራቸው ስር የተቀመጠውን በገንዘብ የተሞላ ሻንጣ ስመለከት፣ የችግር ቀኖቼን እያሰብኩ የሱሪዬን ወገብ ዳር ዳር መፈተሽ ጀመርኩ።
በሕይወቴ... አንዴ ወገቤን፣ አንዴ ብብቴን፣ አንዴ ደግሞ ዋና ቦታዬን እየተሯሯጠች ያሰቃየችኝ ቅማል ዛሬ ደብዛዋ ጠፋ! አጠገቤ ያለ ሰው ሁሉ ቅማል ብርቅ ሆኖበት ምኑንም ምኑንም ይጎረጉራል። "አንድ ቅማል አሥር ሺህ ብር ከተሸጠ፣ ዘጠኝ ቅማል ቢገኝ..." እያልኩ በሐሳብ ስሰላስል፣ ሽማግሌው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፦
"አቁሙ! እናንተ ተላሎች! ይህንን ገንዘብ ለማግኘት ከቅድም ጀምሮ ከልብሳችሁ ጋር ስትታገሉ ነበር፤ ግን ማናችሁም አላገኛችሁም። ንጹሕ መሆናችሁ መልካም ነው... እኔ ግን የጠየቅኳችሁ ነፍሳችሁን የተጣባውን፣ ጽድቃችሁን መጦ በበደል የሚያሳክካችሁን የከረመ ኃጢአታችሁን ነው!"
አስተውሉ! ቅማል ሁልጊዜም ንጹሕ ሰው ላይ አትገኝም፤ መገኛዋ ቆሻሻ ስፍራ ነው። እኛ ደግሞ የልባችንን ግዛት ከፈጣሪ ነጥቀን ለሰይጣን ካስገበርነው ቆየን። ሰይጣን ባለበት ደግሞ ቆሻሻ አለ። ቅማላችሁን ከብብታችሁ ስርና ከጀርባችሁ ኋላ ከደበቃችሁበት አውጡና ጣሉት! ቅማል በሰው ደም ነፍሷን እንደምታስቀጥል፣ ሰይጣንም በበደላችሁ ቁጥር ዕድሜውን እንዳያራዝምባችሁ ተጠበቁ።
"ይህ የምታዩት ገንዘብ አላቂ ነው። ቅማሉን ላጋለጠና ንስሐ ለገባ ግን ዋጋው ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው... ቅማላችሁን ግደሉ! ራሳችሁን በንስሐ አንጹ! እኔ ቅማል አልገዛም፤ እናንተ ግን ቅማላችሁን ጥላችሁ ለአምላካችሁ ተገዙ። በሉ ሰላም ግቡ!" ብለው ከሕዝቡ መሃል ወጥተው ጥለውን ሄዱ።
ሰውየው ሲሄዱ ከካሚሴ ስር ተደብቃ የቆየችው ቅማል ስትርመሰመስ ተሰማኝ። እጄን ሰድጄ ያዝኳት። አባባ እንዳሉት በደሌን እያሰብኩ ያቺን ቅማል በጥፍሬ መሃል ገድዬ ጣልኳት።
እንደ ቅማል የተጣባንን ኃጢአት በምሕረቱ ይጠብልን፤ ያንፃን። አሜን!
........................…................
194
"ድመቷን ወደ ሕይወትህ አታስገባ"
አንድ ታላቅ መነኩሴ ሊሞቱ ሲሉ ለተተኪያቸው ያስተላለፉት የመጨረሻ ቃል "በሕይወትህ ድመትን በጭራሽ እንዳታስገባ" የሚል ነበር። ወጣቱ መነኩሴ ምስጢሩ ባልገባው ጊዜ አንድ አረጋዊ መነኩሴ ታሪኩን እንዲህ አጫወቱት፦
መምህራቸው ዓለምን ትተው በጫካ ሲኖሩ፣ አይጦች ልብሳቸውን ስለበሉባቸው የመንደሩ ሰዎች ድመት እንዲያሳድጉ መከሯቸው። ድመቷን ለመመገብ ወተት ስለሚያስፈልግ ላም መጣች። ላሟን የሚንከባከብና ሳር የሚያጭድ ሰው ስለፈለጉ አንዲት ሴት መጣች። መነኩሴውና ሴቲቱ አብረው መስራት ሲጀምሩ ፍቅር ያዛቸው፣ ተጋቡና ልጅ ወለዱ።
መነኩሴው በመጨረሻ የነቃው የራሱን ቤተሰብ ጥሎ መጥቶ ድጋሚ በሌላ ቤተሰብ ውስጥ መገኘቱን ሲረዳ ነው። ይህ ሁሉ የሆነው ግን መጀመሪያ ካስገባት አንዲት "ድመት" ተነስቶ ነው።
👉"ድመቷን አታስገባ" ማለት ለአእምሮህ መጥፎ ፍላጎቶች ትንሽም ቢሆን በር አትክፈት ማለት ነው።
👉መጥፎ ልማዶች (እንደ ሱሰኝነት ወይም ስንፍና) የሚጀምሩት "ለአንድ ጊዜ ብቻ" በሚል ትንሽ ምክንያት ነው።
👉አንዴ ለአእምሮህ ቦታ ከሰጠኸው፣ ሳታውቀው አንዱን ምክንያት በሌላ እያገናኘ ሙሉ ሕይወትህን ወደማትፈልገው አቅጣጫ ይወስደዋል።
ትናንሽ የሚመስሉ መጥፎ ውሳኔዎች ትልቅ ጥፋት ያመጣሉ፤ ስለዚህ ገና ከመጀመሪያው "ድመቷን" (መጥፎውን ሃሳብ) ወደ ሕይወትህ አለማስገባት ብልህነት ነው።
አእምሮህ እንዲመራህ አትፍቀድለት፣ አንተ ምራው።
አቡን ሺኖዳ እንዲህ ይላሉ
እውነተኛ ክርስቲያን ስሜቱን የሚመራ እንጂ ስሜቱ የሚመራው አይደለም።
194
ጋዳፊን ለግድያ የዳረጉ 10 ነጥቦች #አንብቡት
-------------------
1⚜️ በሊብያ መጠለያ ማግኘት እንደ ሰብአዊ መብት ይቆጠራል። ጋዳፊ የሊቢያ ዜጎች በሙሉ ቤት ካላገኙ ቤተሰቦቹም እንደማያገኙ ቃል የገባ ሲሆን ፣ የጋዳፊ አባት የሞቱት እርሱ ራሱ ሚስቱና እናቱ በድንኳን እንደነበሩ ነው።
2⚜️ በሊብያ ኤሌክትሪክ ለሁሉም ነዋሪዎች በነፃ ነው ሰልፍ ጠብቀህ ክፈል ብሎ ተረት የለም።
3⚜️ በሊብያ ለአዲስ ተጋቢዎች ለመኖሪያ ቤት መግዟ እና ለጎጆ መውጫ ይረዳቸው ዘንድ ከመንግስት 60,000 ዲናር (5000 ዶላር) ይሰጣቸዋል ።
4⚜️ በሊብያ ት/ት እና ህክምና በነፃ ነው ።
5⚜️ ሊብያውያን በግብርና መተዳደር ሲፈልጉ ፣ የእርሻ ፣ መሬት የእርሻ መሳሪያ ፣ ዘሮች እና ከብቶች በነፃ ከመንግስት በአንድ ቀን ያገኛሉ።
6⚜️ ሊብያውያን በሊብያ የሚፈልጉትን ት/ት ሆነ የህክምና
አገልግሎት ማግኘት ካልቻሉ በመንግስት በኩል ወጪያቸው ተችሎ ወደ ዉጪ ሀገር ሄደው እንዲጠቀሙ ከመደረጉም በተጨማሪ ለመኖሪያ እና የትራንስፓርት አበል የሚሆን በየወሩ 2,300 ዶላር ይሰጣቸዋል።
7⚜️ ሊብያውያን መኪና መግዛት ሲፈልጉ መንግስት 50%
የሚሆነውን ዋጋ ይሸፍናል ።
8 ⚜️ሊብያ የሮችስቻይልድ ባንክ እና የውጭ (የአለም ባንክ) ብድር ያልነበራት ሲሆን መጠባበቂያ $150 ቢሊዮን ነበራት።
9 ⚜️አንድ የሊብያ ዜጋ ከዪኒቨርሲቲ ተመርቆ ለጊዜው ስራ ያጣ ከሆነ መንግስት እስኪቀጥረው ድረስ በሙያው ማግኘት ያለበትን ደሞዝ ይከፈለዋል ።
10 ⚜️ሊብያዊት እናት ልጅ ስትወልድ ከመንግስት 5,000 ዶላር ትሸለማለች።
ለዚህ ነው "ምን አጠፋው እያለ" በገዛ ዜጎቹ የተገደለው ።
ዛሬ ያን የመሰለ መሪያቸውን በምእራባዊያን ፕሮፖጋንዳ ተነሳስተው በእጃቸው ገድለው ሃገሪቷ እና ዜጎች በአስከፊ ኑሮ ውስጥ ይገኛሉ።
ነቢል እንድሪስ እንዳሰናዳው
ከመፅሐፍት አለም
https://t.me/Oct13wed
194
አንችም በሐይማኖትሽ....
አንችም በሐይማኖትሽ እኔም በሐይማኖቴ....
የሚለው ግጥም ግን በእውነተኛው አለም ከቶ አይሰራም እቴ
እኔም ካንቺ ፍቅር አንቺም ከኔ መውደድ እየተላመድን
አንቺ ሌላ አምላክ እኔም ሌላ ጌታ ደግሞ ከወደድን...
እዚህጋር ተሸዋወድን...
እሺ ከዚያስ... ምን ሊሆን ፍጻሜው?
የትስ ቦታ ሊሆን ፍቅራችን መድረሻው?
ካልወሰድሽኝ በኒቃ ካላገባሁሽ በተክሊል
ለቅዳሴ አብረን ካልነቃን ሶላት ካልወጣን አዛን ሲል
ልጆችሽ ቁርአን ካልቀሩ ልጆቼ ካልሄዱ አብነት
የሼሁም የቄሱም ትምህርት አይሄድም መቼም በአንድነት።
ሰደቃ ካልሰራሽ፣ አስራቴ ካላጸደቀሽ የኔ
ለልጄ ክርስትና ቀን ከሌለሽ ከጎኔ...
በአንድ ጣራ እየኖርን ሁለት ጌታ ስናመሰግን
ፍቅራችን ብቻውን ሆኖ ጽኑ ቤት ይሰራ ይሆን ግን?...
አንሞኝ ግድ የለም እቴ....
አውቃለሁ እንደምወድሽ ያንቺም ፍቅር ሀያል ነው በጣም
ፍቅረኛ የሆነ ሁሉ ግን አብሮ ጎጆ አይወጣም።
ፍቅር ከምንዘራ...
መውደድ ከምንዘራ የሚፈርስ ጎጆ ላይ
እየተዋደድን...
እየተፋቀርን እጣችን ነው ብለን እዚጋ እንለያይ።
✍️ሮቤል
https://t.me/Oct13wed
194
ሞት ሆይ ምነው ዝም አልክ?
ከለታት ባንዱ ቀን ሰዉ እንደወትሮው በሩጫ ላይ ሳለ
የዓለም ብርሃን ጠፋ ያውም በቀትሩ መሃል ስራ እንዳለ።
አሁን ምን ይባላል ድንገት ሲመሽ ቀኑ?
ግርዶሽም ያይደለ ያልሆነ ቀመሩ
አልመጣም ሰይጣንም ዘዕኩይ ምግባሩ
ግና በመካከል እንዲህ ሆኖ ነበር....
የዓለማቱ ጌታ የፍጥረታቱ አባት
አርብ በፈጠረው አርብ ለፈጠረው፣ አርብለት ሞቶለት።
ነቢዩ ኢሳይያስ እንደተነበየው ስለ እኛ ቆሰለ
በሆዳችን ሰበብ ህይወቱን ከፈለ።
በጥፊ ሲመቱት መላእክቱ አይተው ለሰዉ አፈሩ
እንዴት ቻለው አሉ ምን ቢሆን ነው ፍቅሩ
ያለ በደል ፈርደውበት እውነተኛው ዳኛ
በመስቀል እንዲውል እንደ ወንጀለኛ
አንዳችም አላለ ከመ ጥፋተኛ።
ፍጡር ፈጣሪው ላይ እጁን እንዲያነሳ እንትፍ እንዲልበት
ለማን ተናግሮ ነው ስልጣን የተሰጠው ማንስ ፈቀደለት?
እርሱው ፈቃጅ እርሱው ተማች ዓለማትን ሁሉ በፈጠረው ጌታ
መስቀል ላይ አውሎ እብኖዲን ሚመታ።
ኧረ እንዴት ይቻል? እንዴትስ ይዘርዘር?
የአምላክ መከራ ሞት አለው ጥልቅ ነገር
የምስጢርን ትርጉም ቅዱሱ ሲናገር
የምናየውና የምናምነው ሁሉ አንድ ሳይሆን ሲቀር።
አምላከ አማልክት በሞት ሲያልፍ አየነው
በሰልስት ተነስቶ የጠላትን ሥልጣን ቤቱ ሄዶ ሰዋው።
ታዖስ መቃብር ሲያርፍ ዓለም ተደነቀ
ሞትም ረታሁ ብሎ በድል ፈነደቀ።
ግንስ ያ መቃብር...
ግንስ ያ መቃብር ሕይወትን ያልቻለው
የመለኮት ሀይል ውስጡን በጠበጠው
እንደ ዮናስ አሳ ትፋ ትፋ አለው
ለሞቱትም ነፍሳት ምስራች መሆኑ መርዶ መስሎ ታየው።
አይቀር መቼስ...
አይቀርም መትፋትህ አትሆንም መፍቀሬ
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል? ጠፋ ያንተ ፍሬ
አቅምህ እስቲ ይታይ ጠንከር በል ዛሬ።
አትችልማ..
እነሆ መጣልህ የይሁዳ አንበሳ
ድል እማትነሳው ሁሉንም እሚያነሳ
ለእኛም አታስፈራን አንቆይም መቃብር
አሁን ምን ታመጣ የክርስቶስ ሆንን በዘላለሙ ክብር።
እሰየው ተሸነፍክ...
እሰየው ተሸነፍክ ጥላህን ግፈፈው መሰልጠኑ ይብቃህ
ከእንግዲህ አንርድም አንተም ላንተ ፍራ እዛው ተሸማቀቅ
ለዘላለም ሕይወት መሄጃ መሰላል መሆንህን እወቅ።
ትንሳኤ ማለት ለእኛ አዲስ ሕይወት ምዕራፍ
ጨለማውን ቋጭቶ በምህረት ላይ ማረፍ።
በዚህ ታላቅ በዓል በደስታ በሐሴት፥
እናመስግን ጌታን ለትንሳኤው ህይወት።
አዳም ነፃ ወጣ ሔዋን ተደሰተች
ቤተክርስቲያን ዛሬ በልጇ ተጌጠች።
ክርስቶስ ተነሳ
እንኳን አደረሳችሁ!
እስራኤል ሰይፉ
ሚያዝያ ፬ ፳፻፲፰ ዓ.ም.
https://t.me/Oct13wed
194
ቤተ ክርስቲያናችን ዕለተ ጥያቄ ብላ በምትጠራው በዚህ በሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ ስለ አሥሩ ቆነጃጅትና ሙሽራውን ስለመጠበቅ በምናስብበት ዕለት የሆነ ሰው የልደት ቀን ዋለ።
መብራት መያዝ መብራቱን የሚያበራ ዘይት እስካልያዙ ድረስ ከንቱ መሆኑን የአስሩ ቆነጃጅት ታሪክ ያሳየናል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም "
ዘይት የተባለው ምግባር ርኅራኄና ምጽዋት ነው ብሎ ተርጉሞታል።
ባለ ልደቱን ስመለከት ታድያ ይህንን የቆነጃጅቱን ዘይት በሕይወቱ በተግባር የሚያሳየን ሰው እንደሆነ ይሰማኛል።
እርሱ እንደ ሳይኮሎጂ ተማሪነት የሰውን ልብ በመረዳት እንደ ወንጌል አገልጋይነት ደግሞ የሰውን ነፍስ ለመፈወስ ሲሯሯጥ ችኩልነቱ አይታየውም። (ግርም የሚለኝ ደግሞ አትቸኩል ስለው እሺ የሚላት ነገር.. መልሶ እኮ እዛው ነው..ታጥቦ ጭቃ😂😂)
የሚሮጠው ይህ ስሜት ውስጡ እየተቃጠለ አላስቀምጥ ቢለውና ቢያንስ እንኳ የቻልኩበት ሁሉ ተገኝቼ ኢምንት ቃጠሎ ብቀንስ በሚል ስሜት እንደሆነ የገባኝ የአስሩ ቆነጃጅትን ታሪክ ባየሁ ጊዜ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከምጽዋት ሁሉ የሚበልጠው የተጨነቀች ነፍስን ማረጋጋትና ማዳመጥ ነው ማለቱን የሰማው ጮሌ..መፍትሔ ባያመጣ እንኳ ሁነኛ አድማጭ ሆኖ ለደከሙት ጆሮውን ለተጠሙት ፍቅሩን የሚሰጥ ዘይት እንዳልተለየው መብራት ብልህ ሰው ሆኖ አየሁ።
አሥሩ ቆነጃጅት ሙሽራውን ሊቀበሉ ወጡ። ጮሌው አንዱአለምም በመንገዱ ሁሉ ሰውን ሰላም እያለ ፍቅርንና ፈገግታን እየዘራ የሚጓዝ የመንገድ ላይ ወንጌላዊ ሆነ።
ሰዎች ምሥጢራቸውን ሁሉ የሚያካፍሉት በእርሱ ዘንድ የሚገኘው የመደመጥና የመረዳት ሰላም የክርስቶስን ፍቅር ስለሚያንጸባርቅ ነው። ጌታችን በወንጌል እሺ የሚሉትንና ትእዛዙን የሚፈጽሙትን እንደሚወድ ሁሉ ወጣቱም ለማንኛውም ሰው ጥሪ እምቢ የማይልና ራሱን ለሌሎች አሳልፎ የሚሰጥ ፍጹም የፍቅር ሰው ነው።
ግርም የሚለኝ ደግሞ የድሮ ሰዎች ይኖሩ የነበረውን 800 እና 900 አመት አሁን ላይ 80 እና 90 መሆኑን አስተውሎ ''ይችን 80 እና 90 አመት እንዴት 800 እና 900 ላድርጋት?'' በማለት ሲጨነቅ የመጣለት መፍትሔ።
መፍትሄው ምንድነው?... በ80 እና በ90 አመት የ 800 እና የ900 አመት ታሪክ መስራት።
( ለዛ እንደምትቸኩል ደግሞ ነቅቼበታለሁ😂)
የዛሬ ልደቱ ለቀጣይ እድሜው፣ የያዘው የመንፈሳዊ አገልግሎትና የዕውቀት መብራት ሁልጊዜም በምግባር ዘይት እንዲበራ እንመኛለሁ። እንደ ብልሆቹ ቆነጃጅት ፈገግታው መብራቱን ፍቅሩና ርኅራኄው ደግሞ ዘይቱ ሆነውለት ለታላቁ የትንሣኤ ብርሃንና ለሰማያዊው ሰርግ እንዲያበቃው የቅዱሳን አምላክ ፈቃዱ ይሁን።
ሕይወቱ እንደ መብራቱ የበራ እንደ ዘይቱ የበዛ ይሁን።
መልካም ልደት ለውዱ ወንድሜ ለዲያቆን አንዱአለም!
ምን ውጪ ባልጋብዝህም አስቱን ሳታይ እንደዋልክ እንዳትረሳ!
የስም ትርጓሜ👇👇👇
አ= አንድ ብትሆንም
ን= ንቁ በመሆንህ
ዱ= ዱር ጫካ ሳትል
አ= አንተን ስንሻ
ለ= ለኛ ፍላጎት
ም= ምቹ ሆንክልን።
https://t.me/Oct13wed
194
ጥበብን ማለዳትእንደ ልቡ ምኞት ፦ መሻቱን ሊሰጠው ምን ትሻለህ ብሎ ፦ እግዜር ሲጠይቀው ፨፨፨፨ ቀድምም የተሾመ ፦ ንጉስ ነበረና የዕድሜ ልክ ሀሊዎ ፦ ምድራዊ ክብር ዝና ለሺህ እልፍ ዘመን ፦ ማይሻር ንግስና ዓለማዊ ሞገስ ፦ ንዑደት ልዕልና መች ነበር ፀሎቱ ፦ በእውነት ለመዳኘት ስጠኝ አለ እንጂ ፦ አስተዋይ ልቦና ፨፨፨፨ ንጉስ ሳለ ገዢ ፦ ነብሱን የጨነቃት ዓለምን ጠቅልሎ ፦ የሚገዛው ግዛት እስመ አልቦ ግዜ ፦ የዙፋኑን ፅናት ባርያ ገባር ሎሌ ፦ ወርቅ ዕንቁ ብዙ ሀብት ይህ ሁሉ መች ነበር ፦ የጠቢቡ መሻት ፨፨፨፨ ገንዘብ እና ስልጣን ፦ ግዚያዊ አምሀ ስጠኝ ብሎ አላለም ፦ ተድላ ወፍሰሀ ፨፨፨፧፨ ከሀላፊ ጠፊው ፦ ከምድር ብርቅርቅ አስቦ አቅዶ ፦ ከዚህ ሁሉ ይልቅ አውጥቶ አውርዶ ፦ ማለፍያውን ለፅድቅ ሚበቃውን ያክል ፦ አምላኩን ሲጠይቅ ንጉስ ሆኖ ሳለ ፦ ጥንቱን የተቀባ ሁለት ሶስት አላለም ፦ አስር ሀያ አልጓጓ አርባ አምሳ ስልሳ ፦ አልወደደም ሰባ ሊፈርድ ባለ ግዜ ፦ ፍትህ እንዳያዛባ ሚዛኑን አጋድሎ ፦ ደሀ እንዳስያነባ ምታስፈልገውን ፦ ምትበቃውን ብቻ አንዲት ዘለላዋን ፦ አንዲት ነገር ሀባ ለነብሱ ለስጋው ፦ ሲያውቅ እንደ ሚገባ ፨፨፨፨ ጠቢቡ ሰሎሞን ፦ ከእግዜሩ ሲዋዋል ከምንም አብልጦ ፦ ለህይወቱ ሲሳል "ጥበብ" ስጠኝ ብሎ ፦ ማለለ ቃል በቃል ፨፨፨፨ ታድያ ከጠየቀው ፦ የበለጠው በዕድል ለንጉስ "ሰሎሞን"ኃይሉ ጥበቡም አይደል ? ፨፨፨፨ አንድ የገባኝ እውነት ፦ ሰው ከእግዜር ሲጠይቅ በጎ እና መልካሙን ፦ አንድ ምርጫውን ቢያውቅ ከምንም የበዛ ፦ ከሁሉ የሚበልጥ ከላቀ የሚልቅ ፨፨፨፨ በሁሉ እንዲሞላ ፦ ምኞቱ እንዲሰምር መሻቱ እንዲሳካ መጥኖ መዝኖ ፦ ሚጠቅመውን ብቻ ውጥኑን ቢለካ ቢሰጥ ማያልቅበት ፦ ሰፍሮ ማይጎድልበት ለስጋም ለነብሱም ፦ ካለለት ካደለው ደርሶ ለበረካ አንዱን የሰጠው ለት ፦ ዕልፍ ይሆናል ለካ ✍ሶላ ሀላባው
194
ድንገት በቀኔ ላይ...
✍️እስራኤል ሰይፉ
https://t.me/Oct13wed
''ተደብቀሽ ያለቀስሽው ምን ሆነሽ ነው?' አለኝ እንደ ቀልድ።
ውስጤ እንደ ደራሽ ውሀ በድንገት ሲያጓራ ይሰማኛል።
...አንዳንዴ የምናነሳቸውን ጥያቄዎች ምን ሊያስከትሉ መገመት እንዴት ይከብደናል? ያውም ገና የመጀመርያ ቀን ላገኘነው ሰው?...
...ድንገት ነው የተገናኘነው። ያውም መልዕክት አድርሺለት ተብዬ መልእክቱን ልሰጠው።
ወንድነቱ መልዕክቱን ብቻ ተቀብሎ እንዲሄድ አልፈቀደለትም መሰል ለታማኝነትሽ በሚል ሰበብ ማኪያቶ አዘዘ... ስላልቸኮልኩ አልተቃወምኩትም።
''እስራን የት ነው ምታውቂው?'' አለኝ አስተናጋጇ ዘወር ስትል ዝምታውን ለመስበር በሚመስል መልኩ...
ምን ልበለው? ምኔስ ነው ልበለው?
እስራ ማለት ወንድሜ ነው። መልዕክቱን የላከኝ። ወንድሜ ብቻ ግን አይደለም።
ሁሉን ነገሬን የሚያውቀው ብቸኛው ሰው እሱ ነው። የኔ ሞኖፖስት።
ሞኒ ነው የሚለኝ። ሞኖፖስቲና ስለሚረዝም...
...ብቸኛ እህቱ ነኝ። ምን አልባት ለሱ ያለኝ ፍቅርም ይሆናል ብቸኛ ያደረገው። ''ፍቅር ማለት ታሪክ ነው'' ያለው ማን ነበር? በትዝታ መኖር...
የኋላ ታሪካችን ላይ የሌሉ ሰዎች ለወደፊት ካልገቡ በስተቀር እንደሌሉ ይቀራሉ።
ወንድምነትንም ሆነ እህትነትን ከዝምድና ባሻገር የሚያጠናክራቸው ትልቁ ገመድ ታሪክ ይመስለኛል። ታሪክ የሌለው ቁጥር ነው... ቁጥር በራሱ ከማሟያነት ውጪ ፋይዳ እንደሌለው ሁሉ ታሪክ የሌለው ሰውም እንዲሁ ቁጥር ነው... የሰው ማሟያ።
ወንድሜ ማለት ለኔ እንዲህ ነው ብዬ ከምል እንዲህ አይደለም ብል የተሻለ እገልጸዋለሁ። ወንድም የሚለው ቃል ለወንድሜ አይገልጸውም። ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ ሰው አለ ወይ ብባል ለኔ እሱ ነው።
አንዳንዴ አቻ ለሌላቸው ቃላት ትርጉም ስንሻ ከመዋል እንዲህ አይደለም ብንል የተሻለ እንገልጻቸዋለን። ለዚያም ይመስለኛል ሁለታችንም ሞኖፖስቲና የምንባባለው።
እና ወንድሜ ለኔ ቁጥር አይደለም።
...እንዲህ የምለው ወንድሜን ነው ታድያ ''እስራን የት ነው ምታውቂው?'' ብሎ የጠየቀኝ።
ባያውቅ ነው መቼስ ብዬ
''ወንድሜ ነው..'' አልኩት ቀለል አድርጌ ለማለፍ።
እንዲሁ አንዳንድ ወሬዎችን ስናወራ ቆይተን በመሃል ያዘዝነው ማኪያቶ መጣ...
አስተናጋጁ እስኪሄድ ከአፍታ ዝምታ በኋላ ነበር ልክ... የጋለ ብረት ላይ ውሃ እንደመቸለስ አይነት ስሜት እንዲደማኝ ያደረገኝን ጥያቄ ያነሳው።
''ተደብቀሽ ያለቀስሽው ምን ሆነሽ ነው?'' አለኝ እንደ ቀልድ።
ውስጤ እንደ ደራሽ ውሀ በድንገት ሲያጓራ ይሰማኛል።
...አንዳንዴ የምናነሳቸውን ጥያቄዎች ምን ሊያስከትሉ መገመት እንዴት ይከብደናል? ያውም ገና የመጀመርያ ቀን ላገኘነው ሰው?...
ጥሩ እያወራኝ ነበር እኮ። እንዲያውም ደስ እያለኝ እንደነበርም አስታውሳለሁ... ያልሆነ ጥያቄ አነሳብኝ እንጂ...
... ምን እንድለው ጠብቆ ነው እንዲህ ቀለል ያደረገው? ደርሶ ማኪያቶ ስለገዛ ውስጤን ለማግኘት የሚችል ነው እንዴ የሚመስለው?.. ወይንስ ጥያቄው ለሱም አልገባውም?
ቆይ ልንገርስ ብል ደግሞ የቱን ነው የምነግረው?
ብዙ ማስታወስ የማልፈልጋቸው ለቅሶዎች እንዳሉኝ እንዴት አያስብም?
ከየትስ ነው የምጀምረው? ከልጅነቴ?
ወይስ ከአሁን ካደኩኝ ያለውን?
የልጅነትልስ ቢሆን የቱን አስቀርቼ የቱን ነው የምነግረው?
...ያኔ ወንድሜ እኔ እንዳልራብ ብሎ እሱ እንደጠገበ እያስመሰለ በባዶ ሆዱ አንጀቱን ቋጥሮ የዋለበትን ቀን ሳስብ የማለቅሰውን ልነግረው ነው ወይንስ?...
ደግሞ በጣም የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር እንዳልበላ እያወቅኩ በልቻለሁ ሲለኝ የማምነው ነገር።
ወይ ልጅነት... አበላሌን አይቶ ከፊቴ ዘወር እያለ አልቅሶ ሲመለስ ዛሬም አይኔ ላይ ድቅን ይልብኛል። አልገባውም እንጂ እንባውን ከኔ ለመደበቅ ቢሞክርም ስሜቱን እኔ ላይ ተክሎት ይኸው መቼም የማልረሳው ቀን አድርጎ አትሞ ቁጭ አድርጎታል። ያኔ ምን ሆኖ እንደሆነ ግን ጭራሽ አይገባኝም ነበር።
ሁሌም ቢሆን የሴቶች ቀን ተብሎ ሲከበር አዕምሮዬ ላይ የሚመጣው እሱ ነው። እሱ ለኔ ሴት ስለሆነልኝም ይመስለኛል ብቻ ሁሌም ተደብቄ ከማለቅስባቸው ቀናት አንዱ ማርች 8 ነው። በየ ቴሌቪዥን ጣብያው በየ ቲክቶኩ በየፌስቡኩ ስለ ሴቶች ሲወራ እኔ ግን ስለ ወንዶች ባወራ ምንኛ ደስ ባለኝ። በርግጥ እንደየ ሰዉ ይለያያል። ሁላችንም እንደየ አስተዳደጋችን በህይወታችን ላይ ትልቅ አሻራ ያስቀመጡ ሰዎች አሉ። አብዝሀኛው ሰው ላይ ትልቅ አሻራ ያስቀመጡት ሴቶች መሆናቸው አይዘነጋም። በኔ ህይወት ላይ ትልቅ አሻራ ያስቀመጠው ግን ወንድሜ ነው። ይህንንም ልዘነጋው አልችልም...
... ፊትለፊቴ የቀረበው ማኪያቶን ማኪያቶ ሳልጠጣው ስነሳ ግራ ተጋብቶ ''...ምነው?" ሲለኝ ልመልስለት እንኳ ፈቃደኛ አልነበርኩም።
ሁሉም ነገር እንደ መጀመርያው ቢሆን መልካም ነበር የሚባለው ለዚህ ይመስለኛል።
የማይነሳ ጥያቄ አንስቶ ቁስሌን ከነካካ በኋላ የትስ ብሄድ?
ከዛን ቀን በኋላ እሱ ያለበት መገኘት አልፈልግም።
ልክ ቁስል ይመስል ሽሽሁት። ላለመነካት....
https://t.me/Oct13wed
194
አንዳንድ ሰው ራስን እስከ ማጥፋት የሚደርስ ከባድ ውሳኔ በራሱ ላይ የሚወስነው በተፈጠረ ነገር ሳይሆን ተፈጥሯል ብሎ በገመተው ነገር ግን ጨርሶ ባልሆነ ጉዳይ ነው።
📚 የድንጋይ መአዛ
194
እምዬ ማርያም
✍️እስራኤል ሰይፉ
https://t.me/Oct13wed
..ስለ አድዋ ሳስብ መቼም ቢሆን አእምሮዬ ላይ ቀድሞ የሚመጣው እምዬ ምኒሊክ የተናገሩት ቃል ነው
''... ማርያምን አልምርህም'' የምትለዋ ቃል።
ጦርነቱን ትተን ይህ ቃል ያመጣውን ውጤት በራሱ ብናይ ሌላኛው አድዋ ነው።
https://t.me/Oct13wed
ቀጠሮ ስለማክበር ሲወራ ሁሌም ጭንቅላታችን ላይ የሚመጣው ሀበሻ ሰአት ላይ ችግር እንዳለበት ነው። አዎ ልክ ነው የዚህ ዘመን ሀበሻ ከተቀጣጠረበት ቦታ 30 ደቂቃ ማርፈድ እንደ ባህል ይዘነዋል። ከየት ነው ግን ያመጣነው? በፊት እኮ እንደ ሀበሻ ቀጠሮ አክባሪ እኮ የትም አይገኝም ነበር። ለዚህ ደግሞ አድዋ ትልቅ ምስክራችን ነው።
አስቡት እስቲ የዚያን ዘመን ሰው። ምንም አይነት ዘመናዊ መጓጓዣ ባልነበረበት ዘመን
ፈረስ ያለው ልክ አሁን ላይ መኪና እንዳለው በሚታይበት ዘመን ከደቡብ ከምስራቅ ከምዕራብ ከየማዕዘኑ ያለው የኢትዮጽያ ህዝብ በተቀጠረው መሰረት በተባለው ቀን እኩል ወረ ኢሉ ላይ ተገኝቶ የለም እንዴ? ታድያ አሁን ላይ ምን ነክቶን ነው? ምንስ ሆነን ነው?
https://t.me/Oct13wed
ሌባን ሰው ሁሉ የሚሰርቅ ይመስለዋል እንዲሉት ተረት ይመስለኛል።
ልክ ጥሩ ስራ ሲሆን እኔ ነኝ ያደረኩት መጥፎ ሲሆን ደግሞ እሱ ነው ያደረገው እንደምንለው ሁሉ ነጮች የራሳቸውን ስም ለኛ አሳልፈው ሰጥተውን የኛን ስም ደግሞ ለራሳቸው እንደወሰዱት ከተሰማኝ ሰነባብቷል። ያሉንን ተቀበልንና ስምና ስራ ተወራርሰው አርፋጅ አድርገው አምነነው እንድንቀበል አስገደዱን።
https://t.me/Oct13wed
የግድ ሰአት እንድናከብር በማርያም መባል የግድ ነው እንዳልል አሁን ላይ ብሶብን በማርያም አድርጉ ስንባል በማርያም አታድርጉ የተባልን ይመስል ጭራሽ ብሶብናል። ልክ ገና በማርያም ስንባል
በማርያም እንዳትለኝ ብለን መሃላን ማፍረስ ይቻል ይመስል ለማጥፋት እንሞክራለን። ክብራችንም ጭምር እኮ ነው አብሮ የተገፈፈው።
አይታያችሁም አድዋ ዛሬ ላይ ቢሆን ኖሮ?
ሙድ የምንይዝ ሁላ ይመስለኛል። ጭራሽ ማርያምን ይላሉ እንዴ? ሆሆሆ ብለን ባላየ ባልሰማ የምናልፍ አይነት ነገር።
የመከነ ትውልድ...
ብቻ ልቦና ይስጠን
https://t.me/Oct13wed
194
አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች...
✍️እስራኤል ሰይፉ
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
እነዚህ ጠርሙሶች ግን ለምን አስር ሆኑ? ማንስ ነበር አስር እንዲሆኑ የወሰነው? አሁን ላይ ሲገባኝ ግን ይህን ሃሳብ ሲያመጣው በህይወቱ ብዙ ነገሮችን ሞክሮ አንዱም ያልተሳካለት ሰው ይመስለኛል።
መስበር አሁን ምኑ ያስደስታል?
ጭራሽ ደግሞ ዜሮ ይቀራል ብሎ መደሰት...
ምን ይሉታል አሁን?
መሰበሩ ሊያሳዝነን ሲገባ ጭራሽ በዞሮው መጨፈር?
ያው አባባሎች ከህይወታችን ከተማርናቸው ትምህርቶች መካከል ዋናውን ጨምቀን አይደል የምናወጣው?
... ሲመስለኝ እንደዛ የተቀዳ ነገር ነው ይሄም። ከባዶ ሰው የተቀዳ አይነት ነገር...
ገብረ እግዚአብሔር እባላለሁ። በሙሉ ስሜ ግን ማንም ጠርቶኝ አያውቅም። ገብሬ ነው የሚሉኝ። በእርግጥ ራሴው ነኝ የፈቀድኩት። ''የእግዚአብሔር ስራ'' የሚለውን ሳላምንበት ቀርቼ አልያም
ደግሞ ስሜን ለሚጠራው ሁሉ እንደሰራኝ እንዲሰማው..
'' ገብሬ '' እንዲል ፈቅጄለት ግን አይደለም። ለማሳጠር ያክል ነበር።
አሁን ላይ ሲገባኝ ግን ያኔ ላይ 10 አረንጓዴ ጠርሙሶችን እንድቀንስ ስላስተማሩኝ ከስሜ መጀመሬ ነበር።
ለምን 3 ላይ እንደቀረሁ ግን እንጃ። ዜሮ ማስቀረቱ ላይ አልተስማማሁ ይሆናል።
https://t.me/Oct13wed
ገብሬ ሲሉኝ ታድያ የትም አለሁ። በተለይ መቀነስ ያለበት ቦታ ላይ ስገኝ የሚሰማኝ ደስታ ዛሬም አለቀቀኝም።
ከማስታውሳቸው መሀል አንሁን ለ'ታ ጓደኛዬ
''እኔ የምልህ ገብሬ... ትናንት የገዛሁት ጫማ እኮ በዛብኝ። ሚመችህ ከሆነ የገዛሁበት ሱቅ አብረን ሄደን ቁጥሩን አናስቀንስም?'' አለኝ።
ደስ እያለኝ ነበር የሄድኩት። መቀነስ ነዋ እንዴት ደስ አይለኝ። ምን ብዬ እንደማሳምን ባላውቅም ብቻ ግን እንዴትም ተከራክሬ ቁጥሩን አስቀንሼለት ስመለስ የተሰማኝ ደስታ
የምናምን ሚሊዮን ጥብቅና አሸንፈው ሲመለሱ እንደኔ የፎከሩ አይመስለኝም።
በልጅነቴ የገባው ይህ አስር ጠርሙስ ታድያ ዛሬም በህይወቴ እየገባ ብዙ ነገሮችን አስቀንሶኛል።
እንደዛ እወዳት የነበረችዋን የሺን ሳይቀር።
''ስምሽ ግን አልበዛም?'' ነበር ያልኳት የመጀመርያው ትውውቃችን ቀን።
''ሁለት ፊደል በዛብህ? '' አለች እየተሽኮረመመች
''ለካ ሁለት ነው። ይቅርታ...
ሰው እየጠበቅሽ ነው ወይንስ ብቻሽን ነሽ?"
"አዎ ባሌ እየመጣ ነው። ባይሆን እንዳያይህ ዘወር ብትል ይሻልሀል " አለች ሙድ እንደመያዝ እያረጋት።
''ይምጣ ታድያ ምን ችግር.... የሺ አይደለሽ እንዴ'' አልኳት ሳቅ እያልኩ።
''ማለት?''
''ማለቴ ሚስቱን ያላመነ ማንን ያምናል? ታማኝ ለመሆንሽ ደግሞ ማንም ምስክር ነው''
"ወረኛ ነህ ልበል?''
''በይ ምን አባቱ። ለማንኛውም ገብሬ እባላለሁ!"
እጄን ዘረጋሁ እንደ አዲስ።
በዚህ ሁኔታ ነበር ከየሺ ጋር የተዋወቅነው። ባል አለኝ እንዳላለችኝ ሁሉ... በቆይታ ማንም የማይለየን ጥንዶች ሆነን አረፍን። ስሟ ገባ እንጂ..
ሶስት አመት በፍቅር እንደቆየን እንኳ ያወቅኩት ከተለያየን በኋላ ነበር።
ሁሌ በየቀኑ ሳገኛት ልክ አዲስ የተፋቀሩ ጥንዶች አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ። አልጋ ላይ ሆነን እንኳ ልክ ለመጀመርያ ጊዜ የማውቃት አይነት ነገር...
https://t.me/Oct13wed
እንደምታፈቅረኝ አውቃለሁ። ነገሮችን እንድታደርግ የማስገድዳት እኔው ነኝ። ምንም ቢሆን ለኔ ስትል ታደርጋለች።
ትልቁ ችግሬ ግን ዛሬም እንዳዲስ ነው የማያት። ልክ የሺ የሆነች አይነት።
ለኔ ብላ ስሟንም ቀይራለች። የሺነቷ ካልቀረ ስሟ ምን ያደርጋል እሚል የጥርጣሬ መንፈስ ቢያጠቃኝም።
በተቻላት አቅም ሁሉ እኔን ለማሻሻል እና የጥርጣሬ መንፈስ እንዳይሰማኝ ጥረቷን መቼም አልረሳውም።
እኔ ግን በጭራሽ የምመለስ አይነት አልሆንኩላትም። እንደውም ከቀን ቀን ጥርጣሬዬ እየጨመረ ከመሄዱ የተነሳ አብረን ወክ እያደረግን መንገድ ላይ ሰላም የሚላትን ወንድ ሁሉ መጠርጠር ጀምሬአለሁ።
ጠርጥሮ ዝም ቢሆን መልካም ነበር። ልጣላ ሁላ ያምረኛል።
በውስጤ ብዙ አንጎራጉራለሁ።
ማን ስለሆነ ነው እንዲህ የሚያያት? ሰላም አባባሉ ሁሉ ይለያል እኮ!
ጥቅሻ መሆኑ ነው? ከሱ እንደተለየሽ ደውይ አይነት ነገር?
https://t.me/Oct13wed
እሷንም ቢሆን በጥያቄ አፋጥጣታለሁ።
ማነው?.... ምንሽ ነው?...ለምንድነው እንዲህ የሚያይሽ?... አይነት ለሷም ግልጽ ያልሆኑ ጥያቄዎችን እየጠየኩ ግራ አጋባታለሁ።
አንድ ቀን ግን አልቻለችም። የበቃው አይነት አነጋገር ነበር...
''....ገብሬ በዚህ ሁኔታ አብረን መቀጠል አንችልም።'' አለችኝ እቅጩን ስትነግረኝ።
''...ማለት ለምን?"
"...በሆነው ባልሆነው እንዲህ እያሰብከኝ ነገ እንኳ ተጋብተን ብንወልድ ልጁ የማን ነው? ማለትህ የማይቀር ነው።"
አ...ሀ....አልኩኝ ያኔ
''እኔ እኮ ትናንት ከቤተ ክርስቲያን ስንመለስ ስልክ ሲደወልልሽ አላማረኝም ነበር። እንደተለያየን... የት... ነበር... የሄድሽው?"
"...ኧረ እባክህ ገብሬ ተረጋጋ። አጎቴም አይደውል?"
"በጣ..ም አጎት... እንደውም እሱ ነዋ የሺ ብሎ ስም ያወጣልሽ? ሲገርም ልክ ነበር..."
https://t.me/Oct13wed
ተናዳ ጥላኝ ሄደች። በዛው ቀረች ቀረች!
ለካ እሷን ለመቀነስ ሰበብ ነበር ስፈልግ የነበረው?
የበፊት ፍቅረኞቼንም በሰበብ ስቀንስ እንደኖርኩ የገባኝ የሺ ከሄደች በኋላ ነው። የሺን አፈቅራት ነበር። ምንም ውብ ያልነበረ ነገር አልነበራትም። ከጥርሷ በስተቀር...
እነዛ የድሀ አጥር የመሰሉ ጥርሶቿ ባይኖሩ ከሰው ዘር ተፈጠረች ለማለት ትንሽ የምቸገር ይመስለኛል።
ፈጣሪ ልክነቱ የሚታየኝ የሷን ጥርስ ሳይ ነው። አሰብኩት እኮ ሙሉ አድርጎ ቢፈጥራት... ላመልካትም እችል ነበር።
አሁን ላይ ስረዳው ታድያ አፈቅራት እንደነበር እና ሳላስተውለው የመቀነስ በሽታዬ አላስችል ብሎኝ ሌሎቹን እንደቀነስኩት እሷንም ለመቀነስ ሰበብ መፈለጌን ነው።
ስለያት ግን ልቧን ብቻ ሳይሆን ህልሟን እና ሙሉ ተስፋዋን እንደሰበርኩት ገብቶኛል ግን አልገረመኝም።
መስበር እንዲያስደስተን አድርገው አዘምረው አሳድገውን ዛሬ የስንቱን ሰው ተስፋ እና ህልም እንደቀልድ ሰብረን ብንደሰት ምኑ ያስገርማል?
ፍቅረኛዬን እንዲህ ያስቀነሰኝ የልጅነት ጠርሙስ መሆኑ ሲገባኝ ታድያ ልክ እንዳልነበር አስቤ ላስተካክለው ወሰንኩ።
ካሁን ወዲያ ስሜን በማጉደል የጀመረው የመቀነስ ጠርሙስ ስሜን በመሙላት የመደመር ስራውን ይጀምራል።
" ሶስት አረንጓዴ ጠርሙሶች በግድግዳ ላይ
ድንገት 7 ጠርሙስ ሲጨመር አስር ይሆናል" ብዬ አልኩ ለራሴ።
'ከአሁን ጀምሮ ገብረ እግዚአብሔር ነው ስሜ!"....
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
194
''ልሙትልህ...''
✍️እስራ
https://t.me/Oct13wed
የአነሳሴን ፍጥነት ላየ ምን አልባትም ለዛሬ 2x የተደረኩ ሊመስለው ይችላል። የሆነ አጓጊ ፊልም እያየን በመሀል የማያጓጓውን ክፍል ለማለፍ ጫን አድርገን እንደምናሳልፈው አይነት ነገር።
ልክ ነው ቸኩያለሁ። በዚህ አካሂዴ ግን አጓጊውንም ክፍል ሳላልፈው እምቀር አይመስለኝም። አልጋዬ እንኳ ብትጠየቅ እንዲህ የቸኮልኩበት ቀን ላለመኖሩ ምስክር ነች።
https://t.me/Oct13wed
... በዛ 2x በሆነ ፍጥነት በቻልኩት መጠን ከወትሮው ለየት ያለ አለባበስ ነጭ ሸሚዝ በጥቁር ሱሪ ለበስኩና ሄጄ ካፌ ስደርስ... የሰልፉ ርዝመት እንኳን ለ2x ለ ለምንም አይመችም።
ልክ በቲቪ አሪፍ ፊልም ቁጭ ብዬ እያየሁ በመሀል ረጅም ማስታወቂያ ሲገባ አይነት ነገር ነበር ሰልፉ።
ይሁን ብዬ ልሰለፍ ወደመጨረሻው ሄጄ ስሰለፍ ግን መጨረሻ ያለችው ልጅ...
ሰልፉን Pause ቢያደርጉት ታሰኛለች።
ስለ ሰውነቷ ምንም አልልም።
ቃላት መች ይገልጻሉ ወገን?
እሷን ለመግለጽ እንኳን ቃላት ዝምታ በራሱ ዝም ይላል።
ቃል እባላለሁ አለችኝ ድርቅናዬ አስገርሟት።
እስራኤል... አልኳት
''ሳልጠይቅህ ነገርከኝ እኮ ቅድም..'' አለች እየሳቀች።
ለካ ሳይታወቀኝ ለ3ተኛ ጊዜ ነው ስሜን ስናገር!
https://t.me/Oct13wed
ቆይ ግን ሰልፉ ረጅም አልነበር እንዴ? ወይስ በ3x ነው ያስኬዱት?
ወሬዬን ማቆም እንዳለብኝ ሲገባኝ ስልኳን ተቀበልኳት። ቲከሩ ጋር ደርሼ ትንሽ ተጨቃጨቅን... የፈረደበት ጸጉር..... ይሁን ብቻ ውስጥ ገባሁ። በጊዜ ስለመጣሁ ነው መሰል ካፌ ሞላ ብሏል።
ቃል ግን የለችም። ሲመስለኝ ምግቧን ይዛ ቁጭ ብላለች።
እኔም ምግቤን ይዤ እሷን በአይኔ መፈለግ ጀመርኩ። የለችም።
ነገሩ በዛ ሁሉ ግርግር መሀል እንዴት ልትገኝ ኖርሯል?
ደግነቱ ስልኳን ተቀብያለሁ።
በአይኔ እሷን እየማተርኩ ምግቤን ይዤ ወደ መውጫው በር ሳመራ በአንዱ አቅጣጫ መሀል ላይ ቁጭ ብላ እያየችኝ ነው። ተያየን። ሰው እንዴት በአይን ያወራል?
አንዳንዴ በቃላት ከምናወራው በላይ በአይናችን አልያም በሌላ አካላችን የምናወራው የበለጠ ሚዛን ይደፋል።
አፍ ዝም ቢል ሌላው ይናገራል እንዳለ ደራሲ
ምን አለ ግን ባልቸኩል?
ብዙ ጊዜ እንደቸኮልን እንጂ ለምን እንደቸኮልን ለውስጣችን ስለማንነግረው ማምለጥ የሌለባቸው ጉዳዮች ያመልጡናል።
ውስጣችን እሚያውቀው መቸኮላችንን ብቻ ይሆንና ሳንፈልግ ያቻኩለናል። ብቻ ለምን እንደቸኮልኩ ሳስበው ሳቅ አልኩኝና ተመልሼ ቃል ጋር ልመለስ ቆም ስል አንሸራተተኝ።
ወይኔ...
እኔ የምለው?... ከላይ እግርን የሚስብ አካል አለ እንዴ ቆይ?
ግራቪቲ ምናምን ያሉትስ የት ሄደ?
መሬት ለመንካት ከእግር እንዴት ወገብ ይቀድማል?
ወይንስ እግሬ ከመሬት ጋር እንደ ተመሳሳይ ማግኔት ይገፋፋል?
ብቻ አወዳደቄ የሆነ የተወረወረ ኳስ ልቀልብም መስሎኛል።
ወይኔ ሳቅ....
ተማሪው በሳቅ ሞተ አይገልጸውም። በዛ ሁሉ ጫጫታ መሃል ግን
''ልሙትልህ...'' የሚል የድንጋጤ ድምጽ ስሰማ አልቻልኩም።
ቃል ነበረች።
አስር ጊዜስ ብወድቅ ነው ያሰኘኝ።
አንዳንዴ ከመውደቃችን አወዳደቃችን ያመናል።
ድንገት የምንሰማቸው ድምጾች ደግሞ ህመማችንን ያስረሱናል። ምን አለ ድጋሚ ብወድቅም ያሰኙን ይሆናል።
ለመውጫው በር ቅርብ ስለነበርኩ ይሁን አልያም ''ልሙትልህ...'' የሚለው ድምጽ ሀይል ሆኖኝ እንደው ባላውቅም ወደ ቀልቤ ስመለስ ግን ዶርም እየሄድኩ መንገድ ላይ ነኝ። ነጭ ሸሚዜ ላይ ያለው ቀይ ወጥ የሆነ ቅርጽ ሰርቷል። ጽሁፍም መሰለኝ። የሆነ ቃለ አጋኖ የሚመስል ቅርጽ በታች በኩል ሰርቷል።
ምን አልባት ወጥ የሚጨልፉ ሰዎች መዕክት ማስተላለፊያ መንገዳቸው ይሆን እንዴ?
ዶርም ገብቼ ሸሚዜን አወለቅኩና አዙሬ ወጡን በደንብ ሳስተውለው የምርም ጽሁፍ ነው። ግን ደግሞ አረብኛም መሰለኝ።
ሙስሊም ጓኛዬ ኢማድ እስኪመጣ እንዴት ልቀመጥ?
እስከዛው ብዬ ቅድም ያስቸኮኝን ፊልም ልጨርስ ጋደም አልኩኝ።
የሚያናድደው ደግሞ እንደዛ ያስቸኮለኝ ፊልም ለካ ያለቀ ነበር
ላለቀ ነገር ግን እስከመቼ ቸኩለን እንችለዋለን ጎበዝ?
ትንሽማ ሰከን እንበል እንጂ። ያላለቁ የመሰሉን ግን ደግሞ ያለቁ ነገሮች ናቸው እኮ ዋጋ ያስከፈሉን።
https://t.me/Oct13wed
ኢማድ ሲመጣ አቻኩዬ ጠየቅሁት።
'' ስማኝማ ኢሙ... የእከዛሬ አረብኛህ ለየት ያለ ስራ ይጀምር እስኪ በኔ..''
ብዬ አሳየሁት።
ከት ብሎ ሳቀና ''ብለህ ብለህ በነጭ ሸሚዝ ቀለም መቀባት ጀመርክ?"
አለኝ። በርግጥም ከላይ ከላይ ጠርጌው ስለነበር ቀይ ሆኗል እንጂ ወጥ እንደሆነ አያስታውቅም ነበር። ቀይ ይሁን እንጂ ሽሮ ስለነበር ሽታውም የለም።
''..አትቀልድ ባክህ ተርጉምልኝ። ነው ወይንስ አትችልም?...''
'' እስኪ አምጣው?...''
ተቀብሎኝ እያገላበጠ ያየዋል። የገረመው ይመስላል።
ትንሽ ካየው በኋላ
'' አንተ ነህ የጻፍከው ግን...?''
''ምንድን የሚለው ለምን አትነግረኝም ቆይ?..''
ፈገግ አለና...
'' አይ ገርሞኝ እኮ ነው። ፊደላቱን ገለባብጠሀቸዋል እንጂ ልክ ነህ.. የተለያዩ ቃላት ናቸው..
ይኼውልህ እዚጋ... ''እሰይ..'' ይላል..
እዚጋ ደግሞ... ''እንኳን... ''ይላል ብቻ በጣም ብዙ ቃላት ናቸው... በእልህ ነው እንዴ የተቃባችሁት..?''
https://t.me/Oct13wed
''እስቲ ቃለ አጋኖ ያለበትን አንብብልኝ!..'' አልኩት ጥያቄውን ችላ ብዬ።
''ይህ ደሞ ምን ማለት መሰለህ...'' አለና በአረብኛ የሆነ ነገር ካለ በኋላ
''ልሙትልህ...' ነው የሚለው... ኧረ ለየት ያለ ቃል... እንዴት አየኸው ባክህ..!'' ምንም አላልኩትም።
ሲገርም።
የማይሰሙ የሚመስሉን ነገሮችም ለካ አይሰሙም ማለት አይደለም?
https://t.me/Oct13wed
194
ቅድመ ጥያቄ
እስራ✍️✍️✍️
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
...አንዳንድ ቀን የውስጣችን ጥያቄ ካልተመለሰ ከውጪ የሚመጣ ጥያቄ ለማስተናገድ እማንችልበት ሁኔታ መፈጠሩ ግድ ነው።
...አንድ ቀን ክፍል ተቀምጠን እየተማርን መምህሩ አንድ ጥያቄ ሊጠይቅ ፈለገ እና ረዘም ያለውን ልጅ ሊጠይቅ
'..ስምህ ማን ነው?...'' አለው
ትምህርት የተጀመረ ሰሞን ስለነበር ሁላችንም እርስ በዕርስ እንኳን አንተዋወቅም ነበር።
'' ኢብሪሃም..'' አለ ልጁ
'' እሺ አብርሀም... '' ብሎ ሊቀጥል ሲል አቆመው።
''No ኢብሪሃም..''
'' ok sory Ibrahim emm''
አሁንም አስቆመው ''I said I b ri ham...''
https://t.me/Oct13wed
''Ow ምን አይነት ስም ነው? ይቻላል እንዴ ሁለቱንም?
የሙስሊም ሲሆን ኢብራሂም የክርስቲያን ሲሆን ደግሞ አብርሐም ነበር እማውቀው ሌላም አለ እንዴ? '' አለና
''... any ways ወደ ትምህርታችን ''
ብሎ ሊጠይቅ የነበረው መምህር ወደማስተማሩ ሄደ።
https://t.me/Oct13wed
በሌላ ቀንም ታድያ በሌላ መምህር ይሄው ተደገመ።
ይሄ ልጅማ ጥያቄ ላለመጠየቅ ማምለጫ መንገዱ መሆን አለበት ለማንኛውም ልጠይቀው ይገባል ብዬ ልክ ከክላስ ስንወጣ ጠብቄ ጠራሁት
''ኢብሪሃም'' አልኩኝ በስሙ
''እስራ እንዴት ነህ? አንተ ብቻ እኮ ነው የኔን ስም የምትችለው።
ምን ነበር ጥያቄህ?'' አለኝ። ደስ ሲለው ፊቱ ላይ ይታያል። ልክ የረጅም አመት ጥያቄ የተመለሰለት አይነት ፊት...
ምንም ልል አልቻልኩም።
''ኧይ እንዲሁ ሰላም ልበልህ ብዬ ነው'' ብዬው አለፍኩኝ።
ለካ ከጥያቄ በፊት መቅደም ያለበት መልስ አለ!
ብዙ ጊዜ ልናወራቸው ፈልገን ሌላ ነገር እሚያወሩን ሰዎች በዛ ጉዳይ ማውራት ያልፈለጉ ይመስለናል እንጂ ከዛ በፊት ሊመለስላቸው የሚገባውን ጥያቄ ማስቀደማቸው ነው።
እኛም ብንሆን ታድያ ውስጣችን ያሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲመለሱልን ነው ወደ ውጫዊው የምንሄደው።
የውስጣችን ጥያቄ ምን ይሆን?
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
194
"አምላኬ ሆይ....!"
ከደጅህ ስመጣ ሳልመላገድ
ስሻ ስፈልግህ ላየኝ እመንገድ
የበደልኩህን ሳይሆን የሰጠኸኝን አይቶ
ባይነጣጠሉም ቅሉ አዪው ግን ለይቶ
የሰጠኸኝ ክፉን አያላቅቅ
ስራዬ'ንጂ የሚያላ'ቀኝ፣
እምነቴ እንጂ እሚያጸድቀኝ
ምግባሬ እንደው አያጸድቀኝ
ታምነኛለህ ወይ? ብትትለኝ አዎን እላለሁ
አልወድህ እንደሆነም እንድታውቅ አምናለሁ
እንድወድህ እናገራለሁ ያንን ባይልም ልቤ፣
ደግሞ አልሰማኝ እላሁ በኀጢአት ደልቤ!?
ከሀጢአቴም በኋላ ትዝ ሲለኝ ቃልህ
በደሌ ገብቶኝም ጌታዬ ሆይ ስልህ፣
ይቅርታን ተማምኖ መበደል ቢሆንም
ሁሉን ሐጢአት መተው ላንተ አይሳንም!
እስራኤል ሰይፉ
ግንቦት 2016 ዓ/ም.
194
ጣል ጣል አረግሽኝ
እስራ✍️
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
በፊት እንዴት እንደነበርን እና ዛሬ እንዴት እንዳለን ልነግራት ፈልጌ
''ምንድነው ጣል ጣል አደረግሽኝ እኮ...''
ስላት እንዳልገባት ሆነች።
ልክ እንደ አባቶቻችን ዘመን በወረቀት እንጻጻፍ ይመስል
''ስልኬን ብዙም ስለማልጠቀመው እኮ ነው በአካልም ያን ያህል አንገናኝም ለዛ ይሆናል...'' አለችኝ።
''ስልክሽን አለመጠቀምሽንማ እንደ ምክንያት አትስጭኝ...
ላግኝሽ ስልሽስ መች ፈቀድሽና?... ያው ጣል ጣል ማድረግሽ ነው እንጂ...''
''...ቆይ ግን ጣል ጣል ማድረግ እንዴት ነው ላንተ?''
አለችኝ ሌላ አይነት አጣጣል ልል ፈልጌ መስሏት።
አውቃ እያደረገች እንደሆነ ውስጧ እንደሚያውቀው ባውቅም በምሳሌ ልንገራት ብዬ ምሳሌ መረጣ ጀመርኩ።
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
ምሳሌ አንድ
''ጣል ጣል ማለትማ ልክ... ጓደኛው ከሰው ጋር ሲጣላ እያየ... ገላግለኝ እያለው እንኳ.. ዝም ብሎ እንደሚያልፍ...
አልያም ደግሞ
ልክ የጓደኛው ሰርግ ላይ ሚዜ እንዳልነበር ሁሉ... ወንድሙ ሲያገባ ለግብዣ እንኳን ጓዱን እንደረሳ ሰው አይነት።
መርሳቱ እንኳ ይሁን ግን ረስቼ ሳልጠራህ ላለማለት ወንድሜ አላገባም ብሎ እንደሚሸመጥጥ አይነት... ባተሌ
ወይም ደግሞ
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
ምሳሌ ሁለት
...
...በፊት ለክብር እንግዳ ይሆን የነበረ እና ዛሬ ላይ ልክ አዲስ ሲገዛ ህጻናት ሳይቀር እንደናቁት ወንበር
አልያም ደግሞ ነጭ ሰሌዳ ስለመጣ ተገልጋይ በማጣት ጠመኔ ተርቦ እንደተሰቀለ ጥቁር ሰሌዳ
አይነት ስሜት።
...ብቻ እንዴት ልበልሽ ይግባሽ አይግባሽ ባላውቅም ምሳሌዎቹ ግን በጥቂቱ የሚገልጹልኝ ይመስለኛል'' ስላት
አልገባትም መሰል ሳቀች።😂😂😂
https://t.me/Oct13wed
https://t.me/Oct13wed
ከገባችሁ ጨምሩላት።
194
https://t.me/Oct13wed
ቆይቼ ስነቃ አልጋ ላይ ነኝ።
ማን ነው ያመጣኝ? እንዴትስ መጣሁ?
ፈተናውስ? ህልሜስ? እንዲህ ነው ራስ መሳት?
ውዝግብግብ እንዳልኩኝ ቀና ለማለት ስሞክር ራሴን አልቻልኩትም።
" ልቀቁኝ! '' ብል ማን ሊሰማኝ። ሳይያዙ ልቀቁኝ የለም ለካ...
...በዚህ ሁኔታ ጂኦግራፊ ሳልፈተን እንዲሁ ተሞልቶ
ቀሪዎቹን ደግሞ በድጋፍም በምንም እያልኩ ጨረስኩኝ።
...የትምህርት ቤታችን ጥበቃ መታመሜን ሲሰሙ ቤት ድረስ መጥተው ጠየቁኝ
''...አይዞሽ ታልፊያለሽ። ባታልፊስ ምን አባቱ በትምህርት ብቻ አይኖር! እንደውም አንቺን የመሰለ አንባቢ ቀረበት'' አሉ።
ህልም ለሌለው ቢሆን ነበር ይህ ንግግር።
...እህቴ እንኳ እኔ ጋ ነይ ብትለኝም እንዴት ልስማት?
እነሱ መተው ካልጠየቁኝ በቀር እህቴም ወንድሜም ጋር ሄጄ አላውቅም። ጥገኛ የሆንኩ ያህል ይከብደኛል መሄዱ።
...ከቆይታ በኋላ ውጤት መጣ ተባለ። እዴት ልይ?
የተፈታኝ መለያ (Admission) ካርዴን ወንድሜ ወስዶታል። ቁጥሩን በቃሌ አላውቀውም። ደውዬ ስጠይቀው እሺ አይቼ ልደውልሽ ብሎኝ በዛው ጠፋ።
ቆይቼ ስጠይቀው "connection" የለም አይቼ እኔ እራሴ እደውልልሻለሁ አለኝ።
እንዲህ እያለ መሽቶ ነጋ...
ዛሬም ኮኔክሽን የለም...
እያለ እያለ ልክ በሶስተኛው ቀን የጓደኛዬ ስልክ ላይ ክጎኔ እንዳትለየኝ
የተላከ መልዕክት አየሁ። ከወንድሜ ነበር።
https://t.me/Oct13wed
ወደቅሁ ማለት ነው?
እንዴት ልመን? ቀልድ መሆን አለበት።
ልብሴን ከላዬ ላይ ቀደድኩት። ጓደኛዬ ሌላ ልብስ አለበሰችኝ።
ግን እንዴት ልረጋጋ?
መሻሽቶ ስለነበር ቤት ወሰደችኝ። ወይ እንቅልፍ መተኛት?
ልክ ለሊት አስራ ሁለት ሰአት ይመስለኛል ተነሽ ሂጂ ተነሽ ሂጂ የሚል ስሜት ይሰማኛል። ማንም ሳያያኝ ተነስቼ ወጣሁ።
እግሬ ወደ መራኝ።
...ከደብረዘይት በእግር መጥቼ ታሪክ ሰራሁ ብል ማን ያምነኛል?
ሆሆሆ ለኔም ቅዠት ነው የሚመስለኝ። እውነታውን ግን መካድ አልችልም። በትክክል ራሴ እማውቀው ግን አዳማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን በረንዳ ላይ ተደፍቼ መሆኔን ነው። አንዳንዴ ራሴንም እጠራጠራለሁ። እውነት እኔ ነኝ ግን? 47 ኪሎ ሜትር ስጓዝ የት ነበርኩ? ሰው ራሱን ሲስት የት ነው የሚሄደው?
አካል ብቻውን ሙሉ ሰው አይደለም ማለት ነው?
ነፍሴም ያለ እኔ እኮ አካሌም ቢኖር ምንም ዋጋ የላትም።
47 ኪሎሜትር ስጓዝ አካሌም ነፍሴም ነበሩ መቼስ።
አብሮኝ ያልነበረው አካል ማን ነው ታድያ?...
አዕምሮዬ እንዳልል የማደርገውን እያንዳንዷን አስታውሳለሁ።
እዛው ተደፍቼ... ወንጌል ይነበባል
''...ህጻኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ...'' የካህኑ ዜማ አጣጣል ለውስጤ ጥያቄ መልስ የተላኩ ይመስል ረጋ ያለ ነው። እጣኑ "የካህኑን ቃል አታቃዪ.." እንዲል ሸተተኝ። ውስጤ ገብቶ የነበረውን ጥያቄ በሚማርክ ሽታ ሲያፈራርሰው ይታወቀኛል።
"...በመንፈስም ጠነከረ..." የሚለው ድምጽ በጽና ታጅቦ አዕምሮዬ ላይ ይመላለሳል። የት ነበር ይህን ድምጽ የማውቀው?
አው አስታወስኩ ጥበቃው ቅጭል ቅጭል ያደረጉት ቁልፍ አይነት ድምጽ? አዎ ልክ ነኝ።
መንፈሴ ነው ማለት ነው አብሮኝ ያልነበረው?....
ይቀጥላል....
https://t.me/Oct13wed
194
አብሮኝ ያልነበረው...
✍️እስራኤል ሰይፉ
https://t.me/Oct13wed
...ከደብረዘይት በእግር መጣሁ ብል ማን ያምነኛል?
ሆሆሆ ለኔም ቅዠት ነው የሚመስለኝ። እውነታውን ግን መካድ አልችልም። በትክክል ራሴ እማውቀው ግን አዳማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን በረንዳ ላይ ተደፍቼ መሆኔን ነው። አንዳንዴ ራሴንም እጠራጠራለሁ። እውነት እኔ ነኝ ግን? 47 ኪሎ ሜትር ስጓዝ የት ነበርኩ? ሰው ራሱን ሲስት የት ነው የሚሄደው?
አካል ብቻውን ሙሉ ሰው አይደለም ማለት ነው?
ነፍሴም ያለ እኔ እኮ አካሌም ቢኖር ምንም ዋጋ የላትም።
.
.
.
... ታሪክ እባላለሁ። ጓደኞቼ ግን ችኮ ብለው ነው የሚጠሩኝ። አንድ ነገር ላይ ካተኮርኩ ሌላውን ስለምረሳ ነው ይህን ስም ያወጡልኝ።
ለነገሮች ትኩረት የምሰጠው ከአስተዳደጌ ይመስለኛል።
ትምህርቴ ላይ ብቻ ትኩረት እንዳደርግ ስላሳደጉኝ ሌላ ምንም ትኩረቴን የሚወስድ ነገር የለም።
...ብዙ ሰው በጎን ስራ ለመስራት ወይ ሙያ ነክ ነገር ለመማር ይሞክራል። እኔ ግን ትምህርቴ ላይ ብቻ ነኝ። ትምህርቴ ላይ ብቻ።
ከመምህራን ጋር በጣም ከመግባባቴ የተነሳ እንደውም ጓደኞቼ ባልሽ መጣ ይሉኛል። ሁሉንም ማግባት ይቻል ይመስል።
ከልባቸው እንደሆነ አውቃለሁ። ግን እኔ አላድርገው እንጂ ሰው የፈለገውን ቢል ግድ አይሰጠኝም።
ደግነቱ ቤተሰቦቼም ይህንን ጸባዬን ያውቁታል። እኛ ቤት ማንም ሰው ፍቅረኛ ቢይዝ እንኳ በግልጽ ነው የሚወራው። ለዛም ይሆናል የሚረዱኝ። እንደውም አንድቀን አባቴ ሳሎን ቁጭ ብዬ እያለሁ ሙድ ሲይዝ "...እድሜአለም መቼ ነው ሽማግሌ የሚልከው?..." ነበር ያለኝ።
እድሜአለም ማለት የታሪክ መምህሬ ነው። ታሪክ በጣም ስለምወድ
ከእድሜአለም ጋር እንግባባለን። ወይ እድሜአለምና ታሪክ....
ኧረ እንደውም ትምህርት ቤት ''... እድሜአለም ማርክ ጨምሮላት ነው 98 ያመጣችው..." ተብሎም ተወርቷል...
በእርግጥ ጂኦግራፊ መምህራችን ሲመጣም መወራቱ አልቀረም።
"...ደግሞ ከሱ ጋርም ጀመረች?...'' እንዳሉ ሁሉ ሰምቻለሁ... ግድም አልሰጠኝ እንጂ።
ትኩረቴ ትምህርት እና ትምህርት ብቻ ስለነበር ማንም ሰው ከትምህርት ሚያሰናክለኝ መስሎ ከተሰማኝ ከዛ ሰው መሸሽ እጀምራለሁ።
ጓደኞቼን መራቅ የጀመርኩትም በዚሁ ምክንያት ነው። ጓደኛ ጥሩ የምትሆነው ለወደፊት ጥሩ ህልም ያላት እና አብራት ያለችውንም ወደ አላማዋ እንድትደርስ የምታግዝ እና አንባቢ እንጂ.. "ተበለጥኩ" ላለማለት ''ማርክ አስጨመረች.." እያለች ሙድ የምትይዝ ሴት አይደለችም።
ንባብ ከተነሳ...
..የትምህርት ቤቱ ቤተ መጻህፍት ማለት ለኔ ቤቴ ማለት ነው። ሁሌም ቢሆን አለሁ። ትምህርት ባይኖር እንኳን ቀርቼ አላውቅም። ቤተ መጻህፍቱ ውስጥ ከትምህርት ባሻገር ደስ የሚሉ የልቦለድ፣ የታሪክ፣የሳይንስ፣ የፍልስፍና እና የሳይኮሎጂ መጻሕፍት አሉ። ነጻ በምሆን ሰአት ደስ ያለኝን እየመረጥኩ ባነብም የታሪክ እና የሳይኮሎጂ መጻህፍት ግን ቅድሚያ የምሰጣቸው ናቸው።
...ሁሌ ቤተ መጻሕፍት ቆይቼ ስወጣ ታድያ የትምህርት ቤቱ ጥበቃ ጋሽ መብራቱ ተገርመው እያዩኝ
"...ልጄ!.. እስካሁን እዚው ነሽ?.." ይሉኛል።
የለመድኳት ጥያቄ ሰለሆነች የሚገርም ነገር አይመስለኝም።
https://t.me/Oct13wed
...እዛ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ስምንት ሰአት ብቆይ አራቱን ሰአት ስለ ወደፊቴ እያሰብኩ ነው ያማሳልፈው። እንዲህ እያለምኩ...
...ትምህርቴን ጠንክሬ ተምሬ አባቴን ማስደሰት ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡም መትረፍ ነው አላማዬ።
... ታላቅ እህቴ በአካውንቲንግ ተመርቃ የባንክ ሰራተኛ ስትሆን ወንድሜ ደግሞ በህክምና ተመርቆ ጻውሎስ ሆስፒታል ሜዲካል ዶክተር ነው።
...የሁለቱም ህይወት አያስደስተኝም። በርግጥ ለራሳቸው ጥሩ ህይወት ይኖራሉ። እኛንም በተወሰነ ሊረዱን ይችላሉ ግን ከዚህ ያለፈ ምንም ነገር ማድረግ ስላልቻሉ ይመስለኛል አጥጋቢ መስሎ ያልተሰማኝ።
...ዲግሪ መሳርያ ነው ብዬ አምናለሁ። ዲግሪአችንን ተጠቅመን የምንፈልገው ነገር ላይ መተኮስ እንዳለብን እንጂ ዲግሪያችን ወደፈለገው እንዲተኩስ መፍቀድ እንደሌለብን ይሰማኛል። የእነሱ ዲግሪ ታድያ እነሱ በፈለጉት ሳይሆን ዲግሪያቸው ወደፈለገው የሚተኩስ ይመስለኛል።
ከብዷቸው ይሆን?..እንጃ...
ወንድሜ የዶክትሬት ዲግሪው የሚተኩሰው ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ እንጂ ሌላ የትም አይደል። ከጻውሎስ ሲወጣ የተፋለመበትን ዲግሪ እና የመመርመርያ መሳሪያዎቹን አስቀምጦ ባዶ እጁን ወደ ቤቱ ሲመጣ መንገድ ላይ እንኳ እንደ ተራ ሰው ነው የሚታየው። ባዶ እጁን ነዋ!.. ለራሱ ብቻ እሚፋለም ምስኪን ወታደር።
እህቴም ብትሆን በተመሳሳይ። ዲግሪዋ ከባንክ ውጪ እማያስተኩሳት ልክ እንደ ቆመህ ጠብቀኝ አይነት ነገር።
እስክመረቅ እዛው..!
...የኔ ዲግሪ ታድያ እኔ የምፈልግበት ቦታ ሁሉ የምተኩስበት እንዲሆን ነው ማልመው።
መንገድ ላይ እየሄድኩ እንኳ ሰዎች እንዳዩኝ "..አስተኩሽኝ.." እንዲሉኝ።
እናም ደግሞ ለቤተሰቦቼም ከወንድሜና እህቴ በተሻለ ጥሩ ቦታ እንደምደርስ ማሳየት የምችል እና ማህበረሰቡንም የተሻለ ኑሮ እንዲኖር ማስቻል ነው ህልሜ። ታሪክ ሆኜ ታሪክ መስራት።
ሰው ተምሮ ማህበሰሰቡን ካልጠቀመ ምኑን ተማረው? ለራስ ለራስማ መማርም አይጠበቅ እኮ። ሳይማሩስ ይኖር የለ እንዴ? ለሰው ላይተርፉ መማር ጊዜ ማቃጠል እኮ ነው ትርፉ። ከንቱነት።
...ቤተ መጻህፍት ቁጭ ብዬ ለማህበረሰቡ መጥቀሚያ መሳሪያነት የሚጠቅመኝን ዲግሪ ሳስበው ታድያ ጋዜጠኝነት የመጀመርያው መንገድ ይመስለኛል። በሚድያ በኩል የተሻለ ስራ እንደሚሰራ ስለማስብ ጋዜጠኝነት ደግሞ ትምህርቱ የተሻለ ግንዛቤን ያስጨብጣል። ከማህበረሰቡ ጋርም በደምብ ሊያግባባኝ የሚችል እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ እንድገባ የሚያደርገኝ ሙያ ጋዜጠኝነት ነው። ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ ግን ህዝቤ ሚድያው ላይ ትኩረቱ ስለተሳበ እድሉ ያመዘነ ነው።
... እንዲህ አይነቱን ሀሳብ እያሰብኩ እና የተወሰነም እያነበብኩ ከቆየሁ በኋላ ከቤተ መጻሕፍት ስወጣ ጋሽ መብራቱ ተገርመው እያዩኝ
"...ልጄ!.. እስካሁን እዚው ነሽ?.." ይሉኛል።
ፈገግ እያልኩ ራሴን እነቀንቃለሁ።
"...ታሪክን የመሰለች ብርቱ ሴት የወለደች እናት እንዴት ታደለች?.."
እያሉ በሩን ይከፍቱልኛል።
ወጥቼ ስሄድ ከኋላ በሩ ሲዘጋ ይሰማኛል።
ቅጭል... ቅጭል የሚል የቁልፍ ድምጽ....
...የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና እየተፈተንን ታድያ የመጀመርያዎቹ ሁለት ፈተናዎች በሰላም እንዳለፉ አስታውሳለሁ።
ልክ ጂኦግራፊ እየተፈተንን... ገና እንደጀመርኩ ሃሳቤ ተሰረቀ።
ትኩረት እያጣሁ እንደመጣሁ ይሰማኛል።
ድንገተኛ ሀሳብ ወስዶኝ ስለ ጥበቃው ወሬ ማሰብ ጀመርኩ። እንደዛ ቤተ መጻህፍት ስመላለስ እያየኝ አይበለውና ድንገት ብወድቅ ምን ይል ይሆን? እሚል ሀሳብ ረበሸኝ። ምንም መስራት አልቻልኩም።
ስለ ቤተሰቤ፣ ስለ ማህበረ ሰቡ ስለ ወደፊቴ... ማሰብ እንደጀመርኩ ትዝ ይለኛል።
ትንሽ ቆይቶ ብዥታ አይነት ነገር...
ምን እየሆንኩ ነው?...
https://t.me/Oct13wed
194
https://t.me/Oct13wed
...ግልብጥ ሳደርገው ግን ባዶ ወረቀት።
አላመንኩም።
መናን ጠየቅኋት
"ይህችን ልጅ ታውቂያታለሽ?" ብዬ ፎቶውን ሰጠኋት።
"እስራ ምን ሆነህ ነው ባዶ ወረቀት እኮ ነው!"
ግራ ገብቷት ታየኛለች።
ትንሽ ቆም አልኩና እጇን ይዤ ወደ ግሮሰሪዋ አመራን።
ግራ ገብቷት ብዙ የማያልቁ ጥያቄዎችን ታከታትላለች።
ምን አለ እኔንም ግራ እንደገባኝ ብትረዳ።
ገብተን ከመቀመጣችን ደብል ጂን አዘዝኩኝ።
ገና ከመቀዳቱ ጭልጥ...
''ድገሚኝ"
አስተናጋጇ ደነገጠች።
አዝዤ ሳልጠጣው ከፍዬ የምወጣ ልጅ ድንገት ስጨልጥ እንዴት አትደነግጥ?!
መና አሁንም እንዳፈጠጠችብኝ ነው ምኑም አልገባት።
....የያዝኩትን ጂን እያጣጣምኩ
''ተቀበል..." አልኩ ጮክ ብዬ።
ገርሞት አየኝና ተቀበለኝ
''ታፈጫለሽ አሉ ደሞ አይን እንዳለው!"
"ድገመው "
"ብታዪም ባታዪም ዛሬስ ቆርጫለሁ"
... ሰው ሁሉ ግራ ገብቶት ያየኛል።
የኔ ግራ መጋባት እንደባሰ ማን በነገራቸው።
https://t.me/Oct13wed
