SU|ኤስዩ
前往频道在 Telegram
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።
显示更多未指定国家未指定类别
672
订阅者
+324 小时
+57 天
+330 天
帖子存档
674
#ተጠናቋል
#የደቡብ_ምስራቅ_ኤስዩ #ሐዋሳ
----- ------ ------
ከማክሰኞ እስከ ዓርብ (20—23/2017ዓ.ም) ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ምስራቅ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ የመለስተኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት የፌሎሽፕ መሪዎች ጉባኤ ትላንት ምሽት ፍፃሜውን አግኝቷል።
ከቦረና ፣ ከጉጂ፣ ከባሌ፣ ከጌዲዮ፣ ከአርሲ፣ ከባሌ እና ከመሳሰሉት የዞን ከተሞች እና በሲዳማ ክልል በሐዋሳና ዙሪያው ከሚገኙ ዞኖችና ልዩ ልዩ ከተሞች የተወጣጡ የፌሎሽፕ መሪ የሆኑ ተማሪዎች ተካፋዮች ሆነዋል።
በሕይወት ለዋጩ የእግዚአብሔር ቃል ዙሪያ በግልና በጋራ ተሰባስበናል። የዘፍጥረትን መጽሐፍ አጥንተናል። የእግዚአብሔርን ለኪዳኑ ታማኝ መሆን፣ መንገዱን ለሚከተሉ ያለውን ተስፋና እረፍት ተመልክተናል።
በሴሚናር መርሐ ግብር ለመሪዎች የግል ሕይወትና ለፌሎሽፕ አገልግሎት የሚጠቅሙ ርዕሰ ጉዳዮች ተዳሰዋል።
በየከተሞቹ እግዚአብሔር በተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት የሰራቸውን ድንቅ ታሪኮች ከመሪዎች ሰምተናል። በሰማናቸው አንዳንድ ተግዳሮቶች ዙሪያ በእግዚአብሔር ፊት ፀልየናል።
አስደናቂ የእርስ በርስ ሕብረት፣ ልምድ የመለዋወጥ የፀሎት፣ እንዲሁም የምክክር ጊዜያቶችን አሳልፈናል።
ይህ ክልላዊ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን የኤስ.ዩ ደቡብ ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ አገልጋዮች በብዙ ትጋት አገልግለዋል። እግዚአብሔር እነሱን ጨምሮ ለዚህ ጉባኤ መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉትን፣ ሐዋሳ ገነት አጥቢያ ቤ/ክ፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና ግለሰቦች ከልብ እናመሰግናለን። ተባረኩ!
----------------------
#ደቡብ_ምስራቅ_ክልል_ኤስ_ዩ
#ኢየሱስን_የሚከተሉ
#በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ
#ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ
#ክልላዊጉባኤ
#ሐዋሳ
#RHLS_2025
