ወደ ኢየሱስ ደረት
前往频道在 Telegram
Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.
显示更多未指定国家未指定类别
276
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-530 天
帖子存档
276
' 2 ጢሞቴዎስ 1:6 - ስለዚህ በእጆቼ መጫን የተቀበልኸውን በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታቀጣጥል አሳስብሃለሁ፤' ማቀጣጠል ፤መቀጣጠል ጳውሎስ መንፈሳዊ ልጁ የሆነውን ጢሞቲዮስን (2ጢሞ 1:6)እንዲህ ይለዋል ለቤተክርስቲያን መሪ እንድትሆን እጅ በመጫን የተቀበልከውን የእግዚአብሔርን ስጦታ አቀጣጥል ይለዋል። ➡በውስጣችን ያለው ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ስጦታ ዕለት ዕለት መቀጣጠል አለበት ይህን ሀሳብ ነው የሚለው ጳውሎስ.... 🔑ማቀጣጠል🔒? ማቀጣጠል :እየነደደ ያለ እሳት እንዳለ እንዲቀጣጠልም ለዕሳቱ የሚመቸውን ነገር እየጨመርን/ሊያጠፋው የሚችለውን ነገር እያራቅን....እንደምናቀጣጥል፣ ያ ሚታየው ዕሳት እንዳይጠፋ ብዙ እንደምናደርግለት እንደዚያው፣ ለማይታየው ለውስጣችንም ዕሳት like that የምናደርገው ነገር ስለዚህ እንድንቀጣጠል የሚያደርጉንን ነገር በማድረግ መራቅ ካሉብን ነገር በመራቅ ማቀጣጠል ከዚያ መቀጣጠል........ በውስጣችን ያለው እሳት እንዲቀጣጠል ከእኛ ምን ይጠበቃል፦ #ንስሀ ያልተገባበት ሀጥያት ካለ ንስሀ በመግባት #በመስማት እና በማየት ወደ ውስጣችን የሚገቡ ነገሮችን መጠንቀቅ #ውሎን ማስተካከል #በቃል እና በፀሎት ህይወት መቆየት #እያንዳንዱን ነገር እንደ እግ/ር ቃል መመርመር #ለመንፈሳዊነት ከማይመች ጓደኛ በመራቅ
276
'
2 ጢሞቴዎስ 1:6 -
ስለዚህ በእጆቼ መጫን የተቀበልኸውን በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታቀጣጥል አሳስብሃለሁ፤'
ማቀጣጠል ፤መቀጣጠል
ጳውሎስ መንፈሳዊ ልጁ የሆነውን ጢሞቲዮስን (2ጢሞ 1:6)እንዲህ ይለዋል ለቤተክርስቲያን መሪ እንድትሆን እጅ በመጫን የተቀበልከውን የእግዚአብሔርን ስጦታ አቀጣጥል ይለዋል።
➡በውስጣችን ያለው ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ስጦታ ዕለት ዕለት መቀጣጠል አለበት ይህን ሀሳብ ነው የሚለው ጳውሎስ....
🔑ማቀጣጠል🔒?
ማቀጣጠል :እየነደደ ያለ እሳት እንዳለ እንዲቀጣጠልም ለዕሳቱ የሚመቸውን ነገር እየጨመርን/ሊያጠፋው የሚችለውን ነገር እያራቅን....እንደምናቀጣጥል፣ ያ ሚታየው ዕሳት እንዳይጠፋ ብዙ እንደምናደርግለት እንደዚያው፣ ለማይታየው ለውስጣችንም ዕሳት like that የምናደርገው ነገር ስለዚህ እንድንቀጣጠል የሚያደርጉንን ነገር በማድረግ መራቅ ካሉብን ነገር በመራቅ ማቀጣጠል ከዚያ መቀጣጠል........
በውስጣችን ያለው እሳት እንዲቀጣጠል ከእኛ ምን ይጠበቃል፦
#ንስሀ ያልተገባበት ሀጥያት ካለ ንስሀ በመግባት
#በመስማት እና በማየት ወደ ውስጣችን የሚገቡ ነገሮችን መጠንቀቅ
#ውሎን ማስተካከል
#በቃል እና በፀሎት ህይወት መቆየት
#እያንዳንዱን ነገር እንደ እግ/ር ቃል መመርመር
#ለመንፈሳዊነት ከማይመች ጓደኛ በመራቅ
መልካም ቀን✋
276
አስመሳይ ነን
ማን ያውቀዋል ውስጣችንን፣
በ በኖራ የተለሰነውን፣ ሬሳችንን
አደባባይ እየወጣን፣ ልናገኝ እውቅናን
ናቸው ለመባል፣ አንተን አደበዘዝን
ከሰው አይነን ለመግባት፣
ተቀብተን አመድን
የሌለንን ፀሎት፣ ቀጣጥለን እየፀለይን
ጭብጨባ እንዲበዛል፣ ተመናፍሰን
ኧረ ስንቱን አደረግን፣ አስመስለን
ጉዱ እየወጣነው እኛም፣ ደነገጥን
የኛ ያልሆነውን፣ ማንነትን ይዘን
ያደረግነው ጭንብል፣ እንዳይገፈፍ ተሳቀን
ይኸው አሁንም አለን፣ ምህረቱ ገኖልን
የምልኮመንፈስ ያለን፣ የምንመስል
ግን የሰማይ ሀይል፣ የሌለን የደረቅን
እረ እኛስ በቃን ፣አስመስለን ጨረስን
አይ ደንዳና ልብ፣ መች ተምሮ
አሁንም ያስመስላለ ፣በአምላኩ ፊትደማምሮ
አሁንስ አምላክ ሆይ፣ ዝምታህስ በዛ
ቆይተህ ቆይተህ፣ በመአት እንዳትመጣ
አሁን መልሰን፣ ወደ ማንነታችን
እያስመሰልን፣ ወደ ጋሀነም እንዳንገባ
መምሰል ካልቀረ፣ ልጅህን
ማድመቅ ካልቀረ፣ የተሰቀለውን
እባክህ ጌታ ሆይ፣ አንተን ወደመምሰል
ውብ ወደ ሆነው ማንነት፣ አሳድገን
የተጠራንበትን ፣የምንኖርበትን
አዓላም ሳንረሳ ፣በድል መንገድ ምራን
✍አስመሳይዋ🥹
276
ውሸታም
መች ሆነ ለልቤ የነገርከኝ
ይሆናል ብለህ የማልክልኝ
ቀርብ ነው ብለህ የጠቆምከኝ
*
*
*
አልልህም እንደዚያ አገቴን አግጥጬ
ወገቤን በልበ ጽናት አስሬ
*
*
ነብሴ ሆይ እርሱ ውሸታም አደለም
ቃሉን ሊፈፅም ሲጠጋሽ አልተመቸሽለትም
ስንፍና ይዞሽ ከተስፋው እንዳትሆኚ
ጠፍሎጎ ይዞሽ እንዳትቀላጠፊ
በጭፍን ሚሆን መስሎሽ ስትሞኚ
በቃ
እርሱ ውሸታም ብለሽ እራስሽን አታሳምኚ
ካንቺም ይጠበቃል ለቃልኪዳኑ ታመኚ
276
ይሁዳ 1÷24 ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፥ለእየሱስ ክብር ይሁንለት👏👏🙏🔥
276
Repost from N/a
አገር አለን
እንደ ዥዋዥዌ ሕይወት፣ ወዲህ ወዲያ፤
ከንቅልፍ እንደ ነቃን፣ እረፍት የለም፣ ጥድፊያ።
አንዱን መለስኩ ስንል፣ አሥር ነው ጠያቂ፤
መች ነው የምናርፈው? ስንትስ ይሆን በቂ?
ብንዋደድ፣ ዛሬ ልዩነት ይመጣል፤
እየሳቅን ውለን፣ ለቅሶ ይቀጥላል።
ደስ ቢለን እንኳን፣ ጭንቀት ያጠቃናል፤
ተስፋ ብኖረንም፣ እምነት ይጎለናል።
እረፍት መች ይገኛል? ዓለም የት ይመቻል?
ሁሉ ጎዶሎ ነው፤ ኑሮ ይሰለቻል።
ሰርተን፣ ጥረን፣ ግረን፣ ተሯርጠን ቀን ማታ፤
ጥቂት ነገር ይዘን፣ ደላን ስንል ላፍታ።
ደግሞ ማጣት አለ፤ ይመጣል ኪሳራው፤
ብልጭ ያለችውን ሳቅ፣ ይነሳል በተራው።
ያጀበ ስበተን፣ "ዋናው ጤና!" ብለን፤
ለጤናውም ለመብላት፣ እንጨነቃለን።
ብቻ እሱም ይገኝ፤
በሰለ፣ አረረ፣ ጣፈጠ፣ መረረ፤
ለአንጀት ነው ሩጫ፤ አሁን ሁሉ ቀረ።
ለምነንም እንብላ፤ አዎ፣ ዋናው ጤና፤
ስንል ያስጨንቃል፤ እርሱም ይጎልና።
ደግሞ አመዛዝነን፣ ከመቃብሩ ጋር፤
"ይሻላል!" እያልን፣ ከሚበቅልብን ሳር።
መኖር ይበቃናል ብለን፣ ስንፅናና፤
ሥጋ እንደ ሣር ነው፤ መሞትም አለና።
ሁልጊዜ ሩጫ ላይ፣ እያለከለክን፤
እፎይ ሳንል፣ ከአፈር እንመለሳለን።
ዓለም ማለት ይህ ነው፤ ጠቅለል አድርገን ስናይ፤
ማን ለፍቶ ረካበት? አትርፍ ባይ፣ አጉዳይ።
ምንም በቂ የለም፤
ምንም ሙሉ የለም፣ በዚህች ምድር ላይ።
ዓለም አታላይ ነች፤ አጥፍታ የምትጠፋ።
በቂ ኢየሱስ ነው፤ አስተማማኝ ተስፋ።
ታዲያ...
በኢየሱስ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግረን፤
ድነናል እያልን፣ ቀን ሌሊት ዘምረን።
የሚናዝን ከሆነ፣ በክርስቶስ አምነን፤
እኛን ከአለመኞች፣ ታዲያ ምኑ ለየን?
እኛስ እንፅናና፤ ይብላኝ ለእነሱ፤
ኢየሱስ እንዲያድን፣ ያላመኑ በእርሱ።
ሁለት ሞት የሞቱ፣ ዳግም የማይነሱ፤
ተስፋ የሌላቸው፣ እነዚያስ ያልቅሱ።
ምንም እንኳን፣ ምንም ቢያልፍ እንደ ዋዛ፤
የምድር ላይ ሕይወት፣ እንኬኑ ቢበዛ።
ስለ ምን እንቆዝም? ለምን እናዝናለን?
ይሄኛው ዓለም ሲያልፍ፣ እኛስ አገር አለን።
አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፣ ቅድስት ከተማ፤
ተዘጋጅታ ከላይ፣ ስትወርድ ተሸልማ።
እነሆ፣ እዚያ ነው አገራችን፣ እኛ፤
ያኔ እንሆናለን፣ ፍጹም ደስተኛ።
እዚያ ከቶ የለም፤ ሰኞና ቅዳሜ፣
መስከረምና ጥር፣ ነሐሴና ጳጉሜ።
የሰዓት ቁጥጥር፣ ማርፈድ በቀጠሮ፣
ፊት አይቶ መጣደፍ፣ ፀፀት ኋላ ዞሮ።
እዚያ ከቶ የለም፤ ክረምትና በጋ፣
የአየር ንብረት፣ ቆላ ወይና ደጋ።
መዝራትና ማጨድ፣ ፀሐይና ዝናቡ፤
ስለ ወቅት ማማረር፣ መስኖና ግድቡ።
እዚያ ከቶ የለም፤ ቱታ ለብሶ ሥራ፣
ወጪ ገቢ ድምር፣ ትርፍ እና ኪሳራ።
የኑሮ ውድነት፣ በገጠር ከተማ፣
ከነጋዴዎች ዱቤ፣ ከመንግሥት ድጎማ።
እዚያ ከቶ የለም፤ ገባሪና ቀራጭ፣
ነጋዴና ሸማች፣ ተሿሚና መራጭ።
ተጓዥና መንገድ፣ ድልድይና ኬላ፣
ማስመጣት ወይ መላክ፣ አሻሻጭ ደላላ።
እዚያ ከቶ የለም፤ መምህር ወይ ተማሪ፣
ጡረተኛ፣ ሥራ አጥ፣ ሠራተኛ ዟሪ።
ሰነፍና ልባም፣ መሪና ተመሪ፤
ባለቅኔዎች እንጂ፣ ሁሉ ሰው ዘማሪ።
እዚያ ከቶ የለም፤ የውጭ የውስጥ ዜጋ፣
እርስ በርስ ልዩነት፣ በቀለም በሥጋ።
ፈረንጅ ወይም ሀበሻ፣ ዘር፣ ጎሳና ብሔር፤
ኢየሩሳሌም ነች፣ የሁላችን ሀገር።
እዚያ ከቶ የለም፤ ቤተሰብና ቤት፣
የአባትነት ድርሻ፣ ፍቅር የእናትነት።
ጎጆ ተቀልሶ፣ በልጅ መደራጀት፤
አምልኮ ብቻ ነው፣ የሁሉ ኃላፊነት።
እዚያ ከቶ የለም፤ ሕመም ወይም በሽታ፣
ሐዘንና ትካዜ፣ ለቅሶና ዋይታ።
ተስፋ መቁረጥ፣ ሆነ በተስፋ መጠበቅ፤
የሐሳብ ውጣ ውረድ፣ ስጋት ወይም መጨነቅ።
እዚያ ከቶ የለም፤ ኃጢአት ወይም ስንፍና፣
የጸሎት ንትርክ፣ ወይም ደግሞ ፈተና።
ሕልውናውን መናፈቅ፣ መሻት እንደ ዋላ፤
እንባችን ታብሷል፤ የለም ያልተሟላ።
የእግዚአብሔር ድንኳን፣ በሰው መሀል ነውና፤
ሁሉ አዲስ ይሆናል፤ አሮጌው ያልፍና።
ሁሉን የሚገዛ፣
ጌታ አምላክና በጉ ያበራሉ፤
ፀሐይና ጨረቃ፣
ከእንግዲህ አይታዩም፤ ያኔ ይጠፋሉ።
የሕይወት ውኃ ወንዝ፣
ከዙፋኑ ሲፈስ፣ ከእግዚአብሔር ስፍራ፤
ከዳሩ ያለው ዛፍ፣
በወር ሳያቋርጥ፣ ፍሬ እያፈራ።
ከዚያ እየበላን፣
ከዚያ እየጠጣን፣ መኖር ነው ዘላለም፤
ከቶ አንራብም፣
ከቶ አንጠማም፣ ያኔ በኢየሩሳሌም።
የጠበቅነውን ጌታ፣ ፊት ለፊት እያየን፤
ምርኮ ሲካፈሉ፣
ደስ እንደሚላቸው፣ እኛም ደስ እያለን።
የምንኖርበት እኛስ አገር አለን፤
በደስታ፣ በሐሴት፣
እስከዘለዓለም እዚያ እንኖራለን።
✍Alazer Teshome
276
ሙሴ እንዲህ አለ፦
በዘፀአት 33:15
ፊትህ ሀለዎትህ ከእኛ ጋር ካልወጣ አታውጣን ምንም በዳዮች ብንሆን ግን በመልአክ አብሮነት ግን የሚለይ/የሚደሰት ማንነት የለንም ያላይተ ከወጣን ከነአን ለእኛ ምንም ነው ከአንተ አብሮነት ጋር ምድረበዳ ገነት ነው እይዳለ፥ ሙሴ የእግ/ር አብሮነት ምን ያክል ህይወት እንደሆነ ስለ ኖረው ያውቀዋልና ዛሬም በውሎዋችን የእግ/ር አብሮነት ሊሰማን ይገባል እርሱ ካልወጣ አንወጣም!
የእግ/ር ህልውና መገኘቱ በውሎዋችሁ ይሰማችው የቀልድ ጉዳይ አደለም የህይወት ጉዳይ እንጂ!
276
Repost from አዶናይ
የ 1 ቀን መጠጥ ለ 1 ቀን ብቻ ነው የሚያሰክረው
መጠጥ የሚጠጣ ሰው የሚሰክረው በጠጣው ልክ ነው፤ ለአንድ ቀን
የጠጣው መጠጥ ሳምንቱን ሙሉ አያሰክረውም በየቀኑ ለመስከር በየቀኑ መጠጣት ይኖርበታል፤ መንፈስ ቅዱስም ልክ እንዲሁ ነው አንዴ በመንፈስ ተሞልታቹ ሳምንቱ ሙሉ ሳትፀልዩ ሳምንቱን ሙሉ በመንፈስ መቀጣጠል አትችሉም ዘውትር በመንፈስ ለመስከር ዘውትር በፀሎት መትጋት ይኖርባቿል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost276
እናንተ እግ/ር ግን እንደት መልካም ነው ሁል ጊዜም ልባችን እንዳያዝን ሁሌ ለምነነውም ከእጁ ፤ፈልገነውንም እርሱን ይሰጠናል።ይህ እግ/ር አልችልም አላውቅም የሚሉ ስንፍናዎች የማያውቁት በሁሉ ባለጠጋ የሚስተካከለው የሌለው አምላክ ነው።
ግን እግ/ር በእውነቱ ስለ እኛ ደስታ ሲል ብቻ እርሱ ያልተደሰተበትን ነገር ምንም አይስጠን🙌 ስንቀበልም ሲደረግልንም ከእርሱ ደስታ ጋር ይሁንልን ሁሉም ነገር ከፈግታው ጋር ይጣፍጣል
ስኬት ሲገናኘን እውቅና ሲመጣ እግ/ር ሆይ ያንተ ደስታ አለበት ወይ ብለን መጠየቅ ይህ የልጅ ተግባር ነውና።
