fezekir
الذهاب إلى القناة على Telegram
710
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-730 أيام
أرشيف المشاركات
710
Repost from tezkir channel
🌿🌿🌿الله🌿🌿🌿
✅ ምን አይነት ጌታ ነው ያለን፤ ለፍጥረቱ ሁሉ ተንከባካቢ የሆነ ጌታ፤ፍጡሯን ሁሉ የሚረዝቅ። ሀራም የሆኑ ነገራት ሲከለክል በተቃራኒው ደግሞ ለኛ የሚጠቅም ነገር ሐላል አደረገልን። ወለድ ለሰው ልጅ ስለሚጎዳ ሀራም ሲያደርገው በምትኩ ማንንም ሊጎዳ የማይችል መበዳደርን ፈቀደ ታበድራለህ ተበዳሪውን ትጠቅማለህ ከጌታህም አጅር ታገኛለህ። ንግድን ፈቀደ ትሸጣለህ ታተርፋለህ።
👉 ዚናን ሲከለል ኒካህ ፈቀደ።
- በዚና ዝርያን ሲበላሽ፤ የአባትና የልጅ ዝምድናን ሲቋረጥ፤የዲቃላ ልጅ ሲባል።
- ኒካህ ደግሞ ዝርያን ሲያሳምር፤ዝምድናው በአባትና በልጅ የሚገደብ ሳይሆን ከእናቱ ቤተሰብ ከአባቱ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ያዘማምዳል።
👉 ወጣቶች ሆይ በአሏህ ተመክታቹ ኒካህ ድፈሩ ከሐራም ግኑኝነት ራቁ።
وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا
✅ የሚያከብርሽ ወንድ የራሱም ክብርና ልቅና የሚፈልግ ወንድ በሐላሉ ይፈልግሽ የሐራም በር ዝጊበት ሐላሉን ክፈችለት ልቅና ክብር የምታገኚበትን።ጉዳያቹ ወደ አሏህ አስጠጉ።
✅ በሀላል መብቃቃት የነፍስ መረጋጋት የሪዝቅ መስፋት ሰበብ ሲሆን በአኼራም ትርፋማ ያደርጋል። ሐራም ደግሞ በተቃራኒው የነፍስ ባዶነት፤የሪዝቅ መጥበብ ሰበብ ሲሆን በአኼራ ለኪሳራ ይዳርጋል።
https://t.me/tezkirr_channel
https://t.me/tezkirr_channel
710
Repost from ስለ ቀልባችን
ኢላሂ...
እግሬ ወደ ወንጀል ሲያመራ መንገዱን ዝጋብኝ፤ ልቤ ጥፋትን ባሰበ ጊዜ አታሳካልኝ፤ ከውድቀቴም ጠብቀኝ።
አይኖቼን ከሀራም እይታ፣ ልቤንም ካልተፈቀደ ምኞት በብርሃንህ ጋርድልኝ።
ጌታዬ ሆይ...
በስህተቴ ብዛት፣ በድካሜም ክምችት ሪዝቄን አታጥብብኝ፤ በርህራሄህ እንጂ በስራዬ አትመልከተኝ።
የኔ ጌታ እኔኮ ወንጀል ስሰራ ያንተን ሀያልነት፣ አዋቂነትና ታላቅነት ዘንግቼ አይደለም፤ በፍጹም!
ደካማይቱ ነፍሴ ተሸንፋ፣ የሸይጧን ወጥመድ በርትቶብኝ እንጂ።
ያ ረብ... እኔ አቅም የሌለኝ ባሪያህ ነኝና፣ በይቅርታህ እለፈኝ!!
t.me/Sle_qelbachn1
710
🌿🌿🌿ሞባይሌ🌿🌿🌿
ሰብሬ እንዳልጥልህ ውለታህ አለብኝ
እውቀትን ለማግኘት ሰበብ የሆንከኝ
የአንድ ቀን ጥፋትህ ወደ ኋላ አስቀረኝ።
ጥፋቱ የኔ ነው ያንተ ግን አይደለም
ወንጀሉም የኔ ነው ያንተማ አይደለም።
አዎ ሞባይል ስልክ ላወቀው ፀጋ ነው
ላላወቀበት ሰው ትልቅ ሙሲባ ነው።
ጣትህ ስታሰርፍ ወዴት ነው የሚነካው
ወደ ቲክቶክ መንደር ወደ ወንጀል ተራ
ወይስ ኡለማዎች ዘንድ ወደ እውቀት ጎራ።
ወይስ ይወስደሃል አጅነብዮች ተራ
ሊወስድህ ሲፈልግ ኢብሊስ በየተራ
ነፍሴን ጠብቅልኝ አሏህ ሆይ አደራ።
https://t.me/mbfezekir
https://t.me/mbfezekir
710
🌻
ምርጥ እንስት!
ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦
«ከሴቶች ምርጥ ማለት ጥሩ መዓዛ እና ምርጥ የምግብ አሰራር ሙያ ያላት። ወጪ ቆጣቢ እና አግባብ ባለው ቦታ እና ጊዜ የምትቆጥብ ናት። ይህች እንስት ከአላህ ሰራተኞች(ሞግዚት) አንዷ ናት። የአላህ ሰራተኛ ደግሞ ጥረቱ ባክኖ በከንቱ አይቀርም»
በህጀቱል መጃሊስ (33–34)710
Repost from Abdur-Razzaq|Al-Habeshi
ለመሆኑ ማግባት ማለት የኪስ መንጠፍ፣ የጉልበት መድከም፣ የድህነትና የችግር መጥሪያ ይመስልሃልን? በፍጹም አይደለም! ይልቁንስ አንተ በቅን ልቦናና በሃላፊነት የጋብቻን ደጅ ስታንኳኳ፣ ያ ፈጣሪ ደግሞ ላንተና ለቤተሰብህ የሚሆን የሲሳይንና የበረከትን ትልቅ በር ወገግ አድርጎ ይከፍትልሃል።
እስኪ በጥልቀት አስተውለው፤ ወደ ቤትህ የምታስገባት ያቺ ሙሽራ እኮ ያንተን ጥቂት እንጀራ ልትጋራ፣ ኪስህን ልታጎድል አትመጣም። ይልቁንስ አምላክ ለሷ የጻፈላትን፣ ከሰማይ የወረደውን የራሷን አዲስ ርዝቅና በረከት ይዛ ነው ወደ ቤትህ የምትገባው!
ብቸኝነት ያረከሰውና ያበላሸው ጥረትህ፣ በጋብቻ ቅዱስ ማዕሰር ሲታሰር ሙሉነትን ያገኛል። ወንድ ልጅ ባገባ ጊዜ ወገቡን አጥብቆ የመስራት ወኔው ይነሳሳል፤ አእምሮው ይረጋጋል፤ ቤቱም በፍቅር፣ በሰላምና በበረከት ይሞላል። ጋብቻ የድህነት ምክንያት ሳይሆን፣ ለሀብትና ለብልጽግና መከፈቻ የሆነ የጸጋ ቁልፍ ነው!
ስለዚህ ያን የፍርሃትና የጥርጣሬ አረንቋ አራግፈህ ጣለው። በፈጣሪህ ቸርነት ላይ ሙሉ እምነት ይኑርህ፤ ወኔህን አዘጋጅተህ የፍቅርን መንገድ ተከተል ... ሲሳይማ አጅባህ በእግረ-መንገዷ ትከተልሃለች!
https://t.me/abdurezaq27
710
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
በነገራቹህ ላይ "አህሉል አሠር" የተሰኘው አፕ አንዴ የተጫነ የደርስ ስብስብ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በአቡ ዒምራን የቀረቡ ሙሉ የደርስ ስብስቦች የሚገኙበትና በየቀኑ በሁለቱ የቴሌግራም ግሩፖች ማለትም፦ በ"በአህሉል አሠር" እና በ"መድረሰቱ ዒልሚል ዓረቢያ" የሚሰጡት ደርሶች የሚለቀቁበት ህያው መተግበሪያ ነው።
አፑ ለመማር እጅግ በጣም አመች በሆነና ቀለል ባለ ጥንቅር የተዘጋጀ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን ደርስ ካጠናቀቁ በኋላ "ይህንን ትምህርት ምን ያክል ተገንዝቤዋለሁ?" የሚለውን ለመገምገም ያመች ዘንድ ከደርሱ መጨረሻ ክፍል ቀጥሎ ከኪታቡ የተውጣጡ ፈተናዎች ይገኛሉ። ፈተናውን ሰርተው ካጠናቀቁ በኋላ ከአፑ እራስጌ በአረንጓዴ ቀለም "ገምግም" የሚለውን በመጫን የፈተና ውጤትዎን ማየት ይችላሉ።
አፑን ለማውረድ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahlulaser.hs.app
