ሐሳቦቻችን
الذهاب إلى القناة على Telegram
በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን! ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb
إظهار المزيدEthiopia13 750الفئة غير محددة
983
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
+130 أيام
جارٍ تحميل البيانات
القنوات المماثلة
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
أكتوبر '26أكتوبر '26
أكتوبر '26
+6
في 0 قنوات
سبتمبر '26
+19
في 3 قنوات
Get PRO
أغسطس '26
+8
في 1 قنوات
Get PRO
يوليو '26
+37
في 1 قنوات
Get PRO
يونيو '26
+43
في 3 قنوات
Get PRO
مايو '26
+5
في 1 قنوات
Get PRO
أبريل '26
+8
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '26
+15
في 3 قنوات
Get PRO
فبراير '26
+11
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '26
+14
في 1 قنوات
Get PRO
ديسمبر '25
+33
في 2 قنوات
Get PRO
نوفمبر '25
+31
في 5 قنوات
Get PRO
أكتوبر '25
+17
في 1 قنوات
Get PRO
سبتمبر '25
+28
في 1 قنوات
Get PRO
أغسطس '25
+85
في 1 قنوات
Get PRO
يوليو '25
+122
في 1 قنوات
Get PRO
يونيو '25
+52
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '25
+686
في 8 قنوات
Get PRO
أبريل '250
في 2 قنوات
Get PRO
مارس '25
+142
في 0 قنوات
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 21 أكتوبر | 0 | |||
| 20 أكتوبر | 0 | |||
| 19 أكتوبر | 0 | |||
| 18 أكتوبر | 0 | |||
| 17 أكتوبر | 0 | |||
| 16 أكتوبر | 0 | |||
| 15 أكتوبر | +1 | |||
| 14 أكتوبر | +3 | |||
| 13 أكتوبر | 0 | |||
| 12 أكتوبر | +1 | |||
| 11 أكتوبر | 0 | |||
| 10 أكتوبر | 0 | |||
| 09 أكتوبر | 0 | |||
| 08 أكتوبر | 0 | |||
| 07 أكتوبر | 0 | |||
| 06 أكتوبر | 0 | |||
| 05 أكتوبر | 0 | |||
| 04 أكتوبر | 0 | |||
| 03 أكتوبر | 0 | |||
| 02 أكتوبر | 0 | |||
| 01 أكتوبر | +1 |
منشورات القناة
ቡናን ለመጀመሪያ ጊዜ ፍየል ማግኘቱ ወይ መቅመሱ አያስገርምም። ይልቅ ከፍየሏ ቀጥሎ ለመሞከር የተነሳበትን የዛን እረኛ ብርታትና የማወቅ ጉጉት ስነ ልቦና ነው የሚደንቀኝ።
@ourrthought
| 2 | Avatar
Avatar የሚለውን የ James Cameron ፊልም በጣም ከምወዳቸው ፊልሞች ውስጥ የምመድበው ነው። ፊልሙ የሚነግረን ብዙ ነገር ሳይወሳሰብ እንድናስተውል እና ስለ ሰው ልጅ የ አኗኗርና ዝግመተ ለውጥ ሂደት ይዘግብልናል።
ፊልሙ በዋናነት ጭብጡን ያደረገው ስለ ሰው ልጅና ስለ ሌላው አለም ግንኙነት ፣ ከተፈጥሮ ጋር ስላለን ዝምድና ፣ እኛ የተቀረውን አለም የምናይበትና የተቀረው አለም (ኤልየን) እንዴት ይገነዘቡናል? ፣ የቴክኖሎጂ ዝማኔያችንና ተያይዞ የሚመጣው የ አጥፊነት ስነ ልቦናን ይተነትናል።
ዛሬ ፊልሙን ከኔ ትዝብት አንፃር ልተንትነው። Avatar 3 በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ክፍሎች አሉት እና እስኪ ወደ መሬት አውረደነው የአውሮፓ ግንኙነትና የ አፍሪካን እንዳስበት።
Avatar ፊልም ላይ Pandora የምትባል ግዛት ናት። አፊሪቃ በሏት። የተፈጥሮ ሀብት ያላቸው ፣ ከተፈጥሮ ጋር የሚግባቡ ፣ እንስሳቱን በቋንቋቸው የሚያናግሩ ፣ ደስተኛ የሆኑ ንጡል ህዝቦች። የ ሰማይ ሰዎች (አውሮፓ) እስከሚያገኟቸው ድረስ። የ ፓንዶራ ህዝቦች የሰማይ በራሪው ፣ የየብሱ ፣ የባህሩ እንስሳት ሁሉ ልክ እንደ አንድ አባሎቻቸው የሚያይዋቸው እንጂ ለነሱ የተፈጠሩ መገልገያ አድርገው አይቆጥሯቸውም ነበር። ይህ አንዱ የ አፍሪካ ፍልስፍና ውስጥ የሚገኝ ትልቁ መሠረት ነው። ከጥንት አያቶቻቸው ጋር በተፈጥሮ በኩል የሚገናኙ ናቸው። መንፈሳዊነት ዋና መገለጫቸው ነው።
አውሮፓዊ ስልጣኔው በራሱ ከ አፍሪካን ፍልስፍና የተጣረሰ የሆነ ነው። ከተፈጥሮ ጋር ግንኙነት የሌለው አራዊቱ ፣ ደኑ ፣ መላው አለም ለሱ መጠቀሚያነት ብቻ የተፈጠሩለት መገለገያው አድርጎ የሚቆጥር እንጂ ሌላው አለም አራዊቱ ፣ እፅዋቱ ፣ መንፈሳዊነት የሚባል ነገርን የማያውቅ ነው። በቅኝ ግዛት ወደ አፍሪካ ሲመጡ ከበረዙት አንዱ ነገር የተፈጥሮና የሰው ግንኙነትን ነው።
በ Avatar ፊልም ላይ የ sky people (አውሮፓ) ስልጣኔውን በዛ ለመዘርጋትና የተፈጥሮ ሀብቱን ለመጠቀም ኢንደስትሪ ለመገንባትና የምርምር ማዕከሉን በዛ ለማድረግ የሚያደርገውን በዘመናዊ መሳሪያ ተጠቅሞ የ pandoraን ግዛት ሰፍሮበት ይታያል። እንስሳቶቹን ለምርምርና ለገንዘብ ብለው እንደቀልድ ይገላሉ ፣ ደኖቹን ይጨፈጭፋሉ ሁሉንም ነገር በገንዘብ ነው የሚተምኑት። የ አውሮፓ ስነ ልቦና በግልፅ ይታያል። የአፍሪካን የቅኝ ግዛት ታሪኮች ብትመለከቱ ይህን ይገልፅላቹሀል።
የ sky people ከ Pandora ጋር በ 3ቱ ክፍሎች ላይ ብዙ ጦርነቶችን ሲያደርጉ ይታያሉ። የ sky people በየጊዜው ጦራቸውን እያዘመኑ የ pandoran ህዝቦች ሲያጠቁና ሲያጠፏቸው በየጊዜው የሚያደርጉትን መሻሻል ያሳያል። ቋንቋቸውን እየለመዱ ፣ የነሱን የሰውነት ጥንካሬ እየተላበሱ ፣ ከራሳቸው ህዝብ ጎሳዎችን እየመለመሉ አብረው የተቀሩትን ሲያጠቁ ይታያል። ይሄ የአውሮፓን የ ቅኝ ግዛት እና አፍሪካን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በኛ ሀገርም ብዙ የሚጠቀሱ ቋንቋችንን እየለመዱ የገዛ መፅሐፎቻችንን የሚበርዙ የሚዘርፉ የነበሩ ታሪክን ያነበበ የሚያውቀው ነው። ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ።
በዚህ ሁሉ የ Pandora ሀገር የ Na'vi ህዝቦች ምንም የሚያደርጉት መሻሻል የለም። ብረት መንካት ነብስን ያጎድፋል ብለው ስለሚያስቡ የሚዋጉት በአያቶቻቸው ቀስትና ጩቤ ነው። እራሳቸውን ለመንከባከብ ሲዘምኑ አይታይም። በዘመናዊ መሳሪያ እያጠፏቸው ቀያቸውን እየለቀቁ ከመሄድና ከማዘን ውጪ። በዚህ ሁሉ ለ Pandora የሚዋጋው ዘመናዊነትን ለነሱ ለመስጠት የሚሞክረው Jake sully የሚባለው የራሳቸው የ sky people የሆነ ነው። ይሄ ግልፅ ነው የትኛው የ አፍሪካ ሀገር እራሱን በዘመናዊነት ያሳደጋ አለ? በቅኝ ግዛት ደጋግመው ቢገዙንም እኛ ግን ባያቶቻችን ጋሻና ጎራዴ እንጂ በቴክኖሎጂ ለመዘመን ጥረን አናውቅም። ጦርነቶች ስናሸንፍ እንኳ የነሱ እገዛ ከጀርባ እየገባ እንጂ።
የ Sky people በጦርነት ደጋግመው ቢያሸንፉም ሁሌ የሚሸነፉበት ነገር የ Pandora ሀገረ ሰዎች ሁል ጊዜ በአንድ ነገር ያሸንፏቸዋል ያም መንፈሳዊነት ነው። ከተፈጥሮ ጋር በመተባበር ፣ አራዊቱን ፣ እፅዋቱን ፣ የባህር ፍጥረቱን በማስተባበር Eywa የምትባለዋ አምላካቸው እየረዳቻቸው ያሸንፋሉ። እንግዲ እኛ አፍሪካውያን አንድ ያለን ነገር ከመንፈሳዊነት ውጪ ሌላ ምን አለን እነሱን የምንረታበት?
ፊልሙን ያላያቹህ እንድታዩት እጋብዛለሁ።
@ourrthought | 407 |
| 3 | لا يوجد نص... | 341 |
| 4 | አፄ ኃ/ሥላሴና አንድ ስማቸው የጠፋኝ ደጃች (ማን ነበሩ?) በሳንቲም ድብ ድብ ይጫወታሉ።
ደጃች ሳንቲሟን ወርውረው ምንድነው ዘውድ ነው ወይስ አንበሳ? ይላሉ። አፄ ዘውድ ይላሉ። ደጃች እጃቸውን ሲገልጡ ሳይቲሟ አንበሳ ናት። አፄ ፈጠን ብለው ታዲያ አንበሳ እኛ አይደለን እንዴ? ይላሉ። ደጃች ፈርተው ድጋሜ ይወረውራሉ። ሳንቲሟ ስትታይ ዘውድ ናት። አፄው ዘውዱስ ቢሆን የማን ነው? የኛው አይደል? ይሉታል እያፈጠጡበት።
ይሄኔ በስጨት ብለው ደጃች " ዘውዱም ጎፈሩም ከሆኑ ቆይ እሺ የኛ ተራ ታዲያ መቼ ነው የሚደርሰው?" አሉ ይባላል። ጥያቄውም እስካሁን አልተመለሰም።
@ourrthought | 468 |
| 5 | አንድ ፈረንጅ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እየጎበኘ በ እለተ ሰንበት ቤተክርስቲያን ከጎበኘ በኋላ ሰንበቴ ቤት ይዘውት ይገባሉ።
በላ ጠጣ ተደሰተ በሉ ሂሳብ ንገሩኝ አለ አሉ። አይ አይከፈልም አሉት። እንዲህ አይነት ድግስማ በነፃ አያዋጣም ያከስራል። አይ አያስከፍልም ነፃ ነው ተብሎ ጉድ እያለ ወደ ማደሪያው አመራ።
ታዲያ በንጋታው በለተ ሰኞ ቢርበው ጊዜ ገንዘብ ለመቆጠብ ከሰንበቴ ቤት ያቀናል። ሲደርስ ሰንበቴ ቤቱ ዝግ ሆኖ ያገኘዋል አላልኳቹህም ይከስራል ብዬ ነበር ይሄው ከሰሩ አለ አሉ።
@ourrthought | 400 |
| 6 | ለምንድን ነበር አህያን እንዲህ የናቅናት? የስድብ አርማ ያደረግናት? በጠንካራነቷ ወይስ በታታሪነቷ? ወይስ ሸክምን በፀጋ መቀበሏ?
@ourrthought | 423 |
| 7 | ስለ ኢትዮጵያ የድሮ ሁናቴ አሁን ካለችበት ሁኔታ ጋር እያጣጣሙ ኢትዮጵያ ለምን አሁን ያለችበት ሆነች? በሚል እሳቤ ከተፃፉ መፅሐፍት መሀከል ያነበብኩት በ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የተፃፈውን መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ እና አዳፍኔ ፍርሀትና መክሸፍ የሳቸው ሲሆን በቅርብ አመታት ከተፃፉ ያዕቆብ ብርሀኑ በፍም እሳት ማቃመስ ናቸው።
እኚ መፅሐፎች ላይ ኢትዮጵያ ለምን ከሸፈች? ለምን ቁልቁል ተንደረደረችና ሳትለወጥ ቀረች የሚለውን ጥያቄ በማንሳት ያብራራሉ። በያዕቆብ መፅሐፍ ላይ ኢትዮጵያ ሥልጣኔዋን የጎተተው ገዢዎቿ ዘላን መሆናቸው እንደ ትልቅ ክሽፈት ያየዋል። የሀይማኖትንም ተፅዕኖ ይዳስሰዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን በበኩላቸው በሁለቱ መፅሐፎቻቸው ውስጥ ብዙ ሀሳቦችን ያነሳሉ። ለምን ስልጣኔያችን ከቦታ ቦታ የማይዛመት ሆነ? እነ አክሱም እነ ላሊበላ ሌሎችን ጥበብ ያረፈባቸውን ግንባታ ያነፅን ህዝቦች ከ አክሱም ከላሊበላ ሀውልት አጠገብ ያን የመሰለ ጥበብ ትተን የሳር ጎጆ ውስጥ መኖርን መረጥን? የራሳችን ፊደል ኖሮን ስለምን በስነፅሑፍ መራቀቅ አቃተን? የነ ኮንሶ የእርከን ስራ የነ ሐረር ግንብ አንዳንድ ቦታ ያለ የ እርሻ ጥበብ ስለምን ህዝቡ ሳያስፋፋው እዛችው ብቻ ቀረ? ለት/ት ወደ ውጭ የተላኩት ለምን ከሸፉ? የመንግስት ለውጦቻችንስ? የሚለውን እያነሱ ያጠይቃሉ።
በነዚህ መፅሐፎች ብዙ ነገሮችን ማግኘት ይቻላል። በ ፕሮፌሰር መስፍን መፅሐፍ ውስጥ ይበልጥ የሚጠየቁት ከሚደርሱብን ብዙ መከራና ስቃይ እንዴት መማር ቻልን? ለውጥን እንዴት አንሻም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።
አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዝ መንግስት ሲከበብና ራሱን ማጥፋቱን በራሱ ይጠይቃሉ። እንግሊዝ በዘመናዊ ጦር እንዲያ ስታርበደብደን እና የፈለገችውን አድርጋ ከሀገራችን ስትለቅ እኛ ግን ሴባስቶፖል እንኳ ሳይቆጨን የ አፄ ቴዎድሮስ ራዕይን ችላ በማለት እራሱን ማጥፋቱን ስናራግብ አፄ ዩሐንስን መሐዲስት እንዲያ ሲያደርጉት ጣልያን በ አድዋ ሲያፋጥጠን እኛ ግን በ አክሱም ጊዜ በነበረ አልተላቀቅንም ነበር። ጣሊያን ከ 40 አመታት በኋላ እራሱን አዘምኖ በቴክኖሎጂ ረቆ በአየር በምድር በማይጨው ሲመለስ እኛ ግን ጋሻና ጎራዴ እንደያዝን በአይሮፕላን ከሚወርድ ቦምብና ጋዝ አለቅን። የሚገርመው ይሄ ሁሉ እንኳ ሲሆንና ጣሊያን አምስት አመት እንዲያ ሲገዛን ሰንብቶ በውጪ እርዳታ ሲወጣ እኛ ግን ያንን ሁሉ መበለጥና ወደ ኋላ መቅረት ሳያንገበግበን እዛው ኑሮዋችን ተመለስን። የሚገርመው ስለ አድዋ ጣሊያንን ማሸነፋችንን እንጂ አሁን ላይ ጣሊያን ቢመጣ እናሸንፋለን ወይ የሚል ቁጭት የለንም። ሽንፈቶቻችን ውድቀቶቻችን ቆጭተውን አያውቅም ኋላ መቅረታችን አንገብግቦን እራሳችንን ለመቀየር የተነሳንበት ጊዜ የለም። ይሄ እንደ ሀገርና ህዝብ ምን አይነት ስነ ልቦና እንዳለን ግራ ያጋባል።
ሮም ለምን ወደቀች? የሚል ብዙ ጥናቶች ቢኖሩም። ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለምን ከዛ ገናናነት አሽቆለቆለች የሚል ጥናቶች የሉም። እንደ ህዝብ እንደ ሀገር ያለንን ስነ ልቦና የሚያጠናና የሚተነትን የለም። ታሪካችን ምንድነው? እንዴት እንለወጥ? እንዴት እንሻሻል? የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች መነሳታቸውና መወያየታችን አስፈላጊ ቢሆንም እኛ ግን ዛሬም አለም የትናይት ጥሎን መሄዱን አይተን አንደነግጥም ዝምታችን ያስፈራል።
ቡርሀን አዲስ በአንድ ቃለ መጠይቅ ኢትዮጵያውያን ትዝታ ላይ ነን ይላል። እሳቤው እውነትነት አለው። ኢትዮጲያውነት ትላንትና ላይ የቆመ የትላንቱን ብቻ ድል ተራኪ ሆነናል። ሁሉ ነገራችን ትላንት ስለነበረን ገናናነት ትልቅነት እንጂ ስለ ወደ ፊታችን ያለ የመለወጥ የመነሳሳትና አሁን ላይ እራሳችንን ስለመቀየር በጋራ አንድ የሚያደርጉን እሳቤዎች ስንመክር አይታይም። ይሄን ሳስተውል እውነትም ኢትዮጵያ መች ይሆን ከክሽፈቷ የምትነሳው? የሚለው የሁልጊዜ ጥያቄ ነው።
@ourrthought | 492 |
| 8 | لا يوجد نص... | 386 |
| 9 | ጥቁር ወይ ነጭ (black and White)
በብዙ ነገር ችግሮቻችን የሚመነጩት ግራጫዋን የማጣትና የጥሞና ቦታ አለመኖሯ ይመስለኛል። ከ አብዮትም ከ ፊውዳሉም ወገን ገለል ብለህ ማስተዋል የምትችልበት። ከ ነጭ ሽብርና ከ ቀይ ሽብሮች ፋታ የምቶስድበት። የጋርዮሽና መንጋነት ያለበት ቦታ ግራጫ ሀሳብ አትወደድም ከመንጋው የምትነጥልህ በመሆኗ ወይ ከነሱ ወይ ከኛ ነው የምትባለው። ምርጫው ላይ መሀሉ ግራጫው አይቀርብም መሀል ሰፋሪ በተባራሪ ጥይት የመሞት ዕድሉ ሰፊ ነው።
ጥቁር ወይ ነጭ የሚል ሀሳብ እኛ ሰዎችን ሁል ጊዜ የሚቸግረን የፅንፈኝነት ጉዳይ ነው። ወይ ነጭ ሽብር አልያ ቀይ ሽብር ህይወት ሌላ ምርጫ የሌላት እስኪመስል መወጠር። ወይ ከሴጣን ወይ አምላክ የመሆን ያለ እሳቤ።
ግን ከሁለቱም መሀል የሆነውን ግራጫው መሀሉ ይጠፋናል። ገጣሚ ነብይ መኮንን ግራጫ ነኝ እንዲል መሀሉ ላይ የመሆን ዘይቤ ይማታብናል። ህይወት እንደ ወተት አልያ እንደ ቡና ያለ ሳይሆን እንደ ማክያቶ ነው እንደሚለው አቦይ አልያ "መሐል ሰፋሪ የ እግዜርም የሴጣንም ናቸው" እንዲል እሱባለው አበራ መሀሏ ትጠፋናለች።
ግራጭን የመሰለ መታዘቢያ መድረክ አይገኝም። ቀይ ሽብርም ነጭ ሽብርም ሳትሆን መሀል ሆነህ ነገሮችን ማስተዋል መቻል ለግራጫነት የተመቸህ ካልሆንክ የማይሰራ ነው። ህይወትም በሁለት ፅንፎች በኩል ማመዛዘን መቻል ነው። አንዱ ስትገባ አንዱ ጋር ያለው በረከት ይጎልብሀል። የዛኛውን በረከት ማጣጣም አትችልም በራስህ ኩሬ እንደመዋኘት ያለ የራስህን አለም ከማጠር ውጪ።
ጨዋታውን በ አውጉቾ ተረፈ (ህሩይ ሚናስ) ገጠመኝ ልዝጋው።
አውግቸው ቡና ለመጠጣት ወደ ቀኝ ሲያማስል ቀኝ ዘመም ነህ ሲሉት ወደ ግራ ሲያማስል ግራ ዘመም ሲሉት ከዚህ ሁሉ ስኳሩን ቢተወው መሀል ሰፋሪ ነህ ብለውት አረፉ። መሀል ሰፋሪነቱ ግን ከሁሉ በላይ ሳያንገበግባቸው አልቀሩም።
በርግጥ ሀገራችን ለግራጫ ቦታ የላትም ወይ ከነሱ አልያ ከኛ ወገን ትሆናለህ የሚል አማራጭ ብቻ ነው የሚቀርብልህ።
ግራጫነት ስትታይ ዋዛ ብትመስልም ከመንጋነት የምታስመልጥ ግለሰባዊ ቦታ ናት። ከኛም ከነሱም ከሚል የመንጋ እሳቤ ታወጣሀለች። ግን ለግራጫነት ዕድል ለማግኘት ለግለሰብ ነፃነት የሚሰጥ ማህበረሰብ ግድ ይላል። ግራጫነት ይለምልም።
@ourrthought | 1 927 |
| 10 | لا يوجد نص... | 386 |
| 11 | የዛሬ አመት ለ ቀለም ዲጅታል መፅሔት መግቢያ የምትሆን ፅሑፍ ስለ አዲስ አመት የከተብኳትን ዛሬ ደግሜ ላካፍላቹህ።
“ጊዜ በረርክ፤ በረርክ፤
ጊዜ በረርክ፤ በረርክ፤
ግና ምን አተረፍክ፤
ግና ምን አጎደልክ፤
ሞትን አላሸነፍክ፤
ሕይወትን አልገደልክ፡፡”
ገጣሚ ደበበ ሠይፉ “ ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ” በሚለው የግጥም መድብል ውስጥ ይህቺን ግጥም ታስደንቃለች። በስድስት አጫጭር መስመር ብዙ ሀቅን ይነግረናል። ጊዜ እንደዚህ ሮጦ ሞት የሚባልን የሰው ልጅ ዕዳ ካላሸነፈ መወለድ የሚሉትን የህይወት ትግል ካልገደለልን ታዲያ እውነትም ጊዜ ይሄ ሁሉ ዘመን ያለማቋረጥ መገስገሱ ምን ይሉት ብሂል ነው? ግዜ ራሱ የት እየሔደ ይሆን? እንጃ እኛ የምናውቀው ከጊዜ ጋር አብረን መፍሰሳችንን እንጂ ምስጢሩ ገና በውል የገባን አይመስልም።
ብዙ ጊዜ እኛ ሰዎች ጊዜ መሸምጠጡን የምናስተውለው ዓመት ሲቀየር ነው። ታዲያ ዛሬም አዲስ ዓመት የተቀየረ በመሆኑ ስለ ጊዜ ቆም ብሎ ለማሰብ ፋታ ያገኘንበት ሰሞን ይመስለኛል። የሰው ልጅ ከ አቻው ጀምሮ ተፈጥሮን ፣ አራዊቱን ፣ ሥነ-ፈለክን ፣ አፅናፉን ወዘተ ያለምረመረውና ያልታገለው ነገር የለም። ኧረ እንደውም በመፅሐፍ ቅዱስ ሰው ከፈጣሪው ሁሉ ታግሏል ካልባረከኝ አለቅህም ብሎ አምላኩን ሙጥኝ ብሎ እምብኝ ማለቱን አንብበናል። ግን ይሄን ጊዜ ይሉት ነገር የት አግኝቶ ይታገለው? እዳ ነው ጃል።
ገጣሚው በዕውቀቱ ስዩም በስብስብ ግጥሞቹ ውስጥ እንዲህ ይለናል:-
“እኛኮ ለዘመን
ክንፎቹ አይደለንም ሰንኮፍ ነን ለገላው
በታደሰ ቁጥር የምንቀር ከኋላው።” ይለናል።
እንደልቤ የተባለለት ልብ አምላክ ዳዊት በመዝሙሩ ውስጥ “የጣቶችህን ስራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፤ ጨረቃንና ክዋክብትን አንተ የሰራካቸውን ፤ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጎበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?” እንዳለው የሰው ልጅስ ለጊዜ ምኑ ነው? ሀያል ሆንህ ደቃቃ ፣ አዋቂ ሆንህ መሀይም ፣ ሶሬሳ (ሀብታም) ሆንህ ቤሳ የሌለህ ደሀ ፣ ታማኝ ሆንህ ከሀዲ ምንስ ብትሆን ለግዜ ምን ገዶት? እንዳልነበርክ ሁሉ እርስት ያደርግሀል። ትቶህ ሂድት ጥሎህ ፍርጥጥ። ለ አፈር ሰጥቶህ እብስ። በቃ ይሄን እውነት ነው ገጣሚው የሚነግረን።
ከ ቀለም መፅሔት መግቢያ ከ መስከረም 15/2018 ዓ.ም ቅፅ 1 ዕትም 3 ላይ የተቀነጨበች።
@ourrthought | 522 |
| 12 | لا يوجد نص... | 427 |
| 13 | የዛሬ አመት ለ ቀለም ዲጅታል መፅሔት መግቢያ የምትሆን ፅሑፍ ስለ አዲስ አመት የከተብኳትን ዛሬ ደግሜ ላካፍላቹህ።
“ጊዜ በረርክ፤ በረርክ፤
ጊዜ በረርክ፤ በረርክ፤
ግና ምን አተረፍክ፤
ግና ምን አጎደልክ፤
ሞትን አላሸነፍክ፤
ሕይወትን አልገደልክ፡፡”
ገጣሚ ደበበ ሠይፉ “ ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ” በሚለው የግጥም መድብል ውስጥ ይህቺን ግጥም ታስደንቃለች። በስድስት አጫጭር መስመር ብዙ ሀቅን ይነግረናል። ጊዜ እንደዚህ ሮጦ ሞት የሚባልን የሰው ልጅ ዕዳ ካላሸነፈ መወለድ የሚሉትን የህይወት ትግል ካልገደለልን ታዲያ እውነትም ጊዜ ይሄ ሁሉ ዘመን ያለማቋረጥ መገስገሱ ምን ይሉት ብሂል ነው? ግዜ ራሱ የት እየሔደ ይሆን? እንጃ እኛ የምናውቀው ከጊዜ ጋር አብረን መፍሰሳችንን እንጂ ምስጢሩ ገና በውል የገባን አይመስልም።
ብዙ ጊዜ እኛ ሰዎች ጊዜ መሸምጠጡን የምናስተውለው ዓመት ሲቀየር ነው። ታዲያ ዛሬም አዲስ ዓመት የተቀየረ በመሆኑ ስለ ጊዜ ቆም ብሎ ለማሰብ ፋታ ያገኘንበት ሰሞን ይመስለኛል። የሰው ልጅ ከ አቻው ጀምሮ ተፈጥሮን ፣ አራዊቱን ፣ ሥነ-ፈለክን ፣ አፅናፉን ወዘተ ያለምረመረውና ያልታገለው ነገር የለም። ኧረ እንደውም በመፅሐፍ ቅዱስ ሰው ከፈጣሪው ሁሉ ታግሏል ካልባረከኝ አለቅህም ብሎ አምላኩን ሙጥኝ ብሎ እምብኝ ማለቱን አንብበናል። ግን ይሄን ጊዜ ይሉት ነገር የት አግኝቶ ይታገለው? እዳ ነው ጃል።
ገጣሚው በዕውቀቱ ስዩም በስብስብ ግጥሞቹ ውስጥ እንዲህ ይለናል:-
“እኛኮ ለዘመን
ክንፎቹ አይደለንም ሰንኮፍ ነን ለገላው
በታደሰ ቁጥር የምንቀር ከኋላው።” ይለናል።
እንደልቤ የተባለለት ልብ አምላክ ዳዊት በመዝሙሩ ውስጥ “የጣቶችህን ስራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፤ ጨረቃንና ክዋክብትን አንተ የሰራካቸውን ፤ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጎበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?” እንዳለው የሰው ልጅስ ለጊዜ ምኑ ነው? ሀያል ሆንህ ደቃቃ ፣ አዋቂ ሆንህ መሀይም ፣ ሶሬሳ (ሀብታም) ሆንህ ቤሳ የሌለህ ደሀ ፣ ታማኝ ሆንህ ከሀዲ ምንስ ብትሆን ለግዜ ምን ገዶት? እንዳልነበርክ ሁሉ እርስት ያደርግሀል። ትቶህ ሂድት ጥሎህ ፍርጥጥ። ለ አፈር ሰጥቶህ እብስ። በቃ ይሄን እውነት ነው ገጣሚው የሚነግረን።
ከ ቀለም መፅሔት መግቢያ ከ መስከረም 15/2018 ዓ.ም ቅፅ 1 ዕትም 3 ላይ የተቀነጨበች።
@ourrthought | 1 |
| 14 | የ ህይወት ትርጉም (meaning of life)
የህይወት ትርጉም ምንድነው? ህይወትስ በራሷ ትርጉም አላት ወይስ እኛ ነን በራሳችን ትርጉም የምንሰጣት? የሚሉትን ጥያቄዎች ለዘመናት አከራካሪ ጉዳይ ቢሆንም አሁንም የተጨበጠ ሁሉንም የሚያስማማ መልስ ማግኘት ይቸግራል።
ሀይማኖት ህይወት በራሷ ትርጉም አላት ሲል እንደነ ካሙ ያሉ ፈላስፎች ሀይማኖት በሚሰጠው ትርጉም ማመን ትርጉም በሌለው አለም ውስጥ ለትርጉም ነው የተፈጠርኩት ማለት በራሱ እራስን በማታለል እራስ ላይ ያለ እራስን ማጥፋት (Philosophical suicide) ይላል።
ለምንድነው እዚህ ምድር የመጣሁት? ምን እየሰራሁ ነው? ለምንድነው የምኖረው? አላማዬስ ምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎች ከየትኛውም ጊዜ በላይ ከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን ትልቁ ጥያቄ ሆኗል። ለምን ይሄ ጥያቄ ከሌላው ጊዜ በላይ አሁን ይበልጥ ሰውን ማስጨነቅ ጀመረ? የህይወት ትርጉም ማጣትስ? እራስን ማጥፋት ቁጥሩ ለምን ጨመረ? የሚሉት ብዙ ምክንያቶች አሉ።
እንደ ካምዩ ሀሳብ ሲጀመርም ህይወት በራሷ ትርጉም የላትም ስለዚህ ትርጉም አላት እያሉ ከመሞኘት ይልቅ እና ህይወት ትርጉም ባይኖራትም የራስህን ትርጉም ፈጥረህ የራስህ ጀግና (Absurd hero) ሆነህ መኖር ትችላለህ ይለናል። እንደ ሲሲፈስ ድንጋዩን ማንከባለሉን ማቆም ባይችልም ግን ለመግፋቱ ለራሱ ምክንያት እንደሰጠው ሁሉ አንተም ለራስህ የሆነ ግብ ይዘህ ለሱ መኖርና ትርጉም መስጠት ትችላለህ ይለናል። ግን ሰው እራሱ ለራሱ የሚሰጠው ምክንያት በቂው ነው? የራሴ ነው የሚለውስ ጥያቄ እውን የራሱ ነው ማለት ይቻላል? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው።
ለምሳሌ አስቡትና ብቻችሁን ምድር ላይ ቀራችሁ እንበል። ሌላ ማንም ሰው ምድር ላይ የለም። እና ትልቁ የህይወት ግባቹህ ምን የሚሆን ይመስላቹሀል? የራሳችሁን ትርጉምስ ምን ሊሆን ይችላል? አሁን የህይወታቹህ ትርጉም አድርጋችሁ የምትኖሩለትን ነገር አለም ላይ ብቻችሁን ብትሆኑ ታስቀጥሉታላቹህ? ጥያቄውን ለናንተ ልተው።
ወደ ጥንታዊው ሰው ስንመለከት የማህበረሰቡ ኑሮ በጋራ የሆነና እኔነት የሌለው ነው። ኑሮው ሁሉ በጋራ እንደመሆኑ መጠን በጋራ እራስን የማቆየት (survival) የሆነ በመሆኑ አንድ ህፃን ሲወለድ ጀምሮ እስከ መሞቻው ኑሮው የታወቀ እና የተገመተ ማህበረሰቡ በቀደደው የጋራ መስመር የሚፈስ የነበረ ነው። በጋራ ማደን በጋራ መጨፈር መብላት መዋለድ ውስን ተግባሮች የነበሩበትና የጋራ የሆነ በመሆኑ ሰው ግራ መጋባት በህይወቱ እምብዛም የለውም ነበር።
ሀይማኖት ተደራጅቶ ከመጣ በኋላም የህይወትን ትርጉም ከፈጣሪ ጋር በማያያዝ በቂ የሆነ ምላሽ ለማህበረሰቡ የሰጠ የነበረ በመሆኑ የተፈጠረለት አላማ በፈጣሪና ስለፈጣሪ መሆኑን አማኙ ተቀብሎ በደስታ ይኖር ነበር። ከ ዘመነ አብርሆት በኋላ (Age of enlightenment) ሀይማኖቶች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው ሀይማኖት ይሰጥ የነበረው ትርጉምም አብሮ ተጠየቅ ውስጥ ገብቷል።
አሁን ላይ ይበልጥ የህይወት ትርጉም ለምን ጥያቄ ውስጥ ገባ? የሚለው ዘመኑ የ ግለሰባዊነት (Individualism) በመሆኑ እንደ ቀደምት ዘመን የጋራ ትርጉምና ኑሮ የሌለው የተወሰነለት ትርጉም የሌለው በመሆኑ ፡ ጥያቄው ከጋራ ምላሽ ይልቅ በግለሰብ ደረጃ በመሆኑ የየራሳችንን ትርጉም መፈለግ ለብዙ ሰው አዳጋች ሆኗል። ምን ላድርግ? ምን ልስራ? ወዴት ልሂድ? የሚሉ ጥያቄዎች ከራሳችን ተነስተው እራሳችን ላይ የሚያቆሙ በመሆናቸው የራስን ትርጉም ከምን አንፃር መመለስ እንዳለብን ግራ ይገባናል። ይህ ግራ መጋባት ብዙ ሰዎችን የሚያስጨንቅ በመሆኑ ህይወቱን ትርጉም ለመስጠት ፡ አብዛኛው ሰው አሁን ላይ ዋጋ የሚሰጠውን ነገር በመምረጥ ለዛ ነገር ለመኖር ይወስናል። ለምሳሌ ሀብታም መሆን ፣ ቤትና መኪና መግዛት ፣ ታዋቂ መሆን ትርጉም አድርጎ ለመኖር ይወስናል። አሁን ላይ አብዛኛው የህይወት ትርጉም ከ ቁሳዊ ነገሮች (materialisem) ጋር የተሳሰረ እየሆነ መጥቷል። ይህ ለምን ሆነ ስንል ዘመኑ ለ ቁሳዊ የሚሰጠው ወጋ ከፍ ያለ በመሆኑ ላይ የተመሠረተ ነው። የህይወት ትርጉም ምንድነው? ብንል አሁንም ያልተመለሰ ጥያቄ ነው።
@ourrthought | 581 |
| 15 | لا يوجد نص... | 382 |
| 16 | እንደ ዶሮ ወጥ 12 ዙር እናያለን ብለን ብንጓጓም እንደ ኢንዶሚን ከ 3 ደቂቃ የማያልፍ መሆኑ ያንገበግባል።
ከ ሀገራችን EFC ኢንዶሚን ይቆያል። | 560 |
| 17 | "ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ዓለም ረስተውት ለአንድ ሺህ ዓመታት ያህል አንቀላፉ።"
ኢንግሊዛዊው የታሪክ ተመራማሪው ኤድዋርድ ጊበን
@ourrthought | 510 |
| 18 | ሀሳቡን ከመፅሐፉ ቦታ ካስገረመኝ ቦታ ጠቅሼ ላብቃ። አንድ የሀገራችን ሰው በደቡብ አፍሪካ የገጠር አከባቢ አነስተኛ ሸቀጣሸቀጥ ከፍቶ ይሰራል። በዛ አከባቢ ስትራይካ (መጤ ጠል አመፅ) አሁን አሁን በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ነው። እና የሰፈሩ ደንበኞች በጣም የሚግባባቸው ሁለት የደቡብ አፍሪካ ዜጎች በማታ ወደ ሱቁ መጥተው ልጁ እያለ አንገታቸውን አስገብተው በራሳቸው ቋንቋ በዙሉኛ ነገ አመፅ ሲነሳ የትኛውን እቃ ማን እንደሚወስድ ይከራከራሉ። እሱን ከመጤፍም አልቆጠሩት። እኔ ነኝ ያን እቃ የምወስደው ሲል አንደኛው ታያለህ ቀድሜ ስለምመጣ እኔ ነኝ የምወስደው ተባብለው የሚፈልጉትን እቃ መርጠው ይሄዳሉ። በነጋታው አመፁ ተነስቶ ሌሎች አመፅኞች ቀደሟቸውና በሱቁ ደና እቃውን ወሰዱት። እነሱ ሲመጡ ሌላ እቃ ይዘው እየወጡ ደንበኛ የሀገራችንን ልጅ "በርታ እንግዲህ እኛም እናግዝሀለን "try again" ብለውት ወጡ። እንግዲ ከዜሮ መጀመር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሀገራችን ላይ የሆነ እቃ ላይ በነጋታው ስትሄዱ ዋጋ እንደመጨመር በሉት። ደቡብ አፍሪካዊ የስደተኛ ሱቅ ገብቶ ነገ ያቺን ዕቃ አዘጋጅልኝ መጥቼ ወስዳለው ብሎ በነጋታው መጥቶ ይወስደውና በርታ አግዝሀለሁ ብሎ ይሄዳል።
ስደት በሌሎችም አውሮፓ ሀገሮች ከአፍሪካ የሚሄዱ ስደተኞች ከሰውነት በታች በደልንም የሚቀምሱበት ቦታም ነው። ከዩኒቨርስቲ ዶክተር የነበረ አስተማሪ አሁን ላይ አሜሪካ ሽንት ቤት እንደሚያፀዳ ሰምቼ ምን እንደምል ግራ እስኪገባኝ በዚህ ልክ ስደት የሚንቆለጳጰስ መሆኑ ያስገርመኛል።
@ourrthought | 579 |
| 19 | ዛሬ በባስ ታጭቄ እየሄድኩ በባስ የተከፈተ ሬዲዮ ላይ ጆሮዬን ጣል አድርጊያለሁ። ወንድና ሴት ጋዜጠኛዋ ስለ ቡሄ ወሬ ይጠርቃሉ። በመሀል ወንዱ ጋዜጠኛ ሆያ ሆዬ ማለት ጀመረ።
"እዚህ ማዶ አንድ ጄሪካን
እዛ ማዶ አንድ ጄሪካን
የኔማ እከሌ (ስሟን ረስቸዋለሁ) ልሸኝሽ አሜሪካ።" ብሎ ግጥሙን ሲጨርስ በደስታ እየተፍነከነከች ግሩም አለች። ወዲያው ግርምታ ይሉት ቁጭት ውልብ አለብኝ። በየቤታችን ልናወራ እንችላለን ግን በሚዲያ የሚተላለፍ ጉዳይ ላይ እንዲህ በግልፅ ስደትን የሚያበረታቱ ጉዳዮች መወሳታቸው ቁጭት ቢጤ ዳሰሰኝ።
ከሁለት ቀን በፊት አባይ ቲቪ ላይ የጨርቆስ ልጆችን ሰብስበው ስለጨርቆስ የ አብሮነት ኑሮ መተሳሰብ ፍቅር እያወሩ ፊልሞች ላይ የተወነ አቼኖ ይመስለኛል ስሙ "የጨርቅስ ልጅ ፈር ቀዳጅ ነው። ሊቢያ በመሰደድ የመጀመሪያው የጨርቆስ ልጅ ነው። ከማንም በፊት ስደትን ሀ ብሎ የጀመረ ጨርቅስ ነው። የትም ሀገር ብትሄጂ የጨርቆስ ልጅ አይጠፋም።" ብሎ በኩራት ቲቪ ላይ የሚታይ ፕሮግራም ላይ ሲተላለፍ ታዝቢያለሁ ዩቲዩብ ላይ አሁይም አለ።
ሰሞኑን አላፊ መንገደኛ ቁጥር 2 በሚል ርዕስ በደቡብ አፍሪቃ ዙሪያ የሚያጠነጥን በስደት ዙሪያ የተፃፈ የ ዮርዳኖስ አልማዝ የምርምር መፅሐፍ እያነበብኩ በመሆኑና በስደት ዙሪያ የተደረጉ ቃለ መጠይቆች እያየሁ በመሆኑ የስደት ርዕሶች ሲወራ ጆሮዬ ይቆማል።
በሀገራችን ስደት መቼ ተጀመረ የሚለውን አንድ አርቲክል ሳገላብጥ ከ አፄ ምኒልክ ጊዜ ጀምሮ ስልጣኔን ተምረው እንዲመጡና ለትምህርት ጉዳይ ከሚላኩት የሚነሳ ነው። ከዛም በመቀጠል አፄ ኃ/ሥላሴ የ አፄ ምኒልክን ፈለግ ተከትለው ተማሪዎችን ወደ ተለያዩ ሀገራት መላክ መቀጠላቸውንና በፋሽስት ጊዜ እራሳቸው ንጉሱ መሰደዳቸውን ማንሳት ይቻላል። ከዛን በኋላ በደርግ ጊዜ የስደት ሥርዐትና ቅርፁን በመቀየር የ ፖለቲካ ነክ ይዘት ይዞ ከዘመቻ ለመሸሽ ወደ ተለያዩ ሀገራት በ አራት መስመሮች ወደ ስደት ያቀኑት። በ ኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ተባብሶ የመጣው የፖለቲካ ስደት ኢኮኖሚንም አካቶ እስከ አሁን እንደ ቀጠለ ነው።
ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚደረጉ የስደት ጉዞዎችና ደቡብ አፍሪቃ ያሉ የሀገራችን ልጆችን ጉዳይ የሚያጠናው ዮርዳኖስ አልማዝ በደቡብ አፍሪቃ ስለሚደረጉ ጉዞ እና እዛ ያለ የስደተኞች ሁኔታ የሀገሩን ነባራዊ ሁኔታ በ 2 መፅሐፍት ጀባ ብሏል። ከዛም ውስጥ አንዱ እጄ ላይ ያለው እላፊ መንገደኛ ቁጥር 2 መፅሐፍ ነው። በዚህ መፅሐፍ ላይ ደቡብ አፍሪቃ ያሉ የሀገራችን ስደተኞች አፓርታይድ ካበቃ በኋላ ደቡብ አፍሪካ በሯን ለስደተኞች የከፈተች በመሆኑ ብዙ የተለያዩ የ አፍሪካ ሀገራት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለስራ አቅንተዋል። በዛም የመጀመሪያ ስራቸው ቀበቶ ሰዐት የተለያዩ በእጅ የሚያዙ እቃዎችን ይዘው መንገድ ለመንገድ ይሸጡ ነበር። ደቡብ አፍሪካውን አፓርታይድ አብቅቶ ከእስር ሲፈቱ ቀበቶ የሌላቸው በመሆኑ ቀበቶ መሸጥ አዋጭ ቢዝነስ ነበር።
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከ ኢትዮጵያም ከተለያዩ ቦታዎች የሚሄዱ ስደተኞች ህጋዊ ስለማይሆኑ የ ስደተኛ የመሆኛ ጥያቄ መጠየቂያው እንኳ ሂደቱ ብዙ ስለሆነ ያለምንም ወረቀት የሚሰሩ በመሆኑ የባንክ አገልግሎት ስለማይጠቀሙ ገንዘባቸውን በኪሳቸው ወይም በሌላ ቦታ በካሽ ይዘው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ የደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ቀማኞች Mobile ATM ሁላ ይሏቸዋል። በቀንም ሆነ በለሊት የሰሩበትን ሁሉ በአንድ ቀን ይቀማሉ። ነብሳቸውንም ይቀማሉ። ደቡብ አፍሪካ 40% የስራ አጥ ቁጥር ያለባት ሀገር ስትሆን መንግስት በሚሰጣቸው የወር ድጎማ የሚተዳደሩ ገንዘብ የመቆጠብ ልማድ የሌላቸው ናቸው። በዛ በዛ ስደተኞችን እያጠቁ ገንዘባቸውን ይቀማሉ ይሰርቃሉ። ደቡብ አፍሪካ በቀን ራሱ መንቀሳቀስ ጭንቅ ጥብ የሆነበት ሀገሮ ነው። በማንኛውም ሰዐት ልትዘረፉ ሊገድሏቹህ ይችላሉ። ግን ደግሞ የሀገሬው ነዋሪ የመግዛት አቅሙ ከሀገራችን ጋር ሲነፃፀር 40% ይበልጣል። ይህ ማለት ፍላጎቱም አቅሙም አለ ማለት ነው።
በደቡብ አፍሪካ የስጋት ህይወት የሚኖሩ በፖሊስም ጭምር የሚዘረፉ ሞልተዋል። ግን ህጋዊ ባለመሆናቸው ብዙ ስቃይና እንግልት ይደርስባቸዋል። አሁን አሁን መጤ ጠልነት Xenophobia እየተበራከተ በመምጣቱ "ምንድነው ጫጫታው ሀገሩ የኛ ነው" የሚል መፈክር በመያዝ በገጠራማው በሚገኘው ደቡብ አፍሪቃ ላይ በተጋጋሚ ሱቃቸውና ብራቸው ይዘረፋል። የሀገራችን ውሾች ከናንተ ይሻላሉ የሚሉም ተበራክተዋል። የሰው ነብስ እንደ ቀላል የሚጠፋበት ሀገር ነው። ብዙዎች ደሞ ተቀይረው ኑሯቸውን ሊደጉሙ ችለዋል። ጥሩ ኑሮም የሚኖሩም አሉ። ህጋዊ ቢሆኑም ብዙ የመብት ጥሰቶችን ያስተናግዳሉ። ገንዘብ ከፍለው እንኳ ልጆቻቸውን ማስተማር የሚከለከሉበት ጊዜም አለ።
በሆሳዕናና በሌሎች አንዳንድ የደቡብ አከባቢዎች ሁሉም ደቡብ አርፍሪካ የቃል ኪዳኗ ምድር ለመግባት የሚጓጓ ብዙ ነው። በሻሼጎ ቦኖሻ የሚገኝ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ሰባ በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ፓስፖርት አውጥተው ለመሰደድ የተዘጋጁ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ብዙዎቹ እዛ ከሄዱ በኋላ በአመት አንድ ጊዜ የሚዝናኑበትን ቦታ በፎቶ በመልቀቅ ሀገር ቤት ያሉ ሰዎችን ያጓጓሉ። የቤተቦቻቸውን ቤት እቃ ይሞላሉ። በሆሳእና አከባቢ ሀገር ቤት ያሉ ያልተሰደዱ ቤተሰቦችና የተሰደደ ልጅ ያላቸው እኩል አይከበሩም የተሰደደ ልጅ ያላቸው የተሻለ ክብርና ቦታ ይሰጣቸዋል። ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄደው ሞተው የሚመለሱ ስደተኞች የሀገር ቤት መቃብራቸው የአይሮፕላን ምስል ይሳልበታል። ቢያንስ ሬሳው በአይሮፕላን ነው የመጣው ብለው ቦታ ይሰጡታል። በተቃራኒው በሀገር ቤት ያለ ወዳጅ ዘመድ ቦታ አይሰጣቸውም። ዬሄ ለስደት ይገፋቸዋል የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ይገፋፋቸዋል። የሚሄዱት በህገወጥ መንገድ በመሆኑ መሬት ሸጠው ተበድረው ሄደው በመንገድ ላይ የሚሞቱም አሉ። በስደት ጊዜ ከ 6 ወር በላይ የሚፈጅባቸውም አይጠፉም። በ ድንበር ጠባቂዎችና ደላሎች የሚደፈሩ ሴቶች በመብዛታቸው ሴቶቹ ቀድመው የወሊድ መከላከያ ይጠቀማሉ።
ወደ አረብ ሀገርም የሚሰደዱ ሴቶች እውቀትና የዘመናዊ ኑሮ ልምድ የሌላቸው በመሆኑና የሀገራችንም የቆንፅላ ፅ/ቤት የደከመ በመሆኑ ቦታና ክብር አይሰጣቸውም። በአንድ ወቅት ባህሬን ያሉ ሰራተኛ አገናኞች አንድ ፊሊፕናዊት ሰራተኛ ሲቀጥሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ሴት በነፃ ትመረቅላቹሀለች የሚል ክብር የሚነካ ማስታወቂያ አውጥተው ደራሲ ፕሮሞተር እስከዳር ግርማ ተከራክረው ደላላውን ከሰዋል። ይህ የሆነው ያለ እውቀትና ልምድ ስለሚጋዙና የሀገራችንም ግንኙነትና ለህዝቡ ደንታ ቢስ የሆነ በመሆኑ ነው።
በዚህ በ ዮርዳኖስ መፅሐፍ ላይ ሰዎት ከመሰደዳቸው በፊት ስለሚሰደዱበት ሀገር ቋንቋ ባህል ቢያውቁና መኪና ሳይክል ዋና ምግብ ማብሰል ሁነኛ ጉዳዮች እንደሆኑ አፅኖት ይሰጣል። የኛ ሀገር ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ብዙ የሚሄዱት ከ ገጠር የሀገሪቷ ክፍሎች በመሆኑ ቋንቋ እጥረት ያለባቸው በመሆኑ ብዙ ነገር ይስተጓጎልባቸዋል። | 483 |
| 20 | لا يوجد نص... | 352 |
