Black 🖤͙͙͙*͙*❥⃝∗.ʚɞ.∗❥⃝**͙͙͙͙
الذهاب إلى القناة على Telegram
✦͙͙͙*͙*❥⃝∗⁎.ʚ ɞ.⁎∗❥⃝**͙✦͙͙͙ 。・::・゚★,。・::・゚☆ ☆。・::・゚★,。・ ʟⁱᵏᵉ〠 ᴄᵒᵐᵐᵉⁿᵗ☟ ⛁ sʰᵃʳ join 🤝 https://t.me/blackprofil38k
إظهار المزيد586
المشتركون
-124 ساعات
-87 أيام
-1330 أيام
أرشيف المشاركات
ድሮ ትዝ ካላችሁ የምንፈራውን አስተማሪ የቤት ስራ ካልሰራን ሁላ የአለም መጨረሻ ይመስለን ነበር። አሁን እነዛን ጊዜያት አስቧቸው ምን ያህል ለማይረባ ነገር ስንጨነቅ እንደነበር ... አሁንም የሚያስጨንቁን ነገሮች፣ ነገ ስናልፋቸው "ውይ ያቺ ነበረች እንዴ" ነው የምንለው።
አትጨነቁ፣ የማያልፍ የሚመስለው ሁሉ ያልፋል ለማለት ነው።
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
ከሁሉም ሰው መራቅህ
ስለራስህ ቆም ብለህ እንድታስብ ያረግሃል እንጂ
ብቸኛ አያደርግህም
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
ታገስ🙂
ሁልጊዜም በህይወት መነሻህና መድረሻህ ስታስበው ቀላል ነው፤ መሀሉ ግን አይነገርም! አየህ ፈተናው፣ ተስፋ መቁረጡና ከባዱ ጊዜ ያለው መሀሉ ላይ ነው። ይሄን ወሳኝ ጊዜ በጥበብ ልታልፍ የምትችለው በአንድ ነገር ብቻ ነው 'በትዕግስት!' ወዳጄ ታገስ አለበለዚያ ምንም ብትለፋ ህይወትህን አትቀይርም!
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
ምናልባት ላይመስልህ ይችላል ግን
ፈጣሪ በ 2019 እስከሚገርምህ ድረስ የሚገርም ሕይወት ያኖርሃል
ብቻ አሜን በል!🙏
መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ 🌻🌻
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
ሶቅራጠስ እንዲህ ይላል፡-
ልጅ ሆኜ ጠዋት መነሳት አይሆንልኝም ነበር፣ እናቴ ጎበዝ ነጋዴ እንድሆን ስለምትፈልግ ይህን ባህሪዬን አትወድም ነበር፡፡ አንድ ግን እንዲመክረኝ ብላ ወደ መምህሬ ይዛኝ ሄደች፡፡ መምህሬም
“ሶቅራጠስ፤ የሆነች አጭር ታሪክ እነግርሃለሁ፤ ከዚያ ምን እንደተማርክ ትነግረኛለህ ፡፡” አለኝ፡፡
“እሺ” አልኩት፡፡
“ሁለት ወፎች ነበሩ፡፡ አንደኛው በጠዋት ተነሳና ብዙ ትላትሎችን አገኘ ለራሱ በላ፤ ልጆቹንም አበላ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አርፍዶ ሲነሳ የሚበላዉን አላገኝም፡፡ ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? ” አለኝ፡፡
“ማልደው የሚነሱ ትላትሎች በወፎች እንደሚበሉ ነው።😂
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
አጋጥሟችሁ ግን ያዉቃል ❓....
የሆነ ጊዜ ላይ በህይወታችሁ ዉስጥ ሰላም ነበር...ቤተሰቦቻችሁ,የቅርብ ጓደኞቻችሁ, በውሉ የማያዉቃችሁ ሰዉ ራሱ ስለ እናንተ 𝓹𝓮𝓻𝓼𝓸𝓷𝓪𝓵𝓲𝓽𝔂 ይመሰክርላችሁ ነበር። ህልም ያላችሁ..ትልቅ ተስፋ ያላችሁ ከእናንተም አልፎ ተርፎ ለሌሎች የምታበሩ ብርሃኖች ነበራችሁ...........ፈገግታችሁ ከልብ..ሳቃችሁ የምር..ያላችሁ 𝓯𝓻𝓮𝓮𝓭𝓸𝓶 100%..በአጠቃላይ የህይወታችሁ መስመር የተስተካከለ..ህይወትን በመልካም ጎኗ የምታዩ..ከሱስ የነፃችሁ..ሱስ ከመጥላታችሁ የተነሳ ሌሎችን ከዚህ ነገር እንዲርቁ ተግሳፅ የምትሰጡ ነበራችሁ። ሰዎች ለምሳሌነት በሚያነሷቸው መጥፎ ተግባራት ተብለዉ በማህበረተሰቡ ህገ-መንግስት ታፔላ የተለጠፈባቸውን ነገሮች የምትጠየፉ ነበራችሁ.."እከሊት እንደዚህ ታደርጋለች አሉ" ስትባሉ "እከሌ እክ እንዲህ የሚባል ሱስ አለበት" ስትባሉ በየሀይማኖታችሁ አማትባችሁና የ44ቱን ታቦታት ስም ጠርታችሁ"እረ እኔ ብሆን አላደርገዉም" ብላችሁ በአንደበታችሁ ተናግራችሁ ነበር..ያኔ ሰዎች ላይ ያለምንም ምክንያት ፍርዱ ትሰጡ ነበር..ጉድ እኮ ነዉ ማን ፈራጅ እንዳደረጋችሁ❓❓
የፍርድ ቤቱ መመሪያ ህግ:- የማህበረሰቡ የተጨመላለቀና የከረፋ ህግ
ዳኛ:- አንተ/አንቺ..እናንተ..ማህበረሰቡ
ምስክሮች:- ከዳር ቆመዉ ያለ ምክንያት ሰዉ ላይ ጠቋሚ ጣቶች በሙሉ
ተከሳሽ:- የሆነ 𝓼𝓸𝓶𝓮 𝓸𝓷𝓮...
ለሚያደርጋቸው ነገሮች ስሜት አልባ የሆነ ምስኪን ነፍስ
የፍርዱ ጉዳይ/ወንጀል:- የማህበረሰቡን የከረፋ ህግ መጣስ
....አንዳንዴ "ለምን❓" ብሎ ከመጠበቅ ይልቅ እንዲህ ነዉ ብለን አራት ነጥብ መስጠት እንወዳለን። ሌሎች የነበሩትን/ያሉበትን "የሚደብር ቦታ" ብለን ያስቀመጥነዉ ቦታ ላይ እንዴትና ለምን..እንደሆነ ሳናዉቅ ከተጠየፍነዉ ማጥ ዉስጥ እናገኘዋለን.."እኔማ በጭራሽ አላደርገውም" ብለን የዘጋነዉ ፋይል ዉስጥ ማለት ነዉ..የዛኔ በፈረድንበት አፋችን ራሳችን ላይ እንፈርዳለን❓...ወይስ...ዝምታን እንመርጣለን❓ብቻ ሀሳቡ ምንድነው...
"𝙙𝙤𝙣'𝙩 𝙟𝙪𝙙𝙜𝙚 𝙩𝙝𝙚 𝙗𝙤𝙤𝙠 𝙗𝙮 𝙞𝙩𝙨 𝙘𝙤𝙫𝙚𝙧.." 𝓬𝓸𝔃 እናንተም እዛ ቦታ ላይ ህይወት ባላሰባችሁት የ 𝓶𝓲𝓬𝓻𝓸 𝓼𝓮𝓬𝓸𝓷𝓭 ፍጥነት ያህል ቁጭ ልታደርጋችሁ ስለምትችል ከቻላችሁ "𝙬𝙝𝙮?" ብላችሁ ጠይቁ 𝙤𝙧 ደግሞ 𝙟𝙪𝙨𝙩 𝙨𝙩𝙖𝙮 𝙦𝙪𝙞𝙚𝙩 & 𝙢𝙤𝙫𝙚 𝙤𝙣 𝙬𝙞𝙩𝙝 𝙪𝙧 𝙡𝙞𝙛𝙚...በቃ❗️...ብቻ..ገና ብዙ እንቀጥላለን....
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
ካነበብኩት
:-ትክክለኛ ውሳኔዎች በሰዓቱ እና በጊዜው ካልተወሰኑ ስህተት ይሆናሉ ።
!!አስተውል
የጀበና ቡና እንደተቀዳ ወዲያው አይጠጣም እስኪሰክን መጠበቅ አለብህ ፤ ምክንያቱም በፍጥነት ከጠጣኸው አተላውን ትጠጣለህ ፤ እንዲሁም ለረጅም ደቂቃዎች ካቆየው ይቀዘቅዝ እና ጣዕሙን ያጣል ።
ስለዚህ እናንተም በህይወታችሁ ውስጥ ስትወስኑ በትክክለኛው ጊዜ እና ሰዓት መሆን አለበት
ከቸኮላችሁ ልክ እንደቡናው አተላውን ይደርሳችኋል
በጣም ካቆያችሁ ውሃ ውሃ ይላችኋል ስለዚህ በትክክለኛው ሰዓት በመጠቀም ትክክለኛ ጣዕም ያጣጥሙ ።
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
"በቀልድ የተናገርነው ቃል በሰው ልብ ላይ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል። በቀልድ የጀመርነው ሱስ ሕይወትን ያጨልማል። በዋዛ የጀመርነው ፍቅር የነፍስ ዋጋ ይጠይቃል። ሕይወት በቀልድ አትያዝም፤ ምክንያቱም የምትከፍለው ዋጋ በቁም ነገር ነው።" ❤️🩹
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
ለቅሶ ላይ የምናያቸው ሰዎች በሙሉ እድሩ ከሚቀጣን ብለው የመጡ ናቸው
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
✍ሁለት ጓደኛሞች አብረው ከተማ ውስጥ እየዞሩ ሳለ አንደኛው ወደ ትላልቅ ህንፃዎች #ተመለከተና ለጓደኛው እንዲህ ብሎ ጠየቀው።
:
"ይህ ሁሉ ሀብት ሲታደል እኛ የት ነበርን?" አለው
:
ጓደኛውም "ና" ብሎ እጁን ይዞ ወደ ሆስፒታል አስገባውና "ይህ ሁሉ በሽታ ሲታደል እኛ የት ነበርን?" ብሎ ጠየቀው።
ያልተሰጠን ከተሰጠን አይበልጥም!
ባለንና በተሰጠን እናመስግን
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡
--------------------------------------------------
ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፤ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን።
--------------------------------------------------
በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤ የሚገባበትን አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤ በቃ መጥፎ ዜናውን ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።
--------------------------------------------------
በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።
--------------------------------------------------
አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው።
🔅 በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል። እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
"የሰውን እህት አበላሽቶ መልካም ሚስት መመኘት፣ እሾህ ዘርቶ ስንዴ እንደመጠበቅ ነው። እጣ ፈንታህ ዛሬ በሰበርካቸው ልቦች ልክ ነገ ያንተኑ ቤት ያንኳኳል። ለሴት ልጅ ክብር የሌለው ወንድ፣ ለእናቱ ክብር የለውም!
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
And at the end of the day
ቤተሰቦቻችን ተዉ ያሉን ነገሮች
በሙሉ ልክ ነበሩ ከመንገድ ላይ አንሱ
የተባልነው ያላነሳነው እቃ ሁሉ
አደናቅፎ ጥሎናል 💔😞
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
Someone said ፦
ከደደቦች ጋር አትጣላ በቁጥር ብዙ ናቸዉ 👌
Goodnight my family 😴
👉 @blackprofil38 👈
"ፅጌሬዳና ደመና"
የፀሀዩ🌞 ንዳድ ያጠቃት በብዙ
ጠውልጎ የሚታይ የቅጠሏ🌱 ወዙ
አንዲት ፅጌሬዳ🥀 ቃሏን አስተዛዝና
እንዲህ ተናገረች ለሰማይ ደመና☁️።
ድርቀት በጣም ጎድቶኝ እየኝ ስንገላታ
እባክህ ጣልልኝ የዝናብ💧 ጠብታ
ቶሎ ካላራስከኝ ጉልበቴ እንዲፅናና
ምንም ተስፋ የለኝ መሞቴ ነውና።
"ደመና"
አሁን መሄዴ ነው ለትልቅ ጉዳይ
ስመለስ መጥቼ ሳልፍ ባንቺ ላይ
እዘንብልሻለው ጠብቂኝ እያለ
ምንም ሳይጥልላት መንገዱን ቀጠለ።
ጉዳዩን ጨርሶ ቆይቶ ሲመጣ
ያቺ ፅጌሬዳ ስሯ ውሀ ያጣ
እንደዚያ አስተዛዝና ጭንቋን ያዋየችው
የፀሀዩ 🌞ንዳድ አድርቋት ቆየችው!
እስኪጎርፍ ድረስ የወንዝ ውሀ ሙላት
ወድያው እንደመጣ ዝናቡን🌧 ጣለላት
ግን ደርቃለችና አልቻለም ሊያድናት።
ሳልደርስላት ቀረሁ አዬ ጉድ እያለ
ደመናም ጉዞዉን ወደፊት ቀጠለ።
ሰውም እንደዚሁ ጭንቁን እያዋየ
ከችግሩ ብዛት እየተሰቃየ
ብዙ ጊዜ ኖሮ ቆይቶ ሲጉላላ
የሚረዳው አጥቶ ከሞተ በኋላ
ዘመድ ወዳጆቹ እንባ እያፈሰሱ
ተስካር ቢያወጡለት አርባ ቢደግሱ
ይህ ሁሉ ከንቱ ነው አይጠቅመውም ለሱ
እውነት ከወደደው ሲቸገር ሲጎዳ
በህይወቱ ሳለ ሰው ወዳጁን ይርዳ።
✍ ደራሲ: ከበደ ሚኬል
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
👉 @blackprofil38 👈
