ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS
الذهاب إلى القناة على Telegram
👉 "የምታነበው መጽሐፍ ለአንተ የሚያስብልህ ሳይሆን አንተ እንድታስብ የሚያደርግ ነው።" ሃርፐር ሊ Fiction (ልቦለድ), History (ታሪክ), Politics (ፖለቲካ), Psychology (ስነልቦና), Biography (ግለ-ታሪክ), Self-help(ራስ አገዝ),& Philosophy(ፍልስፍና) የሀገር ውስጥ & የውጪ ሀገር መጽሐፎችን ያገኛሉ!አስተያየትዎን እዚህ @Desutech_bot ያድርሱን
إظهار المزيد1 991
المشتركون
-124 ساعات
-47 أيام
-5230 أيام
أرشيف المشاركات
☝️ ☝️🏻 ☝️🏾
📒 ርዕስ: በፍቅር ስም
✍ ደራሲ: አለማየሁ ገላጋይ
📖 የገፅ ብዛት: 219
🗓 የህትመት ዘመን: 2009
📜 ዘውግ: ልቦለድ
📚 የደራሲና ሀያሲ አለማየሁ ገላጋይ አምስተኛ መፅሀፍ የሆነው ይህ 'በፍቅር ስም' የተሰኘ 219 ገፆች ያሉት መፅሀፍ "በሴት የመከበብን ጥቅም የምናውቀው እኔና ጠቢቡ ሰለሞን ብቻ ነን....'' እያለ ልብ አንጠልጣዩን ትረካ ይጀምራል። አንብቡት ትወዱታላችሁ!
Join_us;
👉 @et_books1
👉 @et_books1
Id፣ Ego፣ Superego!
•
፩) Id (ደመ-ነፍስ)
፨ ምግብ፣ ውኃ፣ ጤና፣ ሙቀት፣ ወሲብ…ወዘተ የስነ ሕይወታዊ ፍላጎቶች ማዕከል ነው።
፨ አብሮን የተወለደ በመሆኑ ምንግዜም ደስታን፣ እርካታን ይሻል።
፨ ጊዜና ሁኔታ ስለማይገዱት ተጨባጭ እውነታን አይለይም።
፨ ምክንያት፣ ግብረ ገብነት አይገዛውም።
፨ እንደ ራስ ወዳዱ ብላቴና ደስታውን ብቻ ያስቀድማል።
፨ ማመዛዘን የጎደለው በመሆኑ እውነታን ያማከለ አይደለም።
•••
፪) Ego (እውነታ መር)
፨ የፍላጎትና የእውነታ አስታራቂ ነው።
፨ ንቁ በመሆኑ ከእውነታ ጋር ነው የሚተዋወቀው።
፨ የላቀ ምቾት እንድንጎናፀፍ ድርጊያዎቹን በጊዜና በሁኔታ ያከናውናል።
፨ የሁልጊዜ ስራው ኢድን ማገልገል ነው።
•••
፫) Superego (የሞራል ቋት ወይም ሕሊና)
፨ ማህበረሰባዊ ሕግና ደንብ ይመራዋል። ሕጉ ከባህል፣ ከሃይማኖት፣ ከመንግስት የተቀዳ ሊሆን ይችላል።
፨ የሕብረተሰቡ ልማድ፣ ስነ-ምግባር፣ ግበረ ገብበት ይገዛዋል።
፨ ትክክልና ስህተት ያውቃል።
፨ ኢድና ኢጎ ግለሰብን ሲወክሉ ሱፐር ኢጎ ግን ኅብረተሰብን ይወክላል።
••••••••••••••••••••••••••
ማሳያ…
ሀ/ መጸዳዳት ብንፈልግ
በልጅነት Id ላይ ስለምንሆን በለበስነው ላይ ወይም ሰው እየተመለከተንም ቢሆን ሜዳ ላይ ባለማፈር ልናራግፍ እንችላል። ዋናው ፍላጎታችን ከውስጥ የታፈነውን ማቅለል እንጂ ስለምንም ነገር አይመለከተንም፣ አያገባንም።
Ego ሲመጣ እውነታውን ስለሚያውቅ ከሰው ተከልለን እንድናደርገው ይገፋፋናል።
Superego ግን የማህበረሰቡ ውጤት ስለሆነ በልጅነት የሽንት ቤት አጠቃቀምን (toilet training) አጣቅሶ በፖፖ (ሽንት ቤት መጠቀም ለማይችሉት ነው) ወይም ሽንት ቤት መጠቀም እንደሚገባን ያሳውቀናል።
ለ) የሰው ልጅ የሚላስ የሚቀመስ ከሌለው ወደ ሌብነትም ሊሄድ ይችላል።
Id የሚያስጨንቀው የርሃቡ ስሜት ስለሆነ ጊዜና ሁኔታ ሳይመርጥ እንዲሰርቅ ያስገድደዋል።
Ego ብልጥ ስለሆነ "ሰው በሚተኛበት ሰዓት በውድቅት ለሊት ይሻላል። ምክንያቱም ጨለማ ስለሆነ የመያዝ እድልህ ዝቅተኛ ነው። በተለይ ደግሞ ቢነቃብህ እንኳን በአንዱ ስርቻ ትደበቃለህ ወይም እብስ ብለህ ታመልጣለህ" ብሎ ለደህንነትህም ጭምር እንደሚያስብ ይቀደዳል። እስቡት ኢጎ ስህተት ስለመሆኑ ከመናገር ይልቅ የተሻለ ውጤት የሚያመጣውን መንገድ ይጠቁማል።
Superego ግን መስረቅ በህግ የተከለከለ ስለሆነ ያሳስርሃል። ይቅርብህ! ብትያዝ ደግሞ በማህበረሱ አስነዋሪ ተግባር ስለሆነ እራስህንም ቤተሰብህንም ታሰድባለህ፣ ታዋርዳለህ ይቅርብህ! ደግሞ ሌብነት ሀፅያት ስለሆነ በፈጣሪ ዘንድም ያስቀጣሃል ብሎ ሽብርና ፍርሃት ይለቅባሃል።
ሐ/ የጓደኛህ ወይም የወንድምህ ሚስት በጣም ውብ ነች። በተመለከትካት ቁጥር ወሲባዊ ስሜትህን ትቀሰቅሰዋለች። ከቅርብ ጊዜ በኋላ እሷም ፍላጎት እንዳላት ተረድተሃል። እናም በድንገት ቤታቸው ስትሄድ ጓደኛህ ወይም ወንድምህ ቤት የለም።
Id የወንድሙ ወይም የጓደኛው ቤት መሆኑን በመዘንጋት አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወሲባዊ ፍላጎቱን እዚሁ ለማርካት ይፈልጋል።
Ego ያለበትን ቤትና ሁኔታ ፈፅሞ አይዘነጋም። ሰው ሊመጣ ስለሚችል ሌላ የሚያስተማምን ድብቅ ቦታ ቢሆን የተሻለ ነው ይላል። ኢድና ኢጎ እጅና ጓንት ናቸው። በደንብ ይግባባሉ። ኢጎ ከኢድ አንፃር አልሸሹም ዞር አሉ አይነት ነው።
Superego "ዝሙት ሀፅያት ነው። በሰማይ ቤት ያስቀጣሃል። ለዛውም የወንድምህን ወይም የጓደኛህን ሃራም ነው። በጣም አስነዋሪና አጸያፊ ተግባር ነው። ይቅር ይበልህ ከየት አሰብከው?" ይልሃል።
ግን የሚያሳዝነው በአብዛኛው ሰው ዘንድ ሱፐር ኢጎ በኢጎና በኢድ ይሸነፋል። ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን ካሻሽ ሱፐር ኢጎህን አድምጠው!
በመጨረሻ ወረታ (reward) ይኖርሃል። ሱፐር ኢጎህን ከሰማህ የሽልማት ወረታህን ኩራትና ክብር ታገኛለህ (ከራስህ)። ግን አልሰማ ብለህ ውጤቱ በመጥፎ ከተጠናቀቀ የቅጣት ወረታ ጥፋትና ፀፀት ያጎሳቁልሃል። ምናልባት Ego ድርጊቱ መጥፎ (መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ) መሆኑን ካወቀ Superego ለማሳመን ወይም የቅጣት ወረታህን ለመከላከል ስልተ-ምት (Defense Mechanism) ሊጠቀም ይችላል።
Join_us;
👉 @et_books1
👉 @et_books1
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
