cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Kedir_Jobs

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 851
المشتركون
-524 ساعات
-297 أيام
-22130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
ጀርመን የሰራተኛ ዕጥረቷን ለመፍታት በሚል ወደ ሀገሯ እንዲገቡ የፈቀደችላቸው ሀገራት እነማን ናቸው? ጀርመን የሰራተኛ ዕጥረቷን ለመፍታት በሚል ወደ ሀገሯ እንዲገቡ የፈቀደችላቸው ሀገራት እነማን ናቸው? የአውሮፓ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ጀርመን ከፍተኛ የሰራተኛ ዕጥረት እንደገጠማት አስታውቃለች፡፡ ሀገሪቱ በተለይም ረጅም ዓመታትን ሊሰሩ ለሚችሉ የሰለጠኑ ወጣቶች ብዙ አማራጮችን ያቀረበች ሲሆን በተለይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና የጤና ሙያዎች የበለጠ ተፈላጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡ ጀርመን እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ፣ የሙያ ባለቤት እና ልምድ ያላቸው አመልካቾች ስራ እንዲፈልጉ በሚል ለአንድ ዓመት የሚቆይ ቪዛ እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡ እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ ከሆነ ጀርመን በዓመት 400 ሺህ የሰለጠኑ ሰራተኞችን የምትፈልግ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆኑ ሀገራት ስራ ፈላጊ ዜጎች በቀላሉ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ አመቺ የቪዛ ስርዓት መዘርጋቷንም አስታውቃለች፡፡ ጀርመን በሀገሯ ከሶስት ዓመት በላይ ለኖሩ ዜጎች ዜግነት ልትሰጥ ነው እንደ ዘገባው ከሆነ የመጀመሪያ ድግሪ አልያም የቴክኒክ እና ሙያ የሰለጠኑ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች የሆኑ ዜጎች በሚኖሩበት ሀገር ባለ የጀርመን ኢምባሲ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አመልካቾች ጀርመንኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን መቻል እንደ ተጨማሪ መስፈርት አስቀምጣለች፡፡ የሙያ ልምድ ኖሯቸው ጀርመንኛ ቋንቋ የሚችሉ እና እድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች የሆናቸው አመልካቾ የበለጠ የመስራት ፈቃድ የማግኘት እድል አላቸውም ተብሏል፡፡ ስራ ለመፈለግ በሚል ዝቅተኛውን መስፈርቶች አሟልተው የጀርመን ቪዛ አግኝተው በጀርመን ስድስት ወር እና ከዛ በላይ ለሚቆዩ አመልካቾች ለተጨማሪ ዓመታት የስራ ፈቃድ እንደሚያገኙም ተጠቅሷል፡፡
إظهار الكل...
👍 17 5
Photo unavailableShow in Telegram
Amal Microfinance SC Position:- 1. Internal Audit Manager 2. Branch Accountant 3. Operation Officer How To Apply: Send your Application later and CV to: [email protected] or [email protected] #ለእርስዎ_ካልሆነ_ለሌሎች_ያጋሩ!
إظهار الكل...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ለንተቡር አካዳሚ አ.ማ ※ የትምህርት ዝግጅት፡- አካውንቲንግ ※ የስራ መደብ፦ ሲኒየር የሒሳብ ሰራተኛ ※ የስራ ልምድ፦ ዲግሪ 3 ዓመት ወይም ዲፕሎማ 6 ዓመት ※ ብዛት፦ አንድ(1) ※ ፆታ፦ ሴት ※ ደመወዝ፦ በስምምነት ለተጨማሪ መረጃ ፦ 0962206781 0912221285 0113695905 #ለእርስዎ_ካልሆነ_ለሌሎች_ያጋሩ!
إظهار الكل...
1
We Need Nurse ※ Position: Nurse ※ Place: Tolay, Jimma Zone (60Km From Wolkite) ※ Experience: 0Years and  Above ※ CGPA: Above 3.5 ※ Salary: Negotiable ※ Sex: Male We prefer if he can speak Afan Oromo How To Apply: Call to 0928101516 #ለእርስዎ_ካልሆነ_ለሌሎች_ያጋሩ! === Kedir_Jobs ቴሌግራም👉 https://t.me/Kedir_Jobs
إظهار الكل...
👍 2
ግሬስ ሊድ ቴክ ኃ/የተ/የግል ማህበር Position: Tender and procurement assesor and digital advertisement technician           በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ / በኮምፒውተር ሳይንስ / በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ / ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ / ኤሌክተሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ሙያ የተመረቀ/ች  አዲስ ተመራቂ ወይም አንድ አመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው/ያላት የትምህርት መረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን በቴሌግራም አድራሻ @J7user በመላክ እስከ ግንቦት 17/2016 መመዝገብ ትችላላችሁ የስራ ቦታው፦ አዲስ አበባ 22 አካባቢ #ለእርስዎ_ካልሆነ_ለሌሎች_ያጋሩ! === Kedir_Jobs ቴሌግራም👉 https://t.me/Kedir_Jobs
إظهار الكل...
👍 2
ወደ ካናዳ መሄድ ላሰባችሁ እባካችሁ በቅድሚያ ይህን #video ይመልከቱ
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
እንግሊዝ የመጀመሪያዎቹን ፈቃደኛ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ ላከች የእንግሊዝ መንግስት በፍቃደኝነት ወደ ሩዋንዳ ለሚመለሱ ስደተኞች ለእያንዳንዳቸው 3ሺ ዶላር እንደሚሰጥ ገልጿል።
إظهار الكل...
👍 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በአውሮፓ ህብረት ውሳኔ ማዘኗን ገለጸች የአውሮፓ ህብረት ከሰሞኑ በኢትዮጵያዊያን ላይ የቪዛ ገደብ መጣሉ ይታወሳል ኢትዮጵያ ህብረቱ በኢትዮጵያዊያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ዳግም እንዲያጤነው ጠይቃለች 👇👇👇👇👇
إظهار الكل...
👍 1
የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት (ካውንስል) ኢትዮጵያውያን ላይ በጊዜያዊነት የቪዛ ገደብ ማሳለፉን አስታወቀ። በአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ድረ ገጽ ላይ ዛሬ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ. ም. በወጣው መግለጫ መሠረት፣ በአውሮፓ ኅብረት ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ ተደርጓል። በዚህ ዕገዳ መሠረት፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም። ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉም። የዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል። መግለጫው እንደሚለው፣ ይህ ውሳኔ በኮሚሽኑ የተላለፈው “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ካውንስሉ ባደረገው ግምገማ ስለተገነዘበ” ነው። አክሎም “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ ለመውሰድ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም” በማለት መግለጫው ያብራራል። የአስቸኳይ ጊዜ የጉዞ ሰነዶች በመስጠት እንዲሁም በፍቃድ እና ያለ ፈቃድም የሚደረግ ስደተኞችን የመመለስ ሂደትን በተመለከተም ኢትዮጵያ “በቂ ትብብር አላደረገችም” ሲልም መግለጫው የውሳኔውን ምክንያት ያስረዳል። ስደተኞችን በመቀበል ረገድ በኢትዮጵያ በኩል ያለውን “ትብብር” በድጋሚ እንደሚቃኝም ኮሚሽኑ አክሏል። በኢትዮጵያ በኩል ስደተኞችን የመቀበል መጠኑ “አናሳ” እንደሆነ ጠቅሶ፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ለኢትዮጵያ ያቀረቡት ስደተኞችን የመመለስ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ “እምብዛም አለመሆኑ” ያለውን ትብብር “ትንሽ” ነው ብሎ እንዲደመድም ምክንያት እንደሆነው ማብራሪያ ሰጥቷል። ውሳኔው ጊዜያዊ ቢሆንም ቀነ ገደብ እንደሌለው የኮሚሽኑ መግለጫ ይጠቅሳል።
إظهار الكل...
👍 5 1